Telegram Web
የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 8
───────────
ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ሰደቃ የሚሰጥ የሆነ ሰው የሚሰጠው ሰደቃ በምስኪኑ እጅ ከማረፉ በፊት በአላህ እጅ ላይ እንደሚያርፍለት ቢያውቅ ኖሮ ተቀባዩ  ከሚያገኘው የደስታ ስሜት የበለጠ ሰጪው  ይደሰት ነበር።»

📚 ۞ مدارج السالكين【1/26】۞
──────────
Allaah The Almighty created mankind with an innate inclination to love those who are friendly. A person who meets others with a smile drives away their anxiety and troubles and spreads tranquility and comfort. This is because smiling is a commendable characteristic, and the one who smiles is complimente.
Sadaqah also describes a voluntary charitable act towards others, whether through generosity, love, compassion, or faith. These acts are not necessarily physical or monetary. Simple good deeds such as a smile, or a helping hand, are seen as acts of sadaqah.
እንደመልአክ መጥቶ እንደነብይ ታይቶ
እንደአምላክ ተወዶ እንዴ አማኝ አውርቶ
በዛ በዚህ ብሎ መግቢያውን ደላድሎ
አፉን ማር ቀብቶ በውስጡ መርዝ አዝሎ
ቀንሶ ጨረሰን እንደመር ብሎ
አይ አብይ
ገና እንደገባ የፊቱን ስርአት አሸባሪ አለው
የዋሁን የኔን ህዝብ
         ተደመሩ ብሎ በመርዙ ደለለው
መደመር የሚባል መፅሐፍ አሳተመ
ከሻዕቢያ ተታርቆ ኖቤል ተሸለመ
አለም ዘፈነለት ስለሱ ተወራ
ሙስሊም ክርስቲያኑን ሰበከ ተጣራ
የዋሁ የኔ ህዝብ ነብይ ነው ብሎ እስከሚጠራጠር
በ7አመቴ እናቴ ስለኔ ተንብያልኛለች ብሎ ስደሰኩር
እውነቱን ነው አለ ህዝቤ ድምፅ ሰጠው
ሸህ ሁሴን ጅብሪልም ተናግረውለታል
ብሎ ህዝቤ አሁንም
      ከትንግርተኞች ውስጥ ስሙን አስቀመጠው
መሰሪው አብይ ግን
ልክ እንደአገባቡ እንዳቀማመጡ
ትናንትና ዛሬ እንዴት ይቆይ ውስጡ
እስከምሽት ድረስ ጠብቆ የመረጠኝን ህዝብ
ስርአቱን የጠበቀ አስተዳደር ሊያገኝ ይገባዋል።
ብሎ ነበር የሆነ ሰአት
እኛ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን ብሎም ነበር
ለኛ የሚያስፈልገን ብቸኛ ነገር መደመር ብቻ ነው ብሎ ሰክሶን ነበር
አልገባንም እንጅ ንግግሩ ሁሉ
እንዳሰብነው ሳይሆን ሌላ ነበር ቅሉ
ተደመሩ ያለን አንድ ስንሆንለት ሊያጠፋን ከጅሎ
ነበር ለካስ ህልሙ ቢለይም ውሎ አድሮ
ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ
                                    ብሎ የሰከሰን
ለካስ በኛ ደም ነው ሀገር ሊገነባ እኛን ሊጨርሰን
አይገርምም
በመጀመሪያማ ሸይጣንም አንድ ቀን
                                              መልአክ ነበረ
ከፍጡሮች ሁሉ ልቅናው ያማረ
ግና ሲያልቅ አያምር ነውና ተረቱ
ገሀነም ሆነበት ዘላለም ህይወቱ
እኔ ልል ያሰብኩት ስለ ሰይጣን ህይወት
                 ስለመጨረሻው ገሀነም አይደለም
በህይወት እያለ ምን ያደርጋል ብየ ነው ምገጥም
አብይም እንደሱ እንደጀሌው ሰይጣን
ቤተ እምነት በማፍረስ ገነትን ሊያሳጣን
ሌት ተቀን ይሰራል አብሮ ከሰይጣን
አይ አብይ
ግና መቼ ገባው መስጅድ ሲያፈርስብን አንድ    
                                                  እንዳደረገን
ገደልኳቸው ብሎ በኩራት ሲኮፈስ ሸሂድ እንደሆነን
ይሄ እንከፍ የሰው ሞኝ
ይሰማ ከሆነ እስኪ ንገሩልኝ
በሰው ደም መጨቅየት ጌታን
                      መፈታተን ተው ይብቃህ በሉልኝ
ይህን የሰው ጭራቅ ጨካኝነት ይብቃህ ጭራቅነትን ሰልች ብሎሃል በሉልኝ።

በሃሚድ

https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
ደም ለማን ይስጡ? ከማንስ ይቀበሉ?

☑️ የደም አይነት: A+

🔸 ለማን ይሰጣል
ለ A+, AB+ ይሰጣል።
🔸 ከማን ይቀበላል
ከ A+, A-, O+ እና O- ይቀበላል።

☑️ የደም አይነት: O+

🔹 ለማን ይሰጣል
ለ O+, A+, B+, AB+ ይሰጣል።
🔹 ከማን ይቀበላል
ከ O+, O- ይቀበላል።

☑️ የደም አይነት: B+

🔸 ለማን ይሰጣል
ለ B+, AB+ ይሰጣል።
🔸 ከማን ይቀበላል
ከ B+, B-, O+ እና O- ይቀበላል።

☑️ የደም አይነት: AB+

🔹 ለማን ይስጥ፦
ለ AB+ ብቻ ይሰጣል።
🔹 ከማን ይቀበል፦
ከሁሉም ይቀበላል።

☑️ የደም አይነት: A-

🔸 ለማን ይስጥ፦
ለ A+, A-, AB+, AB- ይሰጣል።
🔸 ከማን ይቀበል፦
ከ A-, O- ይቀበላል።

☑️ የደም አይነት: O-

🔹 ለማን ይስጥ፦
ለሁሉም ይሰጣል።
🔹 ከማን ይቀበል፦
ከ O- ይቀበላል።

☑️ የደም አይነት: B-

🔸 ለማን ይስጥ፦
ለ B+, B-, AB+, AB- ይሰጣል።
🔸 ከማን ይቀበል፦
ከ B-, O- ይቀበላል።

☑️ የደም አይነት: AB-

🔹 ለማን ይስጥ፦
ለ AB+, AB- ይሰጣል።
🔹 ከማን ይቀበል፦
ከ AB-, A-, B- እና O- ይቀበላል።


➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 9
───────────
ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ሐቅ እንደተነጠረ ንፁህ ወርቅ ነው፤ በተፈተነ ቁጥር ጥራቱ ይጨምራል። ባጢል ደግሞ እንደ አርቲፊሻል ወርቅ ነው፤ በተፈተነ ቁጥር ግድፈቱ ይጎላል።»

📚 ۞ الجواب الصحيح【1/88】۞
───────────
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
ስለ ጠይረን አባቢል ምን አሳወቀህ?!

@degmolela

እርሱ እንደሌሎች ወፎች እንደሌሎች አዕዋፋት በምድር ላይ ጎጆውን ቀልሶ አይኖርም። ከድንቢጥ ወፍ ከፍ ከእርግብም አነስ ይላል። መልከ ጥቁር ነው። የገዘፉ ዓይኖቹ ጎላ ብለው ሰፊ አፉ ውበትን አላብሰውታል። እግሮቹ ላይ ያረፉት ትላልቅ ጥፍሮቹ ከትንሽነቱ ጋር አይመጣጠኑም። ግዙፍ ናቸው።

የተቀደሰውን ምድር የአላህን ቤት ካዕባን ለማውደም ወደ መካ ያቀናውን የአብርሃ አል አሽረምን ሠራዊት ለማጥፋት ለታላቅ ተልእኮ ታጭተው የተሰጣቸውን ግዳጅ ሊወጡ የመካን ሰማይ እየሰነጣጠቁ ህዋውን አጥለቀለቁ። በቡድን ቡድን ከየአቅጣጫው እየጎረፉ ወደ ውስጥ ዘለቁ። አባቢል ተብለውም ተሰየሙ።

እያንዳንዳቸው በጀሃነም እሳት ውስጥ የተነከሩ ሦስት የሸክላ ድንጋዮችን ይዘው ዘመቱ። ሁለቱን በእግራቸው አንዱን በአፋቸው ታጥቀው በአብርሃ ሠራዊት አናት ላይ ለቀቁት። በአናታቸው ገብቶ በፊንጢጣቸው በኩል እየወጣ የውስጥ አካላቸውን አንድዶ አንፈራፍሮ ይገላቸው ያዘ። የሸሸም ወደ ኋላ ያፈገፈገም አልተረፈም።

ይህ ወፍ ከተልዕኮው በኋላ በቅፅበት እንደታየው ጠፋ። አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር እርሱን ማየት ብርቅ ሆነ። ካልያዙት መሬት አያርፉም። ካላደኑትም በቀላሉ አያገኙትም። የዚህን ወፍ እንግዳዊ አወቃቀር ለማጥናት የአሜሪካ ሳይንሳዊ ተመራማሪዎች እስካሁንም ያድኑታል።

የዘመኑ አብረሀም የአላህን ቤት እያወደመ ነውና ጠባቂው ጌታ ምላሹ የከፋ ነው ኢንሻ አላህ።
የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 10
───────────
ኢማሙል_አልባኒይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ሐቅ ከባድ ነው፤ እናንተ ደግሞ በመጥፎ ባህሪያችሁ የባሰ ክብደት አትጨምሩበት። ከዚህ በፊት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግር “ዐቂዳ” ብቻ ይመስለኝ ነበር፤ አሁን ላይ ግን ችግራቸው  “ዐቂዳ እና መልካም ስነ ምግባር” መሆኑን ተገልፆልኛል።»

📚 ۞ سلسلـة الهـدى والنـور رقم【900】۞
─────────
https://www.tgoop.com/hamid
➡️የጧት ዚክር

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

▪️የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

ውሎህን በዚክር ጀምር
ትውልድ እናፍራ
እስኪ እናፍራ ትውልድ እስኪ እንገንባ ዜጋ
ለድኑ ሚዋደቅ ለእምነቱ ሚዋጋ
ነፍሱን ያሸነፈ በሱና ሚመራ
ወደተውሂድ መንገድ ሌላውን ሚጣራ
ውሎውን የሚያደርግ ከሷሊሆች ጎራ
ባለ ጠንካራ አቋም ኑ ትውልድ እናፍራ

ልክ እንደቢላል ያበሻው ሙአዚን
ለሰላት ኑ ብሎ በመልካም የሚያዘን
አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም ብሎ
ከእንቅልፍ የሚያነቃን በፍቅር አባብሎ
ምንም ባዶ ቢሆን ባይኖረው ከቤቱ
ለተራበ ሚሰጥ ሩህሩህ አንጀቱ
ጥቁር፣ ነጭ፣ቢጫ ቀለም ሳያማርጥ
ብሄር ሳይገድበው ድኑን የሚያስበልጥ
በእልፍ አመታት ታሪክ ስሙ የሚጠራ
እገሌ ነው ሲባልሀገሩን ሚያኮራ
እንደቢላል አይነት ኑ ትውልድ እናፍራ


የተነገረለት ፍትሀዊነቱ
እንግዳ ተቀባይ ለሰው ሰፊ ቤቱ
አቋምና መልኩን ሳይዩ በቅርቡ
የመሰከሩለት ስለመልካም ልቡ
ኢስላምን ተቀብለው ሲንገላቱ አስሀቡ
ሂዱ   ወደዛ ሰው ወደአርዱል ሀበሻ
በደል ከሌለበት ከርሱ መናገሻ
እዛ አትበደሉም ፍትህ አለው ፍርዱ
እዛ አንድሰው አለ ወደርሱ ዘንድ ሂዱ
ተብሎ በሩቁ እንደተወራለት
ያን ሰው የሚተካ ኑ ትውልድ እንመስርት
ደካማ ማይጨቁን ድሃን የማይበድል
በሩን የሚዘጋ ለአድሏዊነት እድል
በኢስላም ህገ ደንብ ህዝቡን የሚመራ
በእልፍ አመታት ታሪክ ስሙ የሚጠራ
የእርሱ ነው መባሉ ልጁን የሚያኮራ
የሚያፈርስ ሳይሆን መስጅድ የሚያሰራ
በደል አይን አውጥቶ እያየን ሲሰራ
በኢስላም ስብእና እኛን የሚመራ
ለነገ መሪያችን
እንደነጃሽ አይነት ኑ ትውልድ እናፍራ


የኢስላም ስም መጥፋት
                          የሚያንገበግበው
ከራሱ አስበልጦ ለድኑ ሚያስበው

ለኢስላም ከፍ ማለት ለልቅናው
                                             ብሎ
ለጅሃድ ሚወጣ በህብረት ሆ ብሎ
ብልህና ብርቱ በሁሉ ነገሩ
ደግ በሄደበት መልካም ስመጥሩ
እንደኢማም አህመድ ጠንካራ በድኑ
ራሱን የሚሰጥ ለእምነትና ቃሉ
ጥማቱ ለሆነው ሸሂድነት ለርሱ
በ አደብ በሱና የተገራች ነፍሱ
ድኑን ከነኩበት ለነፍሱ ማይራራ
ጠላትን ለመቅላት ጦሩን የሚመራ
በኢስላም ሞገሱ በጠላት ሚፈራ
ስልጣን የማያምረው አላህን ሚፈራ
ሰይፉ ስለፍትህ ዘውትሮ ሚያወራ
ከፍ የሚያደርግልን የኢስላምን ባንድራ
በጠላቶች ልሳን ተብሎ ቢሰየም     
                       ስሙ         ቢሆን ግራ
እንደኢማም አህመድ ኑ ትውልድ እናፍራ

ኑ ትውልድ እናፍራ
ኑ ዜጋን እንስራ
ተውሂድን እንስበክ መልካም ፍሬ እንዝራ
መስጅዶች ሲፈርሱ በፌስቡክ ዘመቻ
ነገር የሚያባብስ ያልሆነ ቃል ብቻ
ቲክቶክ ላይ ተጥዶ ሰላት የማያልፈው
በሱብሂ ሰላት የማያንቀላፋው
መስጂድ ላይ ዘውታሪ ጀማአ ማያልፈው
"የነገን ማን ያውቃል "እያለ አጉል ነገር ከማይፈለስፈው
ሀየ አለል ሰላህ እያለ ኢማሙ
                                 ለሶላት ሲጣራ
መስጂድ የሚቻኮል የሚሰግድ በጋራ
እመክራችኋለሁ ኑ ትውልድ እናፍራ


ዝሁር ላይ እመስጅድ አስር ላይ ሲኒማ
በመግሪብ ከኳስ ቤት ምሽቱን ቅምቀማ
ፈጅር ላይ ተኝቶ አይሰማ አይለማ
ወሬወቹ ሁሉ ስለኳስና ፊልም
ስራው ሴትን መልከፍ ውሎው ሰው
                                     መዞለም
ከእንደዚህ አይነቱ የራቀ የጠራ
ነገሩ በሙሉ በኢስላም የተሰራ
ከእዩልኝ የራቀ ለአላህ የሚሰራ
ከራሱ አልፎ ተርፎ ቤተሰብ ሚያስጠራ
በአደብ የተካነ ኑ ትውልድ እናፍራ


ቦረናው ሸህየ የጎንደር ቃጥባሬ
ነጃ በለኝ ከጉድ አድነኝ አድባሬ
ጌታው ደገርየ የሩቁን አዋቂ
የገሌው አውሊያ ከአላህ አስታራቂ
የታመመን ፈዋሽ የደከመን አንቂ
አውሬን አናጋሪው፨
የነገን መስካሪው
ነፍስያን አዋሪው ብለው ከሚሰብኩ
ፀበል ከሚራጩ ድንጋይ ከሚያመልኩ
ጅኒን ከሚገዙ በዛፍ ከሚመኩ
መውሊድ ትንሹ ኢድ ምናምን ምናምን
ክብሩን ከሚያጠፋ ከሚያረክስ ኢስላምን
ሸህና ወሊዩን ስሙን ከሚጠራ
አባባ ሸህየ ብሎ ከሚያጋራ
ከሽርክ የራቀ ለተውሂድ ሚሰራ
ቢድአ ሚጠየፍ ኑ ትውልድ እናፍራ
የኛ ውዱ ነብይ ልክ እንዳስተማሩን አድርጉ አታድርጉ ብለው እንደመሩን
በነብዩ ሱና አህላቁን አስውቦ
ባዘዙት ላይ ታዞ ባቀቡት ታቅቦ ሽርክን ተጠይፎ ተውሂድን አንግቦ
ሞት አፋፍ ላይ ሆነው አደራ ያሉትን
በምንም ሆኔታ የማይተው ሰላትን ፆሙንም የሚፆም ሰኞ ሀሙስ ሳይቀር
እጁ የረዘመ ለሌላው ሚቸገር
ሀጅን የሚፈፅም በተሰጠው ፀጋ
ችግሩን ብሶቱን ለአላህ የሚያስጠጋ
በጌታው ውሳኔ አንዳች ቅር የማይለው
የአላህ ቃል ቁርአን የማይነጠለው
የነብያት መንገድ መንገዱ የሆነው
መላኢካወችን እስከነስራቸው
አክብሮት የሚሰጥከአፉ ማይለያቸው የመጨረሻ ቀንቂያምን የሚፈራ
እንደዚህ አቢድ ሰው
ኑ ትውልድ እናፍራ።
በሃሚድ
@degmolela
June 1 2023
ነቢዩ ﷺ አንድ ጉዳይ ሲያሳስባቸው ሶሏት ይሰግዱ ነበር፤
"ያ ሀዩ ያ ቀዩም ቢረህመቲከ አስተጊስ" ይሉም ነበር።።
እንዴት አመሻቹሁ ተማሪዎች ምን እያሳሰባቹህ ነው ?
አንዳንድ ጊዜ ራሴን ከሌሎች ሰዎች ጋር ሳወዳድር ማንም እንደእኔ እድለኛ እና ሙሉ ሰው ያለ አይመስለኝም።
በርግጥም የለም ፣ኢስላም ሙሉ ያደርግሃል ፣ የነብዩ ኡመት መሆን ደግሞ ከሙሉነትም በላይ እድለኝነት ነው።
ነብዩ ለተከተላቸው ሰው ራሳቸውን የቻሉ አንድ ህይወት ናቸው።
ነብዩ ላነበባቸው ሰው ራሳቸውን ችለው በዚህ አለም ላይ አሉ የሚባሉ መፅሀፍት በሙሉ በነብዩ ህይወትና አስተምህሮ ላይ አለ።
አንድ ሰው ታሪክ፣ወይም ልብወለድ አሊያም አነቃቂና ለህይወት መመሪያ ሊሆን የሚችል አንድ መፅሐፍ ብቻ ነው ሊፅፍ የሚችለው።

የነብያችን ግን ከዚህ ይለያል ፣
ለምሳሌ መገሰፅ፣ማነቃቃት፣ሁሉም ነገር ያካትታል። ነብዩ ሲያስተምሩ ያልዳሰሱት ነጥቦ ያላነሱት ርዕስ የለም።
ከነዛ ውስጥ የህይወት መመሪያ የሚሆን አስተምህሮት እንኩላችሁ ልላችሁ ወደድኩ።
♦️የመኝታ ሰርዓቶች

➡️ከመተኛት በፊት በር እቃዎችን መዘጋጋት መከዳደንና እሳት ማጥፋት፣-

ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል እቃዎችን ከዳድኑ ፣ኮዳዎችንም እሰሩ ፣በሮችንም ዝጉ ሰይጣን የታሰረን አይፈታም። የተዘጋን በር አይከፍትም፣ የተከደነንም አይከፍትም።መክደኛ ካጣችሁ እቃችሁ ላይ እንጨት አድርጋችሁ ቢሆን እንኳን የአላህን ስም ጥሩበት ።እሳትንም አጥፉ አይጥ ቤታችሁ ታቃጥላለች ።

➡️ጀናባ ከሆነ ውዱዕ አድርጎ መተኛት፣-
አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ - እንድህ ብላለች ነብዩ ስለሏ አለይሂ ወሰለም ጀናባ ሆነው መተኛት ሲፈልጉ ውዱዕ ያደርጉ ነበር።

➡️ፍራሹን ጠረግ ማድረህ፣-
ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ለመተኛት ወደ ፍራሻችሁ ስትቀርቡ በሽርጣችሁ ውስጠኛውን ክፍል ሶስት ግዜ ጠረግ አድርጉት።

➡️ቤት ውስጥ ለብቻ አለመተኛት፣-
አብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዳስተላለፉት ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም ለብቻ መተኛትና ለብቻ ጉዞ መውጣት ከልክለዋል።

➡️ውዱዕ ማድረግ
ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ወደ መኝታ ስትሄድ ለሰላት የምታደርገውን ውዱዕ አድርግ።

➡️የመኝታ አዝካሮችንና የተወሰኑ የቁርአን አንቀጾች ማንበብ፣-

♦️ከቁርአን
ፋቲሃ ፣አየተል ኩርሲይ ፣ የበቀራ የመጨረሻ ሁለት አንቀጾች ፣ ሱረት ካፊሩን ፣ሱረት ኢኸላስ ፣ሱረት ፈለቅ፣ ሱረት ናስ፣ ከተቻለ ሌሎችም የአላህ መልእክተኛ ሲተኙ ያነቧቸው እንደነበረ የተዘገቡ አንቀጾችን ማንበብ።

አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ እንዳስተላለፈችው፣የአላህ መልእክተኛ ዘወትር ሌሊት ሲተኙ ፣

👈قُلْ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ
👈قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلْفَلَقِ
👈قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلنَّاسِ
እነዚህን በማንበብ እጃቸው ላይ  ሶስት ሶስት ግዜ ተፍተው ከራሳቸውና ከፊታቸው በመጀመር የደረሱትን ያህል አካላቸውን ያብሱ ነበር።

♦️ከአዝካሮች
👈 بِاسْمِكَ رَبِّ وَضَعْتُ جَنْبِي وَبِكَ أَرْفَعُهُ، إِنْ أَمْسَكْتَ نَفْسِي فَارْحَمْهَا، وَإِنْ أَرْسَلْتَهَا فَاحْفَظْهَا بِمَا تَحْفَظُ بِهِ عِبَادَكَ الصَّالِحِين
▪️ትርጉም ፣- ጌታየ በስምህ ወገቤን አሳረፍኩ በስምህም አነሳዋለው፣ነፍሴን ከያዝካት እዘንላት ፣ከለቀካትም መልካም ባሮችን በምትጠብቅበት ጠብቃት።ሌሎችንም አዝካሮች ማለት--

➡️በቀኝ ጎን መተኛት
ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል፣- ወደ መኝታህ ስትሄድ ለሰላት የምታደርገውን ውዱዕ አድርገህ በቀኝ ጎንህ ተኛ።

➡️በሆድ አለመተኛት
ነብዩ ስለሏ ሁአለይሂ ወሰለም በሆዱ ተኝቶ ላዩት ሶሃባ ተነስ ይህ አተኛኝ አላህ የማይወደው ነው ብለውታል።

♦️መተኛትህ ካልቀረ በሱና ላይ ሁነህ ተኛ
👉ሱና የዱንያም የአሔራ ብርሀን ነው።
ህይወት ያለ ሱና ድቅድቅ ጨለማ ነው።
ሼር አድርጉት
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
ጁሙዓ~የሳምንቱ ምርጥ ቀን~📩

    ➫"ዛሬ ቀኑ ጁሙዓ ነው ሡረቱል ካህፍን (የዋሻው ሠዎች ምዕራፍን) መቅራት እንዳይረሡ !

  📖ስለ~ሡራዋ (ምዕራፏ)በጥቂቱ 📖

የምትገኘው በ 15 ጁዝ ማብቂያ እና 16 ጁዝ መጀመሪያ ነው ።
110 አያ (አንቀፆችን) ይዛለች።
በተርቲብ (ተራ) 18 ነች

    በውስጣ በጣም አስተማሪ እና አስደሳች ታሪኮችን ይዛለች ከነሡም መካከል:-

     በመግቢያዋ ላይ ለዓማኞች የብስራት ዜና በመንገር  ትጀምራለች።

     በመቀጠልም ለዲን (ተውሂድ) ሲሉ የተመቻቸ ኑሯቸውን ትተው ከቤተ ዘመድ ተነጥለው ወደ ዋሻ ስላመሩትና በውስጡም 309 ዓመት በዋሻ ውስጥ በእንቅልፍ ስላሳለፉት  ቁጥራቸው በወል ስለማይታወቀው ድንቅና ብርቅዬ ወጣቶችን ታሪክ ትገልፅልናለች። አላህም ለነዚህ ወጣቶች የዋለላቸውን እንክብካቤ ባማሩ ቃላት ይዳስሳል።

[ወጣቶች ከነሱ ብዙ ትምህርት ልንወስድ ይገባል።]

      በመቀጠልም ከኡሉል አዝም የቆራጥነት ባለቤት ነብያት
[ኑህ ፣ኢብራሂም ፣ሙሳ ፣ዒሳና ነብዩ ሙሀመድ‏ ‏(ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) ‎]
ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው ሙሳ
(ዐለይሂ ሠላም)‌‌‎ እውቀትን ለመፈለግ ያደረገውን ጉዞ እና ከመምህሩ ኸድር ጋር ያሳለፈውን ቆይታ ቀልብን በሚገዛ ሁኔታ እየገለፅን እውቀትን መፈለግ እንዳንሠላች ያስተማረናል::

      እንዲሁም በዒልም ፍለጋም ጊዜ ይሁን በአጠቃላይ የህይወታችን እንቅስቃሴ  የትዕግስትን ኩታ መደረብ እንዳለብን ያስገነዝበናል።

   በመቀጠልም አላህ ከመልካም ፀጋዎቹ ከዋለላቸው ባሮቹ መካከልና ምድርን በጠቅላላ አስተዳድረዋል ከሚባሉት ንጉሶች አንዱ ስለሆነው ዙልቀርነይን ያወሳልናል።

  በምድር ላይ ስላደረጋቸው ጉዞ እና ሳላገኛቸው ህዝቦች እና የቂያማ መቃረቢያ ጊዜ ወጥተው ምድርን ያበላሿታል የተባሉትን የእጁጅ እና መእጁጅ መውጫ መድፈኛ ግንብ የሠራላቸውን ታሪክ ባማረ ቃና ይገልፅልናል።

      በመጨረሻም ሡራውን አላህ (ሡብሀነሁ ወተዓላ)‌‏ ‏ለከሀዲያን ያዘጋጀላቸውን የቅጣት ድግስ፣ እንዲሁም ለምእመናን ያዘጋጀላቸውን የጀነት ፀጋ ገልፆልን መሠረታዊ በሆነው፦

➫አላህ ባዘዘው ትልቁ ጉዳይ!
➫የሰው ልጆችን በፈጠረበት!
➫መልዕክተኞችን በላከበት!
➬የጀነት ቁልፍ በሆነው።
       
 
የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 11
───────────
ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ከበደሎች ሁሉ ትልቁ በደልና ከድንቁርና ሁሉ ትልቁ ድንቁርና ማለት ሰዎች እንዲያልቁህና እንዲያተልቁህ እየፈለክ፤ የአንተ ልብ ግን አላህን ከማተለቅና ከማላቅ ባዶ ከሆነ ነው።»

📚 ۞ الفـوائــد【272】۞
───────────
The Holy Prophet said:

1) 4 things make our body sick:
a) Talking too much
b) Sleeping too much
c) Eating too much
d) Interacting too much with other people

2) 4 things destroy the body:
a) The anxiety
b) Gloom (sadness / sorrow)
c) Hunger
d) Sleep late at night

3) 4 things remove light and joy from the face:
a) The lie
b) Being disrespectful, impudent (knowingly insisting on a bad thing)
c) Argue without adequate knowledge or information
d) Excessive immorality (doing a wrong thing without fear)

4) 4 things increase facial light and joy:
a) Piety
b) Loyalty
c) Generosity (being good)
d) Be helpful to others without them asking.

5) 4 things stop rizq (wersek)

a) Sleep in the morning (fajr at sunrise)
b) Do not pray or be irregular in prayers
c) Laziness / Idleness
d) Cheating / dishonesty

6) 4 things bring and / or increase the rizq:
a) Watch in prayer
b) Excessively doing istighfar
c) Do sadaqa regularly
d) Zikr

The Holy Prophet said: "do nothing during the adhan (call to prayer) even read the Quran, the person who speaks during the adhan will be unable to pronounce the kalima shahada on his deathbed."

The Holy Prophet also said to pass on even one verse to others because this verse will intercede on the day of judgment.

Allahumma-inni-ala-Zikr-ika-wa Shuk-rika wa husni Ibaadatik.

A very powerful du'a has been sent to you. Imagine 1000 people reading it thanks to you. JazakAllah, it will only be Good for you masha Allah🤲💖
@degmolela
የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 12
───────────
ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ኣደም ወንጀል በሰሩ ጊዜ ተመልሰዋል። የዚያኔ ጌታቸው መረጣቸው። አቀናቸውም። ኢብሊስ በወንጀሉ በፀናና በተሟገተ ጊዜ አላህ ረገመው። አራቀውም። ስለዚህ ከወንጀሉ የተመለሰ ሰው አደማዊ ሲሆን በጥፋቱ የፀናና በቀደር የተሟገተ ኢብሊሳዊ ሆኗል። ስለዚህ እድለኞች አባታቸውን ሲከተሉ እድለ ቢሶች ደግሞ ጠላታቸውን ኢብሊስን ነው የሚከተሉት።»

📚 ۞ مجموع الفتاوى【8/64】۞
───────────
እስቲግፋርና ተውበት እያደረግን መልካም ሰኞን እናሳልፍ
@degmolela
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
The Prophet (ﷺ) said : "When any one of you awakes up from sleep and performs ablution, he must clean HIS NOSE THREE TIMES, for the devil spends the night in the interior of his nose."

🖤 Sahih Muslim 238 🤍
ትርጉም፦
ነብዩ (ﷺ) እንደተናገሩት አንድሰው ከእንቅልፉ ተነስቶ ውዱእ ሲያደርግ አፍንጫውን ሶስት ጊዜ ማጠብ አለበት።
ሸይጧን ሌሊቱን የሚያሳልፈው በአፍንጫ የውስጠኛው ክፍል ነው።
ቁርአን እየሰማ ልቡ ምንም አልሰማ ያለው አንድ ሰው ወዳጅ ሼኹን እንዲህ ሲል አማከራቸው፦

"ቁርአንን እሰማለው ውስጤን ግን ምንም አይሰማውም። ረመዳን ይመጣል ይሄዳል። ውስጤ ግን ምንም አይሰማውም። ሼኽ ሆይ ሁሉም ነገር ደክሞኛል።"

ሸኽየውም እንዲህ ሲሉ ለሁላችንም ትምህርት የሚሆን ምክርን መከሩት፦

"ልጄ ሆይ ምንም የማይሰማህ ምክንያቱ ልብህ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ስለሆነ ነው። ልብህ ከባድ ሁኔታ ውስጥ የሆነበት ምክንያቱ ደግሞ ብዙ ወንጀሎችን ስለምትሰራ ነው። ብዙ ወንጀሎችን የምትሰራበት ምክንያት ደግሞ የአላህ ፍራቻ በልብህ ውስጥ አለመኖሩ ነው። ልብህ ውስጥ የአላህ ፍራቻ ያለመኖሩ ምክንያት ደግሞ ምንም አይነት ሸሪዐዊ እውቀት ስለሌለህ ነው። ምንም አይነት ሸሪዐዊ እውቀት የሌለህ ደግሞ በጣም ቢዚ (Busy) ስለሆንክ ነው። በጣም ቢዚ (Busy) የሆንከው ደግሞ ከልብህ ዱንያን አብዝተህ በመውደድህ የተነሳ ነው። ልጄ ሆይ! ዱንያን መውደድ የክፉቶች ሁሉ ሥር መሰረት ነው።"
የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 13
───────────
ኢማሙል_ዓውዛዒይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ  : -

«ሌሊት (በዒባዳ) መቆምን ያስረዘመና ያበዛ ሰው አሏህ የቂያማ እለት ያለውን መቆም ያገራለታል።»

📚 ۞ سـيـر أعـلام النبـلاء【7/119】۞
─────────
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
የዛሬው የ ሀዲስ ቅምሻ



وعن أبي ه‍ريرة رضي الله عنه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم، قال: (( من القرآن سورة ثلاثون آية شفعت لرجل حتى غفر له، وه‍ي: (تبارك الذي بيده الملك).))    رواه أبو داود والترمذي،  وقال: (( حديث حسن)). وفي رواية أبي داود: ((تشفع)).



አቡ ሁረይራ رضي الله عنه እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል:- " በቁርኣን ውስጥ ሠላሳ አንቀጽ ያላት አንዲት ምዕራፍ አለች። ለአንድ ሰው ምህረት እስኪያገኝ ድረስ አማላጅ ትሆንለታለች። እርሷም "ተባረከልለዚ ቢየዲሂል ሙልኩ" ናት።"


                                (አቡ ዳውድና ቲርሚዚ)




https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 14
───────────
ኢብኑ_ረጀብ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ  : -

«ድህነት ማለት ገንዘብ ማጣት እንዳይመስልህ፣ ነገር ግን ዲንን ማጣት ከድህነቶች ሁሉ የከፋውና ትልቁ ነው።»

📚 ۞ مجمـوع الرسائـل【1/65】
─────
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
2024/11/26 11:19:27
Back to Top
HTML Embed Code: