Telegram Web
አርቲስት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) የፌስቡክ ገጿ መጠለፉን አስታወቀች

አርቲስቷ ከ219 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና ቬሪፋይድ የሆነዉ የፌስቡክ ገጿ መጠለፉን በኢንስታግራም አካዉንቷ ባሰፈረችዉ ጽሁፍ አስታዉቃለች።

“የፌስቡክ ገጼ መጠለፉን ሳሳዉቃቹ እያዘንኩ ነዉ። ይህን ጉዳይ ለመፍታት እየሰራን እንገኛለን። ከተጠለፈዉ ፌስቡክ ገጼም ሆነ ትክክለኛ ካልሆኑ (unofficial) አካዉንቶች የሚተላለፉ መልዕክቶች የኔ አይደሉም” ብላለች።

የአርቲስቷ ፌስቡክ ገጽ ፕሮፋይል ምስል ከአስር ቀናት በፊት መቀየሩንና ከዛ ወዲህም የተለያዩ መልዕክቶች በገጹ ላይ መለጠፋቸዉን ተመልክተናል።
@AccessAddis
ድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁን አዲስ ነጠላ ዜማ ለህዝብ ሊያደርስ ነው።

ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አርማሽ(ቀናበል) የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማ በነገው ዕለት ለህዝብ ሊያደርስ መሆኑን በይፋዊ ማህበራዊ ገፁ አሳውቋል።
@AccessAddis
TEDDY AFRO - አርማሽ (ቀና በል...
Teddy Afro
ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አርማሽ(ቀናበል) የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቋል
@AccessAddis
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቅርቡ 10ኛው የለዛ ሽልማት ...
መልዕክት ለዛ ሽልማት አዘጋጆች
የተከበራችሁ የኪነጥበብ ቤተሰቦች እንዴት ከረማችሁ አምላክ ፈቅዶ ዘንድሮ በለዛ የሽልማት ስነ ስርዓት ልንገናኝ ነው። ዘንድሮም ታላላቆችን በስራቸው እናከብራለን።
በዚህ ዓመት የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምጻዊ ምድብን ከዚህ ዓመት ሽልማት ጀምሮ በታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ፣ዜማ ና ግጥም ደራሲ የኤልያስ መልካ መታሰቢያ ሽልማት እንዲሆን ወስነናል። እናም የሽልማቱ ዘርፍ በለዛ ሽልማት ላይ ሲጠራ ፦ የኤልያስ መልካ ሽልማት ፦ የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ ፦ ተብሎ ይጠራል ማለት ነው። ኤሊያስ መልካ የአገራችንን ምርጥ አዳዲስ ድምፃውያንን በማበቃቱ ሂደት ድርሻው የገዘፈ ነውና ለውሳኔያችን ገዢው ምክንያት ይሄው ነው። የመጀመሪያ አልበማቸውን እሡ ሰርቶላቸው ፈልጎ አግኝቷቸው ቀርጾ አውጥቷቸው የየራሳቸው ሙዚቃዊ ማንነት አላብሶ በስራቸው አንቱ ያስባላቸው ክብሩን ያወቁታልና የሃሳባችን ተጋሪዎች ናቸው ብለን እና ስባለን። እናንተስ የኪነ ጥበብ ቤተሰቦች ? ውሣኔያችንን እንዴት አግኝታችሁት ይሆን ? ለማናቸውም ድምፆችሁን ለምትወዱት የኪነጥበብ ስራና ጥበበኛ www.lezashow.com
በመግባት vote የሚለውን በመጫን ድምፆችሁን ሰጡ የኪነጥበብ ቤተሰብን አበርቱ :: ድምፅ መስጠት ሠኞ መጋቢት 12 ይጀመራል ::
የለዛ ሽልማት
የለዛ ሽልማት ድምፅ መስጠት ተጀመረ ::
http://www.lezashow.com
ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮችን ለመሳተፍ የሀገሬ ቴቪን ቻናል ይቀላቀሉ። ቻናሉን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ። ቻናሉን በመቀላቀል በተከታታይ የሚወጡ ውድድሮችን ለመሳተፍ ይጠብቁ።
ለ ለዛ ሽልማት ለመጨረሻው ዙር በ10ሩም ዘርፎች የተመረጡት ዕጩዎች ታውቀዋል :: እባክዎ www.lezashow.com በመግባት ዕጩዎቹን ይመልከቱ ድምፅዎን ይስጡ:: መልዕክቱን ያጋሩ ::
ተወዳጁ ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሜድስታር ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በትላንት ዕለት ግንቦት 11, 2014 በተወለደ በ57 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ዶክሌ ላለፋት ሁለት አስርተ አመታት በኮሜዲው ዘርፍ አዝናኝ፣ አስተማሪ እና ቁምነገር አዘል የኮሜዲ ስራዎችን ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል። ዶክሌ ሀገራችን ካፈራቻቸው ብርቅዬና ግንባር ቀደም ኮሜዲያኖች ውስጥ አንዱ ሲሆን ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር።

የኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ የቀብር ስነስርአት የሚፈጸመው በትውልድ ሀገሩ ኢትዩጵያ ስለሆነ ለዚህም ማስፈጸሚያ የሚሆን እና ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይህ የጎፈንድሚ አካውንት ተከፍቷል።
8ተኛው ጉማ አዋርድ አሸናፊዎች
የህይወት ዘመን ተሸላሚ፦ ፕሮፌሰር ሰሌማ መኩሪያ
የተማሪዎች አጭር ፊልም፦ መባ አብርሃም ከበረ

ተከታታይ ድራማ ዘርፍ
#️⃣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ፅሁፍ፦ ቤዛ፣ አዜብ እና ቅድስት እረኛዬ
#️⃣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ተዋናይት፦ ሳያት ደምሴ በእረኛዬ
#️⃣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ተዋናይ፦ ብርሀኑ ድጋፌ የእግር እሳት
#️⃣ ምርጥ ሲትኮም፦ 9ኛው ሺ ወንድምአገኝ ለማ
#️⃣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ዳይሬክተር፦ አብርሃም ገዛኸኝ የእግር እሳት
ምርጥ ድራማ፦ እረኛዬ

በፊልሞች
1️⃣ ምርጥ ድምፅ፦ አብርሃም ዳንኤል በከርቤ
2️⃣ ምርጥ ኤዲተር፦ ዳንኤል ግርማ በምን አለሽ
3️⃣ ምርጥ ስኮር፦ ጆርካ መስፍን በምን አለሽ
4️⃣ ምርጥ ማጀቢያ ሙዚቃ፦ እሱባለው ይታየሁ የፍቅር ጥግ
5️⃣ ምርጥ ሲኒማቶግራፈር፦ ዳንኤል ግርማ በስንብት
6️⃣ ምርጥ ሜኬአፕ፦ ዳግማዊ አለማየሁ በምን አለሽ
7️⃣ ምርጥ የፊልም ፅሁፍ፦ አንተነህ ሀይሌ ስንብት
8️⃣ ተስፋ የተጣለባት ተዋናይት፦ ህፃን መቅደላዊት አስተርይ በየፍቅር ጥግ
9️⃣ ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ፦ ህፃን ሳሙኤል ወንድይፍራው በስንብት
🔟 ምርጥ ረ/ተዋናይት፦ እታፈራሁ መብራቴ በማንያዘዋል
1️⃣1️⃣ ምርጥ ረ/ተዋናይ፦ ሽመልስ አበራ በየፍቅር ጥግ
1️⃣2️⃣ ምርጥ ተዋናይት፦ አምልሰት ሙጬ በምን አለሽ
1️⃣3️⃣ ምርጥ ተዋናይ፧ እንግዳሰው ሀብቴ (ቴዲ) በግዛት
1️⃣4️⃣ የተመልካች ምርጫ (በደሌ እስፔሻል)፦ የፍቅር ጥግ
1️⃣5️⃣ ምርጥ ዳይሬክተር፦ ኑር አክመል በማን ያዘዋል
1️⃣6️⃣ ምርጥ ፊልም፦ ማን ያዘዋል

በዚህ መሰረት በቲቪ ድራማ እራኛዬ 3ት በማሸነፍ በልጦል 2ት በማሸነፍ ደሞ የእግር እሳት አለ
በፊልም ደሞ 4 አዋርድ በመውሰድ ምን አለሽ እና የፍቅር ጥግ ከፊት ናቸው፣
​​​ለዛ ሽልማት በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ በሂልተን ሆቴል ይካየዳል።

በሂልተን ሆቴል የሚደረገው 10ኛው የለዛ ሽልማት በ 12 የተለያዩ የሽልማት ዘርፎች እጭዎችን አወዳድሮ ይሸልማል።

የመጨረሻ እጩዎች ምርጫ Lezashow.com ላይ በመግባት ይምረጡ
@AccessAddis
#አሳዛኝ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

በርካታ ፊልሞችን በመስራት የሚታወቀው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ /ባባ/ በህመም ዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ማለዳ ላይ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ከሰራቸው ፊልሞች መካከል
3+1፣ 300 ሺ ፣አስነኪኝ ፣ባላ ገሩ፣ የፍቅር ABCD ፣ብላቴና ፣ቦሌ ማነቂያ፣እንደ ባል እና ሚስት፣ኢንጂነሮቹ፣እርቅ ይሁን፣ ኢዮሪካ ፣ጉዳዬ፣ሀገርሽ ሀገሬ፣ ሕይወቴ፣ ህይወት እና ሳቅ፣ከባድ ሚዛን፣ፍቅር እና ፌስቡክ ፣ከቃል በላይ፣ላውንድሪ ቦይ፣ ኮከባችን፣ ማርትሬዛ፣ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣ትዳርን ፍለጋ፣ አንድ ሁለት ፣ብር ርርር፣ወደው አይሰርቁ፣ወፌ ቆመች፣ወንድሜ ያዕቆብ ፣እንደ ቀልድ ፣ወቶ አደር ፣አባት ሀገር ፣የሞግዚቷ ልጆች፣ይዋጣልን፣ዋሻው፣ወሬ ነጋሪ ወጣት በ97 ሌሎችም ፊልሞች ሰርቷል።
ከአርባ በላይ የአማርኛ ፊልሞች ላይ የተወነው ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በድንገተኛ ህመም ዛሬ ጠዋት አርፏል ።

ተዋናዩ ካባለቤቱ የፊልም ተዋናይት
ቃልኪዳን ጥበቡ ጋር ከተለያየ በኋላ ድብርት ተደጋግሞ ያጠቃው እንደነበር ፊደል ፖስት ከቅርብ ወዳጆቹ ሰምተና ሲል ዘግቧል::

ዕድሜው በሰላሳዎቹ አጋማሽ የሚገኘው ተዋናይ ታሪኩ ተውልዶ ያደገው ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሲሆን የአንድ ልጅም አባት ነው።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝናን አና በብዙዎች ተወዳጅነትን ያተረፈ ተዋናይ ነው። በጉዳዬ ፊልም ላይ ደግሞ በድርሰት ፣ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በትወና ተሳትፎበታል::
***
ዳሰሳ አዲስ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅና አድናቂዎች መፅናናትን ይመኛል።
ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ ስለታሪኩ ብርሃኑ (ባባ)...

"እስከ መች ኢንተርቪው እንቢ ትላለህ ? አንተ እኮ በዚህኛው ዘመን ላለው የሀገራችን ፊልም ቀለም ከሆኑ ወጣት አርቲስቶች አንዱ ነህ ፡ በጣም ብዙ አድናቂዎችህ ፡ ያንተን ፈለግ መከተል የሚፈልጉ ወጣቶች ስላንተ ማወቅ መስማት ይፈልጋሉ

አዱ ግድ የለህም ይለፈኝ በዚህ ጉዳይ ከሰይፉም ጋር ተጨቃጭቀናል እኔ ሚዲያ ላይ መቅረብ ብዙም አልወድም ፡ ፊቴ መቀያየሩን ሲያይ አዱ ተክልዬን ከደበረ ኢንተርቪውን ዝም በለን እንስራው እና አንድ ቀን ደስ ካለኝ አሁን አስተላልፈው እልሃለው

ለኔ ስትል ከሆነ አሁን ይቅርና ደስ ያለ ቀን ኢንተርቪው ትሰጠኛለህ አልኩት

እንቢ ሲለኝ ደብሮኝ ነበር ቀርፀን እናስቀምጠው ያለኝን እሺ ባለማለቴ ደግሞ የበለጠ እንድከፋ አድርጎኛል
የድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ ይወጣል !

በዘመን አይሽሬ ድምጿ እና ከመድረክ አያያዟ በተጨማሪ በራሷ ተወዳጅ ግጥምና ዜማዎቿ የምትታወቀው ተወዳጇ ድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ እንደሚወጣ ሰዋሰው መልቲሚድያ አስታውቋል፡፡

በያዝነው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ለሕዝብ የተዋወቀው እና ከመቶ በላይ አንጋፋና ወጣት ተወዳጅ ድምጻዊያንን በጋራ ለመስራት ያስፈረመው ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ፤ አስር የሙዚቃ ስራዎችን ያካተተው የድምጻዊቷ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበምን የጥምቀት ዋዜማ በሰዋሰው መተግበሪያ በኩል ለአድማጮች ያደርሳል ተብሏል፡፡

ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ/ም ድምጻዊ አስቴር አወቀ ከሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጋር ስትፈራረም የሰዋሰው የማኔጅመንት አባላት ድምጻዊ አስቴር አወቀ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ድምጻዊት አስቴር አወቀ ከዚህ በፊት ሃያ አራት የሚደርሱ ዘመን አይሽሬ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችን እና ሁለት ነጠላ ዘፈኖችን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ያደረሰች ሲሆን “ሶባ” ሃያ አምስተኛ አልበሟ ነው፡፡

ድምጻዊቷ ከሃገር ውስጥም በተጨማሪ በታላላቅ ዓለማቀፍ መድረኮች ስራዎቿን በማቅረብ ከፍተኛ አድናቆትን በማግኘት ኢትዮጵያዊቷ የሶል ሙዚቃ ንግስት በመባልም ትታወቃለች፡፡
ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጥበበኞች የሚገባቸውን የፈጠራ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ የሃገራችን ጥበብ ባህር ማዶ ተሸጋሪ እንዲሆን ለማስቻል በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የተቋቋመ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡
የ9ተኛው ዙር የጉማ ሽልማት ጋዜጣዊ መግለጫ

በ2014 አ.ም በሀገራችን ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ ለእይታ የቀረቡ ፊልሞች ውስጥ 22 ፊልሞች ለውድድር ቀርበዋል። በተጨማሪም ከጉማ ጅማሬ አንስቶ በተለያዩ ሙያተኞች ሲጠየቅ የነበረው የተከታታይ ፊልም ምድብ እና የዘጋቢ ፊልሞችን በዚህ አመት እንዲካተቱ ተደርጔል።

በዚህ አሞት ዘርፎቹ ወደ 29 አካባቢ ከፍ ያሉ ሲሆን የጉማ የህይወት ዘን ተሸላሜ ዘርፍ ፤የጉማ የሄርሜላ የሴቶች ሽልማት ተሸላሚ፤ የጉማ የበጎ ስራ ተሸላሚ ብቻ ያለውድድር በኮሚቴው ጥናትና ምርጭ ይወሰናሉ፡፡
#gummaawards #accessaddis #AddisAbeba #BedeleSpecial #heninkin #skylight
2024/11/26 21:19:44
Back to Top
HTML Embed Code: