Telegram Web
ገራሚ ፉጡር ዕኮ ነን እኛ ሰዎች ስንባል

እንደ ምእራባውያን ለመኖር
እየቃጣን
እንደ ሶሀቦች መሞትን እንመኛለን።

♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
@ArkemMy

@ArkemMy
#ማለዳ_መልዕክት

⇛የፈለገ ሰው ይጥላህ፣የሚወድህ መልካም ሰው አንድ አታጣም።
⇛የፈለገ ሰው ይዋሽህ፣ አንድ እውነተኛ የአሏህ (ሱበሃነሁ ወተዓላ) ባሪያ አታጣም።
⇛የፈለገ ሰው ይማህ፣ ወንጀልህ ቀነሱልህ ምን ጎዳህ? ግን እዘንላቸው!።
⇛የፈለገ ሰው ከፍ ዝቅ ያድርግህ፣ አንተነትህን ያወቀ ማንነትህን የተረዳ የአሏህ (ሱበሃነሁ ወተዓላ) ባሪያ የሚገባህ ቦታ ይሰጥሃልና
⇛ አትበሳጭ! ከሁሉ ይበልጥ ከማንም በላይ ከፍ ያለው ፀጋው የበዛው ጌታ አሏህ (ሱበሃነሁ ወተዓላ) አይጥላህ የእርሱ እዝነት በአንተ ካለ ላንተ የሚገቡህ ሁሉ ከእርሱ ታገኛለህ።

⇛በአንድ አሏህ (ሱበሃነሁ ወተዓላ) የተመካ እርሱ ለሁሉም በቂው ነው።!

♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy
ስለ ዐሹራእ ፆም አንድ ልበል‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል:-1
ሙሐረም 10 — የአሹራ ቀን የፊታችን ሰኞ ነው።
( ከረመዷን ቀጥሎ ከሁሉም በላጩ ፆም ነውና የፊታችን እሁድን ማለትም (9ኛውን) እና ሰኞን (10ኛውን) እንፁም መልክቱን አስተላልፉ! )
||
በሙስሊሞች አቆጣጠር — ሙሐረም የአመቱ መጀመሪያ ወር እና አመት መቀየሪያ ነው። ዛሬ ደግሞ ሙሐረም 6, 1444 ዓ.ሂ. ላይ እንገኛለን።

ዓሹራዕ ማለት ደግሞ የሙሐረም 10ኛውን ቀን ሲሆን የዚህ ቀን ኢስላማዊ የታሪክ ክስተቶች ብሎም ትሩፋቶች ብዙ ናቸው።
*
عَنْ أَبِي قَتَادَةَ رضي الله عنه قال: قال النَّبِيَّ ﷺ "وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ، أَحْتَسِبُ عَلَى اللهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَه "وفي لفظ : وَسُئِلَ عَنْ صَوْمِ يَوْمِ عَاشُورَاءَ؟ فَقَالَ:«يُكَفِّرُ السَّنَةَ الْمَاضِيَةَ»
رواه مسلم (1162)
አቢ—ቀታዳህ አል-አንሳሪይ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ስለ አሹራዕ ፆም ተጠይቀው “ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል" ብለዋል።
ምንጭ:-📒ሶሒሁ ሙስሊም (1163)
*
በነገራችን ላይ የዐሹራን ቀን መጾም—የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር።
ነገር ግን የረመዷን ፆም በግዳጅነት ሲደነገግ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰርዟል።
✔️ ለዚህም ማስረጃው:-
عن عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا، قَالَتْ: «وَكَانَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ يَصُومُهُ، فَلَمَّا فُرِضَ رَمَضَانُ فَمَنْ شَاءَ صَامَهُ، وَمَنْ شَاءَ تَرَكَهُ» رواه مسلم (1125)
እናታችን ዐዒሻ (ረደሏሁ አንሀ) እንዲህ ይላሉ፡–
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ አሏህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ ግን የፈለገ ሰው ይፁመው ያልፈለገ ደግሞ ይተወው ነበር።
ምንጭ:-📒ሙስሊም (1125)
*
✔️ የዐሹራእ ፆም የሚፆምበት ምክንያት ምንድን ነው⁉️
ሙሐረም 10 ነብዩል-ላህ ሙሳ (ዓለይሂ - ሰላም) ከፊርዓውን ጭቆና ነፃ የወጡበት ቀን ነው።
...
ኢብኑ—ዐባስ ( ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸውና ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው⁉️ ብለው ጠየቋቸው
:
እነርሱም እንዲህ አሉ:- "ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነርሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡"
:
የአላህ መልክተኛውም (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)፡- ለሙሳ ወዳጅነት ከእናንተ ይልቅ እኛ የቀረብን ሰዎች ነን እኮ በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ"።
ምንጭ:-📒ሙስሊም (2714)
*
✔️ የዐሹራን ቀን —10ኛውን ቀን መፆም በአብዛኛው ዑለማወች ዘንድ የተወደደ ሲሆን 9ኛውን ከ10ኛው ጋር መጨመሩና አጣምሮ መፆሙ በላጭ እና ተወዳጅ ነው።

ኢንሻ አላህ ክፍል:- 2 ነገ ይቀጥላል።
:
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ቤተሰባችንን እና ሌላውንም እናስታውስበት‼️
||

--------------------
ሐምሌ 28, 2014 E.C
ሙሐረም 6,1443 H.C
August 4, 2022 G.C
||
«በየ ጊዜው የምለቃቸውን ጽሑፎች በቀላሉ ለማግኘት ይህን የቴሌግራም ቻነሌን ተቀላቀሉት»።
👇👇👇

ሼር አድርጉት።
||
ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ👇

♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
አንብበው ሲጨርሱ ሼር ይደረግ

#አስደናቂው_አባት_ለሴት_ልጁ የመከራት ታላቅ ምክር!
እህቴ ሆይ! ራስሽን በዚህ ምክር ለውጪ!

@ArkemMy

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
አንዲት ሙስሊም እህት ታብሌት ገዛች። አባቷም ታብሌቱን ባየ ጊዜ ታብሌቱን
ከገዛሽው ቡኋላ መጀመሪያ ምን አደረግሽ? አላት።
ልጅት:- በስክሪኑ ላይ ከመሰነጣጠቅና ከመሰነጣጠር የሚጠብቀውን "screen
protector" እና እንዳይሰባበር ሽፋንና ከለላ የሚሆነውን ከቨር ገዛሁለት።

@ArkemMy

አባት:- ይህን እንድታደርጊ ያስገደደሽ ሰው አለ?
ልጅት:- በፍፁም!

አባት:- አንቺ ይህን በማድረግሽ የታብሌቱን ካምፓኒ እንደናቅሽ ይሰማሻልን?
ልጅት:- በፍፁም አባቴ! እንደውም ካምፓኒው ነው ይህን እንድናደርግ ነው የሚመክረን።

አባት:- ከቨሩን ማድረግሽ ታብሌቱ ጥቅም ስላልነበረው ነውን?
ልጅት:- አይደለም! እኔ እንዳይበላሽብኝ ስክራች በዝቶበትም ዋጋው እንዳይወርድብኝ ነው።

አባት:- ከቨሩንስ በማድረግሽ የታብሌቱ ውበት ቀነሰብሽን?
ልጅት:- በኔ እይታ ውበቱ አልቀነሰም። ውበቱ ቢቀንስ እንኳ የታብሌቱን ደህንነት መጠበቅ ከውበቱ የበለጠ አሳሳቢ ነው።

አባት:- በእዝነት አይን እየተመለከታት እንዲህ አላት:- "ልጄ ሆይ! አላህም
ሙስሊም ሴቶችን ሰውነታቸውን በሂጃብ እንዲሸፍኑ አዘዛቸው።
እነሱን ለመጉዳት ሳይሆን ክብራቸውን በባለጌዎች እንዳይደፈር ለመጠበቅ ነው። ለሞባይሉ የሳሳሽለትን ያህል ለክቡር ሰውነትሽ አስቢለት። ልጄ ሆይ መልእክቴ በአግባቡ
ደርሶሻል ብዬ አስባለሁ።"

sher sher
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
ለኸይር ሰበብ እንሁን!!
📣📣📣📣📣📣📣📣

💎እንደሚታወቀው ከነገ ወዲያ የአሹራ ቀን ነው። ይህን ቀን መፃም የአንድ አመት ወንጀል ያስምራል። በተለይ ደሞ የነገውን ዘጠነኛው ቀን ከተጨመረበት ምንዳው የተነባበረ ይሆናል።

ነገር ግን የነዚህ ቀን ትልቅ ትሩፋት የማያውቁ፣ የተዘናጉና የረሱ ሰዎች ስለሚኖሩ እናት አባቶቻችን፣ ወንድም እህቶቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ የቅርብ ዘመዶቻችንም ሆነ ማንኛውም ለምናውቀው ሙስሊም ሁሉ በማስታወስ የኸይር ሰበብ እንሁን።‼️

【አመላካች የሰሪውን አጅር ያገኛል
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
Arqem[አርቀም]
Photo
ለዉብ ምሽታችን
💚💚💚

በተሳሳተ መንገድ ለረዥም ጊዜ ፣ ብዙ ርቀት ብትጓዝም
በማንኛውም ጊዜ ፣ በየትኛውም ቦታ ትክክለኛ ነው ወደምትለው መንገድ መግባት
ትችላለህ በል ዛሬውኑ የልብህን እውነት ፣ ህልምህን ተከተል……………………
------------------------------------------------

ሀገር የልጅ ብድር እንጂ ያባቶች ስጦታ አይደለም።
ንባብን አፍቅር፤ ራስህን በንባብ ቅበር…
. የመፅሃፍ ቁጥር እየጠራህ አትፎካከር… ያነበብከውን ማብላላትህን ገምግም፡፡
የምታነበውን ሞግት፤ እንዲሁ አትቀበል፤ ወይም አንብበህ ለመጨረስ አትሩጥ፡፡
ጥሩ መነሻ እንዲሆነን!!
ምሁር ወይም አንባቢ የሚባሉ ግለሰቦች በወር ምን ያህል የሚያነቡ ይመስልሃል? አስር ሀያ
ልትል ትችላለህ፤ እውነቱ ግን በወር ሁለት መጽሃፍት ቢያነቡ ነው፡፡ ባጭሩ በቀን 20 ገፅ
ማለት ነው፡፡ ያ ደግሞ ምናልባት ከአንድ ሰዓት ንባብ አይበልጥም፡፡

ስለዚህ ማስተዋልን
የተመረኮዘ የንባብ ባህል አዳብር፤
አንዳንዱ በዘጋቢ ፊልም፤ በፊቸር ሲኒማ፣ በኦዲዮ ቪዢዋል ወይም የሚዲያ መረጃዎች ላይ
ራሱን ያጥራል፤ ይህ ግን ጥቂት እንጂ ብዙ ፋይዳ አይኖረውም፡፡
በንባብና ኦዲዮ ቪዚዋል መሀል ሰፊ ልዩነት አለ፤ ንባብ ውስጥ አእምሮህ የሚቀርበውን
መረጃ እያሰላሰለ ምናቡን እንዲያሳድግ ይጥራል፤ በምታየው ምስል ግን በሰከንዶች
አይተህ ስለምታልፈው ለምናብ አቅም ጥቅም አታገኝበትም፡፡

በአንድ የቪዲዮ መረጃ
አንድን ተራራ በአንድ ሰከንድ አሳይቶህ ያልፋል፤ በመፅሃፍ ቢሆን ግን ስዕሉን ወደ
አእምሮህ ለማምጣት ታስባለህ… እናም የምናብ ስፋትህ ይዳብራል፡፡
በምንም መልኩ ማናችንም ከመፅሃፍ ንባብ ጋር የጠበቀ ቁርኝትን ልናስቀድም የተገባ ነው፤
ከሚዲያ እውቀት በላቀ ጥልቀት ራስን መጠየቅና ማስገኘት የሚያስችሉ እውቀቶች
የምንዝቀው የተመረጡ ጥራዞች ውስጥ ነው፡፡ ምርጥ መጽሃፍትን እንዴት እንምረጥ?
የሚለውንና እንዴት የንባብ አቅማችንን እናሳድግ ስለሚለው ቀስ በቀስ የምለው ይኖራል፤

((( ቡርሃን አዲስ )))

------------------------------------------------

ሸጊቲ ምሽት!!!
የናፍቆት ደብዳቤ
<unknown>
በ መብሩክ
@ArkemMy
ምኞት ...
(ፉአድ ሙና)
.
ለይሉ ጁሙዓ ነው ....
አንቺ አለሽ ከጎኔ፣
በአንድ እየመጠጥን
የሰለዋት መቅኔ።

ከከንፈርሽ ሲዘንብ
የአዝካር ማር ፈሰስ፣
በሲራ ሳብሰው
የናፍቆትሽ ሲደርስ፣
በለይል ሰላት ወግ
ሲባረክ ድግሱ፣
በዱዓ ሲለመጥ
ዱንያ ትርምስምሱ፣
ይታየኛል ቤቴ
በዲን ኑር ሲያበራ፣
ኢማን ሞልቶ ሲፈስ
ቁርዓኑ ሲቀራ።

እንዳትቀሰቅሱኝ .... እንዳትቀሰቀሱኝ ..... እንዳትቀሰቅሱኝ

ቲሽ ቀሰቀሱኝ!!

ባዶ ቤት
ባዶ አልጋ፣
ኢማን ያልሞላበት፣
በሀላል ያልረጋ።

ብትመጪ ምናለ?

ያረብ ኢኒ ፈቂር!!
.
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
#_አንተም_አዲስ_ነህ
አዲስ ነገር ቦታውን ይይዝ ዘንድ አሮጌውና የቀድሞው ነገር ቦታ መልቀቅ ይኖርበታል። አሮጌው ጊዜ ስፍራውን ሲለቅ በአዲስ ይተካል የቀድሞው ማንነትም ሲሻርና ሲተው ብቻ የተሻለው ማንነት ይከሰታል። ያልታሰበ ስኬትና ከፍታ ኬትም ሊመጣ አይችልም። ከዚህ ቀደም ብዙ ሃሳቦች በውስጥህ ተመላልሰው ይሆናል፣ መሆን የምትፈልገውን ሰው እንዳትሆን ፍረሃት አስሮህ ስጋትም ጋርዶህ ይሆናል፣ ላይ ታች በማለትም ብዙ ለፍተህ ይሆናል። አዲስና ልዩ ባልከው ጊዜም ሃሳብህን፣ ምኞትህን፣ ህልምህን መኖር ትጀምራለህ።

በትልቁ ለማሰብ፣ የተሻለውን ለመምረጥ፣ የተሻለ ቦታም ለመገኘት ግዴታ የተፈጥሮን የጊዜ ኡደትና ለውጥ መጠበቅ አይኖርብንም። ስላለን የጊዜን ሽግግር፣ የአመታትን ልውውጥ እናያለን። ከእይታችን ባሻገር ግን የለውጡ ተሳታፊ፣ የሽግግሩም ተካፋይ መሆን ይኖርብናል። ከንግርቱና ከትረካው በላይ በአዲስ ዘመን ተነሳሽነት ሙሉውን አመት በደስታና በፍቅር ማሳለፍ፣ ነገ በሚያረጀው የዛሬ አዲስ አመት የማያረጅ ዘላቂ የህይወት መሰረት ማስቀመጥ፣ የህይወት ስንቅም መሰነቅ የተሻለው አስደሳች ምርጫ ነው።

አንተም አዲስ ነህ በዘመን ከፍታ ከፍ የምትል፣ በአዲስ ተፈጥሮአዊ መስተጋብር የምትደምቅ፣ የለውጥ ወዳጅ፣ እድገትን ፈላጊ ልዩነትን የምትፈጥር ብርቱ ሰው ነህ። ሃሳብህ አዲስ ነው፤ ምልከታህ፣ እይታህ አዲስ ነው። በጊዜያት መታደስ ውስጥ እራስህን አድስ፤ በዘመን ልውውጥ እራስህን ለውጥ፣ በዘመን ሽግግር ችግሮችህን፣ ፈተናዎችህን ጥለህ ተሻገር። ዘመን ብቻውን አይታደስምና በታደሰና በተሻለ ስብዕና ተቀበለው። ደስታን ተሞላበት፣ ሃሴትን አድርግበት፣ በፍካት በድምቀት ጎልተህ ታይበት።

መልካምነትን ከስኬት፣ ከፍታን ከደስታ የሚያስተሳስር የድንቅ አድራጊነታችን ማሳያ የሚሆን ፣ የተረጋጋና ሰላማዊ አዲስ አመት ይሁንልን

♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
@ArkemMy
#ፈጅርን አለመስገድ ያለው አደጋ! እና ከዚህ አደጋ ለመዳን መጠቀም ያለባቹ መፍትሄዎች!

1) የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት
መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!!
[ቡኻሪና ሙስሊም]

2) የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን መፀዳጃ አትሁን፡፡ በአንድ ወቅት ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው ተወራ፡፡ ይህኔ እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው!” አሉ፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 644]

3) የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ የሸይጣን ወጥመድ ሲሳይ ትሆናለህ፡፡ ቀንህን ሙሉ ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ ነፍስ ይዞ እንደሚያነጋና ስንፍና እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

4) ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ
እለተ ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተላለፈው አንድ ሰው
ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን
ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ
እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም እንደ መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡ ቂያማ እስከሚቆም ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ መልኩ የሚሰቃየውን ሰውየ ምንነት ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡

ወንድም እህቶች ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጉ፡፡ ወቅቱን ጠብቃቹ እንድትሰግድ የሚያግዛቹሁን ብልሃትም ተጠቀሙ!

1) በጊዜ ተኛ! የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከዒሻ በፊት እንቅልፍ፣ (ከዒሻ) ቡኋላ ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

2) ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር
ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ
የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ
ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡

3) ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ
ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ
ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለአላርም
እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለእውነት ከባድ
የሞራል ልሽቀት ነው፡ችዋ
4) ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት
ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ
ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡

5) በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ ሸይጣን እና ነፍስያ ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡ መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን አደጋ ላፍታ አስብ፡፡ ብትነሳ 50 ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ ትርፍ የሆነችዋ የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ ፀጋ ሁሉ በላጭ እንደሆነች እራስህን አስታውስ!

6) በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር
ካለህም እሰየው! አልሀምዱሊላ ነው

ይህን መልእክት ለእህት ወንድሞች በማስተላለፍ ከዚህ አደጋ ይታደጎቸው!
እደተለመደው አሁኑም በከይር ስራ እንሽቀዳደም

♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
የትኛው ይበልጥ ይደንቃቹሃል 🤔 ?

1⃣ የረሱልን ደም ድፋ ተብሎ ደሙን ጭልጥ አርጎ የጠጣውን ሶሀባ ፍቅር? 🥺

2⃣ ወይስ ሀቢቡና ለቀናት ሲለዩት ያማረ ገፅታው እና ሰውነቱ ከስቶ የጠበቃቸው ሶሀባ ፍቅር? 😍

3⃣ ነው ወይስ ሀቢቢ ከሞቱ በኋላ በህልማቸው አይቷቸው ከመጣ በኋላ አዛን ማውጣት ያቃተው ናፍቆት? 🥰

4⃣ አሊያም ደሞ እንደሞቱ ሲያረዱት ህልፈታቸውን በጉልበት ላለማመን ሰይፍ እመዛለሁ ያሉት ጥልቅ ፍቅር? 😭

5⃣ በጦር አውድማ ከቤተሰቧ ህልፈት ባሻገር የነቢ መኖር ያስደሰታትስ ቢሆን ታሪኳ የወርቅ ብእር እንጂ ሌላ አያሻውም መለክ እንጂ ሰው አይፅፈውም የተባለላት? ❤️
.

♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
ቀን 2 ሳላወራሽ ...
(ፉአድ ሙና)
.
ሲያፈቅሩ ስቄያለሁ፣ ባለማወቅ ወኔ፣
ይኸው ፍቅርሽ ቀጣኝ፣ አወይ መጥኔ ለኔ፣
ምናለ ባልሳቅኩኝ?
ኧረ እንኳንም ሳቅኩኝ!!!

ናፍቆትሽ ጀመረኝ ...

ትዝ አሉኝ ጣቶችሽ
ውብ ከንፈሮችሽን ‘ምትሸፍኝባቸው፣
እንደው ስለፍቅሬ
ሀራም¹ ይሆናል ወይ አንዴ ብነካቸው?

ትዝ አሉኝ ጉንጮችሽ
ልክ እንደ መንደሪን፣ ግመጡኝ የሚሉ፣
ሳስቅሽ ሳስቅሽ
ስትሽኮረመሚ፣ በደም የሚሞሉ፣

ትዝ አሉኝ ጉንጮችሽ
ምናል ብገምጣቸው፣ ምናል ብነክሳቸው?
ሀራም ይሆናል ወይ?
በቡርቱካን ኒያ²፣ ለሚዳብሳቸው?

ናፈቅሽኝ አለሜ

ተመኘሁ ባቀፍኩሽ፣
ትንፋሽሽ ቢገርፈኝ፣ በተኛሽ በእቅፌ፣
እንጃልኝ እንጃልኝ፣
ያንተ ነኝ ካላልሽኝ አልተኛም አርፌ።

ትዝ አሉኝ አይኖችሽ
መሬት መሬቱ ላይ የሚንከራተቱት፣
በምን ከራማ³ ነው፣
አይኔን ገረፍ አ‘ርገው፣ ልቤን የሚያዩት??
ምንድነሽ አንቺዬ?

ጌታዬ በሰማይ
ለደጋግ ባሮቹ፣ አልቆ ያበጀው፣
እንዳትዋሺኝ ውዴ
ሁረል ዐይን⁴ ምንድነው?
ምድር ተልከሽ ነው?

አንቺን በዱንያ
ጀባ የተባለ እድለኛ ገዳም፣
ሁረል ዐይን ቢሉት
ቅንጣት ታክል ጉጉት ከልቡ አይገባም።
ምን ጉድነሽ በአላህ?

ናፍቀሽኛል በጣም

ከካፌው ተቀምጠን
የቆራረጥሽው ሶፍት ፣ አስቀናኝ በብዙ፣
እንዴት ቢታደል ነው፣
ባንቺ መነካቱ፣ በእጆችሽ መያዙ?
አጅነቢ⁵ ቢሆንስ???

ትዝ አለኝ ስትስቂ

ሲበራ አለሙ፣ ስትሆኚ ጨረቃ፣
ትፈካለች  ምድር፣ በውበትሽ ደምቃ፣
ራሷ ምድር እንኳን፣ ለራሷ አትበቃ።

እየናፈቅሽኝ ነው

ርቦኛል ድምፅሽ፣ የጆሮዬ ሩቃ⁶፣
አንቺን ሳደምጥ ነው
ከግራጫ አለሜ በርግጌ ‘ምነቃ።

ናፍቀሽኛል ውዴ!

ሀያ ቀን እኮ ብዙ ነው!!

ያረብ ኢኒ ፈቂር!!

***
አገባባዊ ፍቺ
¹ ሀራም: – በእስልምና አስተምህሮ የተከለከለ
² ኒያ: – ድርጊተ–አላማ፣ ሀሳብ
³ ከራማ – ከፈጣሪ የተሰጠ ልዩ ፈቃድ
⁴ ሁረል ዐይን – ለጀነት ሰዎች የተዘጋጁ ውብ እንስቶች
⁵ አጅነቢ – ለማግባት የማይከለከል፣ ባዳ
⁶ ሩቃ – መንፈሳዊ ህክምና

♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
ቀን 3 ሳላወራሽ ....
(ፉአድ ሙና)
.
አንቺን የማያውቁ
ጊዜው ተለወጠ፣ አሉኝ ዳግም ነጋ፣
ምንም ብርሀን የለ
እንደጨለመ ነው፣ እስካሁን እኔ ጋ!

አንቺ ነሽ ብርሀኔ ...

አንቺ ነሽ ብርሀኔ
በፊትሽ ፀዳል ነው፣ ወቅቴን የምቆጥረው፣
አይኔን ስትሞዪ
ስትስቂ ስትስቂ፣ ይኸው ነጋ ‘ምለው።

ልቤን ይወጋኛል ....

ልቤን ይቀስፈኛል
ደምኗል አየሩ፣ ጠቋቁሯል ሰማዩ፣
ውስጤ አይረጋጋም
ከርታታ አይኖቼ፣ ፊትሽን ካላዩ።

አመመኝ በጠና ....

ከንፈርሽ ያውና
ዚክር¹ አለስልሶት፣ ተቀብቶ ሙራጃ²፣
አንድዜ ብገምጠው
እስከዘላለሙ፣ መራቤንም እንጃ።

ቅሪልኝ³ ህመሜ
ልስማሽ ስትሞጥዪ⁴፣ እንዳይጠፋሽ ሂፍዙ⁵፣
ብጮህም አልፈራም
ሀጢዓት አይባልም፣ ሰው ባንቺ መያዙ!!
ቅሪልኝ ግድየለም!!

ተራብኩሽ አለሜ ....

ተራብኩሽ በፀና፣
ጆሮዬ አኮረፈኝ፣ አለኝ ድምጿን አምጣ፣
አንደበቴ ከዳኝ፣
በወሬዬ መሀል፣ ስምሽን እያወጣ!!
አወይ የኔ ጣጣ!!

ናፍቀሽኛል እኮ ....

ናፍቀሽኛል በጣም
የሀፍረትሽ አስኳል፣ ተስሏል ከፊቴ፣
ያ ረብ እያልኩኝ ነው
ታፋሽ ላይ እንድሞት፣ ቤትሽ ሆኖ ቤቴ።

ተዪ ግን ራሪ ....

ሲሰቃይ ለኖረ ፣ ልቡን ‘ሚሞላ አጥቶ፣
ትናንት ለሌለው፣ የኔ አይነት ማቶ፣
ራሪ አለሜ፣ ጀግና አትባዪም፣ በፍቅርሽ ሰው ሞቶ።

ግን አንቺስ እንዴት ነሽ?

ናፍቄሻለሁኝ?
ትዝ ብዬሻለሁ፣ ትንሽ እንኳን ለአፍታ?
ወይስ ብቅ አላልኩም፣
በአዕምሮሽ መሀል፣ ከቶም ለብልጭታ?
ቲሽ! ምኔ ይናፈቃል?
እኔ አንቺን አይደለሁ!!

ናፍቆት ሲያም!!

አመመኝ መናፈቅ
የወትሮው ታታሪ፣ አቃተኝ መነሳት፣
አንቺን ብቻ ሳስብ፣
የዝሁርን አዛን⁶፣ ደረስኩ እስከመርሳት።
አልፎኛል ጀመዓ⁷
ጣትሽን አውሺኝ፣ ስቲግፋር⁸ ላ‘ርግበት፣
ባንቺ ያረፈደ፣
ባንቺ ጣት ብቻ ነው፣ መቅቡል⁹ ‘ሚሆንለት።
አስነኪኝ ግድየለም!!

ጨረቃዬ ....

ናፍቀሽኛል
ናፍቆት ራሱ፣ እስኪያየኝ ሀዘን ለብሶ፣
እስኪል ድረስ፣
አላየሁም ያንተን ህመም፣ ሌላው ቀምሶ።

ናፍቀሽኛል ውዴ!!!

20 ቀን እኮ ብዙ ነው!!

ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!!

***
አገባባዊ ፍቺ
¹ ዚክር: – አምላክን ማወደስ
² ሙራጃ: – ቁርዓንን በቃል ሽምድዶ መለማመድ
³ ቅሪልኝ: – ቁርዓን አንብቢልኝ
⁴ ስትሞጥዪ: — ቁርዓን በቃል ስትለማመጂ
⁵ ሂፍዙ: – የተሸመደደው ቁርዓን
⁶ የዝሁር አዛን : – በቀን አካፋይ ላይ የሚሰገደው ሰላት ጥሪ
⁷ ጀመዓ: – ለስግደት መሰብሰብ
⁸ ስቲግፋር: – ምህረትን መለመን
⁹ መቅቡል: – ተቀባይነት የሚያገኘው
.

♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
Audio
ስለምወድሽ ነው
በፉአድ ሙና

@Fuadmu
Forwarded from Arqem[አርቀም]
FUAD MUNA keteweshegn behuala
<unknown>
የኔን ግጥም በኔዉ ድምፅ
ለናፍቆትህ ክብደት ይኑረዉ አይኑረዉ አላዉቅም😔😔😔 ግን.......🥺🥺
አንቱን በናፈኩ ቁጥር ልቤ ተራራ የተሸከመ ያክል ይሰማኛል🥺🥺🥺

ያ ሀቢቢ ያ ረሱለላህ s.a.w 🤗

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
   
@ArkemMy
     
                     @ArkemMy
የስንብት እንባዬ ሳይደርቅ
እንደዘበት ከጎኔ ስትርቅ
መጓዝህን ችዬ ሳልቀበል
መዓዛህ ያውደኛል: ዳግም መጣህ መሰል
****
በመምጣትህ ደስ ብሎናል
ተዘጋጅተን ጠብቀናል
አህለን ቢከ ያ ረመዳን
ኸይሩ ሹሁር ኸይሩ ዘማን

ረመዳን ሙባረክ

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
   
@ArkemMy
     
                    
جدو جہد کا راستہ ہی راہِ وفا ہے
یہ راہِ وفا میرے پیمبر کی عطا  ہے

لوگوں کے اعتراض کو خاطر نہیں لاتا
لڑنے کا  مجھے حکم تو آقا سے مِلا ہے

حکّام حق قبول کریں کیسے کہ اُن کے
غیروں کی غلامی کا نشہ سر پہ چڑھا ہے

اسلام کی عظمت پہ کوئی آنچ نہ آئے
اسلام کی عظمت پہ میری جان فدا ہے

رحمان کی نظروں میں ولایت کا مستحق
شیطان کے لشکر کے مقابل جو کھڑا ہے

بے کار دوستوں سے بھلا کیسے دل لگے
جو لوگ جانتے ہیں محاذوں پہ مزا ہے

مجھ کو بھی ماورائے عدالت نہ مار دیں
اسلام کے دشمن سے مجھے بغض ہوا ہے

یاربِ ذُوالجلال اُسے کامیاب کر
جس نے بھی دل میں غلبہِ اسلام رکھا ہے

اسلام پہ دنیا کو جو ترجیح نہیں دیتے
ہدہد انہیں سلطانِ مدینہ کی دعا ہے

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
   
@ArkemMy
     
                    
2025/03/09 14:59:49
Back to Top
HTML Embed Code: