Telegram Web
ረመዷን ከሪም
🛑ተራዊህ በመስገድ ከሚገኙ ጥቅሞች

📌ቀኑን በጾም ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች እንመደባለን

📌 ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኛለን

📌ተራዊሕ ብዙ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን

📌ከወንጀል ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን

📌ዒባዳ ላይ ትዕግስትን እንማራለን

📌ሰላተል-ለይል እንለማመዳለን

📌በተደጋጋሚ ከኢማሙና ማእሙሞች ጋር "አሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል

📌መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል

📌ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል

📌የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን

📌ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል

📌ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅ ለወጣቱ መልካም አርዓያ እንሆናለን

📌ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እናይበታለን

📌ቁርኣንን በብዛት በመስማት የአላህን እዝነት እናገኛለን እንዲሁም ብዙ በመስማት ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራርም እንማራለን

📌በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "አሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን

📌ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እንሸምታለን

📌የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፥ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውም

📌ሰግደን ስንመለስ የውስጥ ደስታና እፎይታና ሌሎችንም የዲንም የዱኒያ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊህን ሳንሰለች እንስገድ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በረመዷን ላይ እንቅልፍ ማብዛት ክስረት ነው ይሉናል ሼይኽ ፈውዛን!

መተኛት ካለበት የለይሉን መጀመሪያ ክፍል እና ከዝሁር እስከ አስር-(ቀይሉላ)- ያለው ወቅት ይተኛ ለተራዊህ ይጠነክርበት ዘንድ ከዚ በላይ መተኛት ክስረት ነው!

አዩሀል እንቅልፋም ሁላ እየተግባባን ነው?

ከስሁር እስከ ፊጥር ሚተኛ ሰው እንዳለ ታውቃላቹ ግን አህባብ?
,,,ረመዷን -2,,,

ዑመር ኢብኑል ኸጣብ(ረዐ) እንዲህ ብሏል፡ "አላህን በማስታወስ(በመዘከር) በርቱ ተበራቱ (ለልብ በሽታ) መደኃኒት ነውና ሰዎችን በሌሉበት ስማቸው ከማውሳት(ከማማት ) ተጠንቀቁ (የቀልብ) በሽታ ነውና፡፡"

ያ አሏህ! ከወንጀል፣ከሀሜት አርቀን, ረመዷንን ከሚጠቀሙበት አድርገን አሚን
"ስሁርን ተመገቡ ስሁር መብላት በረካ አለው።"

የአላህ መልክተኛው ﷺ
ተሰሃሩ ፈኢነ ፊሱሁሪ በረካ

ስሁር በላችሁ ????
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
«የኃጢያት ጠረን እንዳያዋርዳችሁ የእሰቲግፋርን ሽቶ አርከፍክፉበት»

[ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ]


┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓
    
share
┗━ 🍃 ━━━━ 🍃
____
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
عَنْ سَهْلٍ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ
﴿إِنَّ فِي الْجَنَّةِ بَابًا يُقَالُ لَهُ : الرَّيَّانُ، يَدْخُلُ مِنْهُ الصَّائِمُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، لَا يَدْخُلُ مِنْهُ أَحَدٌ غَيْرُهُمْ، يُقَالُ : أَيْنَ الصَّائِمُونَ ؟ فَيَقُومُونَ لَا يَدْخُلُ مِنْهُ أَحَدٌ غَيْرُهُمْ، فَإِذَا دَخَلُوا أُغْلِقَ فَلَمْ يَدْخُلْ مِنْهُ أَحَدٌ

ሰህል (ረ•ዓ) እንደተረከው ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብሏል!
“ጀነት ውስጥ በትንሳኤ ዕለት "ረያን" የሚባል ፆመኞች ብቻ የሚገቡበት "በር" አለ። ከእነርሱ  ውጭ አንድም ሌላ ሰው አይገባበትም። የት አሉ ፆመኞቹ? ይባላል፤ ይቆማሉ!  ከናንተ ውጪ ሌላ አንድም ሰው አይገባበትም ይባላሉ። ከገቡ በኋላም በሩ ይዘጋል። ከነሱ ውጪ ሌላ አንድም ሰው አይገባም።”

[📚ቡኻሪ መጽሐፍ 30 ሐዲስ 6]
“በጁምዓ ቀንና በጁምዓ ሌሊት በኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ።”

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
የረመዷን የመጀመሪያው ጁምዓ 💚💚💚

"ፆም ጋሻ ነው ከእሳት መጠበቂያ ምሽግ ነው።"

(የአላህ መልዕክተኛ ﷺ)

ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች አንድ ነገር ተመኙ ተብለው ምርጫ ቢሰጣቸው ኖሮ ከረመዷን አንዱን ቀን ባገኝ ብለው ይመኙ ነበር።
 
የተቆጠሩት ቀናት እየፈጠኑ ነው


۞ وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ

ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡(ኢምራን 133)

❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️
በእነዚህ ውብ የተቆጠሩ ቀናት የምንጠቀምበት በፆማችን ራህማ የምናገኝበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ፣ በዱዓ የደመቀ የመጀመርያ የረመዷን ጁምዓ ይሁንልን!!!
ይህንን ምን ትሉታላችሁ ?
መንግስት በእርግጠኝነት 'የጠሉት ሳር ይለመልማል 'ነው የሚለው መቼም።
እኛ ደግሞ ይህን እንላለን
'ባቃጠላችሁን ቁጥር እየበሰልን እንሄዳለን'
በወሎ ዩኒቨርስቲ የተፈጠረው ታሪክ ከወቅታዊ ሁኔታው አንፃር ቃል የሚያሳጣ ሁነት ነው።
ኒቃቢስት እህቶቻችን እያኮሩን ፣በመሸፈን ውስጥ ያለውን ብርታት፣በተሸፈነ ፊት ውስጥ ያለውን ግልፅ ችሎታ እያሳዩን ነው ።
አላህ ይጨምርላቸው።
እያፈጠራችሁ🥓🍩
አቡሁረይራ ረደየሏሁ አንሁ እንዳስተላለፉት
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

ፆመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት
1//ሲያፈጥር ይደሰታል
2// ከጌታው ጋር ሲገናኝም በመፆሙ
     ደስ ይለዋል

📚የፆመኛ የአፋ ሽታ

🌴عن أبـﮯ هريرة رضـﮯ الله عنه
أن رسول الله ﷺ قال :
-ነብዩسلى الله عليه وسلمእዲህ አሉ
*والذي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بيَدِهِ ، لَخُلُوفُ فَمِ الصَّائِمِ أطْيَبُ عِنْدَ اللَّهِ مِن رِيحِ المِسْكِ*
-የሙሀመድ ነፍስ በእጁ በሆነው አላህ እምላለው ከፆመኛ አፍ የሚወጣው የአፋ ጠረን አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽታ የበለጠ ምርጥና የበለጠ ነው
📚【صحيح البخاري ومسلم】
አሁንም ከወደ አርባምንጭ ላሌ የኒቃቢስቶቻችን የጥንካሬ ተምሳሌት ።
እህታችን በሜድስን ትምህርት የሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናልናለች።
አላህ በጥበቡ ቁርአንን በተለያየ መልኩ ጠብቆታል።   ከዚህም ውስጥ ከነብያችን (ሰ.ዐ.ወ ) ጊዜ ጀምሮ እስከ የውመል ቂያማ ድረስ የፊደሉ አወጣጥና የቃላቱ አነባበብ ከተጅዊድ ምሁራን እየተወራረሰ እስካሁን እንዲቆይ አድርጎታል ።

🍃 የቁርአን ተዓምር እጅግ ሰፊ ከመሆኑም ባሻገር ለሚያነበውም ይሁን ለሚያዳምጠው ሰው ደስታና መረጋጋትን ይፈጥራል።

🌲 አላህ ቁርአንን ወዳጃቸው አድርገው ለሚይዙ ባሮቹ በዚህኛውም በቀጣዩም ዓለም ላቅ ያሉ  ሽልማትን አዘጋጅቶላቸዋል ።

🍃 ረሡል (ሰ.ዐ.ወ) " ቁርዓንና ፆም የቂያማ ዕለት ለባልደረባቸው ምልጃ በመቆም ከአላህ ጋር ያስታርቁታል።"

🌴 ዱንያ ላይ ቁርዓንን የህይወት መመሪያው አድርጎ የያዘ ሰው በአላህ ፍቃድ የዚህ ታላቅ ዕድል ተጠቃሚ ይሆናል።

🌿 ይህ ታላቁ የአላህ ንግግር ሙሉ በሙሉ ወደ ቅርቡ ሰማይ (ሰማአ ዱንያ) የወረደው በረመዳን በ 27ኛው ሌሊት ነው።
وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡
Forwarded from Channel Help
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/07/06 04:25:30
Back to Top
HTML Embed Code: