". . . .ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር፤ እንዴት ይዞሻል? የገና በአል ስለደረሰ ነው መሰለኝ፡ ሸገር ድምቅ ድምቅ ምቅ ብላለች። ሸገርን እንዲያው ዝም ብዬ ሣያት አለ አይደል ያኔ እማመይ ልጅ ሆነን የገናን በአል ለማድመቅ ስትል ከገበያ ሄዳ የምታትገዛውን የጥድ ዛፍ ታስታውሰኛለች! ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር ነገሩ እንዲህ ነው። ልጅ አያለን ትዝ የሚልሽ ከሆነ አባቢ አኛን የ ሀገር ባህል ልብስ (ነጭ በነጭ) አልብሶ እንደሚያዚያ ጠሃይ ፍክት ድምቅ ሲደርገን፤ እማመይ ደግሞ የጥዱን ዛፍ በትልቅ ጣሣ ውስጥ አፈርና ድንጋይ ሞልታ ታቆመውና ፊኛውን ነፍታ ፤ አንድም ዛፉን ለማሣመር ሁለትም ከበአሉ ማግስት እኛው ከዛፉ ላይ እየበጠስን እድንበላው በገና ዛፍ መብራት አሽንቆጥቁጣው፤ ከረሜላና ቸኮሌት በክር ታንጠለጥልልን ነበር።..... ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር ግና ኑሮም ሲከፋ ጊዜም ሲነጉድ የገና ጥዱ ከነ ብልጭልጭ መብራቱ እንደነበረ ትዝ የሚልሽ ከሆነ ከረሜለዉና ቸኮሌቹ ቀርቶ በአሱ ፋንታ ወጉ እንዳይቀር በሚያብለጨልጭ ወረቀት ድንጋይ ታንጠለጥልልን ነበር። .. . . ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር ሸገርም አሁን እንደዚያ በሚያብረቀርቀው ወረቀት የተጠቀለለውን የማይበላውን ድንጋይ ያንጠለጠለች ውብ የገና ጥድ መሰለችኝ።. . .ውዴ እንዲው እየራበኝ እየሞረሞረኝ፤ አብረቅርቄ፤ ደምቄ፤ ልሞት ነው መሰለኝ፡፡ "
____ ምንተስኖት
@Bookfor
@Bookfor
____ ምንተስኖት
@Bookfor
@Bookfor