Telegram Web
በጦርነቱ ምክንያት የተዘረፉ ቅርሶች ebay ላይ እየተሸጡ ነው😢

@Aethiop
የፍቅረኞች (Valentines) ቀን በዓል- ድብቅ ሠይጣናዊ ሴራ
================================
ስንቶቻችን ይሆን የቫለንታይን ቀን(የፍቅረኞች ቀን ብለን የምናከብረው) የሚከበርበት ምክንያትና መነሻው የምናውቀው? ወይስ ሰው ስለ አከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው?

ክርስቶስ ከመወለዱ ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት አረማዊ ሮማውያን የካቲት 14 ማታና የካቲት 15 "የተኩላ አዳኙ"ለሚሉት ሉፐርኩስ(Lupercus) ክብር በማለት በጣኦት አምልኮ ያከብሩት ነበር። ሮማውያን ይህ በዓል ሉፐርካልያ (Lupercalia) ይሉታል። ንጉሥ ቆንጠንጢኖስ ክርስትና
የሮማውያን ይፋዊ ሃይማኖት መሆኑ በማወጁ ማንኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተወስኑ ሮማውያን ሰዎች ግን በዓሉን ማክበር አልተዉም። ይህንን አረማዊ በዓል ማለትም ሉፐርካልያ የሮማው ጳጳስ ገላስዮስ ክርስትያናዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር አደረጉ። ጳጳስ ገላስዮስ የካቲት 15 ሲከበር የነበረው በዓል የቅዱስ ቫለንታይን ቀን በሚል አዲስ ስያሜ የካቲት 14 እንዲከበር አደረጉ።

እንዴት ይህ አረማዊ በዓል የቅዱስ ቫለንታይን ቀን የሚል ስያሜ ተሰጠው?
ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው። ቫላንታይን ጥንታዊው ታዋቂው ሉፐርኩስ ነው። ሉፐርኩስ በግሪካውያን ፓን(pan) ተብሎ ይጠራል። በጥንታውያን አይሁድ ደግሞ ባል(Baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል። ባል በመጽሓፍ ቅዱስ ዘፍጥረት 10-9 ላይ ታላቁ አዳኝ ተብሎ ለተገለጸው ኒምሮድ ሌላኛው መጠርያው ነው። ኒምሮድ የሮማውያን የተኩላ አዳኙ ሉፐርኩስ ነበር። በዚህ መሠረትም የቅዱስ ቫለንታይን ቀን የአረማውያን ለኒምሮድ ክብር የሚያከብሩት የጣኦት አምልኮ ነው።

ቫለንታይን የሚል ቃል ቫለንቲኑስ(valentinus) ቫለንስ ከሚል የላቲን ቃል የመጣ ነው። ቀጥተኛ ትርጉሙ ጠንካራ፣ ሃይለኛ ታላቅ ማለት ነው። ዘፍጥረት10 - 9 ላይ እንደምናነበው " እርሱም በእግዚአብሔር ፊት አዳኝ ነበረ ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት ሃያል አዳኝ እንደ ኒምሮድ ተባለ።" ኒምሮድ የሮማውያን ጀግና ሃይለኛ ሰው ቫለንታይን ነበር።
ሌላኛው የኒምሮድ ስም ሳንክቱስ(Sancutus) ወይ ሳንታ (santa) ነው ሳይንት(saint) የሚል የእግሊዝኛ ትርጉም አለው። ማለትም ቅዱስ የሮማውያን ሉፐርካልያ በመጨረሻ ቅዱስ ቫለንታይን የሚል ስያሜ ያዘ ማለት ነው።

ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን በቀዱት አረማዊ የልብ(heart) ምልክት ይጠቀማሉ። በባቢሎናውያን ባል(bal) ልብ የሚል ፍቺ ነው ያለው። በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን(የፍቅረኛሞች ቀንየምንለው) መገለጫ እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን የጣኦት ጌታ ነበር። በሌላ መንገድም ኒምሮድ ወይም ቅዱስ ቫለንታይን ሳተርን ተብሎ ይጠራል። ሳተርን የሮማ-ባቢሎን ከአባራሮዎቹ ለመሸሽ በምስጥራዊ ቦታ የሚደበቅ ጣኦት ነው። ሳተርን የሚል የላቲን ቃል ሴመቲክ(አይሁድ) ቋንቋ ከሚናገሩ ባቢሎናውያን የተገኝ ነው። መደበቅ፣ራስን መደበቅ የሚል ፍቺ አለው። በጥንታዊ እምነትም ኒምሮድ(ሳተርን) ከአባራሮዎቹ በመሸሽ ወደ ጣልያን እንደተጓዘ ይነገራል።የአፐኒን ተራራ ስያሜው ወደ ኔምብሮድ ወይም ኒምሮድ ተቀየረ። ይህ ተራራ ኒምሮድ በጣልያን የተሸሸገበት ቦታ ነበር። ሮማም በዚ ተራራ ላይ እንደ ተመሰረተች ይታወቃል። ሮም ፈርሳ እንደገና ከመሰራትዋ 753ዓ/ዓ በፊት ሳቹርንያ (ሳተርን፡ኒምሮድ የተደበቀባት ቦታ) የሚል ስያሜ ነበራት። ኒምሮድ በዚህ ቦታ ተይዞ በፈጸመው ወንጀል ተገደለ። በንጉሥ ቆንጠንጦኖስ ጊዜም ክርስትያናዊ ሰማዕት የሚል የውሸት ክብር ተሰጥቶት በሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መዘከር ጀመረ። ኒምሮድ፣ ባል፣ ቫለንታይን፣ ታላቁ አዳኝ፣ ፋውኑስና ሉፐርክስ 31ኛ፣32ኛና 33ኛና ደረጃ (ዲግሪ) ላይ ያሉ
ፍሪማሶኖሪዎች ከሚያመልኩት ባፎሜት(የሜንደዝ ፍየል) ጋር የሚስተካከል ነው።

እንግዲህ በሰላቢ እጆች (ኢሊሙናቲ) ሴራ ዘመናዊነት ተላብሶ ድብቅ ጣኦት የሚመለክበት የቅዱስ ቫለንታይን ቀን እኛ ደግሞ የፍቅረኛሞች ቀን በማለት እያከበርን ማለትም እያመለክን ነው። አንድ በአል የሚከበርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሊኖረው ግድ ነው። ሆኖም የምናከብረውን በአል የምናከብርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሳናውቅ ከሴሮኞች ድብቅ አላማ ማስፈጸምያ ከመሆን መቆጠብ ይበጃል።

@Aethiop
Simpsons 2022 prediction
@Aethiop
አዲስ ነገር የለም!

@Aethiop
በቺካጎ ሙዚየም የሚገኘው እና 3000 ዓመት ያስቆጠረው የግብፅ ሀውልት🤔

@Aethiop
Forwarded from ኖህ ኢትዮጵያ
👉ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ እየሆነ ያለው ምንድን ነው? አላማውስ?

ኢትዮጵያ ከዓለም በተለየ መልኩ ለረጅም ሺህ ዓመታት ፈጣሪዋን አጥብቃ የያዘችና የምታመልክ ሀገር መሆኖ ይታወቃል። ከዛም ባለፈ ኢትዮጵያ ታላላቅ ሚስጥሮችን የያዘች ሀገር መሆኗም ይታወቃል። ከነዚህ ሚስጥራት መሃከል ፈጣሪ ከአዳም ነጥቆ በኪሩቤልና ሱራፌል ነበልባል እሳት የሚያስጠብቀው የህይወት ዛፍ አንዱ ነው። የህይወት ዛፍ አዳም ከፈጣሪ ትዕዛዝ በወጣ ጌዜ የተነጠቀው ዘላለማዊ ህይወትን የሚሰጥ ሞትን የሚያስቀር ዛፍ ነው።ይህ የህይወት ዛፍ በጣና ኢትዮጵያ ነው የሚገኝው።

ይህን ጠንቅቆ የሚያቀው ዲያቢሎስ የህይወት ዛፍ መገኛ የሆነችውን ኢትዮጵያ በመቆጣጠር ለሰው ልጅ ዘላለማዊ ህይወት በመስጠት ለሱ የተገዙና ለሱ እየሰገዱ እንዲኖሩ ለማረግ አጥብቆ ይሻል። ያ ብቻም ሳይሆን በመጨረሻው የዓለም ፍፃሜ ውጊያ አርማጌዶን ፈጣሪን ረቶ መላ ፍጡርን ለመግዛት ያልማላ። ትላንትም ታላቅ ስልጣኑን አሳጥቶ ወደ ሲኦል እሳት ያስጣለውን ይህ ስልጣን ወዳድነቱና የፈጣሪን ቦታ መሻቱ ዛሬም አለቀቀውም።

ታዲያ ይህን እቅዱን ለማሳካት ማለትም ፈጣሪን በአርማጌዶን ውጊያ ለመርታት ብሎም በጣና በስውር የሚገኘውን የህይወት ዛፍ በእጁ ለማስገባት ታላቅ ፈተና የሚሆኑብኝ የሚላቸው ለፈጣሪ የሚገዙ ህዝቦችን ነው። በመላ ዓለም ያሉ አማኝ ህዝቦችን በስልጣኔ ስም በተለያዩ ሴራዎች ከሀይማኖት አስተምህሮ እያራቀ ኢ አማኝ ይሆኑ ዘንድ ብዙ ተግቷል በብዙም ተሳክቶለታል። ታዲያ በመላ ዓለም ማፍረክረክ የቻለውን ሀይማኖት በኢትዮጵያ ብቻ ማሳካት አልቻለም። የህይወት ዛፍ በምትገኝበት ብሎም የመጨረሻው ውጊያ አርማጌዶን በሚካሄድባት ኢትዮጵያ ሀይማኖትና ሃይማኖተኞች እያሉ ፈፅሞ ህልሜን ማሳካት አልችልም የሚለው ሳጥናኤል ፤ ኢትዮጵያን ዋና ጎሌ ናት ብሎ ከተነሳ ረዘም ያሉ ዓመታት ተቆጥረዋል።

በኢትዮጵያ ሀይማኖትን ለማፍረክረክና ህዝቡን እንደሌላው የአለም ህዝብ ኢ አማኝና የሱ ተከታይ ለማረግ በግብርአበሮቹ ኢሉሚናቲዎች አማካኝነት አንድ እቅድ ነድፎ በመሥራት ላይ ይገኛል። ይህም 'ኢትዮጵያንን በኢትዮጵያውያን የማፍረክረክ እቅድ ነው። ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ ሊአፍረከርኳቸው የመጡትን ጠላቶች ሁሉ በመመከትና በመደምሰስ ፍፁም መሆናቸውን የተረዱት እኒህ የሳጥናኤል አላማ አስፈፃሚዎች ኢትዮጵያን በራሷ ልጆች(ባንዳዎች) ለማፍረክረክ ወስነው ወደተግባር ገብተዋል። እኤአ ከ2014 በፊት የዓላማችን አስፈፃሚ ይሆናሉ ያሏቸውን 180 ኢትዮጵያውያን በየዘርፉ መልምለው በተለያየ ሽፋን ወደ አሜሪካ በመላክ በሲአይኤ በኩል ከፍተኛ የተባለ ስልጠና እንዲሰጣቸው አድርገዋል። ይህ በአይነቱ ረቀቅ ያለ ስልጠና እኒህን ሀገራቸውን ለማፍረክረክ ለተስማሙት 180 ባንዳዎች ትልቅ ችሎታን ያላበሰ ነበር። ከሰው ሳይኮሎጂና የማሰብ አቅም በላይ በሆነ መልኩ ተልኳቸውን ለመከውን የሚያስችላቸው ረቂቅ ስልጠናም እኤአ በ2014 ዓም አጠናቀው ለመመረቅ ችለዋል። ከዛ በኋላ ባለው ጊዜ ወደ ኢትዮጵያን በመግባት በመንግሥት ደረጃ
የስልጣን መንበር ላይ በመቆናጠ በግል ደረጃ ደሞ በሁሉም ዘርፍ ወሳኝ ቦታዎችን በመያዝ ስራቸውን በረቀቀና በተናበበ መልኩ በመከወን ላይ ይገኛሉ። እኒህ 180 ሀገራቸውን ለማፍረክረክና ለመሸጥ የተመለመሉ ባንዳዎች ዋና አላማ የሚከተሉት ናቸው

1. በሀገሪቱ ያሉ ሀይማኖትና ሃይማኖተኞችን በተቻለ ሁሉ ማፍረክረክና ኢ አማኝ ማድረግ። የሀይማኖት ተቋማትን ማውደም አባቶችንና ሀይማኖተኛውን መግደል ወዘተ....

👉 በሀገራችን ብዛት ያላቸው ገዳማት ፣ ቤተክርስቲያንናትና መስኪዶች በረቀቀ ሴራ በየቀኑ እየወደሙ እንደሚገኙ ልብ በሉ።
👉 በርከት ያሉ የሃይማኖት አባቶች በጅምላ እየተረሸኑ ነው።
👉 በየጊዜው እንደ ቀልድ ከባባድ እሳቶች እየተነሱ ገዳማት ፣ አድባራትና ታላላቅ ቦታዎች እንዲወድሙ እየተደረገ ይገኛል።
👉 በቀጣይ ደሞ የለየለት የሃይማኖት ግጭት አስነስቶ ተቋማቱን ለማፍረክረክ እየተሰራ ይገኛል።

2. ጠንካራ ሀገራዊ ፍቅርና ስሜት ያለው ትውልድ እንዳይፈጠር ከስር ከስር መስራት። ሀገር ወዳዱን ማህበረሰብ መረሸን መጨፍጨፍ ማዳከም

👉 ስለ ሀገራችን ያገባናል ፣ ባህልና እሴቶቻችን አይሸርሸሩ የሚል ጠንካራ ማህበራዊ መሠረት ያላቸውን ህዝቦች የመጨፍጨፍ ስራ በብዛት እየተከናወነ ይገኛል። በሲአይኤ በኩል ባሰለጠኗቸው አክቲቪስት ኢትዮጵያዊን አማካኝነት እኒህን ሀገር ወዳድ ህዝቦች የተለያየ ስም በመስጠት ለማመን በሚከብድ ቁጥር በሌላው ህዝብ ይጨፈጨፉ ዘንድ የሴራ ስራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ። ከሰሜን እስከ ደቡብ በብሄርና ፖለቲካ ግጭት ስም በገፈ የሚቆጠሩ ሀገር ወዳድ ማህበረሰቦች የጅምላ ጭፍጨፋ የሚደረግባቸው መንግስት አቅም አጥቶ ሳይሆን ስውር አላማቸው በማስፈፀም ላይ ስለሆኑ ነው።

3. የኢትዮጵያ እሴቶችን በነደፉት የተለያዩ የሴራ ስልቶች በመሸርሸር በሰይጣኒዝም ሀይማኖት እሴቶ መተካት። ማለትም ግብረሰዶማዊነት ፣ ልቅነት ፣ እራስ ወዳድነት፣ ገንዘብና ዝና ወዳድነት ወዘተ.....

👉 ትውልዱ ከሀገሩ እሴቶች ይልቅ በምዕራባውያኑ ልቅ ባህል ይሳብ ዘንድ ከ30 ያላነሱ ቻናሎችን በመክፈትና ሶሻል ሚዲያውን በመጠቀም ስልጠናውን በሰጧቸው የተለያዩ አባሎቻቸው በኩል ከፍተኛ የሆነ የትውልዱን አእምሮ በማጠብ ላይ ይገኛሉ።
👉 በተለይ ኢንርኔትና የቲቪ ቻናሎች ዋጋ እጅግ እርካሽ እንዲሆን የተደረገው አዋጭ ሁኖ ሳይሆን የትውልዱን አይምሮ ለመሸርሸር ሁነኛ አማራጭ ስለሆነ ነው። በቀጣይ ደሞ ኢንተርኔትን በየቤቱ በነፃ ሁላ ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል።

4. በኢንዱስትሪ ማስፋፋትና ስራ ፈጠራ ስም ለመጨረሻው የአርማጌዶን ውጊያ ይሆነናል የሚሉትን ቦታዎች በኢንዲስትሪ ፖርክ ስም ከልሎ በመያዝ የረቀቁ መሳሪያዎች ማምረት። እነዚህ ቦታዎች ወሳኝና እስትራቴጂካዊ ቦታዎች ከመሆን ባለፈ ከፍተኛ የሆኑ ረቂቅ ማዕድናት የያዙ ስፍራዎች ናቸው።

👉 በነገራችን ላይ አብዛኞቹ የኢንዱስትሪ ፖርኮች የተገነቡት ገዳማት አድባራትና መስኪዶች በነበሩበት ባሉበት ስፍራ ነው። አባቶቻችን እኒህን ስፍራዎች በመንፈስ እየተመሩ ቀድመው አውቀው የያዟቸው አስፈላጊነታቸውን ስለተረዱት ነው።

5. በቴክኖሎጂና ዘመናዊነት ስም ረቂቁንና መላ ህዝቡን በቁጥጥር ስር የሚከተውን ማይክሮ ቺፕ በመላ ኢትዮጵያዊያን መቅበር ይገኙበታል።

👉 በአሁኑ ሰዓት መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው የዲጂታል ገንዘብ ልውውጥ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ለማጥመድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ነው።

6. Privatization! ሀገራችን ኢትዮጵያን በዘመናዊነት መውረስ። የኢትዮጵያን የጀርባ አጥንት የሆኑ ተቋማት ለምዕራባውያኑ መሸጥ።

👉 ኢትዮቴሌኮም በከፊል ተሽጧል። በቀጣይ ደሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ ፣ መብራት ሀይልን ፣ የማዕድን ቦታዎችን ፣ ኢንደስትሪ ፖርኮችን ወዘተ ለመሸጥ ታቅዷል።

7. ወዘተ.....

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የሚደረጉ አብዛኞቹ ነገሮች በሴራ የተተበተቡና ፍፁም ሰይጣናዊ መሆናቸውን ልናስተውል ይገባል። በስሜት ተነሳስተን ከመወሰናችን በፊት ደጋግመን ማሰላሰል ይገባናል።
Forwarded from ኖህ ኢትዮጵያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ዋና ስር መሠረታዊ ችግር - አንቀጽ 39

ምዕራባውያኑ ስለ አንቀጽ 39 በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም የሰጡት የሴራቸውን ማብራሪያ አድምጡት። ሀገሪቱን በብሔር ብሔረሰብ መብት ማስከበር ስም በህገመንግስቱ እንዲካተት የተደረገው በማር የተለወሰ መርዝ አንቀፅ አደገኝነት በሰፊው ተብራርቶበታልና አድምጡት ሼርም ተደረጋጉት። አዲሱ ትውልድ ሊነቃና ካለፈው ታሪኩ ሊማር ይገባዋልና።
Forwarded from ኖህ ኢትዮጵያ
ስለ NIKE ጫማ ማወቅ ያለብን

Nike በአለማችን ተወዳጅ የሆነው Brand ጫማ ስያሜውን ያገኘው ከጥንት የግሪክ አማልክት የ Pallas(Titan) እና የStyx ልጅ ከሆነችው Nike ነው ፡፡Styx መሬትንና የሲዖልን መግቢያ የሚከፍል ወንዝ ነው ብለው ግሪኮች ያምኑ ነበር፡፡
Nike የጥንታዊ ግሪኮች ጣዖት የነበረች ሲሆን የፍጥነት የጥንካሬና የድል አምላክ ብለው ያመልኳት ነበር፡፡መመለኳም አሁን ድረስ ቀጥሏል፡፡

Nike በ Zeus(የጥንት ግሪክ ዋና አምላክ) የፍጥነት የጥንካሬና የድል አምላክ ለዘላለም እንደሆነች ቃል ስለተገባላት አምላክነቷ አሁንም ድረስ ቀጥሎ በእሷ ስም የተሰየሙት ምርቶች የሚከተሉት ናቸው፡
1.Honda motor cycles የ Nike'ን ምልክት እንደ አርማ/logo ይጠቀማል፡፡
2.በአሜሪካ anti aircraft missile system የ nike'ን ምልክት ይጠቀማል፡፡
3.በዋነኛነት የ nike ጫማ አምራች የ nike'ን ምልክት ይጠቀማል፡፡

ስለዚህ አብዛኞቻችን የምንጠቀመው Nike ጫማ ሰይጣንን የሚወክል ስለሆነ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡በዙ ሰወች "ካላመለኩት ምን ችግር አለው" ይሉ ይሆናል ነገር ግን እኛ የእግዚአብሔር ተከታዮች እንጂ የሰይጣን አደለንም፡፡ ሰይጣን አምላኪዎቹ ኢሉሚናቲዎች ብዙ በጀት መድበው ይህንን ሁሉ የሚከውኑት የሚያመልኩትን ሰይጣን ከፍ ከፍ ለማረግና የዓለም ህዝብን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሱ አቀንቃኝ ለማረግ ነው።

አሁን አሁን ላይ ለእኛ ለክርስቲያኖች ጊዜው ከባድና በፈተናዎች የተሞላ ነው::እያንዳንዷን እርምጃችን ቆም ብለን ማሰብ ይገባናል፡፡ምክንያቱም እኛ ግሎባላይዜሽን በሚባል በዘመናዊ ባርነት የታጠርን ሰወች አብዛኛው እንቅስቃሴያችን በእኛ ሳይሆን የሰይጣን ጭፍራ በሆኑ ሀገሮች የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡የሚሰጡንን ቀጥታ እንቀበላለን ለምን ብለን አንጠይቅም። የእነሱን እንቀበላለን የእኛን እንንቃለን የእነሱ የሆነው ሁሉ ይጥመናል፡፡ ነገር ግን ምን ያህል ስለምንከተላቸው ሰወች ፣ ስለ አለባበሳቸው ፣ ስለምንመገበው ምግብ ፣ ስለምንጠቀመው ቴክኖሎጂ እናውቃለን?

አሁንም ለመንቃትና ለማስተዋል ጊዜው አረፈደም!

#ፀረ_ኢሉሚናቲዝም
Forwarded from ኖህ ኢትዮጵያ
ቅዱስ ጊዮርጊስ - ቢራ ወይስ ሰማዕት?

የቅዱሳን ስዕል አድህኖ በክብር መቀመጥ ሲገባው የቅዱስ ገዮርጊስ ስዕል ግን

1/ በየጠርሙሱ ተለጥፎ የሰካራም እጅ ያለ ንጽህና በድፍረት ይጨብጠዋል።

2/ ስዕል አድህኖው በየመጠጥ ቤቱ እየወደቀ ይረገጣል። ከቆሻሻ ጋር ተጠርጎ ይጣላል።

3/ በስሙ ታቦት መቀረጽ ሲገባው የሚያሰክር መጠጥ ሆኖ ስሙን ለማርከስ ተሰርቷል

4/ ኢትዮጵያ ከሰማዕቱ የምታገኘውን ክብርና ጥበቃ ለማሳጣት በ1915 ዓ.ም ጣሊያኖች አቅድው አቋቋሙት።

የሚገርመው መጠጡን የሚጠጣው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዩ ነው።
አንዳዴ እንደቀላል የምናያቸው ነገሮች ከፍተኛ የሆነ ጥፋቶች ናቸውና እንንቃ።

ይህን ጽሁፍ ያነበበ ለነፍሱ ይወስን!
2024/09/28 05:47:10
Back to Top
HTML Embed Code: