Telegram Web
#ኖላዊ ወበግዕ#(እረኛም በግም)

#ትጉህ #እረኛችን #አማኑኤል ከድንግል #ማርያም ተወልዶ በበረት ተኛ።ቅዱስ ዳዊት “እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም።”(መዝ 121፥4) ሰው ሆኖ በሕፃናት ልማድ በበረት ውስጥ ተኛ።(ሉቃ 2:7)

#እረኛ ሲሆን በግ ፣ በግ ሲሆን እረኛ ነው።መልአኩም በጎቹን (ምዕመናንን) ተግቶ የሚጠብቅ የጌታን ልደት ያበሠረው መንጎቻቸውን ተግተው ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች ነው።በእረኛነቱ ይጠብቀናል ፤ በበግነቱም በመስቀል ላይ ተሠውቶልናል (ዮሐ 1:29)።

#የጌታችን እረኛነት ግን ልዩ ነው።እረኛ በጎቹን አስብቶ ኋላ ይበላቸዋል ወይም ሽጧቸው ጥቅም ያገኛል።ይህ እረኛችን ግን ስለ ራሱ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”
(ዮሐ 10፥11) ሲል ተናግሯል።

#እርሱ ከሚገኝባት የበጎች በረት (ከቤተክርስቲያን) ያልሆኑ ሌሎች በጎችን አስመልክቶ ሩኅሩኅ እረኛ #መድኃኔዓለም እንዲህ ይላል “ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።”(ዮሐ 10፥16)

#በዓሉን አከባበራችን ሁሉ የተዘክሮተ #እግዚአብሔር ሊሆን ይገባዋል።ስንበላ እውነተኛ መብላችን ክርስቶስ መወለዱን ፤ ስንጠጣም እውነተኛ መጠጣችን አምላካችን መወለዱን ፤ ስንለብስ ስናጌጥም እውነተኛ ልብሳችን ክርሰቶስ መወለዱን ልናስብ ይገባናል።ይህ ካልሆነ ግን ጌታ ለእኛ ያደረገውን ውለታ የዘነጋን ውለተ ቢሶች እንሆናለን።
በዓሉን በዓል የሚያደርገውም የጌታን የፈቃድ ተዋርዶውንና ውለታውን እያሰብን ካመሰገንን ብቻ ነው ፤ እንጂ የምግብና መጠጡ ጉዳይ አይደለም።ይህን #የጌታችን ውለታ ከሚያረሳሱ የቴሌቪዥን መርኃግብሮችን ሁሉ ልንጠነቀቅም ይገባናል!!!

#በዓለ #ልደቱን በተዘክሮ እግዚአብሔር እንድናከብር አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ይርዳን!!!

#በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ
#ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ!!!

ልደተ #እግዚእ / 2017 ዓ.ም
#ዛሬ #እግዚአብሔር “ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።” (ዘፍ 11፥7) ብሎ ለራሱ በብዙ ቁጥር ተናግሮ ሦስትነቱን ገልጧል።ስለዚህም ቅድስት #ሥላሴ ብለን እናከብራለን።ቅድስት #ሥላሴ ማለትም ልዩ ሦስትነት ማለት ነው።

#እግዚአብሔር ያንጻል #እግዚአብሔር ያፈርሳል

#“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።”( ዘፍ1፥1) በሚለው ቃል የእግዚአብሔርን አናፂነቱን ተረዳን ፤“እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተው።"ዘፍ 11፥8) በሚለው ቃልም የእግዚአብሔር አፍራሽነቱን ዐወቅን።የሰናዖርን ግንብ የገነቡ ሰዎች ዓላማቸው እግዚአብሔርን ከንግሥና ዙፋኑ አውርዶ ለመንገሥ ነበር።

#እነዚህም ቅዱስ #ዳዊት"የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።"(መዝ 2:2-5) ብሎ የተናገረላቸው ዓይነት ሰዎች ናቸው።ዓላማቸውም #የእግዚአብሔር አምላክነቱን (ገዢነቱን) ከላያቸው ላይ መጣል ነው።ነገሩ ግን አስቂኝ ነው።ሰው የማይሆንለትን ነገር ሲሞክር ቂልነቱ ያስቃል።

#የሰው ፍላጎት በአጭሩ #እግዚአብሔርን መሆን ነው።የአዳም ምኞት ፣ የባቢሎን ሰዎች ፍላጎት፣ የአላውያን ነገሥታት ጉጉት ፣ አሁን ያለን ሰዎች ፍላጎትም አምላክ መሆን ነው።አምላክ የመሆን ፍላጎታችን ማሳያዎችም አሉ።መውሰድ #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንሰርቃለን ፤ መግደል #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንገድላለን ፤ መፍረድ #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንፈርዳለን።

#ቅድስት #ሥላሴ በዛሬው ዕለት የባቢሎንን ግንብ እንዳፈረሰ የእኛንም የትዕቢትና የኃጢአት ግንብ በቸርነቱ አፍርሶ ፤ ሰውነታችንን ለእርሱ ማደሪያነት ያንጽልን።

#ጥር #ሥላሴ / 2017 ዓ.ም
ኢዮብ ክንፈ
#ከሕግ በላይ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ንጽሕት ነሽ።ከአንቺ በቀር መርገመ አዳም ወሔዋን የቀረለት የለምና።
#ከሕግ በላይ ጌታን በድንግልና ፀንሰሽ በድንግልና ወለድሽ።ድንግልም እናትም ሆንሽ፤ያውም ወላዲተ አምላክ
#ከሕግም ውጪ መርገም ሳያገኝሽ ኃጢአት ሳይኖርብሽ ሞትን ቀመስሽ።ሞት የኃጢአት ውጤት ነውና!!!
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ #ለማርያም የዐፅብ ለኩሉ"
"ሞትስ ለሟች ይገባል ፤ #የማርያም ሞት ግን ለሁሉ ይደንቃል"

#ኃጢአትን ሳይሠሩ ሞትን መቅመስ(ሞተ ሥጋም ቢሆን በቀደመው በደል የመጣ ነውና) ፤ ደግሞ ኃጢአትን ሠርቶ #በእመቤታችን የዕረፍት ቃልኪዳን ተማምኖ ዝክር አድርጎ ከዳግም ሞት መዳን!!!
#የእግዚአብሔር ፍርዱ ምን ይደንቅ! ምን ይረቅ!

#የእመቤታችን በረከቷ ይደርብን፤ፍቅሯ አይለየን!!!

#አስተርእዮ #ማርያም / 2017 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ
የማይቀርበት የመጽሐፍ ምርቃት ኦርቶዶክሳውያ ሁላችሁ የካቲት 29 በዕለተ ቅዳሜ ከ 7:30 ጀምሮመርካቶ በሚገኘው ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ ደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ገዳም እንዳይቀሩ በረከታቸው ይድረሰንና የብጹሕ አባታችን የአቡነ ሰላማ መታሰቢያም የሚሆኑ መርሐግብራት ስለተዘጋጁ ብጹሐን ጳጳሳትና መምህራን የመጽሐፉን ይዘት እና ፍሬ ነገር ትንታኔን ይሰጡበታልና ተጋብዘዋል !!!! 🙏🙏🙏

መጽሐፉን የሚፈልግ ሰው በዚህ ሊንክ ያናግሩኝ
@Redu21Da
#ዛሬ የኪዳናት ሁሉ ፍጻሜ #ኪዳነ #ምሕረት ናት።ለቅዱሳኑ ለአዳም፣ለኖኅ፣ለመልከጼዲቅ፣ለአብር
ሃም፣ለዳዊት የተገባው ቃልኪዳን ሁሉ በእግዝእትነ ድንግል ማርያም ፍጻሜውን አገኘ።ይህ ኪዳነ እግዚአብሔር ምንድነው? ቢሉ የእግዚአብሔር ወልድ ሰው መሆን ነው።ሰው ሆኖም መዳናችንን መፈጸም ነው።

#ቅዱስ ዳዊት “ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።” መዝ 3፥8
ብሎ እንደተናገረው ሰውን ከተፈረደበት የሞት ፍርድ ማዳን የሚቻለው የፈረደበት እግዚአብሔር ነው።

#“ጽድቅንና ፍርድን ይወድዳል፤ የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች።”(መዝ 33፥5) በሚለው ቃልም ምን እግዚአብሔር ሰውን ማዳን(ጽድቅ) ቢችልም ፍርድንም ይወድዳል።ሰውን በቸርነቱ የማዳን ፈቃዱ ጽድቅ ሲሆን፤የበደለ ሰው ነውና ሊክስ የሚገባውም ሰው ነው፦ይህ ፍርድ ይባላል።
ሰው ደግሞ ራሱ የሞት ፍርድ ስላለበት ሰውን ማዳን የማይቻለው ነው።ታዲያ ምን ተሻለ? የሞት ፍርድ የሌለበት፤የባሕርይ ጉስቁልና (fallen nature)፤መርገመ አዳም መርገመ ሔዋን ያላገኘው ንጹሕና ቅዱስ ሰው ነዋ !!! ይህንን ነቢዩ ኢሳይያስ
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር።”
(ኢሳ1፥9) በማለት የገለጸው ከላይ ካነሣናቸው ጉዳዮች የቀረች ንጹሕ ዘር ታስፈልግ ነበር።ከዚህች ንጹሕ ዘር ነው ራሱ እግዚአብሔር የነሣውን ሥጋዋን ነፍሷን ተዋሕዶ የሚያድነን።

#ይህቺ አዳምና ሔዋን በበደሉት በደል ከመጣው ጣጣ ሁሉ ከአዳም ልጆች በተለየ መልኩ ያስቀራት ዘር እመቤታችን ናት።ልብ በሉ "ዘርን ባያስቀርልን" አለ እንጂ "ዘሮችን" አላለም።ዘርዪቱ አንዲት ናት።ልዩ ናት!!!አትደገምም፤አትነገርም።ይህቺ ሰዎች ሁሉ ላይ ከመጣው የሞት ዕዳ የቀረች (የተረፈች) ዘር እመቤታችን ለመሆኗ ሰማያውያን መላእክትን ምድራውያን ጻድቃንን ምስክር እናቆማለን።“እግዚአብሔር ተናግሮአልና ሰማያት ስሙ፥ ምድርም አድምጪ።”(ኢሳ 1፥2)

1.“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።”
(ዘፍ 3፥15) የሰማዮች ሰማይ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ነው።ይህቺ ከእባቡ (ከሰይጣን) ጋር ጠላትነት ውስጥ የምትገባ ዘር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።ሔዋን ከመሰለችህ ተሳስተሃል።ስለ እርሷማ ቅዱስ ኤፍሬም "ከይሲ ዲያቢሎስ ያሳታት ሔዋንን እግዚአብሔር ምጥሽንና ፃዕርሽን አበዛዋለሁ ብሎ ፈረደባት"ብሎ ተናገረ ።በምክረ ሰይጣን የተስማማ ሰው ከሰይጣን ጋር ጠላትነት ውስጥ ሊገባም አይችልም።ይህ የእመቤታችንና የሰይጣን ጠላትነት “ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ”
(ራእይ 12፥17) ተብሎ ተጽፎለታል።ዘንዶው ማንነው? ካልክ “ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።”(ራእይ 12፥9) በማለት የቀደመው እባብ (ሰይጣን) መሆኑን ቅዱስ ዮሐንስ ይነግርሃል።ሴቲቱስ?“ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።”ራእይ 12፥1
የተባላለት ድንግል ማርያም ናት።በዘፍጥረት በሴቲቱና በእባቡ ጠላትነት እንደሚደረግ እግዚአብሔር ነገረን።ቅዱስ ዮሐንስ ይህን ጠላትነት በተግባራዊ መልኩ በራእዩ አስረዳን።

2. “ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።”(መዝ 45፥4) ልዑል እግዚአብሔር ማደሪያውን ለየ፤አመሰገነ፤አከበረ።
ቅዱስ እግዚአብሔር ማደሪያው የምትሆን ድንግል ማርያምን ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ጠበቀ ፤ በመጠበቁም አከበረ።

3.“ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።”ሉቃ1፥27
ቅዱስ ገብርኤል የተላከው "ከደናግል ወደ አንዲቱ" አይደለም፤ወደ "አንዲት ድንግል" እንጂ!!!በሥጋ ደናግል የሆኑ ሴቶች ሊኖሩ ይችላሉ።እነዚህ ግን እንደ ማንኛውም የሰው ዘር መርገመ አዳም ወሔዋን ደርሶባቸዋል።እመቤታችን ግን ከዚህ ሁሉ ንጽሕት ናትና "አንዲት ድንግል" አላት።"አንዲት ድንግል" ማለትም "ብቸኛዪቱ ድንግል" ማለት ነው።ይህ ዓይነቱ ድንግልና ነው "የድንግልናሽ ምስጋናና ክብር ታላቅ ነው" ተብሎ የተመሰገነ።

4. “መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፦ ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።”(ሉቃ 1፥28)
ሰው ሁሉ ኃዘን አግኝቶት "ደስ ይበልሽ" የተባለች፤ሰው ሁሉ ከጸጋ እግዚአብሔር ጎድሎ "ጸጋ የሞላብሽ ሆይ" ተብላ የተመሰገነች፤በበደል በደሉንም ተከትሎ በደረሰብን መርገም ከእግዚአብሔር ተለይተን በነበርን ጊዜ መርገምም ሆነ በደል ካላገኛት ከእመቤታችን ጋር ጌታ እግዚአብሔር ነበር።ከሌሎች ሴቶች መካከል የተባረከች ናት እመቤታችን።መባረክ የመረገም ተቃራኒ መሆኑ ግልጥ ነው።ሌሎች ሴቶች ላይ “በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።” (ዘፍ 3፥16) የተባለው መርገም ሲደርስባቸው በእመቤታችን ግን ይህ ሁሉ የለባትም።

#በእውኑ #የእመቤታችን ሥጋ የወደቀው የአዳም ሥጋ እንዳልሆነ፤አዳም ሳይበድል የነበረው ሥጋ እንደሆነ ዐወቅን ተረዳን!!!ይህንን የገለጠልን ለእመቤታችን የምሕረት ቃል ኪዳን የሰጠ ቅዱስ እግዚአብሔር ስሙ ይክበር ይመስገን!!!

#የካቲት #ኪዳነ #ምሕረት /2017 ዓ.ም

#ኢዮብ ክንፈ
የቀዳሚት ሰንበት መርሐግብርዎን ከአሁኑ በማስተካከል አብረውን ይሁኑ !🙏🙏🙏
2025/03/01 10:36:27
Back to Top
HTML Embed Code: