Telegram Web
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌴Alwan..

#ከታሪኮቻችን
.
.
.
አባት የመጀመርያም የመጨረሻም የሆነ ብቸኛ ልጁን ሊድር ድል ያለ ሰርግ
ደግሶ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆቹን ጠርቶ የምሳ ግብዣውን እየተዟዟረ
ይመለከታል።
‹‹ማን ቀረ ማን መጣ›› የሚለውን በትኩረት እየተመለከተ ሳለ የቅርብ የግድግዳ
ጎረቤቱን ከእይታው ያጣዋል። ግራ በመጋባት እየተዟዟረ ቢመለከትም
ጎረቤቱንም ሆነ የጎረቤቱን ልጆች ሊያይ አልቻለም።
‹‹የልብ ወዳጄ በዛሬ ቀን እንዴት ከጎኔ ይጠፋል›› እያለ በንዴት ስሜት
በመብሰልሰል ላይ ሳለ ድንገት የጎረቤቱ ልጅ ብቅ አለ ና በፍጥነት ትንሽ ምግብ
ቀማምሶ ትቶ ወጣ።
ይህን ትዕይንት የተመለከተው ደጋሽ በንዴት ተብከነከነ።የአባቱ በደስታው ግዜ
አለመገኘት ሳያንሰው ልጁ መጥቶ በምግቡ አላግጦ መውጣቱ አበሳጨው።
በዚህ መሀል የሙሽራው አጃቢዎች ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት ጉዞ
ሊጀምሩ መኪናቸውን ማንቀሳቀስ ሲጀምሩ ምግቡን ቀማምሶ በፍጥነት
የወጣው የጎረቤቱ ልጅ ሙሽራውን ለማጀብ ከግቢ መኪናውን ይዞ ይወጣል።
አባት ተበሳጨ፣ ንዴቱን መቆጣጠር ቢያቅተው በቁጣ መንፈስ ተሞልቶ ወደ
ጎረቤቱ ልጅ በመሄድ፦‹‹አባትህ ጎረቤቴ ሁኖ ደስታዬ ላይ አልተገኘም፣ ታላላቅ
ወንድሞችህም እንደዝያው፤:ታድያ አንተ ምን አስበህ ነው በምግብ አላግጠህ
ትተህ የወጣኸው? አሁን ተመለስ ያንተን አጃቢነት አንፈልግም›› ብሎ መለሰው።
ልጁም እቤቱ ገባ፤ ሰርገኛዎችም ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት አቀኑ።
በመጨረሻም አጃቢዎች ሙሽሮችን ይዘው ወደ ቤት በመግባት የደስታቸው
ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ቀኑ ሲጨልም ሁሉም ተበታትኖ ሰርግ ቤቱ በሙሽሪት እና
በሙሽራው ጭር አለ።
አባት አሁንም በጎረቤቶቹ ንዴት እየተብሰለሰለ ነው። ድንገት ከመሸ ያለ ወትሮው
የጎረቤቱ ጊቢ ተከፈተ። የሙሽራው አባት እየተመለከተ ነው።
የጎረቤቱ ልጆች በትከሻቸው አስክሬን ተሸክመው ከቤታቸው ሲወጡም
ተመለከተ። ፍፁም ዝግታ እና እርጋታም በሚስተዋልበት እርምጃ ልጆቹም
ይራመዱ ጀመር።
የሙሽራው አባት ጠጋ አለ። ፦‹‹ምንድነው? የማንን አስክሬን ነው
የተሸከማችሁት ›› ሲልም ጠየቃቸው።
‹‹አባታችን ጠዋት ሙቶ ነው፤ ሲሞትም በሱ ለቅሶ ምክንያት ያንተ ደስታ
እንዳይጓደል መሞቱን ከሰርግህ በፊት ለማንም እንዳንናገር እና ድምፅ
አውጥተን እንዳናለቅስ ተናዞልን ነበር። ለዝያ ነው ድግሱ ላይ መገኘት
ያልቻልነው። ›› በማለት ጀናዛ የተሸከሙ ልጆች ጉዳያቸውን አስረዱ።
ደጋሽ ተፀፀተ፦‹‹ወላሂ እኔ በሱ ቦታ ብሆን ይህን የማድረግ አቅም አይኖረኝም
ነበር›› ሲልም የፀፀት እንባ ያነባ ጀመር።

#Sefwan Ahmedin
@copypast

በህይወታችን ችላ ያሉ እየመሰሉ በቁስላቸው ደስታችንን ላለማበላሸት ሲሉ
ከአከባቢያችን የሚርቁ ሰዎችን አላህ ይዘንላቸው።

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
🌴Alwan..

<< ከንብረቱ ሲከላከል ከቤተሰቡ ሲከላከል ከነፍሱ ሲከላከል ከዲኑ (ከሀይማኖቱ ሲከላከል የሞተ ሁሉም ሸሂድ ነው። >>
{{ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ}}

[አብዳውድ ዘግበውታል]

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌴Alwan...

'' የፍጥረታት ሁሉ ነፍስ በእጅህ የሆነች ቀኗ ስትደርስ የምትወስድ <አል ቃቢድ> ሆይ! ሩሀችን ተወስዳ መቃብር የገባን ቀን እዘንልን በህይወታችን ነፍስ የምትዘራ ሲሳይን የምትዘረጋ <አል ባሲጥ>ሆይ! ኑሯችንን አታጥብብን ሀያታችንን የጭንቅ አታድርግብን የፈለግከውን ዝቅ የምታደርግ<አል ኻፊድ> ስትሻ ደግሞ ከፍ አድርገህ የምታስቀምጥ <አር ራፊዕ> ከአንተ ውጭ ማንም የለምና ከዘቀጥንበት አውጣን ከወደቅንበት አንሳን የተዋረደን ለክብር የምታበቃ <አል ሙዒዝ> የተከበረን የምታዋርድ <አል ሙዚል> ነህና ከተከበርን በኀላ አታዋርደን ነውራችንን ገልጠህ መሳቂያ መሳለቂያ አታድርገን🤲🤲

💛copy past

ዱአቹን መቅቡል የሚሆንበት ጁምአ ይሁንልን !!!

🌴happy_ juma🌴

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌴Alwan

''وَٱلَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَٰجِنَا وَذُرِّيَّٰتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍۢ وَٱجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَامًا

እነዚያም «ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያን ለእኛ ስጠን፡፡ አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን» የሚሉት ናቸው፡፡

Surah Al-Furqan - 25:74

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
የተከፋችሁበትን ነገር ሁሉ ለአላህ ንገሩ። ከርሱ ዉጭ ጉዳታችንን የሚጠግን ማን አለ?

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
ፈጣሪ እውነት ነው!!

በጥንት ዘመን በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ንጉሥ ነበር። ይህ ንጉሥ ታዲያ በፈጣሪ መኖር አያምንም። ንጉሡ "ፈጣሪ በእውነት ያለ ሳይሆን ሰውች በሕልማቸው ወይም በሃሳባቸው የፈጠሩት ነው" ብሎ ነበር የሚምነው። በዚህም የተነሳ ፈጣሪ የሚለው ቃል በአገሪቱም ሆነ በቤተሰቡ ውስጥ እንዳይነገር የተቻለውን ጥረት ሁሉ ያደርግ ነበር።
ከዕለታት አንድ ቀን የንጉሡ ሚስት ወንድ ልጅ ትወልዳለች። ነገር ግን እናትየው በወሊድ ወቅት በተፈጠረባት የጤና ችግር ምክንያት ትታመምና ትሞታለች።
ንጉሡም የተወለደው ልጅ ስለ ፈጣሪ መስማትና ማስብ የለበትም በሚል ዓላማ ከሰዎች ተነጥሎ የሚያድግበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይጀምራል። ለሕፃኑ የሚሆን ቤት በጣም ከፍታ ካለው ማማ ላይ ያሠራል። ሕፃኑን ልዑል የሚንከባከቡና የሚያስተምሩ አገልጋዮችን ይመድብለታል። አገልጋዮቹንና መምህሩን ለሕፃኑ የፈጣሪን ስም በምንም መልኩ እንዳይገልጹ መመሪያ ይሰጣቸዋል። ሁሉንም ነገር ባሰበው መንገድ አከናውኖ አጠናቀቀ። እንዲህ በማድረጉም ሕፃኑ በምንም መንገድ ስለፈጣሪ መስማትም ሆነ ማሰብ አይችልም ብሎ እርግጠኛ ሆነ።
ሕፃኑ ልዑል በዚህ መልኩ እየኖረ ሳለ ከዕለታት አንድ ቀን ንጉሡ ሕፃኑን ሊጎበኝ ማማው ቤት ላይ ይወጣል። በዚህን ጌዜ ሕፃኑ የሚመለከተው የሚያምሩ አበቦችንና የአካባቢውን የተፈጥሮ ሁኔታዎች ነበር። ሕፃኑ እርግቦች ሲበሩና ወራጅ ወንዞች አካባቢውን አቋርጠው ሲያልፉ የሚመለከተው ትእይንት እንደሚያስደስተው ከገጽታው ያስታውቅ ነበር። ወደ ውጭ እየተመለከተም ጭንቅላቱን ወደ መሬት ዝቅ ያደርጋል።
ንጉሡም በሕፃኑ ሁኔታ ተገርሞ ምን እያደረገ እንደሆነ ይጠይቀዋል። ሕፃኑም "ለፈጣሪዬ ምስጋና እያቀረብኩ ነው!" በማለት አስደንጋጭ መልስ ለአባቱ ይሰጠዋል።
በሕፃን መልስ በጣም የደነገጠው ንጉሡም "የቱን ፈጣሪ ነው የምታመሰግነው? ለመሆኑ ስለፈጣሪ ማን ነው የነገረህ?" ሲል በቁጣ ይጠይቀዋል።
ሕፃኑም "ማንም ስለፈጣሪ አልነገረኝም፤ በዚህ ተፈጥሮ ውስጥም የፈጣሪዬን ውበት እና እውነት በግልጽ እመለከታለሁ። ምክንያቱም እነዚህን የሚማርኩ ነገሮች የፈጠራቸው አለ ብዬ አምናለሁ፤ ይህንን ታላቅነቱን ሳስብ ደግሞ ጭንቅላቴን ዝቅ በማድረግ ለክብሩ ስል እሰግድለታለሁ" በማለት ለአባቱ ጥያቄ መልስ ስጠ።
ንጉሡ በሕፃኑ ንግግር ሁኔታ በጣም ደነገጠ። የሽንፈት ስሜት ውስጥ ሆኖም ወደ ኋላው አፈገፈገ። ትንሹ ልዑል አባቱ ፈጽሞ እንዳይሰማውና እንዳይስበው ይፈልገው የነበረውን ነገር ተፈጥሮን በማየትና በማድነቅ ብቻ ደረሰበት። ማንም ሳይነግረውና ሳያስተምረው የፈጣሪን መኖር አወቀ። ፈጣሪያችን እሱ በእርግጥም እውነት ነው!

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
🌴Alwan...

በፎቶው የምትመለከቱት ወጣት ፍልስጤማዊው የነፃነት ታጋይ ዘከሪያ አዝ-
ዘቢዲ ይባላል።ዘከሪያ ከእስር ካመለጡት ስድስቶቹ መሃል አንዱ ነው።
ከሁለት አመት በፊት በወራሪው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ነበር፤ልብ በሚስብ
የጀግና ፈገግታ ተሞልቶ ለዳኛው:-"ነፃ ሆኜ የምንገናኝበት ቀን ቅርብ ነው።"
ያለው።ሽብር የተፈጠረበት ዳኛውም በጥብቁ የጀልቡዕ እስር ቤት በእስር
እንዲማቅቅ ፈረደበት።
ታዲያ በእስር ቤቱ ለሁለት አመታት ያክል በተለየ ክፍል ውስጥ አሳለፈ።አለምን
ጉድ ያሰኘው ክስተት ከመከሰቱ ከአንድ ቀን በፊት ግን አሏህ የውህኒ ክፍሉን
እንዲቀይሩለት የእስር ቤት አዛዦችን አገራለት።በአዲሱ የእስር ክፍልም የምድር
ጉድጓዱን ቁፋሮ ሚሽን ከመጀመሪያው ጀምሮ ካስተባበረውና ከሃያ አመት በላይ
በእስር ቤቱ ከታሰረው ሙጃሂድ መህሙድ አል-አሪዳና አራት ጓደኞቹ ጋር አንድ
ክፍል ውስጥ ታሰረ።ከአንድ ቀን በኋላም እሱ ስድስተኛቸው ሆኖ ከእስር ቤቱ
አመለጡ።

©Ibrahim Taj Ali

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
🌴Alwan....

<< ትክክለኛ አማኝ ማለት እሱ ጥሩ ባህሪ ያለውና ለሚስቱ መልካም የሆነው ነው >>
{ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም}

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
🎡 ጣፍጭ የሆኑ የሳሀቦች ታሪክ 🎡

🍂 ክፍል 6

(ሑዘይፋ ረዲየላሁ አንሁ)

*የሑዘይፋ ረ.ዐ የስለላ ተልዕኮ

~ ሑዘይፋ ረ.ዐ እንደገለፀው :- ''በኸንደቅ ጦርነት ግዙፍ የጠላት ጦር ጋር መጋፈጥ ነበረብን። የመካና የአጎራባች ጎሳዎች ስብስብ ኃይል ወሮናል። የመዲና አይሁዳውያን በኒ ቁረይዟ ከጀርባችን ሊወጉን በዝግጅት ላይ ነበሩ። ሁላችንም መዲናን ከጥቃት ለመከላከል በመውጣታችን ቤታችንን እና ቤተሰባችንን እንደሚዘርፉና እንደሚያስቸግሩ ተሰምቶናል። መናፍቃን ወደ መዲና ለመመለስ ነብዩን ﷺ ፈቃድ መጠየቅ ጀመሩ። ቤቶቻቸው ያለ ጠባቂ የቀሩ መሆናቸውን ና በአይሁዳውያንም ሊጠቁ ስለሚችሉ ጥበቃ እናድርግ የሚል የሀሰት ምክንያት አቀረቡ።


~ ለሁሉም ፈቃድ ሰጡ። በእነኛ የፈተና ቀናት አንድ ምሽት ከሌላው ጊዜ የተለየ የጨለማና ንፋስ ነበር። ከጨለማው ከፍተኝነት የተነሳ አንድ ሰው የገዛ እጁን እንኳን ማየት አይችልም ነበር። ንፋሱም እጅግ አደገኛ ነበር። መናፍቃን ወደ መዲና በመመለስ ላይ ናቸው። ሦስት መቶ ሰዎች ብቻ በተጠንቀቅ ለመወጋት ተዘጋጅተናል። ነብዩ ﷺ ወደ እያንዳንዳችን በመጠጋት ይጠይቁናል ። እኔ ራሴን የምከላከልበት የጦር መሣሪያ አልነበረኝም። ከብርድ የሚያድነኝ ልብስም አልነበረኝም። አንድ ትንሽ ፎጣ ቢጤ ብቻ ነበረኝ ከሚስቴ የተዋስኩት። ከጉልበቴ ሎሚ ላይ ጠመጠምኩት። ከዚያም በጉልበቴ ተንበረከኩ። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በአጠገቤ ሲያልፉ ' ማንነህ?' አሉኝ:- 'ሑዘይፋ ነኝ ' አልኳቸው።


~ ከብርዱ የተነሳ መቆም አልቻልኩም። ሀፍረት እየተሰማኝ ጉልበቴን ከመሬቱ ጋር ቸክዬ ቀረሁ። እርሳቸው ግን :- ''ሑዘይፋ ተነስ! ወደ ጠላት ካምፕ በመሄድም መረጃ ሰብስበህ ተመለስ ' አሉኝ። ከሁሉም ሶሓባ ለጠላት መመከቻ መሣሪያ የሌለኝ ፤ ራሴን ከብርድ ለመከላከልም ልብስ የሌለኝ እኔ ነበርኩ። ቢሆንም በፍጥነት በመነሳት ወደ ጠላት ካምፕ አመራሁ። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ በማለት ጸለዩልኝ:- '' አላህ ሆይ! ከሁሉም አቅጣጫ አንተ ጠብቀው።' በቅጽበትም ፍርሃቴና ቅዝቃዜው ልቀቀኝ ።በሞቃታማ ና ሰላማዊ ክልል የምጓዝ መሰለኝ። ነብዩም ﷺ 'እነርሱም የሚሠሩትን ካጤንክ በኋላ በቶሎ ተመለስ። ሌላ እርምጃ እንዳትወስድ።' አሉኝ።

~ በጠላት ካምፕ ስደርስ የሚቀጣጠል እሳት ተመለከትኩ። ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠዋል። እያንዳንዱ ሰው እጁን በእሳቱ እያሞቀ ሆዱን ያሻል። የማፈግፈግ ድምጽ በሁሉም አቅጣጫ ይሰማል። ሁሉም ለጎሣ አባላት ዕቃቸውን እንዲጭኑና እንዲሸሹ በማሳሰብ ላይ ነው።


~ ድንኳናቸው በነፋስ ኃይል በሚገፉ ድንኳኞች ተነረተ። የድንኳኖቹ ገመድም ተበጣጠሱ። እንስሳዎች ቅዝቃዜውን መቋቋም ተስኗቸው መሞት ጀመሩ ። የጠላት ጦር አዛዥን አቡ ሱፍያንን ተመለከትኩት። ከእሳት አጠገብ እጁን በማሞቅ ላይ ነበር። ልገድለው አሰብኩ። ቀስቴን አነጣጠርኩ ። በቅጽበት ግን የነብዩን ﷺ ትዕዛዝ አስታወስኩ ። ቀስቴን ወደ ቦታው መለስኩ። በመካከላቸው ባለሁበት ወቅት ባዕድ ኃይል ሊኖር እንደሚችል የጠረጠሩ ይመስለኛል ። አቡሱፍያን ' በመካከላቸው ሰላይ እንዳይገባ። እያንዳንዳችሁ ከአጠገባችሁ ያለውን ሰው እጅ ያዙ።' በማለት ለፈለፈ ። በአጠገቤ ያለውን ሰው እጅ በቅፅበት በመጨበጥ ' አንተ ማን ነህ!' አልኩት።' እንዴ አታውቀኝም እገሌ እኮ ነኝ' አለኝ።


~ ከዚያም ወደ ነብዩ ﷺ ተመለስኩ ። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሶላት ላይ ነበሩ። ከባድ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ምን ጊዜም የሚያቀኑት ወደ ሶላት ነው። ሶላት ሰግደው እንደጨረሱ በጠላት ካምፕ ያየሁትን በዝርዝር አቀረብኩላቸው ።

~ ሰላይ በመካከላችሁ ገብቷል በማለት ሰላዩን ለመያዝ ያደረጉትን ጥረት እንዴት እንዳከሸፍኩ ስነግራቸው የሚያምር ጥርሳቸውን መመልከት ችያለሁ...''። ፊዳከ አቢ ወ ኡሚ ያረሱለላህ !!

እኛም በጀነት ፊታቸውን ከነ ፈገግታቸው ከሚያዩት ያድርገን አሚን🤲

#Bint_nassir

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
🌴Alwan.

وَمِنَ ٱلَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِۦ نَافِلَةًۭ لَّكَ عَسَىٰٓ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًۭا مَّحْمُودًۭا
ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ (በቁርኣን) ስገድ፡፡ ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል፡፡

(Quran17:79)

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
❤️አላህ (ሱወ) ሰባት ነገሮችን ይወዳል❤️

ተውበት ☆ “አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል” አል በቀራህ [2:222]

ጦሀራ ☆ “አላህ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡”አል በቀራህ [2:222]

ተቅዋ ☆ “አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡” አተ ተውባ[9:4]

ኢህሳን ☆ “አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡” አል ኢምራን[3:134]

ተወኩል ☆ “አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና” አል ኢምራን[3:159]

ዐድል ☆ “አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና፡፡”አል ማዒዳህ{5:42]

ሶብር ☆ “ ..”አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡”አል ኢምራን[3:146]


@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
🌴Alwan.

وَكُلُّهُمْ ءَاتِيهِ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فَرْدًا
''ሁሉም በትንሣኤ ቀን ለየብቻ ኾነው ወደርሱ መጪዎች ናቸው፡፡''

(መርየም : 95 )

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors
🌴Alwan..

<< የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ ወደ ጀነት ተመለከትኩኝ እና ብዙ#ሰዎችም_ድሆች መሆናቸውን አየሁ። >>

Alwane_colors
Alwane_colors
Alwane_colors
Forwarded from ውብ ታሪኮች®
❤️አዲስ ዜና ❤️

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላህ ወበረካቱህ

ውድ የ “ውብ ታሪኮች” ቻናል ቤተሰቦች እንዴት ከረማችሁ??🤔
አልሃምዱሊላህ 💕💙 😊😍

ቻናሉ በተለያዩ ምክንያቶች ምንም ፕሮግራሞች ሳያስተናግድ ቆይቷል።

አሁን በአድስ መልክ እንጀምራለን ኢንሻ አላህ 😍💕

«የባከኑ ቀናት» የሚለው ድርሰት ከነገ ጀምሮ ይለቀቃል
መቸም ለመከታተል ዝግጁ ናችሁ አይደል?❤️

ታሪኩን ለመከታተል 👇
ይህን ቻናል ይቀላቀሉ 👇👇
@wub_tarikoch @wub_tarikoch

#ሼር_ማድረግ_አትርሱ
#ሼር_ማድረግ_አትርሱ
በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ


ነባት እንደሁል ጊዜዋ የፈጅር ስግደት ጥሪ (አዛን) ከመውጣቱ ተነስታለች. የስግደት ትጥበት (ውዱ) አድርጋ የፈጅር ስግደት አካሄደች.
እንደጨረሰች እጆቿን ከታፋዋ ላይ ሳታነሳ እንባዋ ከትላልቅ አይኖቿ ስር ሁለት ሁለት መስመር እየሰሩ መውረድ ጀመሩ. ሁኔታዋን ላየ ሰው የ18ዓመት ለጋ ወጣት ሳትሆን የችግር ዶፍ ያስተናገደች እናት ነው ምትመስለው.
ከጌታዋ ጋር የነበራትን ንግግር ስትጨርስ ከመስገጃዋ አጠገብ ባለው ፍራሽ ላይ የተኛውን ታናሽ ወንድሟን በፍቅር እያየች በትዝታ 3ዓመት ወደ ኋላ ተጓዘች እናትዋ፣አባትዋ፣እሷ እና ታናሽ ወንድሟ ሳሊም አንድ ላይ ሆነው በጠባብዋ ቤታቸው ውስጥ በሰፊ ፍቅር አሳልፈውት የነበረው ቆንጆ ጊዜ ትዝ ብልዋት ፈገግ አለች .
ከአንዱ የትዝታዋ ጓዳ ወታ ማስታወስ ወደማትፈልገው ግን ግድ ወደሚሆንባት የትዝታዋ ክፍል ገባች .
እንባዎቿ በቅፅበት ከአይኖቿ ወረዱ .

ሙሉውን ለማንበብ 👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/wubTarikoch/18
Forwarded from ውብ ታሪኮች®
አመሻችሁ😍

አላህ የምንደብቀውን ግልፅ የምናደርገውንም ያውቃል፡
የልባችንን ጭንቀት የውስጣችንን ሃሳብ ከእሱ ውጭ ማን ያየዋል። ወደ እርሱ ቀረብ እንበልና እንንገረው እናማክረው።
አላህ ሆይ ሁሉም ድምፃችንን ይሰማል አንተ ግን የውስጣችንን ጭንቀት ሃሳብ ሁሉ ትሰማለህ፤ ታያለህ ጭንቀታችንን አስወግደህ ደስታን አጎናፅፈን💞
ربنا إنك تعلم ما نخفي وما نعلن "

@wubtarikoch
@wubtarikoch
2025/02/25 03:15:09
Back to Top
HTML Embed Code: