የጌዲዮን ሙላቱ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ
በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ቀደምት ተገልጋይ የነበረው የጌዲዮን ሙላቱ ስርዓተ ቀብር መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ፊት ለፊት በሚገኘው አያት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
በስርዓት ቀብሩ ላይ የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ እንዲሁም የማዕከሉ አረጋውያንና ወደጆቹ መገኘታቸውን የማዕከሉ መረጃ ያመላክታል።
ጌዲዮን በበርካታ ሆስፒታሎች የልብ ሕክምና ሲደረግለት የነበረ ሲሆን፥ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በድንገተኛ ሕክምና ክፍል ተኝቶ ልዩ ክትትል እየተደረገለት በትናንትናው ዕለት ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በተወለደ በ37 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የሆሳዕና በዓል በመላው ኢትዮጵያ ተከበረ
የሆሳዕና በዓል በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተከብሯል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ የዛሬው እሁድ የዐቢይ ፆም የመጨረሻው እሁድ ሲሆን የሆሳዕና በዓል የሚከበርበት ዕለት ነው።
በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በተናቀችው የአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ትህትናን ያሳየበት እንደሆነ አባቶች ያስተምራሉ።
በተመሳሳይ የሆሳዕና በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ በአዲስ አበባ ቅድስት ልደታ ማርያም ካቴድራል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል በተገኙበት በተለያዩ ስነስርዓቶች ተከናውኗል።
የሆሳዕና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ወደ እየሩሳሌም ሲያቀና ህፃናት ‘ሆሳዕና በአርያም’ በማለት ኢየሱስ ክርስቶስን መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፍልስጤማውያንን መከራ ለማሳየት በለንደን ውኃውን ወደ "ደም" የቀየሩት አክቲቪስቶች
የመብት ተሟጋቾች አሜሪካ ለእሥራኤል ጦር መሳሪያ ለመሸጥ መስማማቷን በመቃወም በለንደን የአሜሪካ ኤምባሲ ደጃፍ የሚገኝ ሰው ሰራሽ ኩሬ ላይ ቀለም በመጨመር መልኩን ወደ "ደም" መቀየራቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
ግሪንፒስ የተባለው ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅት አክቲቪስቶች ድርጊቱን የፈፀሙት የፍልስጤማውያን ደም መፍሰስ እንዲቀጥል እያደረገ ያለው መሠል ለእሥራኤል የሚደረግ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ነው በሚል እንደሆነ ተመላክቷል።
ይሁንና ድርጊቱን ተከትሎ የመብት ተሟጋች የድርጅቱን ኃላፊ ጨምሮ አምስት አክቲቪስቶች ወዲያው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዘገበው ዘጋርዲያን ነው።
በቃልኪዳን ይጥና

አድሬ ኦናና ከጨዋታ ውጪ ተደረገ
የማንቸስተር ዩናይትዱ አለቃ ሩበን አሞሪም ቡድናቸው ዛሬ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ግብ ጠባቂውን ከአሰላለፍ ውጪ እንደሚያደርጉት ታውቋል።
"ከእግር ኳስ ራቅ ብሎ እንዲረጋጋ" በሚል ምክንያት ከዛሬው ጨዋታ ውጪ እንዲሆን መደረጉም ነው የተዘገበው። ይሁን እንጂ ግብ ጠባቂው ከሊዮን ጋር በሚደረገው የመልስ ጨዋታ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል።
ከቀናት በፊት ማንቸስተር ዩናይትድ ከኦሊምፒክ ሊዮን ጋር ባደረገው ጨዋታ ሁለት ግብ የሆኑ ስህተቶችን በመፈጸሙ ምክንያት ከፍተኛ ትችት ሲደርስ በት እንደነበር አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጀርመን ሀምቡርግ በተካሄዱ ሁለት መርሃግብሮች ተሸለመ።
አየር መንገዱ “በአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ምግብ አቅርቦት አየር መንገድ” ሽልማት እና በአፍሪካ በቀዳሚነት በተረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላኖቹ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች “Cabin Concept of the Year 2025” ሽልማት አግኝቷል።
ሽልማቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ እውቅና ያጎናፀፉና በዓለም ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት የሚያጠናክሩ መሆናቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል።

መፈንቅለ መንግሥት ያደረጉት የጋቦኑ መሪ በድጋሜ በምርጫ አሸነፉ።
በፈረንጆቹ 2023 የጋቦንን መፈንቅለ መንግሥት የመሩት የጋቦኑ የጦር መሪ ብራይስ ኦሉጉዊ ንጉኤማ በአገሪቱ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በ90 በመቶ ድምጽ ማሸነፍ ችለዋል።
በመሆኑም በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩት ንጉኤማ በምርጫ የተመረጡ የጋቦን ፕሬዝዳንት ሆነዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከአልጀዚራ ጋር በነበራቸው ቆይታ "የአገሬን ክብር እመልሳለው " ሲሉ ቃል ገብተዋል።
ይሁንና ተመራጩ ፕሬዝዳንት ምርጫውን በመንግሥት ገንዘብ ደግፈዋል በሚል ትችት እያስተናገዱ ይገኛሉ።

በዩክሬን በተፈፀመ የሚሳኤል ጥቃት የሆሳዕናን በዓል የሚያከብሩትን ጨምሮ 34 ዩክሬናውያን ዜጎች ህይወት አለፈ።
በፈረንጆቹ 2025 ሩሲያ በዩክሬን ከፈፀመችው ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዜጋ የሞተበት እንደሆነም ዘገባዎች አስነብበዋል።
የዩክሬን የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት እንዳስታወቀው በከተማዋ መሃል ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች መካከል ሁለቱ ህጻናት ሲሆኑ 117 ሰዎች ቆስለዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጥቃቱ የተካሄደው በባለስቲክ ሚሳኤሎች ነው ብለዋል ።አንዱ የዩንቨርስቲ ህንጻ ሲመታ ሌላው ደግሞ በመንገድ ላይ በመፈንዳት ለዜጎች ህልፈት ምክኒያት መሆኑንም ገልጸዋል።
"ሩሲያ በትክክል እንደዚህ አይነት ሽብር ትፈልጋለች እናም ይህን ጦርነት እየጎተተች ነው" ሲሉ ዘለንስኪ ተናግረዋል።
በጽዮን ለይኩን