Telegram Web
​​ማስታወሻ

ዙል-ሒጃ 9 ፆም በኢትዩ… የቀን አቆጣጠር ሐምሌ 12 #ሰኞ ነው ቀኑን የጾመ ሰው ያለፈውና መጪው ዓመት ወንጀል ይሰረዝለታል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

🔅ይጹሙ፤ ዘመድ፣ጓደኛና ጎረቤትም ያስታውሱ::
የረመዷን ቀዷ ያለበት ሰውም ቢሆን ለቀዷው ሰፊ ጊዜ ስላለ የዐረፋን (9ኛውን ቀን) መጾም ይችላል
በዕለቱም ዚክር፣ዱዓ፣ሰላትና ሁሉንም ኸይር ስራ ያብዙ የተከበረው ጌታችን በቀኑ ክ/ጊዜ ወደ ቅርቧ ሰማይ የሚወርድበት ብቸኛው ቀን ነውና ሓጃዎትን በሙሉ ለአዛኙ አላህ ይዘርዝሩ! ይማጸኑት! ከጀሀነም እሳት ጠብቀኝ ይበሉት! እርሱ መሃሪና አዛኝ ነው
رب اغفر لي ولوالدي ولأهل بيتي ومشايخي وأحبابي.
وأصلح شأن أمة محمد عليه الصلاة وسلم
━━━━━━━━━━━━
አላሁ አክበር
አላሁ አክበር
አላሁ አክበር
ላኢላሀኢልለላህ
አላሁ አክበር
አላሁ አክበር
ወሊላሂል ሐምድ 🙏
አላሁ አክበር ከቢራ
ወልሐምዱሊላሂ ከሲራ
ወሱብሐነላሂ ቡክረተን ወአሲላ
ላኢላሀኢልለላሁ
አላሁ አክበር
አላሁ አክበር
ወሊላሂል ሐምድ ☝️

ዱዓችንን አላህ ይቀበለን!🤲
ዒዱኩም ሙባረክ 🕋🎈🎊
ያማረ
Eid mubarek
🇪 🇮 🇩 🇲 🇺 🇧 🇦 🇷 🇪 🇰
መልካም ነፍስ ለሰወች መልካም በመዋል ትደሰታለች ፡ መጥፎ ነፍስ ደግሞ ሰወችን በማስቀየምና በማስከፋት ትደሰታለች።
ኢብኑ ተይሚያ
ምንጭ፦ አል ፈታዋ (560-1)
#ማሳሰቢያ:-👇
✓ልክ ከሆንኩ ከአላህ ነው።ከተሳሳትኩ ከነብስያዬና ከሸይጧን ነውና ስህተቴን ጠቁሙኝ እንጂ "Leave" አትበሉ‼️
()اللـهـمَّ ﷺصَـلِّﷺوَسَـــلِّـمْ ﷺ وَبَارِك ﷺْ عـلـى ﷺ نَبِيِّنَـــا ﷺ مُحــمَّد
┊┊┊┊┊♡ﷺﷺﷺﷺﷺ
┊┊┊┊♡ﷺﷺﷺﷺﷺ
┊┊┊♡ﷺﷺﷺﷺﷺ
┊┊♡ﷺﷺﷺﷺﷺ
መልካም ጅምዓ 🌹
ﷺﷺ
ﷺﷺﷺ
ﷺﷺﷺﷺ
ﷺﷺﷺﷺﷺ
ﷺﷺﷺﷺﷺﷺ
ﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺ
ﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺ
ﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺ
ﷺﺍﻟﻠﻬﻢ ﺻﻞِّ ﻭﺳﻠﻢ ﻋﻠﻲ ﻧﺒﻴﻨﺎ ﻣﺤﻤﺪﷺ
ﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺ
Forwarded from የሙዑሚን ጀማኣ channel
የትኛውም ቃላት የልቤን መግለፅ አይችልም

ይህ ወራዳ ሰው የኛን ነብይ እጅግ ፀያፍ በሆኑ ቃላት በኦሮምኛ ቋንቋ ተሳደበ

አንተ ርካሽ የምድር ሸክም ወላሂ የረሱል ሶለላ አለይሂ ወሰለም ክብር ባንተ ንፍጥ ጭንቅላት በዚህ ደረጃ ልብን ሰርስሮ አጥንትን በሚሰብር ደረጃ ሊሰደቡ ይቅርና

እኛ ሙስሊሞች እንኳን ያለቀሱበትን የሳቁበትን ቀን አስታውሰን የምናለቅስ እንስፍስፍ አፍቃሪያቸው ነን ወላሂ በተሳደብክበት ምላስ በዋይታ ታለቅስበታለህ

ጉዳዩ በህግ መያዙን ሰምተናል እኛም አስፈላጊውን ድጋፍ አድርገን ውጤቱን መስማት እንፈልጋለን

ዛሬም እንደግመዋለን ወላሂ ቢላሂ ተላሂ እስልምናችን ከሀገራችን ፣ ከብሄራችን ፣ ከነብሳችን ሰው ከመሆናችንም ጭምር ይበልጣልና አትነካኩን አድቡ ሙስሊም ከተነሳ አዋጅና መግለጫ አያስቆመውም።

ለሀገር ሰላም ስትሉ የመንግስት አካላት አስቸኳይ መፍትሄ ስጡን።

ፊዳካ አቢ ወኡሚ ወደሚ ወነፍሲ ወአህሊ ወዒያሊ ወማሊ ያሀቢበላህ 😭😭😭

www.tgoop.com/momen_jemma_channel
🔴 የአረፋ ቀን ፆም!

ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

‎﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162

📌 ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።

📌 ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል።ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።

📌 ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።

📌 በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣
1/ ቀኑን መጾም
2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3/ ዱዓእ ማብዛት

📌 ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም። ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።

📌 ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ አርብ ሐምሌ 1 ነው።ለወዳጅና ዘመድም እናስታውስ። ለራሳችን፣ለቤተሰባችንና ለሀገራችን ዱዓ እናድርግ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from القرآن نور
ጌታህ ላንተ የመረጠልህን ምንም ነገር ቢሆን አትጥላ ሁሉም ነገር ለኸይር ነው።

«በሚደርስብህ ፈተና ከታገስክ ትመነዳለህ፤
«በበሽታህ ከታገስክ ትመነዳለህ፣
« ባጣኸውም ነገር ሁሉ ከታገስክ ትመነዳለህ፣
«በመታገስህም ትመነዳለህ፣

የጌታህ ምርጫ ዟሒሩ ሸር ቢመስልህም ከጀርባው በኸይር እንጂ በሌላ አይመጣም።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
አደራ! ቁርኣን እንቅራ
~
በርግጠኝነት እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ ከሚርመሰመሱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁርኣን ያልቀሩ ብዙ ወገኖች ይኖራሉ። ወላሂ ሊቆጨን ይገባል። በዚህ አማራጮች በበዙበት ዘመን እንዴት ድንቁርናን አሚን ብለን ተቀብለን በጨለማ ውስጥ እንኖራለን? የትም ብንሆን ካለንበት ቦታ ሆነን መማር እንደሚቻል የሚታወቅ ነው። አላህ ባገራልን መንገድ እንማር። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን የተማረና ያስተማረው ነው" ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 5027]
ስለዚህ ያልተማርን ጊዜ ሰጥተን እንማር። የተማርን መልክቱን እንማር፣ ባወቅነው እንስራ። በየቀኑ ከጊዜያችን ውስጥ ለቁርኣን ድርሻ ይኑረን። በምንችላት መጠን ለመሐፈዝ እንሞክር። የእድሜ መግፋት ቁርኣን ከመማር አያግድም። በርካታ ሶሐቦች በጎልማሳነት ዘመናቸው ነው ቁርኣን የቀሩት። ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አል0ባድ "አንድ ሰው ከሃምሳ አመቱ በኋላ ቁርኣን ሊሐፍዝ ይችላል ወይ?" ተብለው ተጠይቀው ነበር። ምላሻቸው እንዲህ የሚል ነበር፦
"አዎ! እኔ ራሱ ከሃምሳ በኋላ ቁርኣን ከሐፈዙት ውስጥ ነኝ። ሶሐቦች - ረዲየላሁ ዐንሁ - ትልልቅ ሰዎች ሆነው ነው ኢስላም ያገኛቸው። ከመሆኑም ጋር ቁርኣንን ሐፍዘዋል።"
ስለዚህ በየትኛውም ምክንያት በልጅነቱ ቁርኣን ያልቀራ ሁሉ እራሱን አያዳክም። "በአላህ ፈቃድ እችላለሁ" ብሎ ይነሳ። ኢንሻአላህ ይችላል። አለማወቅን ታቅፈን ፈፅሞ ምቾት ሊሰማን አይገባም። ሰው እንዴት ቁርኣን ሳይቀራ እድሜውን ይፈጃል?!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
#ፉዶይል_ኢብኑ_ዒያድ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

"ምርጡን ዱቄት እያወጣ እንክርዳዱን እንደሚያስቀረው ወንፊት አትሁኑ ፣ ከአፎቻችሁ ጥበብን (ጥሩ ንግግርን) ታወጣላችሁ ፣ ውስጣችሁ ደግሞ ቂምና ጥላቻ ይቀራል።"

📚 ۞【صفة الصفوة【٤٥٧/١】۞
……… ስድስቱ የተውበት መስፈርቶች ………
===========================
በህይወታችን ብዙ ጊዜ ወንጀሎችን እንፈፅማለን። አላህ ያደለው በወንጀሉ አላህ ፊት እንዳይጠየቅ ተውበት ማድረግን ያስባል። ግን ስንቱ ነው ተውበቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ እንዲሆን የሚጨነቀው? እራሳችንን በሚገባ ጠይቀን እናውቃለን?! ለመሆኑ መስፈርቶቹን ምን ያህሎቻችን በሚገባ እንለያቸዋለን? ለማያውቁ ጥቆማ፣ ለሚያውቁ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ እጠቅሳለሁ። የተውበት መስፈርቶች ስድስት ናቸው። እነሱም:–

① ኢኽላስ: – አላህን ብቻ በማሰብ መፈፀም ማለት ነው። አንድ ሰው ወንጀልን የሚተወው ዱንያዊ ጥቅሞችን አስቦ ከሆነ የመጀመሪያውን የተውበት መስፈርት ዘንግቷል።
② ወንጀሉን ማቆም:– አንድ ሰው የሚፈፅመውን ወንጀል ባላቋረጠበት ሁኔታ "ቶብቻለሁ" ቢል ቀልድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ተውበት ያሰበ ሰው ጥፋቱን በቀጠሮ ሳይሆን ቀጥታ ሊያቆም ይገባል።
③ ወደ ጥፋቱ ዳግም ላይመለሱ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ። አንድ ሰው ከወር ቡ በኋላ እንደሚመለስ እያሰበ ረመዳን ሊገባ ሲል አንድን ወንጀል ቢተው መስፈርት ስላላሟላ ተውበት አድርጓል ማለት አይቻልም።
④ በወንጀሉ መፀፀት፦ ሰውየው ሲፈፅመው በቆየው ወንጀል ላይ ደንታ ቢስ ከሆነ ተውበቱ የሐቂቃ አይደለም። ፀፀቱ "ሰው ምን ይለኛል" ወይም "ክብሬ ጎደፈ" በሚል ሳይሆን የጌታውን ህግ በመጣሱ ሊሆን ይገባል። ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ዝሙት ፈፅመው ጌታቸው ዘንድ ካለው ሂሳብ ይልቅ ዱንያ ላይ ያለው የሰው ወሬ ሲያስጨንቃቸው ይፀፀታሉ። እንዲህ አይነት ፀፀት የተውበትን መስፈርት አያሟላም። ይልቅ ከዛሬው የበዛ ህዝብ ፊት ነገ በአኺራ መዋረድ ከመምጣቱ በፊት ትክክለኛውን ፀፀት እዚሁ ልናስገኝ ይገባል።
⑤ ተውበቱ ወቅቱን የጠበቀ መሆን። ይህም ሞት አፋፍ ላይ ከመድረሱ በፊት እና ፀሀይ በመጥለቂያዋ ከመውጣቷ በፊት መሆኑ ነው።
⑥ ወንጀሉ የሰው ሐቅ መግፋት ከሆነ ሐቁን ሊመልስ ወይም ይቅርታውን ሊያገኝ ይገባል። ያን ማድረግ ካልቻለ ዱዓእ ሊያደርግለት እንዲሁም ኢስቲግፋርና ኸይር ስራ ሊያበዛ ይገባል።

© ኢብኑ ሙነወር
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/11/14 03:58:04
Back to Top
HTML Embed Code: