Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
13547 - Telegram Web
Telegram Web
"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_1 #ርዕስ ፦ የእመቤታችን ልደትና ስደት ➯እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደችው በደብረ ሊባኖስ ተራራ ነው:: ድንግል ማርያም በእናቷ በሐና ማሕፀን ከተጸነሰችበት ቀን ጀምሮ የተለያዩ ተአምራትን ታደርግ ነበር። በማሕፀን ሳለች ካደረገቻቸው ተአምራት ሁለቱ የሚከተሉት ናቸው፡፡ ➯ - በአንደኛው ዓይኗ ማየት የተሳናት ቤርሳቤህ የተባለች የሐና አክስት ጐረ ቤት…
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_2

#ርዕስ ሁለቱ ወንበዴዎች

➯ሁለቱ ወንበዴዎች ማለት ጥጦስ እና ዳክርስ ይባላሉ በእግዚአብሔር ቀኝና ግራ የተሰቀሉት ማለት ነው። መተዳደሪያቸው ቅሚያ ነበር፡፡ እነዮሴፍ ከገሊላ በወጡ ጊዜ ወንበዴዎች ተከተሏቸው:: በበረሃ ቢፈልጓቸው እስከ ስድስት ቀን አላገኟቸውም። በሰባተኛው ቀን አገኟቸውና ዛሬስ እግዚአብሔር ከእጃችን ጣላችሁ ብለው እየሮጡ ሄዱባቸው ስሎሜ አስቀድማ ልብሷን ጥላላቸው ሸሸች።

➯ወንበዴዎቹ ከእነዮሴፍ እጅ የተገኘውን ቀምተው ከሄዱ በኋላ ጥጦስ ዳክርስን እንዲህ አለው። ይቺ ቤት የነገሥታት ወገን ትመስለኛለች። ሕፃኑም ከነቢያት አንዱ ይመስለኛል። የቀማናቸውን እንመልስላቸው ዳክርስም ጥጦስን እንዲህ ያለውን ርኅራሄ ከየት አገኘኸው ይህን ውንብድና ያስተማርከኝ አንተ ነህ። ሊላው ደግሞ ዛሬ የቀማነው የእኔ ድርሻ ነው የራስህን ድርሻ ወስደህ የእኔን ድርሻ እንመልስላቸው ትላለህ አለው።

➯እነዚህ ሁለት ቀማኞች አንድ ቀን የቀሙትን አንደኛው ሲወስድ በሌላ ቀን የቀሙትን ደግሞ ሁለተኛው ይወስድ ነበር። በዚህ ዕለት የቀሙት የዳክርስ ድርሻ ነበር። ጥጦስም ከገሊላ እስከዚህ የቀማነውን አንተ ውሰድ ይህን ለእኔ ስጠኝና ልመልስላቸው አለው፡፡ ዳክርስም በዚህ ሐሳብ ተስማማ፡፡ ዳክርስ የልታደለ ሰው ነው። ጥሩ እድል ገጥሞት ነበር አልተጠቀመበትም፡፡ በትንሽ ርኅራኄ ብዙ በረከት አመለጠው ወደ እርሱ ያንዣበበውን ፀጋ ለጓደኛው ሰጠው።

➯እመቤታችን ሁለቱ ወንበዴዎች ቆመው በዚህ ሐሳብ ሲወያዩ እይታ ፈራች። ወንበዴ አዩኝ አላዩኝ ብሎ የቀማውን ይዞ ይሄዳል እንጂ ለምን ቆሞ ይማከራል : ምን አልባት ልጆቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ይሆናሉ። በዚህ ሕፃን ምክንያት ልጆቻችን ሞቱብን ብለው ልጄን ሊገሉብኝ ይሆናል ብላ ጽኑ ለቅሶን አለቀሰች። ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስም እናቱን ድንግል ማርያምን እንዲህ አላት አይዞሽ እናቴ አታልቅሺ አይገሉኝም እንመልስላቸው እያሉ ነው። እኔ በቀራንዮ ስሰቀል እነሱም በቀኜ እና በግራዬ ይሰቀላሉ አንዱ አምላክነቴን አምኖ ይድናል ሁለተኛው ግን አይድንም፡፡

➯ከዚህ በኋላ ጥጦስ የተባለው ወንበዴ ገንዘባቸውን መለሰላቸውና ጌታን አቅፎ ይዞ ሲሄድ ሰይፉ ወድቆ ተሰበረበት፡፡ በጣም አዘነ፡፡ ጌታ የሰይፍህን ስባሪ ሰብስብ አለው፡፡ ጥጦስ የሰይፉን ስባሪ ሰበሰበ፡፡ ጌታም እንደቀድሞው ይሁንልህ አለው፡፡ ሰይፉም እንዳልተሰበረ ሆነ፡ጥጦስ ሕፃኑ ከነቢያት ወገን : ይመስለኛል ብሎ የገመተው ግምት እውን ሆነለት፡፡ ተአምራቱን አየና አደነቀ፡፡

➯ጌታም ጥጦስን እንዲህ አለው አዳምን ቀድመኸው ገነት ትገባለህ፡፡ ጥጦስም ሄዶ ጌታ የነገረውን ሁሉ እና ያደረገለትን ተአምራት ለጓደኛው ነገረው ግን ጓደኛው ዳክርስ አላመነም፡፡ ጥጦስ የተባለው ወንበዴም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ በጌታ ቀኝ ( ተሰቅሎ : ፀሐይ : ስትጨልም : አይቶ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት አምኖ «ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ» አለው። "ኢየሱስም እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው።" (ሉቃ 23:42) ጌታ አዳምን ቀድመኸው ገነት ትገባለህ ብሎ በጫካ የሰጠውን ተስፋ በመስቀል ላይ ፈጸመለት፡፡

➯ከዚህ በኋላ እነዮሴና ገዳመ ጌራራል ገቡ ጌራራል ከተባለ ጫካ ገቡ በገዳመ ጌራራል መላእክት እየመጡ እያጽናኗቸው 40 ቀን ተቀምጠዋል። ከ40 ቀን በኋላ አንድ አውሬ አዳኝ አያቸው እርሱም በፍጥነት ሄዶ ማርያምን እና ዮሴፍን ሰሎሜንም በጌራራል ጫካ ትናንት አየኋቸው ብሎ ለሄሮድስ ነገረው፤ ሄሮድስም በጌራራል ጫካ መኖራቸውን በሰማ ጊዜ በጣም ደስ ተሰኘ። ይህን ወሬ ላመጣለት አውሬ አዳኝ እነዮሴፍን ካሳየኸኝ የመንግሥቴን አኩሌታ እሰጥሃለሁ ብሎ በጣዖቱ ማለለት፡፡ ሄሮድስ በሀገሩ ሁሉ አዋጅ ነገረ መልእክተኛ ላከ፡፡ አዋጅ ነጋሪው በየሀገሩ እየዞረ "ሁላችሁም የሄድሮስ ወታደሮች ነገ በሄሮድስ ቤተ መንግሥት እንድትገኙ" በማለት አስጠነቀቀ።

➯ወታደሮቹ የሄሮድስን ቤተመንግሥት አጥለቀለቁት። ሄሮድስም ወደ ጌራራል ጫካ ላካቸው፡፡ የሄሮድስ ወታደሮች የጌራራልን ጫካ ከበቧት፡፡ ነገር ግን እነዮሴፍን አላገኝዋቸውም፡፡ ወታደሮቹ እርስ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ እነዮሴፍ የት ሄዱ ምድር ዋጠቻቸውን እነዮሴፍን ግን የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ የሄሮድስ ሠራዊት በማያውቁት መንገድ ወሰዳቸው።


#ክፍል_ሦስት_ይቀጥላል.....

@AndEmnet
#ዝክረ_ቅዱሳን_ጥቅምት_28/፳፰ (ስንክሳር)

እንኳን #ለጻድቁ_አቡነ_ይምዓታ ለዕረፍታቸው፣ እና #ለቅዱስ_መርትያኖስና_ለቅዱስ_መርቆሬዎስ በሰማዕትነት ላረፉበት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"

#አቡነ_ይምዓታ_ጻድቅ

➯ጥቅምት ሃያ ስምንት በዚህች ቀን ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ጻድቁ አቡነ ይምዓታ አረፉ።

➯ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት። አባ ይምዓታ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው። ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው።

➯ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው። በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር፦

፩.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ
፪.ዓላማ (የእግዚአብሔር መንግስት) እና
፫.ገዳማዊ ሕይወት ነው።

➯አባ ይምዓታን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው። እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል። አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል።

➯በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ። ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ።

➯በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም። ስለዚህም በ470ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ።

➯ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው። ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው። ይህች ቦታ "ቤተ ቀጢን" ትባላለች።

➯አባ ይምዓታና 8ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር። ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ። በወቅቱ በአቡነ ሰላማ፣ በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ይምዓታ እንደ ገና አቀጣጠሉት።

➯ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት። የካደውን እየመለሱ የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ። ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ።

➯ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው። በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ይምዓታ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር። በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር። ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም።

➯የነ አባ ይምዓታ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ:: ዸንጠሌዎን በጾማዕት፣ ገሪማ በመደራ፣ ሊቃኖስ በቆናጽል፣ አረጋዊ በዳሞ፣ ጽሕማ በጸድያ፣ ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ።

➯አባ ይምዓታ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ገርዓልታ (እዛው ትግራይ) ሆነ። ጻድቁ ወደ ቦታው ሲሔዱ ወንዝ (ባሕር) ተከፍሎላቸዋል። ወደ ቦታው ደርሰውም ገዳም አንጸዋል። በቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠርተው በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ለዘመናት ተጋድለው በገርዓልታ በዚህች ቀን አርፈዋል።

➯የአቡነ ይምዓታ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ትግራይ ገርዓልታ ልዩ ስሙ ‹‹ጎሕ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ሰማይን እንደ ምሰሶ ደግፈው የያዙ የሚመስሉ በጣም ረጃጅም ተራሮች መካከል በአንደኛው ጭፍ ላይ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ከባሕር ወለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ያለበት የተራራው ርዝመት ብቻውን 300 ሜትር ነው፡፡ ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ በጭንቅና በፍርሃት ሆኖ ተራራውን እንደዝንጀሮ በእጅ እየቧጠጡ መውጣት ይጠይቃል፡፡ እርሱም ቢሆን በገዳሙ አባቶች እገዛና ድጋፍ ካልሆነ መውጣት የማይቻል ነው፡፡

➯ቤተ መቅደሱ እጅግ የሚደንቀው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ ብቻ አይደለም ውስጡ ያሉት የግድግዳ ላይ ሥዕሎችም እጅግ ድንቅና ጥንታዊ ናቸው፡፡ ስለዚሁ የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስደናቂ ቤተ መቅደስ ገድለ አቡነ አረጋዊ "በሞት በዐረፉ ጊዜ የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በመላእክት እጅ ነው የተከናወነው፡፡ ይልቁንም ቁመቱና ርዝመቱ ከታላላቅ ገደል እጅግ በጣም የሚበልጥ የድንጋይ ዓምድ ከወንዝ ማዶ ዘንበል ብሎ መጥቶ ሥጋቸውን በክብር ተቀብሎ በተራራው ጫፍ ላይ እስከዛሬም ድረስ ፈጽሞ ሳይነቃነቅና ሳይናወፅ ቀጥ ብሎ ቆሞ ይገኛል በማለት ይገልጻል፡፡
#ቅዱስ_መርትያኖስና_ቅዱስ_መርቆሬዎስ (ስንክሳር)

➯ዳግመኛም በዚህች ቀን ቅዱስ መርትያኖስና መርቆሬዎስ በሰማዕትነት አረፉ። እሊህም ለቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱ ናቸው።

➯ይህም እንዲህ ነው አርዮሳዊ የሆነው ሁለተኛው ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ አባ ጳውሎስን በተጣላው ጊዜ ወደ አርማንያ አጋዘውና በዚያም በሥውር በእሥር ቤት ውስጥ አንቀው እንዲገድሉት አደረገ እሊህ ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ ግን የዕረፍቱን ቀን ገድሉንም ጻፉ አርዮሳዊውንም ንጉሥ ረገሙት።

➯አንድ ክፉ ሰውም ወደ ንጉሡ ሒዶ እነርሱ እንደረገሙት ወነጀላቸው። ንጉሡም ያን ጊዜ ከአታክልት ቦታዎች በአንዲቱ ቦታ ተቀምጦ ሳለ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስቀረባቸው በሰይፍም እንዲገድሏቸው አዝዞ ገደሏቸው። በዚያም በገደሏቸው ቦታ ቀበሩአቸው እስከ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመንም በዚያ ቦታ ኖሩ እርሱም ዜናቸውን በሰማ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ሥጋቸውን ወደ ቊስጥንጥንያ በክብር አስመጣ ያመረች ቤተ ክርስቲያንንም ሠርቶላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖረ በዚችም ቀን በዓልን አደረገላቸው።

➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

@AndEmnet ጥቅምት ፳፰/28 ቀን
"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_2 #ርዕስ ፦ ሁለቱ ወንበዴዎች ➯ሁለቱ ወንበዴዎች ማለት ጥጦስ እና ዳክርስ ይባላሉ በእግዚአብሔር ቀኝና ግራ የተሰቀሉት ማለት ነው። መተዳደሪያቸው ቅሚያ ነበር፡፡ እነዮሴፍ ከገሊላ በወጡ ጊዜ ወንበዴዎች ተከተሏቸው:: በበረሃ ቢፈልጓቸው እስከ ስድስት ቀን አላገኟቸውም። በሰባተኛው ቀን አገኟቸውና ዛሬስ እግዚአብሔር ከእጃችን ጣላችሁ ብለው እየሮጡ ሄዱባቸው ስሎሜ አስቀድማ…
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_3

#ርዕስጉዞ ወደ ጥብርያዶስ

➯ከዚህ በኋላ የእመቤታችን ዘመድ የኬፋዝ ንጉሥ ወደ አለበት ወደ ጥብርያዶስ ሄዱ፡፡ እመቤታችንም ሄሮድስ እንደ ሚያሳድዳት ዘመዷ ለሆነው ንጉሥ ነገረችው:: "ንጉሡም ሄሮድስ የሚያሳድድሽ ለምን ምክንያት ነው ብሎ ጠየቃት።" "ይህን ሕፃን ለመግደል ስለሚፈልግ ነው አለችው::" ንጉሡም እመቤታችንን "ከዚህ ከእኔ ቤት ተቀመጪ አላት።" ቤተሰቦቹንም "ማርያምን ከእርሱ ቤት መኖርዋን ለማንም እንዳይነግሩ አስጠነቀቃቸው።" ሄሮድስ ግን በብዙ አገሮች እየዞረ ቢፈልጋት ሊያገኛት አልቻለም፡፡ ሄሮድስ እንዲህ ይል ነበር ማርያምን ምድር ዋጠቻትን

➯ሄሮድስ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ያደረገው ጥረት የደከመው ድካም እጅግ ብዙ ነው። ያለውን ኃይል አሟጦ ተጠቅሟል የሚፈልገውን አለማገኘቱ ደግሞ ድካሙን ውጤት አልባ አድርጐታል።

➯ከብዙ ቀናት በኋላ ሄሮድስ ጥብርያዶስ በሚባል አገር እመቤታችን መኖርዋን ሰማ፡፡ እመቤታችን ወደ አለችበት ንጉሥ ደብዳቤ ጽፎ መልእክተኛ ላከ፡፡ ሄሮድስ የጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ይላል "ንጉሥ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል #ማርያምን_ከነልጅዋ ያዝልኝ ብዙ ወርቅ እና ብር እሰጥሃለሁ በእኔ እና በአንተ መካከል ጽኑ ፍቅር ይሆናል።" ንጉሡም የሄሮድስን ደብዳቤ አንብቦ በጣም ተገረመ። እንዲህም አለ "ማርያም በእኔ ቤት መኖርዋን ለሄሮድስ ማን ነገረው መቼም ሰው አልነገረውም ሰይጣን ነግሮታል እንጂ።" የእመቤታችን ዘመድ የሆነው ንጉሥም ሄሮድስ የላከውን መልእክት ለእመቤታችን ነገራት። እመቤታችንም በጣም ደነገጠች።

➯ንጉሡም "እኔ ከሞትኩ ትሞቻለሽ እኔ ከዳንኩ ትድኛለሽ አትፍሪ ለሄሮድስ አሳልፌ አልሰጥሽም አላት፡፡" "ወትቤ ማርያም ዘፈቀደ አምላከ እስራኤል ለይኩን /ማርያምም የእስራኤል አምላክ የፈቀደው ይሁን አለች፡፡"

➯በዚያች ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ "ሲነጋ ይህን አገር ለቀሽ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሂጂ አላት፡፡ በዚያም እኔ መጥቼ ተነሺ እስክልሽ ድረስ ተቀመጪ አላት።" በነጋ ጊዜ መልአኩ የነገራትን ለንጉሡ ነገረችው፡፡ ንጉሡም ደስ ብሎት የሦስት ቀን መንገድ እስከ ዛብሎን እና እስከ ንፍታሌም ድረስ ሸኛት። ከዚህ በኋላ ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡


#ክፍል_አራት_ይቀጥላል.....

@AndEmnet
#ዝክረ_ቅዱሳን_ጥቅምት_29/፳፱ (ስንክሳር)

እንኳን ለአባቶቻችን ለቅዱሳን #ለአቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ወገግ ለረፍታቸው፣ #ለቅዱስ_ድሜጥሮስ ዘተሰሎንቄ በሰማዕትነት ላረፈበት፣ እና #ለመምህር_ጸቃውዐ_ድንግል ለረፍቱ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።

#አቡነ_ሳሙኤል_ጻድቅ (ዘደብረ ወገግ)

➯ጥቅምት ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ አረፉ፡፡

➯ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል እንድርያስና አርሶንያ ከሚባሉ የበቁ ደጋግ አባትና እናታቸው የተወለዱት በሸዋ ሀገረ ስብከት ቀድሞ ጽላልሽ ዛሬ ቡልጋ በሚባለው አውራጃ ነው፡፡ የወላጆቻቸው በጎ ምግባርና ሃይማኖት ቅዱስ ተክለሃይማኖትን ከደብረ ሊባኖስ አነሣስቶ በቤታቸው ሄደው እንዲስተናገዱ አድርጓል፡፡ ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበርና አቡነ ተክለሃይማኖትም በጸጋ እግዚአብሔር ተገልጾላቸው "እግዚአብሔር ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ" ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ በትንቢቱም መሠረት አቡነ ሳሙኤል ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም ሲወለዱ መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡

➯አቡነ ተክለሃይማኖትም በአባቱ እንድሪያስ በኩል የሥጋ ዘመዱ ሲሆኑ የመንፈስ ቅዱስም አባት ሆኑትና በ40 ቀን ክርስትና አንስተው ስመ ክርስትናውን "ሳሙኤል" አሉት፡፡ ትርጓሜውም "እግዚአብሔር ጸለቴን ሰማኝ" ማለት ነው፡፡ ከሕፃንነትም ጀምረው በምግባር በሃይማኖት ኮትኩተው አሳድገው ለዲቁና አብቅተው በኋላም አመንኩሰውታል፡፡ "ደብረ ወገግ" የሚለው ስያሜ የተገኘው ከመላእክት ነው፡፡ ድርሳነ ዑራኤል በሰፊው እንደሚያትተው ቅዱስ ዑራኤል የጌታችንን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ ዓለምን እየረጨ ሲቀድሳት የያዘውን ጽዋ በደብረ አስቦ ቆሞ ሳለ ነው ጨልጦ ያንጠፈጠፈው፡፡ ያንጊዜም ደብረ አስቦን የብርሃን ውጋጋን ሲያጥለቀልቀው መላእክትም "ቦታውን ደብረ ወገግ" (የብርሃን ተራራ) ብለው ሰይመውታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም "ወደፊት ፈጣሪውን የሚያገለግል ታላቅ ጻድቅ ይወጣባታልና ይህችን ቦታ ባርካት" ብሎ ቅዱስ ዑራኤልን በነገረው መሠረት ባርኳት እንዳረገ ድርሳነ ዑራኤል ላይ በሰፊው ተጽፏል፡፡

➯በቦታው ላይ ብዙ ጊዜ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ መታየቱን የበቁ ገዳማውያን ብቻ ሳይሆኑ በከተማ ያሉና ለመሳለም ወደ ቦታው የሄዱ ደገኛ ሰዎችም በዐይናቸው ያዩትን ይናገራሉ፡፡ በገዳሙ ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል፡፡

➯ንጉሥ ዓምደ ጽዮን በክፉዎች ምክር የአባቱን ሚስት እንጀራ እናቱን በማግባቱ ምክንያት አቡነ ፊሊጶስ ጋር ሆነው ያወገዙትን የቅዱስ ተክለሃይማኖትን ወገኖች በየአውራጃው በተናቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስንም ደሙ በምድር ላይ እስከሚንጣለል ድረስ ገርፈው ወደነበረበት ቤቱ ወሰዱት፤ ፊሊጶስም በሚሄድበት ቦታ ላይ ሳይደርስ በመንገድ ሞተ፡፡ እንድርያስ፣ አኖሬዎስና ተክለ ጽዮን ሁላቸው ከተከታዮቻቸው ጋር በሰማዕትነት አርፈው እነስድስተይ በምትባል ምድር ተቀበሩ፡፡ ጳጳሱን አቡነ ያዕቆብንም ደሙ በምድር ላይ እንደውኃ እስኪወርድ ድረስ ገርፈው ወደ ሀገሩ እንዲሰደደ አደረጉት፡፡ ከዚያም በኋላ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል ዘወገግን አገኘውና ‹‹መማጸኛ እንዲሆነኝ በእንድርያስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ሥራልኝ›› ብሎ ለመነውና የሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠራለት፡፡ የእንድርያስንም አጽም ከመቅደሱ ስር አኖረው፡፡ ንጉሡም በዚያ በእንደግብጦን አውራጃ ሁሉ ላይ ፓትርያርክ አድርጎ ሾመው፡፡ በእነስድስታይ አገር ላሉ ሰዎችም ሁሉ አባት ሆናቸውና የመንፈስ ቅዱስ ልጁንም ታዲዮስን መምህርና አባት አድርጎ ሾመላቸውና ጽላልሽ ሄዶ እናቱን ይዞ ጽጋጋ ምድረ ወገግ ወስዶ አመነኮሳት፡፡

➯አቡነ ሳሙኤል ወደ ምድረ ርስቱ ደብረ ወገግ እየሄደ በዚያ ያሉ ልጆቹን እያጽናና ወደ እንደግብጦን አውራጃም እየተመለሰ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ፣ ወንጌልን እያስተማረ፣ ጣዖት አምላኪዎችን ወደ ክርስትና እየቀየረ፣ አጋንንትንና መመለኪያ ቦታዎቻቸውን እያጠፋ፣ አብያተ ክርስቲያናትን እያነጸ በብዙ ተጋድሎ ኖረ፡፡ በቅዱስ ገድሉ ውስጥ በጣም አስገራሚ በሆነ መልኩ እጅግ ብዙ ታሪኮች ተጠቅሰዋል፡፡ እነዚህም ታሪኮች ውስጥ አቡነ ሳሙኤል በሀገራችን በጣም ብዙ ጣዖታትንና መመለኪያ ቤቶቻቸውን እያጠፉ፣ በሰዎች (በጠንቋዮች) ላይ፣ በዛፍና በባሕር ውስጥ አድሮ ይመለኩ የነበሩ ሰይጣናት አጋንንትን በሚያመልኳቸው ሰዎች ፊት እያጋለጡና እያዋረዱ ሰዎቹን አስተምረው አጥምቀው ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እየመለሷቸው ቤተክርስቲያንም በመሥራት ሐዋርያትን መሰሉ፡፡

➯ሰይጣን አድሮባቸው የነበሩ ጠንቋዮች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ዕቃዎችን ጻድቁ እየባረኩና እየቀደሱ ለቤተክርስቲያን መሥሪያና መጠቀሚያነት ያውሉት ነበር፡፡ ይህም ገና ሳይወለዱ በአቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት ተነግሮላቸው ነበር፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት ‹‹ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ይሆናል›› ብሎው ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡ ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡

➯ጻድቁ አባታችን አባ ሳሙኤል ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፣ ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፣ በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፣ ይህን ኃላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፣ በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፣ በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ እንደዚሁም ሌሎች ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ በትእምርተ መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሎአቸውን ፈጽመው ከጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈዋል፡፡
#ቅዱስ_ድሜጥሮስ_ሰማዕት (ስንክሳር)

➯በዚህችም ቀን በከሀዲው ንጉሥ በመክስምያኖስ ዘመን ቅዱስ ድሜጥሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ ከተሰሎንቄ ሀገር ነው የከበረች የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምሮ በቀናች ሃይማኖት ጸና ሕዝቡንም የሚያስተምር ሆነ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በመስበክ ብዙዎችን ከስሕተት መለሳቸው።

➯ስለዚህም በከሀዲው ንጉሥ ዘንድ ወነጀሉት ንጉሡም ወደ እርሱ እንዲአመጡት አዘዘ በንጉሡም ዘንድ አንድ ሥጋው የደነደነ የጸና ዐጥንቱ የሰፋ ሰው ነበረ ለሰዎችም ሁሉ እሱ ሁሉን የሚያሸንፍ እሱን የሚያሸንፈው የሌለ ይመስላቸው ነበር ንጉሡም ይወደዋል ይመካበታል እንዲህም ይል ነበር ይህን አካሉ ግዙፍ የሆነ ሰው ለሚያሸንፍ እኔ ብዙ ገንዘብ እሰጠዋለሁ።

➯በዚያንም ጊዜ ስሙ በስጥዮስ የሚባል አንድ ክርስቲያናዊ ሰው ተነሥቶ ወደ ቅዱስ ድሜጥሮስ ሔደ እንዲጸልይለትና በሥጋውም ሁሉ አሸናፊ በሆነ በመስቀል ምልክት እንዲአማትብበት ለመነው። እርሱም በላዩ ጸለየለት በሥጋውም ሁሉ ላይ በመስቀል አማተበበት ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሥ ገብቶ ከዚያ ሥጋው ግዙፍ ከሆነው ጋር ያታግለው ዘንድ ለመነው ንጉሡም ፈቀደለት በታገሉም ጊዜ ሥጋው የደነደነውን ያ ክርስቲያናዊ ሰው አሸንፎ ጣለው ንጉሡም አዘነ አደነቀም ሥጋው የደነደነውም በመሸነፉ አፈረ ተመክቶበት ነበርና።

➯ንጉሡም ስለዚህ ነገር ወታደሮቹን ጠየቀ እነርሱም ቅዱስ ድሜጥሮስ በላዩ እንደጸለየለትና በሥጋውም ላይ በመስቀል ምልክት እንዳማተበበት ነገሩት።

➯ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ በቅዱስ ድሜጥሮስ ላይ እጅግ ተቆጣ ለአማልክትም ዕጣን እስከሚአሳርግ ድረስ እንዲገርፉት አዘዘ ንጉሡም እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉበት የንጉሡንም ትእዛዝ ባልሰማ ጊዜ እስከሚሞት በጦሮች እንዲወጉት ሁለተኛ አዘዘ።

➯ለቅዱስ ድሜጥሮስም ይህን ፍርድ ነገሩት ሃይማኖቱን ትቶ ለአማልክት የሚሰግድ መስሏቸው ነበርና ቅዱስ ድሜጥሮስም እኔ ከዕውነተኛ አምላክ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለረከሱ አማልክት እሰግድ ዘንድ ዕጣን ማሳረግም አልፈቅድም የወደዳችሁትን አድርጉ አላቸው።

➯በዚያንም ጊዜ ንጽሕት ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ እስከ ሚሰጥ በጦር ወጉት ሥጋውንም በጣሉት ጊዜ ምእመናን ወደ ርሳቸው ወሰዱት የስደቱም ወራት እስከሚያልፍ በሣጥን አድርገው በቤታቸው ውስጥ ሠውረው አኖሩት።

➯የስደቱም ወራት ከአለፈ በኋላ እግዚአብሔር ገለጠውና ከዚያ አወጡት ያማረች ቤተ ክርስቲያንንም በተሰሎንቄ አገር ሠሩለት ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ድንቅ የሆነ ታላቅ ተአምርን እያደረገ እስከ ዛሬ አለ።

➯ሽታውም እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ ቅባት ከእርሱ ይፈሳልና በእምነት የሚቀቡትን በሽተኞች ሁሉንም ያድናቸዋል። ይልቁንም በዕረፍቱ መታሰቢያ ቀን ከሌሎቹ ዕለታት ተለይቶ በብዛት ይፈሳል ከአውራጃው ሁሉ ብዙዎች ሰዎችም ይመጣሉ ከዚህም ቅባት ወስደው በማሰሮቻቸው ያደርጋሉ ይቺ ምልክትም እስከ ዓለም ፍጻሜ በመኖር እንደምትገኝ ደጋጎች ካህናት ምስክሮች ሆኑ።
#አባ_ጸቃውዐ_ድንግል (ዘደብረ ዘኸኝ) (ስንክሳር)

➯በዚህችም ቀን የተመሰገነና የከበረ የደብረ ዘኸኝ መምህር ጸቃውዐ ድንግል አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባቱ ካህን ነው በጥበብና በበጎ ተግሣጽም አሳደገው መለኮታዊ ትምህርትን ሁሉ አስተማረው አድጎ አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አባቱ ከአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ለመምህርነትም ተመርጦ በአባ ገብረ ማርያም ወንበር ላይ ተሾመ።

➯በዚያንም ጊዜ አባቱ ለልጁ የምንኵስና ልብስ አለበሰው ስሙንም ጸቃውዐ ድንግል ብሎ ሰየመው ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ ያለ ማቋረጥ በጾም በጸሎት ብዙ በመስገድም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ ። ከዚህም በኋላ አባቱ በአረፈ ጊዜ በአባቱ ፈንታ ተሾመ መንጋዎቹንም እንደ ሐዋርያት ሥርዓት በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው።

➯በሌሊቱም ሁሉ ከባሕር ውስጥ ቁሞ ያድራል ከባሕሩም ሲወጣ ወዙ በምድር ላይ እስከሚንጠፈጠፍ ስግደትን ያዘወትራል ምግቡም ደረቅ እንጀራ ነው ጠጅ ወይም ጠላ አይጠጣም እግዚአብሔርም በእጆቹ ላይ ተአምራትን አደረገ በጐዳናም ሲጓዝ ከታናሽነቱ ጀምሮ ሒዶ የማያውቅ መፃጉዕን አገኘ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ የተጸለየበትን ውኃ በላዩ ረጨ በመስቀልም ምልክት አማተበው በዚያንም ጊዜ ዳነ ። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ ጥቂት ታሞ በሰላም አረፈ።


➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

@AndEmnet #ስንክሳር ጥቅምት ፳፱/29 ቀን
"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_3 #ርዕስ ፦ ጉዞ ወደ ጥብርያዶስ ➯ከዚህ በኋላ የእመቤታችን ዘመድ የኬፋዝ ንጉሥ ወደ አለበት ወደ ጥብርያዶስ ሄዱ፡፡ እመቤታችንም ሄሮድስ እንደ ሚያሳድዳት ዘመዷ ለሆነው ንጉሥ ነገረችው:: "ንጉሡም ሄሮድስ የሚያሳድድሽ ለምን ምክንያት ነው ብሎ ጠየቃት።" "ይህን ሕፃን ለመግደል ስለሚፈልግ ነው አለችው::" ንጉሡም እመቤታችንን "ከዚህ ከእኔ ቤት ተቀመጪ አላት።" ቤተሰቦቹንም…
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_4

#ርዕስተአምረ ማርያም በምድረ ጋዛ

➯እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲዘዋወሩ #ጋዛ ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በጋዛ የሚኖሩ ሰዎች እጅግ ክፉዎች ነበሩ፡፡ ዮሴፍ በጋዛ የሚኖሩትን ሰዎች እንዲሀ አላቸው። "በአገራችሁ ውሃ የለምን?" የጋዛ ሰዎችም እንዲህ አሉ "በሀገራችን ውሃ የለም ውሃ የምንቀዳበት ቦታ ርቀት በእግር 27 ቀን ይወስዳል፡፡ 27 ቀን ተጉዘን በግመል ጭነን አምጥተን ትንሽ ትንሽ እንጠጣለን አሉት።" የጋዛ ሰዎች ክፉዎች ስለሆኑ እንዲህ አሉ እንጂ በሀገራቸው ውሃ የሌለ ሆኖ አይደለም፡፡ የጋዛ ሰዎች ውሃ ከቀዱ በኋላ የውሃውን ጉድጓድ ዝግባ በተባለ ታላቅ እንጨት ይገጥሙታል፡፡ መንገደኞች ውሃ ሲጠይቋቸው ወይም ሲለምንዋቸው ውሃ የለንም ይላሉ፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጅ ሕይወት ይሆን ዘንድ የፈጠረውን ውሃ የሚከለክሉ ጨካኞች ነበሩ፡፡

➯የውሃ ልመናው ያልተሳካለት ዮሴፍ እመቤታችንን እንዲህ አላት፡፡ በዚህ ሀገር የምንጠጣው ውሃ የለም፡፡ እመቤታችንም አተር የአሚወቁ የሚያበራዩ! ሰዎችን አየች። አተር ወደ ሚወቁት ሰዎች እንሂድና አተር ስጡን እንበላቸው አለችው ዮሴፍን እመቤታችን የጋዛን ሰዎች ጭካኔና ርኅራኄ ማወቅ ፈልጋለች ፡ አተር ወደሚያበራዩት / ወደሚወቁት ሰዎች ሄደው "ይህን ሕፃን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለራው ትንሽ አተር ስጡት ብለው ለመንዋቸው። የጋዛ ሰዎች ውሃ እያላቸው ውሃ የለንም እንዳሉ ሁሉ የአተሩን ልመናም አልተቀበለትም። ይልቁንም "ይህ የምታዩት አተር ሳይሆን ድንጋይ ነው" በማለት ቀለዱባቸው።"

➯ከዚህ በኋላ ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን "እንደቃላችሁ ይሁንላችሁ በያቸው አላት፡፡" እመቤታችንም "እንደቃላችሁ ይሁን አለቻቸው።" ወዲያው የሚወቁት አተር ድንጋይ ሆነ፡፡ ውሃ እያላቸው ውሃ የለንም ስላሉ ውሃቸውም ደረቀ። አገራቸውም እህልን ዕፅዋትን የማያበቅል ደረቅ ሆነ። ምንጊዜም ቢሆን ለከፉ ሰዎች የተንኮላቸው ዋጋ ይከፈላቸዋል፡፡

➯ኢየሱስ ክረስቶስ ወንጌልን በሚያስተምርበት ጊዜ ተንኮለኞች በተንኮላቸው እንደሚጠፉ እንዲህ ሲል ተናግሯል ፡ "ወራት ይመጣብሻልና ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኩሉም ያስጨንቁሻል" (ሉቃ 19፥43-44) ኢየሱስ ክርስቶስን ግብዞች ፈሪሳውያን ስለአሉባት ከተማ የተነገረ ቃል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን ሰቅለው የገደሉ የአይሁድ ከተማ ኢየሩሳሌም ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ በ10 ዘመን በሮማውያን ጠፍታለች።


#ክፍል_አምስት_ይቀጥላል.....

@AndEmnet
#ዝክረ_ቅዱሳን_ጥቅምት_30/፴ (ስንክሳር)

እንኳን #ለቅዱስ_ማርቆስ ለተወለደበት፣ #ለመጥምቁ_ዮሐንስ ቅድስት ነፍሱ ከተቆረጠች ራሱ ጋራ በግልጽ ለታየችበት፣ በገድል የተጸመደ #ለቅዱስ_አባት_ባሕታዊ_አብርሃም ላረፈበት ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።

#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ

➯ጥቅምት ሠላሳ በዚህች ቀን ለእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት አለቃ የሆነ ወንጌልን የጻፈ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የተወለደበት ነው።

➯የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አርስጦቡሎስ ነው እርሱም ከአምስቱ አገሮች የሆነ የእናቱም ስም ማርያም ነው እርሷም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ተጽፋለች እርሱም አስቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ነው። በግብረ ሐዋርያት ማርቆስ በተባለ በዮሐንስ እናት ቤት ሐዋርያት ይጸልዩ ነበር ተብሎ እንደ ተጻፈ። እርሷም ባለጸጋ ነበረችና የዮናናውያንን የሮማይስጥን የዕብራይስጥን ትምህርት ለልጅዋ ለማርቆስ አስተማረችው።

➯በአደገም ጊዜ በርናባስ ወንጌልን ለመስበክ ከጳውሎስ ጋራ ሲሔድ ይዞት ሔደ በእነርሱም ላይ የሚደርስባቸውን መከራ አይቶ በጵንፍልያ ከተማ ሳሉ ትቷቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

➯ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን አሕዛብ እንደ ተመለሱ እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ላይ ድንቅ ተአምራትን እንዳደረገ ተናገሩ። ይህ ብላቴና ማርቆስም ከእርሳቸው ስለ መለየቱ አዘነ ተጸጸተ።

➯ከዚያም አብሮአቸው ሊሔድ ፈለገ አስቀድሞ ትቷቸው ስለተመለሰ ጳውሎስ ሊአስከትለው አልወደደም በርናባስ ግን ወሰደው አጎቱ ነውና። በርናባስም ከአረፈ በኋላ ወደ ሮሜ አገር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሒዶ ለእርሱ ደቀ መዝሙሩ ሆነ በዚያም ቅዱስ ጴጥሮስ የተረጐመለትን ወንጌልን ጻፈ በሮሜ አገርም አስተማረበት። ከዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝና በሐዋርያትም ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ። በውስጥዋም የከበረ ወንጌልን አስተማረ ደግሞም በአፍራቅያና በአምስቱ አገሮች በርቃ በሚባልም አገር ወደ እስክንድርያ ከተማ በገባ ጊዜ ጫማው ተቆረጠ።

➯በዚያም በከተማው መግቢያ ጫማ ሰፊ ነበረ። ቅዱስ ማርቆስም እንዲሰፋለት ለርሱ ሰጠው ሲሰፋም ጣቱን ወግቶ ሰነጠቀው ከእርሱም ደም ፈሰሰ በዮናኒም ቋንቋ ኢታስታዖስ አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም ስሙን የምትጠራው አውቀኸው ነውን አለው እንጠራዋለን እንጂ አናውቀውም አለ።

➯እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ አባታችን አዳም ትእዛዙን እንደተላለፈ የጥፋት ውኃም እንደ መጣ ሙሴንም እንደላከውና እስራኤልን ከግብጽ እንዳወጣቸው ሕግንም እንደ ሠራላቸው ናቡከደነጾርም ወደ ባቢሎን ማርኮ እንደወሰዳቸውና ከሰባ ዓመት በኋላ ወደ አገራቸው ኢየሩሳሌም እንደ ተመለሱ ክርስቶስ ሥጋ በመልበስ ወደ ዓለም ስለ መምጣቱ ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩ ያስተምረው ዘንድ ጀመረ።

➯ከዚያም በኋላ ወደ ምድር ምራቁን ትፍ ብሎ ጭቃ አድርጎ ጣቱን ቀባው ወዲያው ዳነ በጌታችንም አመነ። ያም ሰፊ ስሙ አንያኖስ ነው። ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወስዶ ልጆቹን ዘመዶቹንም ወደ ርሱ አቀረበ እርሱም አስተምሮ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።

➯በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሰዎች በበዙ ጊዜ የቅዱስ ማርቆስን ዜና ሰምተው የአገር ሰዎች ሊገድሉት ተሰበሰቡ እርሱም አንያኖስን ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሹሞ ልጆቹን ቄሶችና ዲያቆኖች አድርጎ ከዚያም ወደ በርቃ ወደ አምስቱ አገሮችም ወጥቶ አስተማረ። በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው በእርሳቸውም ዘንድ ሁለት ዓመት ኖረ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው።

➯ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ተመለሰ ምእመናንም ተጨምረው በዝተው በታወቁ ቦታዎች ሁሉ በባሕሩም ዳር በላሞች መካበቢያ በሚባለውም አብያተ ክርስቲያን ሠርተው አገኛቸው።

➯ከሀድያንም የከበረ ሐዋርያን ይገድሉት ዘንድ በብዙ ድካም ፈለጉት እርሱም አምስቱን አገሮች ሲጐበኝ በሥውር ወደ እስክንድርያ ከተማ ይገባ ይወጣ ነበር። በአንዲትም ዓመትም ከአምስቱ አገሮች ተመልሶ ሚያዝያ ዐሥራ ሰባት ቀን በመድኃኒታችን የትንሣኤ በዓል ወደ ቤተክርስቲያን ገባ ሕዝቡም ሁሉ በዙሪያው አሉ። ከሀድያንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በአንገቱ ውስጥ ገመዶችን አድርገው በከተማው ሁሉ ጎተቱት። እነርሱም ገና እንደፍየል ሙክት እንጎትተዋለን እያሉ ይጮኹ ነበር ። በላሞች መካበቢያና በሀገሪቱ አደባባይ በከተማውም ዙሪያ በየቀኑ ሲጎትቱት ኖሩ።

➯ሌሊትም በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያት ጋራ በነበረበት አርአያ ሁኖ ተገለጠለት ሰላምታም ሰጥቶ አጽናናው ቃል ኪዳንም ሰጠው። እነሆ አንተ ከወንድሞችህ ሐዋርያት ጋር ተካከልህ አለው። እርሱም በልቡናው ፈጽሞ ደስ አለው። በማግሥቱም ሁለተኛ ገመዶችን በአንገቱ አድርገው በአገሮች ሁሉ ጎተቱት በቀኑም መጨረሻ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።

➯ከሀዲዎችም ታላቅ እሳትን አንድደው የቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ከውስጡ ጨመሩ ። በክብር ባለቤት ጌታችን ፈቃድም ንውጽውጽታ ጨለማ ቀዝቃዛ ነፋስ መብረቅና ነጐድጓድ ሆነ። ፀሐይም ጨለመ ከሀዲዎችም ሸሹ ምእመናንም መጥተው የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ወሰዱ ምንም ጥፋት ሳይደርስበት ደኀና ሆኖ አገኙት በመልካም ልብስም ገንዘው በጥሩ ቦታ አኖሩት መታሰቢያውንም አደረጉ።
#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቀ_መለኮት (ስንክሳር)

➯ዳግመኛም በዚህች ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ ቅድስት ነፍሱ ከተቆረጠች ራሱ ጋራ በአየር ውስጥ እየበረረች 15 ዓመት ስታስተምር ከኖረች በኋላ በዐረቢያ ምድር በግልጽ ታይታለች፡፡

➯ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- ሄሮድያዳ ልጅ ርጉም የሆነ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገና እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በፅኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡ እርሱም አስቀድሞ "የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ?" እያለ በመሐላ ባላት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ እርሱም ስለማሐላው የዮሐንስን አንገት እንድትቆረጥ አደረገ፡፡ በመጀመሪያም የሄሮድስ ወታደሮች ሠይፍ ይዘው የዮሐንስን አንገት ይቆርጡ ዘንድ ወደ መኅኒ ቤት ሲሄዱ ቅዱስ ዮሐንስም የሄሮድስ ጭፍሮች ሊገድሉት እንደመጡ በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስላወቀ ከጨለማው ቤት ውስጥ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ እንደሚመቻቸው አድርጎ ጠበቃቸው፡፡

➯የንጉሡም ጭፍሮች የመጥምቁን ራስ በወጪት አድርገው ለንጉሣቸው ሄሮድስ ሰጡት፡፡ ሄሮድስም ለሄሮድያዳ ልጅ ሰጣት፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ ግን በወጪት ላይ ሆና ሕዝቦቹና የመንግሥቱ ታላላቅ ሰዎች እየሰሟት በየመኳንንቱ ፊት ንጉሥ ሄሮድስን "የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት አይገባህም" እያለች መጀመሪያ ትዘልፈው እንደነበረው ሁሉ አሁንም ዘለፈችው፡፡ መዓዛዋም እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነበር፣ ዐይኖቹም እንደፀሐይ ያበሩ ነበር፡፡

➯የሄሮድያዳም ልጅ የመጥምቁን ራስ ወስዳ ለእናቷ ልትሰጣት ስትል ዐይኖቹ እንደፀሐይ ሲያበሩ ብታየው "ንጉሡን አትፈራውምን?" በማለት ተቆጣች፡፡ በመቀጠልም "እነዚህን ዐይኖቹን በወስፌ እያወጣሁ እጥላቸዋለሁ፣ ምላሱንም ደግመኛ እንዳይገሥጽ ቆርጨ እጥላቸዋለሁ" በማለት ፊቱን በጥፊ ለመምታት እጇን ስታነሣ ያንጊዜ የዮሐንስ ራስ ክንፍ አውጥታ በረረች፡፡ በአየር ላይ ሳለችም ዳግመኛ "የተረገምሽ ሄሮድያዳ የባልሽን ወንድም ሄሮድስን ማግባት አይገባሽም፣ ቀድሞ የምዘልፍሽ አሁንም የምዘልፍሽ እኔ ነኝ" እያለች የዮሐንስ ራስ የቤቱን ጣሪያ ሰንጥቃ እንደንሥር በአየር በራ ሄደች፡፡

➯ከዚህም በኋላ ለጥፊ የዘረጋቻቸው የሄሮድያዳ እጆቿ ከትከሻዋ እየተቆረጡ መሬት ላይ ወደቁ፤ እውነቷንም  መሬት አፏን ከፍታ ዋጠቻት፡፡ ዘፋኟ ልጇም አብዳ የቤተ መንግሥቱን ዕቃ ሁሉ መሰባበር ጀመረች፡፡ የንጉሡ አንዱ ጭፍራም የሄሮድያዳን በእሳት እንደተለበለበ የግንድ እሳት የመሰለና የተቆረጠ እጇን አምጥቶ ለሄድሮስ ሰጠውና የሆነውን ነገረው፡፡ ንጉሡም ነገሩ እውነት መሆኑን ሄዶ ባየ ጊዜ በሀፍረት እጅግ ተሸማቀቀ፡፡ ዘፍና በማስደሰት የዮሐንስን ራስ እንዲያስቆርጠው ያደረገችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅም አብዳ በቤተ መንግሥቱ ስትለፈልፍ አገኛት፡፡ ሄሮድስም መኳንንቶቹን "በቤተ መንግሥቴ የተደረገውን ይህን ነገር ለማንም አትንገሩ" ብሎ አማላቸው ነገር ግን ያበደችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅ ራሷ ሄዳ ሄሮድስን "የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት ፈጽሞ አይገባህም" እያለች በመኳንንቶቹ ፊት ገሠጸችው፡፡ ንጉሥ ሄሮድስም ይህን ቃል ከእርሷ በሰማ ጊዜ እጅግ ተናደደና "ቀደሞ ያልሆነ ሥራ ታሠራ በኋላ ደግሞ ምሥጢር ታወጣ ንሣ በሰይፍ ቁረጣት" ብሎ አንገቷን በሰይፍ አስቆረጣት፡፡ ሥጋዋንም ዓሣ አንበሪ ተቀብሎ ዋጣት፡፡ ሄሮድም የወንደሙን ሚስት ሲያገባ አስቀድሞ አግብቷት የነበረችውን ሚስቱን በግፍ አባሯት ነበር፡፡ እርሷም ይህንን ሄሮድስ ያደረሰባትን ግፍ ለአባቷ አርጣ ብትነግረው አባቷ ብዙ ጦር ሰብስቦ መጥቶ ምድረ ገሊላን በኃይል አፈራረሳት፡፡ የበላዩ ንጉሥ ቄሳርም የገሊላን መፍረስና መውድም ሲሰማ ምክንያቱን ቢጠይቅ ሄሮደስ ባደረገው ግፍ ምክንያት መሆኑን ነገሩት፡፡ ቄሳርም ሄሮድስን ከሥልጣኑ ሽሮ አጋዘውና በወህኒ ጣለው፡፡ ሄሮድስም በወህኒ ቤት ሳለ አብዶ ራሱን ስቶ የገዛ አካሉን እየነጨ እየበላ ቷ ብሎ ፈንድቶ ተልቶ ሸቶ እጅግ ክፉ አሟሟት ሞተ።

➯ከዚህም በኋላ ጌታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ራስ መለስ ብሎ እንዲህ በማለት ሥልጣን ሰጣት፡- "እነሆ መንፈስሽን በራስሽ ውስጥ አድርጌልሻለሁ በሰማይም የምትበሪበት እንደ ንሥር ክንፍ ሰጥቼሻለሁና እንደንስር በሰማይ እየበረርሽ በዓለም ሁሉ እየዞርሽ የሄሮድስንና የሄሮድያዳን ኃጢአት ግለጭባቸው፤ እስከ 15 ዓመት ድረስ ገቢረ ተአምራት የምታደርጊበት ኃይሌን መንፈሴን በእራስሽ ውስጥ አድርጌልሻለሁ" አላት፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ዮሐንስን "እኔም ከ3 ዓመት በኋላ ለአዳም የሰጠሁትን ተስፋ ፈጽሜ በሞቴ ወደ ሲኦል ወርጄ ነፍሳትን ከዲያብሎስ እጅ ማርኬ በ3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቼ ተነሥቼ ወደ ባሕርይ ክብሬ ተመልሼ ወደ ሰማይ አርጌ ባባቴ ቀኝ በተቀመጥኩኝ ጊዜ ከ15 ዓመት በኋላ ርጉም ሄሮድስ ካስፈጃቸው ከትንንሾቹ ሕፃናት ጋራ ትሆን ዘንድ በአባቴ ፈቃድ እራስህን ተሸክመው ወደ አባትህ ወደ ዘካርያስ ያመጧት ዘንድ እኔ መላእክትን አዛቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ግን ነፍስህን በእኔ ቀኝ ባባትህ በዘካርያስ አጠገብ አኑሬያታለሁ መንፈስህንም እስከ 15 ዓመት በእራስህ ውስጥ እንድትኖር አዝዣታለሁ፣ ሥጋህም ከነቢዩ ከኤልሳዕ ጋር እንዲቀመጥ አድርጌያለሁ" አለው፡፡

➯ከዚህም በኋላ ጌታችን እንዳዘዛት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ እራስ እንደንስር በአየር ላይ እየበረረች የምታስተምር ሆነች፡፡ በምሥራቅ በኩል ሄዳ በዐረብ አገር ውስጥ በሰማይ ላይ ስታስተምር በዚህች ዕለት ጥቅምት 30 ቀን በግልጽ ታየች፡፡ ነጋዴዎች ድምጹዋን ሰምተውና አይተዋት እጅግ ተደስተው ገንዘባቸው ሁሉ ጥለው የቅዱስ ዮሐንስን እራስ ለመያዝ ሰውነታቸውን ብዙ አደከሙ፡፡ ነገር ግን ለመያዝ አልተቻላቸውም፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰማይ "የምትያዝበት ጊዜ ስላልደረሰ ሰውነታችሁን አታድክሙ" የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣላቸው፡፡ መፈለጋቸውንም ተው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስም እራስ 15 ዓመት ስታስተምር ኖራ ሚያዝያ 15 ቀን በዐረብ ሀገር ዐረፈች፡፡

➯የታዘዙ ቅዱሳን መላእክትም መጥተው ከቅዱስ ዮሐንስ እራስ ከተባረኩ በኋላ በታላቅ ዝማሬ እያመሰገኑ የቅዱስ ዮሐንስን አንገት ወስደው በነቢዩ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ አብረው ቀበሯት፡፡ ቅድስትን ነፍሱንም እያመሰገኑ ወደ ሰማይ አሳረጓት፡፡ በዚያም በሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ወድቃ ከሰገደች በኋላ አባቷ ዘካርያስንና እናቷ ኤልሳቤጥን እጅ ነሳቻቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በ3ኛው ሰማይ ውስጥ ተቀመጠች፡፡ ጌታችን ሦስቱን ሰማየ ሰማያት ርስት ጉልት አድርጎ ሰጥቶታልና፡፡
#ቅዱስ_አባት_ባሕታዊ_አብርሃም (ስንክሳር)

➯በዚህች ቀን መኑፍ ከሚባል አገር በገድል የተጸመደ ቅዱስ አባት ባሕታዊ አብርሃም አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያመልኩ ናቸው በዚህም ዓለም ገንዘብ እጅግ ባለጸጎች ነበሩ።

➯ይህም ቅዱስ በአደገ ጊዜ የምንኵስናን ልብስ ሊለብስ ሽቶ በላዕላይ ግብጽ ወደሚገኝ ወደ ሀገረ አክሚም በመርከብ ተጭኖ ሔደ ወደ አባ ጳኵሚስም ደረሰ እርሱም የምንኲስና ልብስን አለበሰው በገድልም በመጸመድ ሥጋውን አደከመ በአባ ጳኵሚስም ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ሃያ ሦስት ዓመት ያህል በማገልገል ኖረ።

➯ከዚህም በኋላ በዋሻ ውስጥ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንዲአሰናብተው አባ ጳኵሚስን ለመነው እርሱም ፈቀደለት ዓሣ የሚያሠግሩበትን መረብ የሚሠራ ሆነ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አንድ ሰውን አመጣለት ያም ሰው መረቡን ሽጦ ምግቡን አተር ይገዛለታል የተረፈውንም ለድኆች ይሰጣል የምግቡም መጠን ሁልጊዜ ማታ ማታ አንዲት እፍኝ ከጨው ጋር በውኃ የራሰ አተር ነው።

➯እንዲህም እየተጋደለ በዚያች ዋሻ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ ልብሱም ከገዳም ሲወጣ የለበሰው ከዘመን ርዝመት የተነሣ አርጅቶ ተበጣጠሰ ሥጋውንም በጨርቅ የሚሸፍን ሆነ። በየሁለት ዓመትም ወደ መነኰሳቱ ገዳም በመውጣት ሥጋውንና ደሙን ተቀብሎ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር። በዚያችም ዋሻ መኖር በጀመረባት ዓመት ሰይጣናት ወደ ርሱ በመምጣት ምትሐት እየሠሩ ተፈታተኑት እርሱ ግን ውሻን እንደሚአበር ሰው አበረራቸው።

➯ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ያን ሕዝባዊ ሰው ልኮ የአባ ጳኵሚስን ረድእ አባ ቴዎድሮስን አስጠራው በመጣም ጊዜ ሰግዶ ሰላምታ ሰጠው እንዲጸልይለትና በጸሎቱም እንዲአስበው ለመነው። ከዚህም በኋላ ሁለቱም በአንድነት ጸለዩ በዚያንም ጊዜ አባ አብርሃም በርከክ ብሎ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ አባ ቴዎድሮስም ወደ መነኰሳቱ ላከ እነርሱም መጥተው ከሥጋው በረከትን ተቀበሉ ሥጋውንም ወሰደው ከቅዱሳን ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት።

➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

@AndEmnet #ስንክሳር ጥቅምት ፴/30 ቀን
"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_4 #ርዕስ ፦ ተአምረ ማርያም በምድረ ጋዛ ➯እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲዘዋወሩ #ጋዛ ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በጋዛ የሚኖሩ ሰዎች እጅግ ክፉዎች ነበሩ፡፡ ዮሴፍ በጋዛ የሚኖሩትን ሰዎች እንዲሀ አላቸው። "በአገራችሁ ውሃ የለምን?" የጋዛ ሰዎችም እንዲህ አሉ "በሀገራችን ውሃ የለም ውሃ የምንቀዳበት ቦታ ርቀት በእግር 27 ቀን ይወስዳል፡፡…
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_5

#ርዕስጉዞ ወደ ምድረ ግብፅ

➯እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ወደ ምድረ ግብጽ ሲጓዙ ሦስት ቀን ጫካ ውስጥ ሰነበቱ። በጣም ተራቡ፣ ተጠሙ። በበረሃ በረሀብና በውሃ ጥም እንዳይሞቱ እመቤታችን ጸለየች። ወዲያው የተሠራ ማዕድ የተዘጋጀ ምግብ መጣላቸው በልተው ጠገቡ። ከዚህ በኋላ #ኢንፍሎን ወደተባለ አገር ሄዱና #ርግባዳ ከተባለ ሰው ቤት ተቀመጡ። ብዙ ሰዎች ዕውቀት ፈልገው ወደ እመቤታችን ይመጡ ነበር። እመቤታችን ከጥበበኞች ከእስራኤል ሀገር ስለመጣች ብዙ ጥያቄዎችን ይጠይቋት ነበር። እመቤታችንም ብዙ ምሳሌ እየመሰለች ጥያቄዎቻቸውን ስትመልስላቸው እያደነቁ ይሄዱ ነበር።

➯ከጥቂት ጊዜ በኋላ የዚያች ሀገረ ገዥ ሞተ። ቤተሰቦቹ መጥተው ለእመቤታችን ነገርዋት፡፡ እመቤታችን ስትሄድ ሞቶ አገኘችው፡፡ የሚያለቀሱትን ሰዎች "ዝም በሉ አለቻቸው።" አልቃሾቹ ዝም አሉ። በቀኝ እጅዋ ይዛ "በእግዚአብሔር ስም ተነስ አለችው።" የሞተው ሀገረ ገዥ ሕያው ሆኖ ተነሣ ለልቅሶ የተሰበሰቡት ሰዎች የጣዖቶቻቸውን ስም የመጥራት አጵሎንና አርዳሚስ ሰው ተመስለው መጡ አሉ። እመቤታችንም "እናንተ የምትሏቸው ጣዖታት አይደለሁም። ከይሁዳ ምድር ተሰድጄ የመጣሁ ሰው ነኝ" ካለቻቸው በኋላ የሞተውን ሰው ማስነሣት የሚቻለው እግዚአብሔር መሆኑን እንዲያውቁና በእግዚአብሔር፡ እንዲያምኑ፡ አስተማረቻቸው።

➯በሀገራቸው ውስጥ የሚኖሩ በሽተኞችን እየፈወሰችላቸው ጥቂት ወራት ተቀመጠች። ምድራችውን ውሃ አፈለቀችላቸውና፡ "በዚህ ተፈወሱ አለቻቸው።" የታመመ ሰውም ሆነ እንስሳ አመቤታችን ባፈለቀችው ውሃ ሲታጠብ ይፈወስ ነበር፡፡

➯ከዚህ በኋላ #ራፋን ወደተባለ ሀገር ሄዱ፡፡ የራፋን ሰዎች መለከት እየነፉ ወጥተው እመቤታችንን ዮሴፍንና ሰሎሜን በድንጋይ ቀጠቀጧቸው፡፡ እነዮሴፍም ከዚያ ሀገር ወጥተው ሄዱ፡፡ በአረብ #አንፃር_ቄድሮስ ከተባለ አገር ደረሱ፡፡ በተቃራኒው የሚጾሙ የሚጸልዩ ደጋግ ሰዎችን አገኙ። ሀገሩም በጣም ደስ የሚያሰኝ ልምላሜ የተሞላበት ሀገር ነበር፡፡ #በቄድሮስ 8ወር ተቀመጡ፡፡ ዮሴፍም እመቤታችንን "ሁሉን ነገር ትተን ከዚህ ሀገር እንቀመጥ አላት።" ሀገር ለሀገር ዋሻ ለዋሻ መንከራተቱን ትተን እንረፍ ማለቱ ነው፡፡ እመቤታችንም "ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ እዚህ መቀመጥ አንችልም" አለችው ዮሴፍን፡፡

➯በዚያች ሌሊት ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ እመቤታችንን ከዚህ አገር ውጪ አላት፡፡ ከዚያች አገር ወጥተው ወደ #ደብረ_አሞር ሄዱ፡፡ የተለያየ ደዌ የያዛቸው ሰዎች ወጥተው ተቀበሏቸው። እመቤታችን ሁሉንም ፈወሰቻቸው እነዮሴፍ በደብረ አሞር በዙ ጊዜ
ተቀመጡ፡፡

➯በደብረ አሞር ወጥተው ሲሄዱ #ሌላውዳ ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በዚያም ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው አገኙ። ርኩስ መንፈስ ከያዘው 70 ዓመት አልፎታል፡፡ ሰውየው አይተኛም ሥጋውን በድንጋይ ይቦጫጭቃል በሰንሰለትም ሲታሰር ሰንሰለቱን ይሰባብራል። እመቤታችንን ባያት ጊዜ "ይቅር በይኝ" ብሎ ከእግሯ ስር ወደቀ፡፡ እመቤታችንም ርኩሱን መንፈስ "በእግዚአብሔረ ስም ውጣ አለችው፡፡" ርኩሱ መንፈስ ወጣ፡፡ ርኩሱ መንፈስ ጦጣ ይመስል ነበር፡፡ ክፉ አራዊት የርኩሳን መናፍስት መገለጫዎች ናቸው። #ዮሐንስም በእባብና በዘንዶ ዲያብሎስን ሲገልጸው እንዲህ ይላል፡፡ "«ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ»" (ራዕይ 12፥9) ርኩሱ መንፈስ የወጣለት ሰው አልለይም ብሎ እየሰገደ እመቤታችንን ተከተላት። እመቤታችንም "ወደ ዘመዶችህ ተመልሰህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ነገር ንገር" አለችው፡፡

➯እመቤታችን የተለያዩ ተአምራትን እንደምታደርግ በአካባቢው ተሰማ፡፡ አንድ ሆዱን የነፋው ሀገረ ገዢ መጥቶ "ፈውሺኝ" አላት፡፡ እመቤታችንም "በልጄ እመን ትድናለህ" አለችው፡፡ እርሱም "አምናለሁ" አለ። ከሆዱም እባብ ወጣለት፣ ከበሽታው ተፈወሰ፡፡ እነዮሴፍን ዘጠኝ ወር ያህል ከቤቱ አስቀመጣቸው፡፡

➯ከዘጠኝ ወር በኋላ ከቤቱ ወጥተው ሲሄዱ #ሌበ የሚባል ባሕር ካለበት ሀገር ደረሱ፡፡ የዚያ ሀገር ሰዎች በጅራፍ እየገረፉ አባረሯቸው፡፡ እነዮሴፍ #ቤልቤል ከሚባል ዛፍ ስር አደሩ፡፡ ነገር ግን መልአክ ወርዶ በሰረገላ ወስዶ ካሳደዷቸው ሰዎች ሀገር መካከል አስቀመጣቸው።

➯እመቤታችንም ከእንቅልፏ በነቃች ጊዜ ያደሩበት ሀገር በጅራፍ እየገረፉ ያሳደዷቸው ሰዎች ሀገር እንደሆነ አወቀች። እመቤታችንም የቅናቱ ጅራፍ ተመልሶ እንዳይመጣ ወደ እግዚአብሔር አጥብቃ ጸለየች፡፡ በጅራፍ የገረፍዋቸው ሰዎችም ከሰውነት ወደ ውሻነት ተለወጠው ውሻ ሆኑ፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ሰዎች የሚቀጣበት መሣሪያው የተለያየ ነው፡፡ አእምሮ ያለውን ሰው አእምሮ የሌለው እንስሳ ያደርገዋል፡፡ ይህ አይነት ቅጣት በጣም የሚታበዩ ሰዎች የሚቀጡበት ነው።

➯የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በትዕቢቱ ምክንያት ወደ አውሬነት ተለውጦ ቤተ መንግሥቱን ለቆ ከአራዊት ጋር ሣር እየበላ ሰባት ዓመት ኖርዋል፡፡ (ዳንኤል 4፥28-34፡፡)


#ክፍል_ስድስት_ይቀጥላል

@AndEmnet
2024/11/13 23:40:41
Back to Top
HTML Embed Code: