Telegram Web
🌷🌷የጁመዓ ቀን ሱናዎች 🌷🌷

💫🌷🌷سنن يوم الجمعة
1⃣💫 الغسل
💫 الطيب
➌  💫 السواك
➍  💫لبس الجميل
➎  💫قراءة سورة الكهف
➏   💫 التبكير لصلاة الجمعة
6️⃣  💫الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي

1🌷መታጠብ
2🌹ሽቶ መቀባት
3🌹 ሲዋክ መጠቀም
4🌹 ጥሩ ልብስ መልበስ
5🌹ሱረቱል ካህፍን መቅራት
6🌹 ለጁመዓ ሶላት መሄድ
7🌷በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን ማብዛት



እንዲሁም ብለዋል ﷺ የጁመዕ ሌሊትና  ቀኑ ለይ በኔ ሰለዋትን  አብዙ ሶለዋታችሁ እኮ ለኔ ይቀርብልኛል

اللَّهُمَّ صلِّ عَلَى مُحمَّدٍ وعلى آلِ مُحمَّدٍ
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آل إِبْرَاهيم إِنَّكَ حَميدٌ مَجيد

ﷺ ........ ﷺ
ﷺ ﷺ ......... ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ.......ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ    ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّ

👋🌹 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

🌹 الدال على الخير كا فاعله

قال رسول الله ﷺ
من دلّ على خير فله مثل أجر فاعله  رواه مسلم
👉📲لمتابعة القناة على التليجرام
🌺💬 ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን
سورة الكهف 01
<unknown>
የጁመኣ ስጦታዬ
ቁርአንን የቻለ ይቅራ ያልቻለ ያዳምጥ
መልካም ጁመዓ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌹ጁመአ
🌹 ሰለዋት
🌹 ዱአ … 

ረሱልም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

🌸﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾

🌸“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”

📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል: 1531

በሌላ ሀዲሳቸው ﷺ፦

🌺﴿أكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يومَ الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ، فمَن صلّى عليَّ صلاةً صلّى اللهُ عليهِ عَشرًا.﴾

🌺“በጁምዓ ቀንና ሌሊት በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ። በኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ: 1209

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

💥﴿إنّ في الجُمُعَةِ لَساعَةً، لا يُوافِقُها مُسْلِمٌ، يَسْأَلُ اللهَ خَيْرًا، إلّا أعْطاهُ إيّاهُ.﴾

💥“በጁምዓ ቀን አንዲት ሰዓት አለች። በዛች ሰዓት አንድ ሙስሊም አላህን መልካምን ነገር እየጠየቀ አይገጥምም፤ ለሱ የጠየቀው የሚሰጠው ቢሆን እንጂ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 852

🌸የጠዋት ዚክር ማለትን አትርሱ
የላቀው አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል

🌸وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

🌹የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

በመልካም ነገር ተበራቱ ወንድም እህቶቼ😍
አላህ  صباحه على وتعالي ሰባት ነገሮችን ይወዳል

①☞ተውበት  “አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል”
አል በቀራህ ☞2:222

②☞ ጦሀራ ☞“አላህ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡”
☞አል በቀራህ 2:222

③ ☞ተቅዋ  ❥አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡” ☞አተ ተውባ 9:4

④ ☞ኢህሳን  ❥ “አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡”
☞አል ኢምራን 3:134

⑤ ☞ተወኩል ❥“አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና”
❥ ☞አል ኢምራን 3:159

⑥ ዐድል ❥ “አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና፡፡”
☞አል ማዒዳህ 5:42

⑦ ☞ሶብር ☞”አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡
☞”አል ኢምራን3:146

☞ሼር አድርጉ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቁርአን የልብ ፈውስ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንደት አደራችሁ
እንግዲህ ሻዕባን ገብቷል በሌላ ቋንቋ ታላቁ ረመዳን እንደገባ ብንቆጥረው የተሻለ ነው። ረመዳን እየመጣልን ነው ብሎ መቁጠር ሳይኾን እኛ ወደ ረመዳን እየሄድን ነው ብሎ ማሰብ ይጠቅመናል። በዚሁ ማንነት ደጃፉ ላይ ቀርበናል። ቀድሞ ረመዳን ውስጥ የገባ ዕድለኛም አለ። ረመዳን ከገባ በኋላም ዘግይቶ ወደ ረመዳን የሚደርስ አለ። ረመዳንን ሳያገኘውም ሳይጠቀምበት የሚወጣው አለ! ረመዳንን አግኝቶ ሳይጠቀምበት የወጣ ሰው ላይ ጂብሪል እርግማን አውርዷል ረሱልም አሚን ብለዋል።

ቁርአን የሚለው "ወደ አላህ ሽሹ ነው!" ነፍሲያችን ደግሞ ተግባሯ ሲታይ "ከአላህ ሽሹ የሚል ነው! የሚመስልባት😐 ግድ የለም ውስን ቀናት አሉን፤ ብንን ብለው ከማለቃቸው በፊት አቅጣጫችንን እናስተካክል። ነፍስን ከሚያቆሽሽ ቂለ ወቃል እንውጣና ነፍስን ወደ ማከም እንመለስ።
ለረመዳን የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ከማዘጋጀት በላይ መንፈሱን ለማግኘት ራሳችንን እናሰናዳ! በተቀሩት ቀናት ቁርዓን እና የለሊት ስግደት ላይ በሚገባ እንሰነቅ ፣ ከአላህ ምሕረት ለማግኘት የሚያነሳሳን ቦታ ላይ እንገኝ።
ኢብኑል ቀይም በዚህ ጉዳይ ሲመክሩን እንዲህ ይሉናል ፦ « ቁርዓንን ማስተንተን እና በመጨረሻው ለሊት አላህን አብዝቶ መማጸን ለልብ ሕያው መሆን ቁልፍ ነገሮች ናቸው። »

በረመዳን ደጃፍ ላይ ሆነን ዝንጉ የሆንን ከመሰለን መድሐኒቱ ዚክር ነው። ከዚክሮች ሁሉ ቁንጮው ቁርዓን ነው ። ረመዳን ዛሬ እንደገባ እናስብ፣ ሁለመናችንን እንዲያስተካክልልን አላህን እንለምነው። አላህ ይህን ችሮታውን ይለግሰን ፤ ድክመታችንን በጥንካሬ ይለውጥልን

በረመዳን የሚጠቀመው ረመዳን ከመምጣቱ በፊት ወደ ረመዳን የሄደ ብቻ ነው!
#ተፍሲር_ሱረቱ_ኒሳዕ
#አያ_117

ሸይጧንን የማይኮንን ፣ የማያወግዝ ፣ የማይረግም የለም .. ግን በተጨባጭ ሸይጧን ነው የሚመለከው ። እንዴት? ቢባል ሽርክ ስሩ ብሎ ያዘዘው ማነው? መዕሲያ ስሩ ብሎ የሚገፋው ማነው? ለዚህ ብሎ አሏህ በሌላ አንቀፅ ምን ይላል፦ "አለም አዕሀድ ኢለይኪም ያበኒ አደመ አላ ተዕቡዱ ሸይጧን" ጠላት ነው ብያችሁ አልነበር? ለአደምም ገና ከመጀመሪያው "ኢነሃዛ አዱውን ለከ ወሊዘውጅክ" ብሎት ነበር .. ጠላትነቱ ጧት ነው የጀመረው ። ጠላትም አድርጋችሁ ያዙት ይለናል አሏህ ..

ምላሱን አለስልሶ ፣ አንገቱን አጎንብሶ ፣ ወዳጅ መስሎ ጠጋ ቢል አትመኑት! አደምንና ሀዋንም እየማለ ነው ገደል የከተታቸው ። በሱ ምክንያት አንድ ቅጠል ቀመሱ .. ከነዝርያቸው አፈር ላይ ተመልሰን ቀረን ። ከዚህ ተነስቶ ጀነት የሚገባ ይኖራል ፤ በዚሁ ወደ ጀሃነም የሚያመራም አለ ። እንዲህ አይነት ከይሲ ጠላታችሁን እንዴት ወዳጅ አድርጋችሁ ከዛም አልፎ አምላክ አድርጋችሁ ራሳችሁ ላይ ትሾሙታላችሁ? እነዚህ ከሃዲያን እያመለኩት ያሉትኮ መሪድ የሆነውን ሸይጧን ነው .. 

"መሪድ" ማለት አመፀኛ ፣ እንቢተኛ ማለት ነው።

«ለአነሁሏህ» አሏህ ረግሞታል ፣ ከእዝነቱ አባሮታል ፣ ከጉርብትናው አርቆታል ።

«ለአተሂዘነ» አለ ደግሞ እሱ ። አሏህ ሲያባርረው ማረኝ በማለት ፋንታ “ከባሪያዎችህ ቢያንስ የሆነ ድርሻ አገኛለሁ” አለ ። እንዴት አድርገህ? «ወለኡዲለነሁም» አጠማቸዋለሁ ፣ አስመስልባቸዋለሁ ። ከፊት ፣ በኋላ ፣ ከግራ ፣ ከቀኝ እመጣባቸዋለሁ ። ለማጥመም ደግሞ የምጠቀመው ዘዴ "ወለኡመኒየነሁም" አይዞህ እድሜህ ገና ነው! እያልኩ አስመኛቸዋለሁ .. ወንጀል ላይ ያለም ከሆነ “ዛሬ ቶብተህ እንዴት ትዘልቀዋለህ? አሁን ዝምብለህ ቀጥልና ልትሞት ስትል ትቶብታለህ” እያልኩ ተውበትን እንዲተው እሸላልምላቸዋለሁ ። የምኞት በሮችን ደግሞ እከፍትላቸዋለሁ ። ምኞት ድካም የለውም አይደል? የምኞት ሰነፍ የለም!

«ወለአሙረነሁም ፈለዩበቲኩነ አዛነል ዐንዓም»
አዛቸውና የእንስሳትን ጆሮዎች ይሰነጣጥቃሉ ። ጆሮዋን ይቆርጡና ይች ለሸህዬ ፤ ይች ለጅላኒ እንዲሉ አደርጋቸዋለሁ ። “እንስሳዎቹን በተለያዬ መልኩ ጆሯቸውን እየሰነጠቁ  እንዲለቋቸው አደርጋለሁ” አለ ። ሱረቱል ማዒዳ ላይ በሰፊው ይሄን ማዕና የያዙ አንቀፆች አሉ ። በሂራ ፣ ሳኢባ ፣ ወሲላ ፣ ሃም እያሉ ...

«ወለአሙረነሁም ፈለዩጘይረ ኸልቀሏህ» አዛቸውና የአሏህን ኸልቅ ደግሞ እንዲቀይሩ አደርጋለሁ ። ንቅሳት ፣ ውቅራት ፣ ታቶ እያሉ ሀውልት እንዲመስሉ አደርጋቸዋለሁ ።

«ወመን የተኺዚ ሸይጧነ ወሊየን ሚንዱኒሏህ » ከአሏህ ሌላ ሽይጧንን ረዳት ፣ ዋቢ አድርጎ የያዘ ሰው ግልፅ የሆነ ፣ የማይጠገን የሆነ ኪሳራ ከስሯል ። ዳግም ላያንሰራራ እስከወዲያው ነው የከሰረው ። የዱንያ ኪሳራ ቢሆን ዘመድም ፣ ባልንጀራም ፣ ጎረቤትም እርዳታ ጠይቀህ ታገግማለህ .. ይሄ የዲን ኪሳራ ግን በቃ አለቀልህ!

«የዒዱሁም» ቃል ይገባላቸዋል ። ይሄን አይነት ሽርክ ከሰራህ ንግድህ ትርፋማ ይሆናል ይለዋል ። ይሄንን ካደረግሽ ባልሽ ይወድሻል ፤ አያገባብሽም ይላታል ። ሄዳ ጠንቋይ በር ትቆማለች ወልኢያዙቢሏህ ። ይሄን ያደረገ ስልጣኑን አይነጠቅም ይለዋል .. አማካሪዎቹ ሳሂሮች ይሆናሉ ። አየህ አሁን በዱንያ ጥቅም ነው የሚያታልላቸው .. ከሌላው የበለጠ እድሜም ላይኖሩ ፤ ምናልባትም ያ የፈለጉት ነገር መጥፊያቸው ቢሆን ኪሳራውን ተመልከቱ ...

«ወማየኢዱሁሙሸይጧኑ ኢላ ጙሩራ» ሸይጧን ማታለል ካልሆነ በስተቀር ተጨባጭነት ያለው ቃል አይገባላቸውም ። በሱረቱ ኢብራሂም እንደተጠቀሰው ሸይጧን ለአምላኪዎቹ በቂያማ እለት እንዲህ ይላቸዋል፦ አሏህ የሃቅ ቃል ነበር የገባላችሁ ፥ እኔም ቃል ገባሁላችሁ (የባጢል ቃል ግን አላለም አሁንም አታላይነቱ አለቀቀውም🙃) ግን ወደኋላ አስቀረኋችሁ ። አሏህን ትታችሁ እኔን አመናችሁ ። ምን ላድርጋችሁ ታዲያ? እኔን አትውቀሱኝ ። እኔ በናንተ ላይ ማስረጃ የለኝ ፤ ስልጣን የለኝ ፤ ማስገደድ አቅም የለኝ.. ብቻ አስመሳይ ሆኜ ቀረብኳችሁ መሰላችሁና ተከተላችሁኝ ። እኔን አትውቀሱ ራሳችሁን ውቀሱ ፤ ምን አደረግኳችሁ እኔ? ብሎ ገደል ከከተታቸው በኋላ ተሳልቆባቸው አብሮ ጀሃነም ይገባል ።

ቀጥሎ በተቃራኒው ስለ ሙዕሚኖቹ ተናገረ ፦
«ወለዚነ አመኑ ወአሚሉሷሊሃት» ቀልባቸው ተስዲቅ አድርጎ አካላቸው ደግሞ በጎ ነገር ላይ የተሰማሩ ሰዎች በስሯ ጅረቶች በሚፈሱባት ጀነት እናስገባቸዋለን ። ጂረቱንም ደግሞ ወደፈለጉት አቅጣጫ በማመልከት ብቻ ይጠሩታል ። ቧንቧ አያስፈልገው ፤ ማስተላለፊያ ቱቦ አያስፈልገው ፤ ዘላለም ይኖራሉ መሰልቸት የለ ። ይሄ የአሏህ ቃል ነው ።

«ወመን አስደቁ ሚነሏሂ ቂላ» ለመሆኑ ከአሏህ የበለጠ ንግግሩ እውነት የሆነ ማን አለ? የአሏህን ቃል ፣ የአሏህን ተስፋ መቀበል ይሻላል ወይስ የአታላዩን ሽይጧን? ከአሏህ የተሻለ ምን አቅርቦላቸው ነው? ጀነት በእጁ የለ ፣ ጀሃነም በእጁ የለ ፤ ዱንያ በእጁ የለ .. ለዛውም ጠላት ነው ተብሎ ተነግሮ እሱን አምኖ አሏህን አልቀበልም የሚል ሰው በጣም ግብዝ ነው እያለን ነው ...!

ባረከሏሁ ሊ ወለኩም ፊልቁርአኒል አዚም ፣
ወነፈአኒ ወኢያኩም ቢማፊሂ ሚነል አያቲ ወዚክሪል ሀኪም🤲

መልካም ለይል
ሼር
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
ሼር
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
share/forward
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
ረመዳን ነክ
=============

ኢብኑል ጀውዚ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦

«በአላህ ይሁንብኝ፥ለቀብር ባለቤቶች "ተመኙ?" ቢባሉ ኖሮ፣የረመዳንን አንድን ቀን በተመኙ ነበር።»

[አት-ተብሲራ፡ 2/85]

እየመጣልን ነው እንግዳችን
ጥንቃቄ!

ረሱል (s.a
W) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تدْعوا على أنفُسِكم ولا تدعوا على أولادِكم، ولا تدْعوا على أموالكم، لا توافِقوا من اللهِ ساعةً يُسأَلُ فيها عطاءٌ، فيَستجيبُ لكم﴾

“በነፍሶቻችሁ ላይ በመጥፎ ነገር ዱአ አታድርጉ። በልጆቻችሁም ላይ ዱአ አታድርጉ። በገንዘባችሁም ላይ ዱአ አታድርጉ። አላህ የጠየቃችሁትን መቼ እሺ እንደሚልላችሁም ሆነ እንደሚቀበላችሁ አይታወቅምና።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 3009
1⃣«ነብያችን ለጂብሪል እንዲህ አሉት ጂብሪል ሆይ! ለምን ይሆን ሚካኢል ካየሁት ጀምሮ አንዲትም ጊዜ ሲስቅ የማላየው? እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው "ሚካኢል የጀሀነም እሳት ከተፈጠረች ጀምሮ ስቆ አያውቅም»።

ምንጭ፦📔ሲልሲለቱ ሶሒሀህ (739/6)

2⃣ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ ላይ እንደተወሳው የአላህ መልእክተኛ ረሱል (ﷺ)
👉በአብዘሀኛው ሰዎችን ጀነት የሚያስገባቸው ነገር ምንድ ነው ተብለው ሲጠየቁ
አላህን መፍራትና መልካም ስነምግባር ናቸው በማለት መለሱ
👉አብዘሀኛው ሰዎችን ጀሀነም የሚያስገባቸው ምንድ ነው ተብለው ሲጠየቁ
አፋቸውና ብልታቸው ነው በማለት መለሱ
በሰላት መሰላቸት

አንድ ሰው ሸሀዳ ሲይዝ ጀነት ውስጥ በጣም ሰፊ #ቦታ (ግዛት)  ይመራል  ይህ ቦታ  በርካታ  ነገሮች ሊኖረው ይገባል ይህ የሚሟላው በመልካም ስራ ልክ  ነው ስለዚህ  በርካታ መልካም ስራ ልንልክ ይጠበቃል አለበለዛ ምድረበዳ ይሆናል

ለዱንያ ስራ በየቀኑ ለብዙ ሰአት #እንለፋለን በቀን ቢያንስ ሶስት ጊዜ እንበላለን አይሰለቸንም ግን በሰላት እሰለቻለን, የምናገኘውን ምንዳ ብናቅ ኖሮ  እንኳን ፈርዱ ሱናው አይቀረንም ነበር ስለዚህ ምንዳውን እያሰብን እንበርታ

#ሰላት በትርፍ ጊዜ ወይም አንዳንድ ጊዜ የሚፈፀም ሳይሆን በወቅቱ በመደበኛነት መደረግ ያለበት ኢባዳ ነው ምክንያቱም  የቀልብ ምግብ ናት ኢማናችን እንዳይሞት ትከላከላለች.        

ነብዩ (ሰአወ  )     

     إِنَّ أَوَّلَ مَا يُحَاسَبُ بِهِ الْعَبْدُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ مِنْ عَمَلِهِ صَلاَتُهُ فَإِنْ صَلُحَتْ فَقَدْ أَفْلَحَ وَأَنْجَحَ وَإِنْ فَسَدَتْ فَقَدْ خَابَ وَخَسِرَ 

አንድ አማኝ  የፍርዱ  ቀን መጀመሪያ  የሚተሳሰበው  ሰላቱን ነው.  ሰላቱ ከተሟለች  ውጤታማ ይሆናል (ነጃ ይወጣል)  ከተበላሸች ግን ይከስራል. ቲርሚዚይ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰላሙ አለይኩም ያጀማአ
አህካሙ ሲያም የሚል ኪታብ በስድስት ተከታታይ የድምፅ ደርስ መልቀቅ ልጀምር ነው።
ያው ረመዷን ደጃችን ቆሞ እየጠበቀን ነው አስራምናምን ቀን ነው የቀረን።
እናም ደርሱ በጣም ያስፈልገናል ።እና ከእናንተ የምፈልገው ሼር እንድታደርጉ እና ስለረመዷን የማናውቀውን አውቀን የማያውቁትንም እናሳውቃቸው።
የእውቀት አንዱ መሰረት ያወቁትን ነገር ዳዕዋ ማድረስ ነው።
ይሄው ደርሱን መልቀቅ ጀምረናል እርሶም ሼር ማድረግ ይጀምሩ
Audio
2025/02/15 22:06:24
Back to Top
HTML Embed Code: