Telegram Web
አዲሱን መጽሐፍ በገበያ ላይ 4ኪሎ የቅድስት ሥላሴ ሕንጻ ሥር ማዮን ቤተ መጽሐፍትና ኢትዮ ፋጎስ ቤተመጽሐፍት እንዲሁም ከአብርሆት ላይብረሪ ጀርባ ሀሁ ቤተመጽሐፍት ታገኙታላችሁ
ፌሚኒስቶች ስሜታዊ ሆነው መናገራቸውን መቃወም ቀላል ነው። ስሜታዊ ያደረጋቸውን ስሜት መረዳት ግን ከባድ ነው።

የኢትዮ ፌሚኒስቶችን ቪዲዮ ሪፖስት ማድረጌን በውስጥ ደጋግማችሁ ምጠይቁኝ እህት ወንድሞቼ ይደብራችሁም አይደብራችሁም Sorry እኔ ግን fully እደግፋቸዋለሁ እወዳቸዋለሁ አከብራቸዋለሁ። የተረዳሁትንና ያመንኩበትንም ነው ፎሎውም ሪፖስትም የማደርገው።።።
እና ደግሞ በተያያዘ ዜና ሰሞኑን ከአመታት በፊት ስለ ክፉ መናፍስት አሰራር ትምህርት እና ትምህርቱን ስለሚሰጡ ሰዎች የተናገርኩትን በቪዲዮ ተለቆ በውስጥ ደጋግማችሁ ለጠየቃችሁኝ

እሱ ያው በጣም የቆየ እዚሁ ቻናል ላይ ተለቆ የነበረ ቮይስ ነው። ለዛ update ላርጋችሁ።

አሁንም የትምህርቱንም አስፈላጊነት በጣም አምናለሁ እነዛን ትምህርት የሚያስተምሩትንም ሰዎች እግዚአብሔር በእነርሱ እንደሚሰራና ብዙ እንደሰራም አምናለሁ እጅግ አከብራቸዋለሁ።🙏
ከ-ህይወቴ

ሰላም ተወዳጆች 👋

ዛሬ አንድ ልዩ መርሃ-ግብር እናስተዋውቃችሁ "ከህይወቴ" የተሰኘ አዲስ መርሃ-ግብር ይዘንላቹ መተናል ። በዚህ መርሃ- ግብር በህይወታችን የገጠሙንን ፈተናዎች
ህሊናችንን   ሰላም የነሱንን ማንኛውንም መፍትሄ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በሙሉ እንዳስሳለን   ከእህት ከወንድሞቻችን ምክር እርዳታ የምናገኝበት  እና ጥያቄ  የምንጠያየቅበት መርሃ-ግብር ይሆናል  መፍትሄ ምትፈልጉለት ያስጨነቃቹ ጉዳይ ካለ ላኩልን ማንነታችሁን  ሳትገልፁ   በስም-አልባ የታሪክ ባለቤትነት ጉዳያቹን እንወያይበታለን በእግዚአብሔር ቃል የተቃኙ የመፍትሄ ሀሳቦችም ይቀርባሉ

ከዛሬ ጀምሮ ከታች ባለው ሃሳብ መቀበያ ቦት ማንነታችሁን ሳትገልፁ ሀሳባችሁን ያጋሩን

ሰላመ ክርስቶስ ይብዛላችሁ

@View277
@View277
@View277
ይድረስ ለሐዋሳ ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶች በሙሉ
ሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል የፊታችን እሁድ እንዳትቀሩ የሐዋሳ ልጆች
ድንግልናዋን ጠብቃ ምትቆይ ሴት
ከየት አገኛለው?

ከ-ህይወቴ :- የዛሬው ባለታሪክ እነሆ

የኔ ህይወት ጠዋት መፀለይ ከዛ ስፖርት ከዛ ስራ ባለኝ ክፍት ሰአት የቻልኩትን መዝሙር ያህል ዳዊት መድገም ከዛ ማምሻ ቤተክርስትያን ከዛ እቤት።

ምን መሰላቹ እኔ በኦርቶዶክስ ስርአት ነው በተክሊል ማግባት ነው ምፈልገው አሁን ሳይሆን 30 ካለፈኝ በኋላ

ግን 30 ካለፈኝ በኋላ በተክሊል ልታገባኝ ምትችል ሴት ከየት አገኛለው
ህፃን ላገባ ነው ወይስ እስከ ዛ እድሜዋ ድንግልናዋን ጠብቃ ምትቆይ ሴት ከየት አገኛለው
በርግጥ ትዳር የሚሰጥ እግዚአብሄር ነው

ካሁኑኑ ይዤ መቆየት አለብኝ ወይስ እንዴት ነው
በዛ ላይ ብመኛትስ ባመነዝርስ ብሳሳትስ

ዲያቆኖች ካላቹ አማክሩኝ እስኪ ለነገሩ እናንተ ከሰንበት ተማሪ ከዘማሪያን ታገባላቹ

ሴት ማውራት መግባባት መጀንጀን ለኔ ቀላሉ ነገር ነው ግን ልባም ሴት በሀይማኖት ምታፀናኝ ለልጆቼ አርአያ ምትሆን ፀሎተኛ ከየት ላገኝ እችላለሁ

ለወንድማችን ያላችሁን ምክረ-ሃሳብ አስተያየት ከታች ባለው ቦት ያድርሱን

@View277
@View277
@View277
መንፈሳዊ ህይወቴ ላይ ጫና ፈጠረብኝ

ከ-ህይወቴ :- የዛሬው ታሪክ እነሆ

ሰላም የድንግል ማርያም  ልጆች እንዴት ናቹህ እኔ እግዘብሔርን ይመሰገን
አንድ ሃሳብ ነበረኝ ይህም መንፈሳዊነትን እና ዓለማዊነትን እንዴት ነው ማስኬድ የምችለው ?
ወደ ዋነው ሃሳብ ልግባላቹህ  የተመረኩት በቅርቡ ነው በእግዚአብሔር ፍቃድ ስራ አገኘው ። የምሰራው ስራ መንፈሳዊ ህይወቴ ላይ ጫና ፈጠረብኝ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ስንጓዝ የምንፈልገው ሳይሆን የሚስፈልገን ነው የሚሰጠን ይህንን ስል የምንፈልገው አይሰጠንም ለማለት አይደለም ፍቃዱን ነው የምንከተል ለማለት ነው። እና ከአመታት በፊት ፀበል ቦታ ነበርኩ በጤና ችግር በያንስ 5 ወር 6 ወር ቆይቻለሁ። ያው ፀበል ቦታ ላይ ራስን መግዛት ፣ አርምሞ አለ። በድንግል ማርያም እና በሰማዕቷ ምልጇ ጤናዬ ተመለሰልኝ ። ትምህርቴን ጨርሼ ወደ ስራ ዓለም ገባሁኝ ።ስራው በባህሪው ጭቅጭቅ እስከ መጣላት አለው። ይህ  ቀደም ከፀበል ቆይታ ያመጣዋቸው ባህሪያት አሉ ይህ ደግሞ ስራዬ ጋር ሊሄዱ አልቻለም ከሰዎች ጋር ቆጣ ብየ ማናገር አልችልም ።ስራውን እንዳልተወው በዚህ ስዓት መስራት አለብኝ ። እንዴት አድርጌ ሁለቱን ማስኬድ እችላለሁ ? ወንድሞቼ እህቶቼ  የእናንተን ሃሳብ በልዑል  እግዚአብሔር ስም እፈልጋለሁ
      ታናሿ እህታቹህ ፍቅርተ ማርያም

ምክራችሁን ከታች ባለው ቦት ያድርሱን

@View277
@View277
@View277
Forwarded from እኔ ክርስቲያን ነኝ
" ወደ ሮሜ 12 : 10 - በወንድማማች መዋደድ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ " እንዲል እኛስ እየተዋደድን ነው ??

አዎ ብቻ ማለት በቂ አይደለም ፤ ያመንበትን በስራ መግለፅ ይገባል ። ወንድማችን ሰዓሊ ቅዱስ ኤፍሬምን ስንቶቻችሁ ትወዱታላችሁ ? እርግጠኛ ነኝ ከግማሽ ሚሊየን በላይ የምትሆኑ ሠዎች የምትከተሉት እርሱንም ስራውንም ወዳችሁ ነው ፤ አሁን ሠዓቱ ፍቅራችሁን የምትገልፁበት ነው ።

ከመንፈሳዊ ቲክቶከሮች መካከል ለ Tiktok Creative Award የታጨ ብቸኛው ቲክቶከር ሆኗል ፤ ይህ ብቻ አይደለም በአንድ ሰው ብቻ እየተመራ ይገኛል ። ታዲያ እኛ ቁጥራችን እልፍ አእላፍ ሆኖ እንዴት ማሸነፍ ያቅተናል ?

ውድ ቤተሠቦቼ ሁላችሁም ሰዓሊ ቅዱስ ኤፍሬምን Vote በማድረግ በአንድም በሌላሞ መልኩ የቤተ ክርስቲያናችንን ስም እናስጠራ እያልኩ በልዑል እግዚአብሔር ስም ከታች ባስቀመጥኩላችሁ ሊንክ እየገባችሁ ድምፅ እንድትሆኑት እጠይቃለው ።

https://www.tiktokcreativeawards.com/categories/16
📖የእነአቡን አዲሱን መጽሐፍ ዛሬ ገዝቻት አለሁ

የመጀመሪያው ስለሆነች ገዝተን እናበረታታው አንብበን አስተያዬትም እንስጥ ምርቃት እሁድ ስለሆነ ቀድመን አንብበን እንገኝ

በገበያ ላይ 4ኪሎ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻ ሥር ማዮን ቤተ መጽሐፍት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ኢትዮ ቤተሰብ ቤተ መጽሐፍት ጋር ታገኟት አላችሁ

🌾ዋጋው ድግሞ ትንሽ ነው እኔ ዛሬ የገዛኋት 320 ብር ነው የአንድ በያይነት ዋጋም አትሞላ እዚያው ቅድስት ሥላሴ ሕንጻ እንኳን አንድ በያይነት 350 ብር ነው ስለዚህ ከአንድ በያይነት ያነሰ ነው ዋጋው ማለት ነው 😁። ስለዚህ አንድ መጽሐፍ ከአንድ በያይነት ዋጋ ባነሰ ገዝተን እናንብብ እንጅ

አቡ እንደነገረኝ ደግሞ ኢትዮ ፋጎስ ቤተመጽሐፍት እንዲሁም ከአብርሆት ላይብረሪ ጀርባ ሀሁ ቤተመጽሐፍት ታገኙታላችሁ
ሰሞኑን በሰንበት ቀን ከቤተክርስቲያን ስመለስ አንዲት እህት አጊንታኝ ሰላም ብላኝ ስልክ ተለዋውጠን ተለያየን የሰፈሬ ልጅ ናት። ከሳምንት በኋላ አካባቢ ደውላልኝ ራሷን አስታወሰችኝና እያለቀሰች አንድ ነገር አጫወተችኝ

ዱባይ ረዥም አመታት ቆይታ ነው የመጣችው እዛ እያለች ነው እኔንም የምታውቀኝ። እዛ እያለች ገንዘቧን አጠራቅማ ከአንድም ሁለት ቤት መሬት ገዝታ አዳማ ላይ አስርታ ነበር። ቤቴን ብላ ስትመጣ ግን የጠበቃት የተገዙት ህጋዊ ባለመሆናቸው ፈርሰው ነበር። ቢያንስ ለአመት ጉዳዩን እየተከታተለች ስትንከራተት ስትመጣ በእጇ የያዘችውን ብር ጨረሰችው። እኔ ምንም መፍጠር የቻለችውም ነገር የለም። እኛ ሰፈር ጓደኛዋ ተከራይታ ምትኖርበት መጥታ ነው የምትኖረው። አሁን ጓደኛዋም ተመልሳ ከሀገር ወጥታ ብቻዋን ናት። ጓደኛዋ ስትሄድ የ3 ወር የቤት ኪራይ ክፍላ ነበር አልቋል።አሁን ላይ በጣም በብቸኝነት ውስጥ ሆና የምታውቀውም የምትቀርበውም ዘመድም ጓደኞም የላትም እያለቀሰች ነው ምትገኘው። ስራ ለመፈለግ እንኳን ምንም የምታውቀው የምጠይቀው ሰው እንደሌለ እያለቀሰች ነው የነገረችን። የቤት ኪራዩዋ ነገ በ14 ነው የሚያልቀው። የሚከፈለው 8ሺ ብር ነው። ሁላችንም እንተባበርና ቢያንስ የሁለት ወር እንቻልላት። ከተቻለ ሥራ ምታገኝበትን ወይም ደግሞ ተመልሳ ሄዳ መስራት የምትችልበትን መንገድ እንፍጠር።

1000629902598 Ayinalem tadese/ ንግድ ባንክ
013471340763800 Ayinalem tadese / አዋሽ ባንክ

0989696323 የሷ የእጅ ስልክ ነው ደውላችሁም ወይም በቴሌግራም እውሯት አበርቷት
Elements - PART 1 - EARTH.pdf
5.1 MB
"Elements"(ባህርይ፤የቁስ አካል መገለጫ?) የተጻፈው ማንነታቸውን ባልገለጡ የአንድ የአርየንታል ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቄስ ነው።
አጻጻፉም ታሪካዊ ልብ-ወለድ የምንለው አይነት እና መንፈሳዊነት ያለው ሲሆን፤ጭብጡ ደግሞ መንፈሳዊ ልውጠትን(Transfiguration) እና እድገትን የሚያሳይ ነው።
Elijah(ኤልያስ) በተባለ በአንድ ገፀ-ባህርይ ሕይወት ላይ መሠረቱን የጣለ ነው ይህ ኤልያስ የተባለ ገፀ-ባህርይ በካናዳ በስደት ከተበተኑ (Diaspora) የግብጽ ክርስቲያን ቤተሰቦች የተወለደ ሲሆን በክርስቲያናዊ አስተዳደግ ያሳደጉት የነበረ ቢሆንም በጉርምስና እድሜው ግን ከቤተክርስቲያን የሚጠፋበት ክስተት ተፈጥሮ ጭራሽ ወደ ኢ-አማኒነት (Atheist) ይሸጋገራል።
ነገርግን ወደ ሕይወቱ አንዲት እንስት መጥታ ሕይወቱ ወደ መቀየሩ ይሄዳል... (መጨረሻውን አንብቡ!)

የእርሱን የልውጠት ደረጃዎችም በአራቱ መሠረታዊያን ቁስአካሎች(መሬት፣ውኃ፣እሳት እና ንፋስ) መስለው ነው የጻፉት እንዲሁም በመጽሐፉ ውስጥ ውበተ ክርስቶስ (Beauty of Christ)፣የቤተክርስቲያን ውበት፣በስደት የተበተነው ማኅበረ ክርስቲያን(Diaspora Christian community) የሚያሳልፈውን ውጣ ወረድ በተለይም በካናዳ ያሉ የግብጽ ክርስቲያኖች የሚያሳልፉትን ውጣወረድ የሚያሳይ እና በጥቅሉ ግብጻውያን ስላላቸው መንፈሳዊ ሕይወት እና ከቅዱሳን ጋር ስላላቸው ኅብረት እና እምነታቸውን የሚያሳይ ደገኛ መጽሐፍ ነው።
የጽሑፉ ውበት እና ጸሐፊው የተጠቀማቸው ቃላትም ለማንበብ ሳቢ ናቸው!
አንብባችሁ ከኤልያስ ጋር አብራችሁ ለመነሳት ያብቃችሁ!
ጌታ እግዚአብሔር ለንስሐ ያብቃን!
2025/03/01 03:07:54
Back to Top
HTML Embed Code: