Telegram Web
የቱ ጋ ነው ጫፉ?
(በእውቀቱ ስዩም Bewketu Seyoum )

አየሩን ሲሞላው፤ ድቀት እና ሽንፈት
እንኳን ባጭር ታጥቆ፥ ዱር ጥሶ መሸፈት
ጉልበት ይፈትናል ፤ አይንን ከድኖ መክፈት ::

በውሀካታው መሀል፥ አንቀላፋን ቆመን
ሳንለፋ ደከመን፤
የት ጋ ነው ምእራፉ
የቱ ጋ ነው ጫፉ ?
-ይሄ ዳገት ዘመን ::

@Bookfor
@Bookfor
ያልተሰሙ ሙዚቃዎች ፤ ያልተገለጡ የመፅሀፍ ገፆች ፤ ከኮመዲና ጀርባ የተጣሉ ያረጁ ጋዜጦች፤ ዝም ያሉ ግን ዝምታቸው የሚከነክናቸው ሰዎች ፤ figure የሌለው ሀይማኖት፤ ብዙ ሰው የማይወዳቸው ሰዎች፤ 8 ወይም 9 reaction ያላቸው የfacebook ልጥፎች ፤ ባዶ ቤት ፤ የተሰቀለ ስዕል ለማየት ጀርባዋን የሰጠች ሴት ፤ በአንድ እጇ መፅሀፍ በሌላው ቁራሽ ሲጋራ የያዘች ፀሀፊ ሴት ፤ ይቅር ማለት ፤ ጥሩ ጥሩ የሚሸት ረጅም እና ኪሱ ባዶ የሆነ ወንድ
አዎ እነዚህም ደግሞ ውብ ናቸው ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

©newal
@Bookfor
@Bookfor
ቅዳሜን በአዲስ መጽሐፍ የመምጣት ብሥራት መጀመር መልካም ዜና ነው። ጋዜጠኛው ታምሩ ከፈለኝ Tamiru Kefelegn አዲስ መጽሐፌ መንገድ ላይ ነው ብሎናል።

@Bookfor
@Bookfor
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል-አድሀ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!🕌☪️
ብቸኝነታችንን ለማሸነፍ ብዙ ተመኝተን ነበር ነገር ግን ጥሎን ያልሄደው ብቸኝነት ራሱ ብቻ ነው።

@Bookfor
"ወንጌለ ውዴ፣ አንድን ቦታ እንዲናፍቅሽ ወይም ደግመሽ ለማየት የሚያጓጓሽ የቦታው ውበትና ድምቀት ብቻ ይመስለኝ ነበር። ግና ከቦታው ውበት በላይ የሚናፍቀው ጊዜ ነው፤ ያውም ያውም ያጊዜ መስፈርት ሣናወጣ የተዋደድንበት ዘመን።

@Bookfor
@Bookfor
"ቡሄ በዘመን ባሕር ላይ የሚያሻግረን የቂጣ ድልድይ ነው።''

(አዳም ረታ)

@Bookfor
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ።

በአሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንላችሁ በቻነላችን ስም ከልብ እንመኛለን !!

@Bookfor
@Bookfor
Am I the tree? Am I the river?

፟ዛፍን ነው ወይ የኔ ህይወት? ግንዱን ነች ወይ እቺ ነፍሴ? አዲስ ፍሬ አዲስ ቅጠል ይበቅላል ብስል ጥሬው በገላዬ። በጋ ክረምት ደግሞ ይረግፋል ቀን ጠብቆ ። ሰው ይመጣል ሰው ይሄዳል በእድሜዬ።

ዛፉን ነሽ ካልከኝ አደራ፦ ከጎኔ የበቀለ ሁሉ ሳያብብ አይክሰም ። እስኪረግፍ ፀደይ መጥቶ ይፍካ ይመርበት አብሮኝ ሲኖር። ላካፍለው ካለኝ ሁሉ። እሱ እንጂ የኔ እንግዳ እኔ መሄዱን አውቃለሁና። ሲረግፍም ቀን ጠብቆ ‘ሂድ መጣሁ’ ልበለው ። እኔስ ብሆን ከመሬት ጎን የበቀልኩ ቅርንጫፍ አይደለሁ?

ምን ቢራራቅ ፍጠረተ አለሙ ሁሉ መርገፍ በሚሉት የጋራ ሃቅ የቆመ አይደለ?

፟ወንዙን ነው ወይ ይሄ ልቤ? የጠለቀኝ የጠለቅኩት ይሰራኛል ያለድካም ።የነካሁት የታከከኝ መልኬ ይሆናል ።
ወንዝ ነሽም ካልከኝ አደራ ፦ የሰው ልጅ ንፅህና እንደውሃ ብዙ ባለመፍሰስ አይለካምና በወንዝነት ትርምስ ውስጥ ስፈስ በመንገዴ ከምገጨው ተራራ ስር የምንጭነትን ንፅህና አቅምሰኝ። የወደደኝ ሁሉ ሊጠጣኝ አይጠየፈኝ። ከመቀመስ ኋላ የምጠላ የምተፋ አታድርገኝ።

ዛፍን ነው ወይ የኔ ህይወት? ወንዙን ነው ወይ ይሄ ልቤ?

إن معي ربي سيهدين
©Newal Abubeker

@Bookfor
@Bookfor
የአስቻለው ፈጠነ አልበም ተለቀቀ!

#Ethiopia | የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) "አስቻለ" የሙዚቃ አልበም ዛሬ አርብ ጥር 3 2016 ዓ.ም በብርቧክስ ሪከርድስ በኩል ተለቋል።

እናትዋ ጎንደር እና ካሲናው ጎጃም በሚሉት ነጠላ ዜማዎቹ ተወዳጅነትን ያተረፈው አስቻለው ፈጠነ ( Aschalew Fetene Ardi ) "አስቻለ" የተሰኘውን የመጀመሪያውን አልበም ለህዝብ ደርሷል።

እመት ሸዋ እና ወሎ የሚሉትን ትራኮች ለቅምሻ ያሰማን ሲሆን ጣፋጭ ጠላ ተገፈቱ እንደሚያስታውቀው ሁሉ አልበሙም የተዋጣለት እንደሚሆን ያሳብቃል።

አስቼ ትክክለኛ መንገዱን ይዞ እየተጓዘ የሚገኝ ባለ ተሰጥኦ ህልመኛ ነው ።

"እናትዋ ጎንደር" በሚለው ስራው አስደምሞኛል።

"እነ እቴቴ ጉርሻ ኧረ እንደምን ናችሁ
ጉብ ጉብ አለብኝ አፈር ልብላላችሁ " ብሎ አንጀትን ሰፍፍፍ የሚያደርግ ስራ ሰርቷል ።

ቃላት እርሷን ለመግለፅ ለሚሽመደመዱላት ሙሽራዋ ጎንደር

"እናትዋ ጎንደር
ትንፋሽዋ ጎንደር
እህልዋ ጎንደር " እያለ በሚያስገመግም ድምፁ ተቀኝቶላታል ።

"እናትዋ ጎንደር" አዕምሮዬ ላይ ላይወርድ ተቀርፆ የተቀመጠ ድንቅ ስራ ነው።
ከግጥም እስከ ዜማ ፣ ከአጀማመር እስከ ፍፃሜው ከሲኒማቶግራፊ እስከ ክሊፕ ትወናው ጥንቅቅ ያለ ስራ ነው።

በ "ካሲናው ጎጃም"
"ድግሱን ደግሶ አይነግሩም አዋጅ
መንገደኛው ሁሉ ሰተት ነው እንጅ " እያለ

መሬት ላይ በአይኔ ያየሁትን ሃቅ በጥበቡ ከፍ አድርጎ አሳይቶኛል።

"የነካኸው ይጣፍጥልህ" ተብሎ የተመረቀው ሰው መሆን ይስማው ሰርቶት ደግሞ እንዴትስ የተዋጣለት ላይሆን ይችላል ?

እንኳን ደስ አለህ ወንድሜ አስቼ😍

ብራቮ ሶሚክ Sewmehon Yismaw

Aschalew Fetene Ardi እንኳን ደስ አለህ!

https://youtube.com/BirbauxRecord
ይሔ ስራ ንግድ አይደለም!
ይሔ ስራ ስም ሸመታ አይደለም!!
ይሔ ስራ ማንገቻም ሆነ መንጠላጠያ አይደለም!!!

💧ሀውልት እድሳት ነው!

💧አንድ ጨዋ ልጅ ለአባቱ መንፈስ ማረፍ የሚያደርገው የነብስ ይማር መታሰቢያ ነው!!

ደሞ ደሞ.....

💧ተዘግቶ የከረመን እልፍኝ ከፋፍቶ እንደማናፈስ ያለ ነገር ፤ አቧራ የለበሱ የሳሎን ጌጦችን እንደመወልወል ያለ ነገር ፤ ርጥብ ቀጤማ ጎዝዝዝጎዝዝዝዝ አድርጎ በጠጅ ሳርና አደስ ሽታ መሀል በእጣን ጢስ ስር ደጅ ደጁን በስስ ፈገግታ እንደመመልከት ያለ ነገር......!!!

እንደዚያ ያለ ነገር🖐🍻

ዋሸሁ?
© ጋሽ ናደው
Thank You Dawit Tsige!

@Bookfor
@Bookfor
አራዳ ነው። ሕይወትን በመሠለውና በወደደው መንገድ ኖሯል።
ባላገር ነው። ሀገር ፍቅሯ ልቡ ውስጥ አለ።
ዕድለኛ ነው። ባህር ማዶ እያለ ደጋግሞ የሎተሪ እጣ ያሸንፍ ነበር። ጌቾ ምን አደረክበት ስትለው " ምን አደርገዋለሁ? Dance and Music ነዋ! " ይልሀል።

ሙዚቃ ነው። ከሁሉ የሚልቀው ይሄ ነው። ጌታቸው ሙዚቃን ራሱን ነው ወይም አንዳች አይነት ሚውዚክል Note። የማይጠፋ ግን የማይተካ።

ሞተ አንልም።
ሙዚቃ አይሞትም።

@Bookfor
@Bookfor
''.....ሰው ሲታመም የምንጠይቀው ከቋጠሮ ሰሐን ጋር ነው... ሰው ሲታሰር ' እግዚአብሔር ያውጣህ ' የምንለው ከፍትፍት አገልግል ጋር ነው ....አራስ የምትጠይቀው ከፔርሙዝ አጥሚት ጋር ነው ... የክርስትና አባታችን ለፋሲካ አክፋዩን የሚጠብቀው ድፎ ዳቦ ና አረቄ ነው ...እዝንተኛ የምናስተዛዝነው ሰባት እንጀራ ከአንድ ሰሐን ወጥ ጋር ነው ...ሟች የምንሸኘው ከገንቦ ጠላና ከለምለም እንጀራ ጋር ነው ...የቅዱሳንና የመልአክታት ተራዳኢነት የሚጎበኘን በስማቸው ከዘከርን ነው...ሰዕለታችን በሬ ወይም በግ ነው ...ሰርጋችን ፣ ልደታችን፣ እርቃችን፣ ሹመታችን፣ አምልኳችን፣ የሚበላ ነገርን ሙጥኝ ያሉ ናቸው ... ...ሌላው ቀርቶ አንድ ሰው ተምሮ ሲመረቅ ይዘን የምንሄደለት ስጦታ ብዕር ወይንም መጽሐፍ አይደለም ፤ ኬክ ፣ ብርቱካን ፣ ሙዝ ...ነው ። በሽተኛ ስትጠይቅ ከብርቱካንና ከሙዝ ይልቅ መጽሐፍ መውሰድ እንደማላገጥ ይቆጠራል ። ጊዜውን ይገፋበት ዘንድ መጽሐፍ ማበርከት በሽተኛው እንዳይድን ከመመኘት እኩል ነው ። ለኛ ለኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ከባዶ ገበታችን በስተዚያ የተቀመጡ ትርፍ ነገሮች ናቸው ። መጻሕፍት የሚያስፈልጉት ገበታችን ሞልቶ ከገነፈለ በኃላ ነው ብለን በይነናል። ገበታችንም አይሞላ ፤ መጻሕፍቱም አይነሱም ። ያልተረዳነው ቢኖር ለገበታ መትረፍረፍ ዙሪያ ጥምጥም ጉዞ መጻሕፍት አቋራጭ መንገድ መሆናቸውን ነው ።እንዴት ታዲያ ማንበብ መብላትን ይቅደም ? መቼ ይሆን ከምንኮራባቸው ባህሎቻችን በላይ ማንበብ ባህላችን ሆኖ የምንታወቅበት ናየምንኮራበት?......'''''

አለማየሁ ገላጋይ

@Bookfor
@Bookfor
#life_Style_Fashion
በጥራታቸውና በአይነታቸው የተመሰከራለችው የተለያዩ የሴቶች አልባሳትን በልዩነት ይዘን ቀርበናል።
ይዘዙን ባሉበት ይዘን እንቀርባለን!

Life Style Fashion ለዘመናዊነት የተመረጠ!

Join የሚለውን በመጫን የሚፈልጉትን ይምረጡ።
https://www.tgoop.com/+ilLeD1LYh9U3NjQ0
Audio
ስለ ታላቁ የጥቁሮች መሪ የነበር ኔልሰን ማንዴላ የመሪነት ክህሎት የዳሰሰ ትረካ እንድትሰሙት ጋበዝኩ።
©መባ
@Bookfor
MARRIAGE Is Like A Shoe.

"MARRIAGE is like a shoe. When you wear oversize, be ready to drag it along through out life, and when you wear under-size be ready to feel the pains through out life".

One thing about marriage is that you don't drop your shoe or remove it at any point, no matter how painful or how stressful it is. That is why I thought it necessary to write you this letter.

Dear Singles, When you are ready to buy your own shoe please take note of these three things:

PHYSICAL APPEARANCE : Do not look for the beautiful ones, the nice ones or the cheap ones. Look for the one that is your size. Not every handsome, wealthy or intelligent guy is for you, not every beautiful woman is for you. Look for the one that is meant for you, the one that aligns with your values and belief, the one who you meet at your life's journey. It is important to know where you're going in life before you think of getting a wife.

POSITION : All sizes of shoes are not placed in the same place. There is a place for court shoes, laced up shoes, sport footwear, snickers etc. We have Children sizes, young people's sizes and the adult sizes. Know where to get your own shoe. Your size cannot be everywhere my brother, your type cannot be everywhere my sister. You cannot be a Christian/Muslim/ religious person, and be looking for a wife material at a club. Your wife or husband can't just be everywhere. Stick to your values and therein you shall find someone like you, but when your values are not defined anyone can just match you. Discover yourself and define your values.

PERCEPTION : In this kind of shoe purchasing enterprise, you are not permitted to try the shoe before you buy. This is why it is important to seek guidance and counseling, from people who have bought shoes before or are into the business of directing people to the right shoes (religious leaders and Relationship coaches). And most importantly to avoid much time wasting time, simply consult the SHOE MANUFACTURER to tell you your size (GOD ALMIGHTY ).

"You do not prepare for wedding, you prepare for marriage." Ladies these days get so motivated when they attend wedding and they will quickly want to say yes to that guy.

Wait!!! It is not just the wedding oh. The wedding is just one day. After the wedding WHAT NEXT?

Finally, it is not something you rush to the market and just pick a shoe because you like or can purchase it. Ask questions -Where is this shoe made from? (Background) -What's the size (Values) -How much (His/Her interest) -How long will it last (His/Her Character) -Who made it? (Is she/He of the same faith This is compatibility) -Will it match me? (This is whether he/she love you and will accept you the way you are)

Dear one, remember many are dragging their foot and they would hardly reach their destinies, many are feeling endless pains and wish they could pull off the shoes but no way!!! I have seen people with beautiful shoes and when they show you their foot, you will see scars.

Beloved, it is not about the physical, it is the size, you can't know the sizel from afar so come close, build a relationship first but remember 'you are not permitted to try it before you buy it'.

And for those who have purchased the wrong shoes, you can still make it your size again if you'd consult the manufacturer and let Him have His way in your marriage. God bless us all.

God bless your relationship 🙏

No copyright infringement intended.
Ceessay Phoday

@Bookfor
@Bookfor
". . . .ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር፤ እንዴት ይዞሻል? የገና በአል ስለደረሰ ነው መሰለኝ፡ ሸገር ድምቅ ድምቅ ምቅ ብላለች። ሸገርን እንዲያው ዝም ብዬ ሣያት አለ አይደል ያኔ እማመይ ልጅ ሆነን የገናን በአል ለማድመቅ ስትል ከገበያ ሄዳ የምታትገዛውን የጥድ ዛፍ ታስታውሰኛለች! ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር ነገሩ እንዲህ ነው። ልጅ አያለን ትዝ የሚልሽ ከሆነ አባቢ አኛን የ ሀገር ባህል ልብስ (ነጭ በነጭ) አልብሶ እንደሚያዚያ ጠሃይ ፍክት ድምቅ ሲደርገን፤ እማመይ ደግሞ የጥዱን ዛፍ በትልቅ ጣሣ ውስጥ አፈርና ድንጋይ ሞልታ ታቆመውና ፊኛውን ነፍታ ፤ አንድም ዛፉን ለማሣመር ሁለትም ከበአሉ ማግስት እኛው ከዛፉ ላይ እየበጠስን እድንበላው በገና ዛፍ መብራት አሽንቆጥቁጣው፤ ከረሜላና ቸኮሌት በክር ታንጠለጥልልን ነበር።..... ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር ግና ኑሮም ሲከፋ ጊዜም ሲነጉድ የገና ጥዱ ከነ ብልጭልጭ መብራቱ እንደነበረ ትዝ የሚልሽ ከሆነ ከረሜለዉና ቸኮሌቹ ቀርቶ በአሱ ፋንታ ወጉ እንዳይቀር በሚያብለጨልጭ ወረቀት ድንጋይ ታንጠለጥልልን ነበር። .. . . ወንጌለ ውዴ የልቤ ማህደር ሸገርም አሁን እንደዚያ በሚያብረቀርቀው ወረቀት የተጠቀለለውን የማይበላውን ድንጋይ ያንጠለጠለች ውብ የገና ጥድ መሰለችኝ።. . .ውዴ እንዲው እየራበኝ እየሞረሞረኝ፤ አብረቅርቄ፤ ደምቄ፤ ልሞት ነው መሰለኝ፡፡ "
____ ምንተስኖት

@Bookfor
@Bookfor
የትከሻዬ ጌጥ
የጫንቃዬ መፅኛ
የአእምሮዬ ትንፋሽ
የደሜ ትዝታ
ከየት ያደርሰኛል እግሬስ ብሄድበት
እታትረው ይዤ በትዝታ አቀበት
አካሌ ሸግዬ ነይ
ከውበትሽ ጋራ... ኦሆ
ገለጠ ሰማይ

በ'ምትወጃት እናት
ሰው ጠራኝ ሳትይ 🎧 🎼🎼🎷🎸

@Bookfor
@Bookfor
#meba
የጋብቻው ዋጋ ከሠርጉ ድግስ ይበልጣል — ብዙዎች ግን ለጭፈራው እንጂ ለህይወቱ አያስቡም

ሁሉም ሰው የተረት ህይወትን ይመኛል።
ማንም ግን ለሚመጣው መዘዝ/ውድቀት አይዘጋጅም ወይም አያስብም።

ለማሳየት፣ ለማስመሰል አይዞኝ ብለሃል።
ለቀናት የአፍ ወሬ ሆንክ።
በረራ አደረግክ፤ ብርህን በተንክ።

ግን መሠረት ጥለሃል ወይ?
የገዛኸው ጥበብን ነው — ወይስ ጊዜያዊ ጌጥና ውጫዊ ውበትን?

ብዙዎች የሚያገቡት ድግሱን/ጭፈራውን ነው፣ ሰዉን አይደለም።
እናም የእውነተኛው ዋጋ ሲመጣ ይደናገጣሉ።

ነገሩን እንየው እስኪ፦

1. ሠርጉ የአንድ ቀን ነው — ትዳሩ ግን የአርባ ዓመት

ለፎቶ አንሺዎች በጀት መድበሃል።
ለትዳር ምክርስ በጀት ይዘሃል?

አበባ መርጠሃል።
የሕይወት እሴቶችንስ መርጠሃል?

ቅፅበቱን አግብተህ — ላላሰብከው ረጅም የህይወት ዘመን እስረኛ ሆንክ።

ድግስ ለስድስት ሰዓት ነው።
ትዳር ግን ስልሳ ዓመታትን ይጠይቃል።

በዚያ ልክ ተዘጋጅ።

2. የውሸት የፍቅር ናዳ አታሎህ እድሜ ልክህን በብቸኝነት እንድትማቅቅ አትፍቀድ

አንዳንድ ሰዎች ፍፁም መስለው መታየት ላይ የተካኑ ናቸው — እስክታገባቸው ድረስ።

ያቆላምጡሃል።
በሐሰት ፍቅር ያጥለቀልቁሃል።
ይዘውህ ይዞራሉ፣ ያሳዩሃል።

እናም የደስታው ጊዜ ሲያልፍና ሲበርድስ?

በሚያምር ልብስ የተሸፈነ እንግዳ እንዳገባህ ትረዳለህ።

ጊዜያዊ መፈላለግ እውነታውን እንዳይጋርድብህ ተጠንቀቅ።

በፈተናው ጊዜ አጥናቸው — የፈገግታ ፎቷቸውን ብቻ አይደለም።

ምክንያቱም በራስህ ቤት ብቸኝነት እየተሰማህ 'ለዘላለም' መኖር በጣም ረጅም ጊዜ ነው።

3. ቤተሰብህና ጓደኞችህ የሚገፉህ ከሆነ — ቆም ብለህ አስብ!

ሁሉም ትውውቅ ከፈጣሪ የተሰጠ አይደለም።

አንዳንድ ቤተሰቦች "ሸክማቸውን ለማራገፍ" ይቸኩላሉ።

አንዳንድ ጓደኞች በሰርግህ ለመጨፈር የቋመጡ ናቸው።

አንተ ግን?

የተሳሳተ ሰዉ ሆኖ ነገር ግን ውብ ፊት ወይም አንደበት ያለው ሰው አይተህ፤ ካመንክ፣ ጥልቁ ውስጥ የምትሰምጠው አንተ ነህ።

የትውልድን መሰረት የሚጥል ራዕይ ከሌላት፣ 'ይሆናል'ን ወይም ጸሎትን ብቻ አታግባ።

ትዳር የማገገሚያ ወይም የመልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል አይደለም።
አንቺም ለማድለብና ለመራባት የታጨሽ እንስሳ አይደለሽም።

ንቃ! ባክህ/ባክሽ!

4. መውጫውም ቢሆን ቀላል አይደለም

"ካልተሳካ እፈታለሁ/እፈታታለሁ።"

እውነት?

ፍቺ ቀላል መውጫ መንገድ እንዳይመስልህ።

ልብህን አስቀድሜ ልስበርልህ፦

ፍቺ የስም ማጥፋትና የነውር ምልክት ይዞ ይመጣል።

የተፋቱ አባቶች በህብረተሰቡ ዘንድ ብዙም አይታዩም፣ ድምፃቸው አይሰማም።

ብቸኛ እናቶች ይገለላሉ፣ የህብረተሰቡን ነቀፋ ይሸከማሉ።

የተፋቱ ሰዎች ሁልጊዜ ራሳቸውን ማስረዳትና ማብራራት ይጠበቅባቸዋል።

በዚህ ላይ ልጆች ካሉበትስ?

ለዓመታት ለሚቆይ የጠበቃ ክፍያ፣ የልጅ የማሳደግ መብት ክርክር እና ለስሜት ፈንጂዎች ተዘጋጅ።

የትዳር አጋርህን ብቻ አይደለም የምታጣው።

ጊዜ፣ ገንዘብ፣ የዋህነት — አንዳንዴም ራስህን ታጣለህ።

5. የምታገባው ፀባይን ነው — መልክን አይደለም

የወገቧ ቅጥነት የሰመጠች መርከብህን አያድንም።
የቁመቱ ርዝመት አመፀኛ ልጅህን አይገስፅም።

ፀባይ ግዛትን ይገነባል።
ውበትና አንደበት ግን በአየር ላይ ግንብ ይሠራል።

በእያንዳንዱ የፈተና ሀሩር የምትቀልጥ ሻማ ካገባህ፣ በጨለማ ለመኖር ተዘጋጅ።

ምክንያቱም የሕይወት ማዕበልና ፈተና አይቀሬ ነው።

6. ሸክም የሆነን ሰው ማግባት የትውልድ አሻራህን ዋጋ ያስከፍልሃል

መጥፎ ጋብቻ፦

ህልምህን ያዘገያል።
ገንዘብህን ያሟጥጣል።
ስምህን ያጠፋል።
የእጣ ፈንታህን መንገድ ያስታል።

አንድ የተሳሳተ ፊርማ የአስር ዓመት ልፋትህን ሊያጠፋ ይችላል።

በጥንቃቄ ምረጥ።
በጤናማ አእምሮ ምረጥ።

ምክንያቱም የምትመርጠው የሠርግ ልብስ አይደለም — ሕይወት ለምትባለው አስቸጋሪ ጉዞ አብሮህ መሪ የሚሆንህን እንጂ።

7. ቅፅበቱን ሳይሆን — የጋራ ዓላማችሁን አግቡ

የምታገቡት አስተሳሰብን ነው።
ቅፅበታዊ ስሜትን አይደለም።

የምታገቡት መላ አካባቢውን፣ ስነ-ምህዳሩን ነው።
የማህበራዊ ሚዲያ ገፅን አይደለም።

ከባባድ ጥያቄዎችን ጠይቁ።
ያለፈ ታሪካቸውን መርምሩ።
አማካሪዎቻቸውንና የቅርብ ሰዎቻቸውን አጣሩ።
ታማኝነታቸውን ፈትኑ።

ምክንያቱም አሁን ያላጣራችሁት ነገር — በኋላ ዋጋ ያስከፍላችኋል፤ ታለቅሱበታላችሁ።

8. ስርዓት የሌለው ፍቅር ለመፍረስ የተዘጋጀ ስሜት ብቻ ነው

ስርዓት ልጆችን ያሳድጋል።
ስርዓት የቤት ብድር ይከፍላል።
ስርዓት ህመምን፣ ክህደትን፣ መሰልቸትንና እርጅናን ለመቋቋም ያግዛል።

የጋብቻህ መመሪያና እቅድ "ፍቅር በራሱ መላ ያበጃል" የሚል ከሆነ…

ፍቅር በእውነተኛው የህይወት ውጣ ውረድና ግፊያ ውስጥ ለመጥፋት ይዘጋጅ።

ስሜቶች ተሳፋሪዎች ናቸው።
ስርዓት ነው መኪናውን የሚነዳው።

አንዱን ያዝ — ወይም ትሰባበራለህ።

የመጨረሻ ቃል፦ እንደ ቤት ሰሪ አግቡ — እንደ ሸማች ሳይሆን

ከራዕይ ይልቅ ጊዜያዊ ስሜትን ከመረጥክ — ለጥፋትና ለህመም ተዘጋጅ።

ከመዋቅርና እቅድ ይልቅ ቅፅበታዊነትን ከመረጥክ — ለሀዘን ተዘጋጅ።

ሠርጉ ማጥመጃው ነው።
ጋብቻው ሂሳቡና ዋጋው ነው።

እናም ማንም የከፈልከውን ዋጋ አይመልስልህም።

አስተዋይ ሁን።
በእሴቶችህ ፅና።
ራስህን መገንባትህን አታቋርጥ።


@Bookfor
@Bookfor
2025/07/01 21:21:41
Back to Top
HTML Embed Code: