Telegram Web
37 አልፋ 73 መጽሐፍ የተወሰደ
👉 "በግእዝ ቀመረ ፊደል ዙሪያ በቀደሙ ሊቃውንተ ኢትዮጵያ የተጻፉ እንደ "ህላዌ ዘአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፣ ኆኅተ አእምሮ ዘሔኖክ፤ ህላዌ መለኮት፣ መጽሔተ መንፈስ ቅዱስ ..." የመሳሰሉና ሌሎችም በርካታ የግእዝ የፊደል ቀመር መጻሕፍት እና ጸሎታት ይገኛሉ፡፡
👉 ፊደላቱን ወደ ቀመረ ግእዝ ስንለውጥ የሚመጡልን ቀመራት አስደናቂ ናቸው፡፡ ይልቁኑ በነዚኽ መጻሕፍት ውስጥ እንደምንረዳው ፊደላቱ በሙሉ “መለኮታዊ ስሞች” Divine Names የያዙ ናቸው፡፡
👉 በመኾኑም በነዚኽ ፊደላት የተዋቀሩ የተቀደሱ ቃላት ታላቁን የእግዚአብሔርን ስሞች የያዙ ናቸውና በአርአያ እግዚአብሔር የተፈጠረ የሰውን አእምሮ፤ በዕውቀት ብርሃን የሚያበሩ፣ ልቡናን የሚያነቁ፣ የማስተዋል ደጅን የሚከፍቱ በከፍታ ያሉ ረቂቅ ዕውቀቶችን ከአልፋ የሚያሰጡ ተብለው በሊቃውንት ይታመንባቸዋል።
👉 ለምሳሌ ያኽል “ኆኅተ አእምሮ ዘሔኖክ” (የሔኖክ የአእምሮ ደጃፍ) የተባለው የግእዝ መጽሐፍ ሲዠምር፡- “በስመ አብ ወወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ኆኅተ አእምሮ በጸፍጸፈ ሰማይ ጽሑፍ፤ ዝንቱ ፊደል ዘአለበዎ ለሔኖክ፤ ወከብደ እንግድዓሁ ወልቡናሁ፤ ወርእየ ኀዋኅወ ሰማይ ርኅወ …” (በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ በሰማይ ሰሌዳ የተጻፈ የዕውቀት በር፡፡ ይኽ ፊደል ሔኖክን የሚያስተውል ያደረገው ነው፡፡ አእምሮውና ልቡናው ከበረ (በረታ) የሰማይ ደጃፍ ተከፍቶ አየ …) በማለት በፊደል [አ] [በ] [ገ] [ደ] … የሚዠምር ሲኾን የእነዚኽን የፊደላትን ዕውቀት አካኼዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገው ሔኖክ እንደተረዳው ይገልጣል፡፡
👉 “መጽሔተ መንፈስ ቅዱስ” የተባለው የቀመረ ፊደል የግእዝ መጽሐፍ ይኽነን የፊደል ቀመር ማወቅ ወደ ከፍተኛ የአእምሮ ልዕልና ስለማድረሱና ለእግዚአብሔር የቀረቡ ቀደምት ነቢያት ኹሉ ጠንቅቀው ይኽን ያውቁ እንደነበር ሲገልጽ፡-
✍️ “አእምር ዘንተ ወትሬኢ ኅቡአተ ወክሡታተ ዘበሰማይ ወዘበምድር ከመ ሔኖክ ወዕዝራ ወኤልያስ ወኢሳይያስ ወዳንኤል ወዳዊት ወሰሎሞን ዘከመ ኅሩያን ሰብእ”
(አንተ ሰው ጠቢብ ስትኾን ይኽንን ዕወቅ፤ እንደ ተመረጡት ሰዎች ሔኖክና ዕዝራ፤ ኤልያስና ኢሳይያስ፤ ዳንኤልና ዳዊት ሰሎሞንም በሰማይና በምድር ያሉ የተሰወሩትንም የተገለጹትንም ታያለኽ) ይላል፡፡
👉 ይኽ የቀመረ ፊደል መጽሐፍ ለአዳም ሰባተኛ ትውልድ ለሔኖክ መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደገለጸለት ሲገልጽ፡-
✍️ “ወአርአይክዎሙ ለሔኖክ ኲሎ ኅቡአተ ወእምዝ አዕረግዎ ወአብጻሕክዎ እስከ ኢዮር ወበህየ መሀርክዎ ሆህያተ ፊደል ዘኊልቈሙ ፴ወ፯፼ ወ፶፻፶ወ፪ቱ” (ለሔኖክ የተሰወሩትን ኹሉ አሳየኹት፤ ከዚኽ በኋላ እስከ ኢዮር ድረስ ከፍ አድርጌ አውጥቼው ቊጥራቸው 37 እልፍ 5,052 የፊደላት ሆህያትን አስተማርኹት) ይላል ...
💥 37 አልፋ 73 መጽሐፍን በሀሁ_መጽሐፍ_መደብር

አድራሻ  ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
               2 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ
              ስ.ቁ  0911006705/0924408461
ያገኙታል።
37 Alpha 73 (Amharic Edition) https://a.co/d/5mCC2gr
37 Alpha 73 (Amharic Edition) https://a.co/d/bGQtrBR
በውጪ ሀገር ለምትኖሩ አማዞን ላይ መጽሐፉ ፈጥኖ በማለቁ ማግኘት አልቻላችሁም ነበር። አሁን ግን አማዞን በድጋሚ ጭኖታልና ኦርደር በማድረግ ቤታችሁ ድረስ ይመጣል
"ከገበያ የጠፉ የበፊት 27 መጻሕፍቶቼን ፈልጋችሁ እንዳጣችሁ ደጋግማችሁ ለምትጽፉልኝ ወዳጆቼ እንደሚታወቀው ከ120 ሚለየን ሕዝብ አንባቢ 10 ሺ የማይሞላ በመሆኑ 5 ሺውም ከጊዜ በኋላ የሚያልቅ በመሆኑ ድጋሚ የመታተም ዕድላቸው አነስተኛ በመሆናቸው መጻሕፍቱ የሚገኙበት ላይብራሪ ብታነቡ ምክሬን እሰጣለሁ።
37 አልፋ 73 መጽሐፉም ካለቀ በኋላ መጽሐፉ በድጋሚ ላይታተም ስለሚችል በእጃችሁ ብታስገቡት ምክሬን እሰጣለሁ።
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
አንድሮሜዳ
የ2016 ዓ.ም ክረምት የአንድሮሜዳ ሥልጠና

👉  የጥበብን ድግስ ዕውቀትን ለተጠማ አእምሮ በዚህ ክረምት አዘጋጅቷል፡፡
👉 ሥልጠናው ከ7 ዓመት በላይ ለሆኑ ሁሉ የዕደሜ ገደብ ሳይኖረው ይሰጣል፡፡

የሚሰጠው ትምህርት
👉  ሥነ ምግባር (Ethics)
👉  ሥነ ፈለክ (Astronomy)
👉  ሀገራዊ ጥበቦች (Indigenous wisdom)
👉 ግእዝ (Geez)
👉 ትምህርተ ዕፅዋት (Botany)

የሥልጠናው ቦታ፡ ቦሌ ዓለም ሲኒማ
የሥልጠና ቀናት፡ ከሰኔ 28/2016 - ሐምሌ 28/2016
ሰዓት፡ ከጧቱ 2፡30-6፡30 (ከሰኞ-ዓርብ)
ምዝገባና ክፍያን በተመለከተ፡ 0900020202 / 0900030303 ይደውሉ፡፡

ወይም ከመገናኛ ወደ ሲግናል በሚወስደው መንገድ ሱመያ መስኪድ እንዳለፈ መልካይ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302
Email: [email protected]
2024/12/19 15:27:31
Back to Top
HTML Embed Code: