Forwarded from ሰ ው
ሰር አይዛክ ኒውተን
(ታህሳስ 15፣ 1642 - መጋቢት 11፣ 1727)
ሰር አይዛክ ኒውተን በ1642 ሲወለድ ፊዚክስ አንድ ወጥ በሆነ መልኩ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡ በ1727 ሲሞት ግን፣ በአካባቢያችን ከሚገኙ ነገሮች እንቅስቃሴ አንስቶ እስከ ታላቁ ሁለንተና ድረስ ጥርት ባለ ሁኔታ እቅጯን የሚናገር የዕውቀት ዘርፍ ትቶልን አልፏል።ትውልዱ፣ እንግሊዝ፣ ሊንከለንሻየር ውስጥ ነው - ታህሳስ 15/1642፡፡
ከጊዜው ቀድሞ (Premature) የተወለደው ይህ ጨቅላ ከመወለዱ ሶስት ወራት በፊት አባቱን በሞት ተነጥቋል፡፡ ሶስት ዓመት ሲሞላው ደግሞ እናቱ ለእናቷ አደራ ሰጥታው ሌላ አግብታ ስለሄደች ከሴት አያቱጋ ይኖር ጀመር፡፡ ኒውተን እንጀራ አባቱን ክፉኛ ይጠላው ነበር፡፡ ለዚህም፣ ከ19 ዓመቴ በፊት የፈፀምኳቸው ሀጢአቶች ብሎ በዘረዘረበት ፅሁፍ፣ እናቱንና እንጀራ አባቱን ቤቱን በላያቸው ላይ ለማቃጠል መዛቱን ይጠቅሳል፡፡
ኒውተን ትምህርቱን የጀመረው በመንደር ትምህርት ቤት ውስጥ ሲሆን፤ ሲቀጥል የንጉሱ ትምህርት ቤት ወደተባለው ተሸጋገረ፡፡ ኒውተን ከመጀመሪያው አንስቶ ጎበዝ ተማሪ ነበር፡፡ በንጉሱ ትምህርት ቤት ቆይታው ወቅት፣ ካረፈበት ከመንደር የመድኃኒት ቀማሚው ዊሊያም ክላርክ እንጀራ ልጅ ከአና ስቶረርጋ ፍቅር ጀምሮ ተጫጭቶም ነበር - ኋላ ላይ ኒውተን ወደ ኬምብሪጅ አቅንቶ ልቡን ሳይንስ ስትሰልበው ያ ሞቃት ፍቅር እንደዋዛ ቀረ እንጂ፡፡
የኒውተን ታሪክ ፀሃፊዎች፣ “ከአና ስቶረርጋ የነበረውን የሞቀ ፍቅር ትዝታ ለረጅም ጊዜያት በልቡ ይዞ ቆይቷል” ይላሉ፡፡ ኒውተን ፈፅሞ አላገባም፡፡ ከአንዲትም ሴትጋ አንሶላ ሳይጋፈፍ በድንግልና እንደኖረም ይነገርለታል፡፡ ባሏን መሞት ተከትሎ ወደ ቤቷ የተመለሰችው እናቱ በማሳዋ ላይ እንዲያግዛት በማሰብ ከትምህርት ቤት አስወጥታ ወደ መንደሩ መለሰችው፡፡
ያ ወቅት፣ ለኒውተን፣ እጅግ አስቸጋሪው ነበር፡፡ በመስኩ ላይ በሳይንሳዊ ሀሳቦች ተመስጦ ሲያስብ የሚያግዳቸው ከብቶች የሌሎች ሰዎች ማሳ ውስጥ ይገቡበታል፡፡ የንግድ ብልሀትና ክርክር እንዲለምድ እናቱ ወደ ገበያ ስትልከው ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ ሂሳብ ሲሰራ ውሎ አመሻሹ ላይ ከመንደሩ ገበያተኞችጋ ተቀላቅሎ ይመለሳል፡፡
በመጨረሻ፣ የወጣቱን ኒውተን የተለየ ችሎታ በተረዱት የንጉሱ ትምህርት ቤት አስተዳዳሪ ጉትጎታ፣ የእናቱን ማሳ ትቶ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለስ ተደረገ፡፡ ከዚያም በከፍተኛ ወጤት ትምህርቱን አጠናቅቆ የኬምብሪጁን ስላሴ ኮሌጅ (Trinity College) ተቀላቀለ...
፩
👉 ጥንታዊ ጥበባት
Channel👉@ancient_wisdoms
Group👉@ancient_wisdoms_group