tgoop.com/Attaqwa3/3418
Last Update:
#ለነፍሳችን እንድረስለት🫵
🍂ሰሌን ደህና ማረፊያ አይደለም ። አካልን ምቾት የሚነሳ መሻከር እንዳለበት የታወቀ ነው ….
🍂ነብዩ ይሄው ሰሌን ላይ ይተኙ ነበር ። ሰሌኑም ጎናቸው ላይ ምልክትቱን ይጥል ነበር ።
🍂ባልደረቦቻቸው “ ለምን የተሻለን ምንጣፍ አናደርግልህም ?” ሲሏቸው
ما لي وللدنيا؟ ما أنا في الدنيا إلا كراكب
استظل تحت شجرة، ثم راح وتركها
“ እኔና ዱንያ ምንና ምንድን ነን ? እኔ እኮ ዱንያ ውስጥ ዛፍ ስር ( ለማረፍ ) እንደተጠለለ አንድ ( መንገደኛ ) ጋላቢ ነኝ .. ከዚያም ሄደ ተዋትም ….
🍂አንዳንዴ ቤታቸው ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ ይጠፋ ነበር … በርግጥ ነው አንዳንዴ በርከት ያለ ነገር የነብዩ እጅ ውስጥ ይገባ ነበር ። ነገር ግን እጃቸው ውስጥ የገባውን ሪዝቅ በአላህ መንገድ ላይ ያከፋፍሉት ነበር ….
🍂የነብዩ ባልደረቦች የሚለበስ በማጣት ተፈትነዋል ፣ ረሃብን አብዝተው አስተናግደዋል … ግባቸው የአላህን ውዴታ ማግኘት ነበርና ታገሱ ፣ ፈተናውን በአግባቡ ተወጡ … ግን ከነ ችግራቸው የደስታን ህይወት ገፍተዋል …
#የኛ ነገርማ..
🍂ትልማችን አለማዊ ሆኗል ! ህልማችን የዱንያው ሸቀጥ ብቻ ሆኖ አኺራን ዘንግተናል … ወጋችን ባንክ ነው .. ሚዛናችን ሃብትና ዘር ነው - አላህ ያዘነት ሲቀር ጠፍተናል እየጠፋን ነው ።
🍂ለነፍሳችን እንዘን ፣ ወደ አላህ መንገድ እንመለስ …
✍አላህ ይመልሰን !!
Share
👇
https://www.tgoop.com/Attaqwa3
BY ERGAA DIINAL ISLAAM!!

Share with your friend now:
tgoop.com/Attaqwa3/3418