በደሴ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሚደረገው እርዳታ...
የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሀት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ በመሆኑን አመላክቷል።
ፅ/ቤቱ ለተፈናቃዮች እርዳታ እየቀረበ እንደሚገኝ ሪፖርት አድርጓል።
ተፈናቃዮቹ በየወረዳ እና ቀበሌ ተለይቶ የምግብ እርዳተው መሰራጨቱ ጥሩ ቢሆንም ፈጥኖ የማሰራጨት ችግር እንዳለ ተናግረዋል።
ቀጣይ በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ተፈናቃዮች ሳይጉላሉ እርዳታውን የሚያገኙበት መንገድ እንዲመቻችም ጠይቀዋል፡፡
እንደ ደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መረጃ ፥ ከሰሜን ወሎ ዞን ከ17 ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ከ90 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች በደሴ ከተማ የሚገኙ ሲሆን ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑት በ8 ትምህርት ቤቶች ጊዚያዊ መጠለያ ውስጥ ይገኛሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በማህበረሰቡ ውስጥ ተጠልለዋል።
እስካሁን ለ45 ሽህ 735 ተፈናቃዮች 6 ሺህ 814 ኩንታል ፍርኖ ዱቄትና ሩዝ መሰራጨቱን የገለፀው ፅ/ቤቱ አንዳንድ ተፈናቃዮች አላግባብ የቤተሰብ ቁጥር የመጨመርና የመረጃ ጥራት መጓደል መኖሩ ስርጭቱ እንዲጓተት አድርጎታል ብሏል።
የተፈናቃዮች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ የመጣ በመሆኑ መንግስት ከሚያደርገው እርዳታ በተጨማሪ ዓለማቀፍ ረጂ ድርጅቶች ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባም ፅ/ቤቱ ጠቁሟል።
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ ፥ ለአንድ ሰው 15 ኪሎ ግራም የሚሆን ዱቄት እና ሩዝ እየተሰራጨ ነው፤ በተጨማሪ ለእናቶችና ህፃናት አልሚ ምግብ ተሰራጭቷል ብሏል።
መረጃው የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

ጊዜው ያለፈበት እርዳታ ቀርቧል ?
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ጊዜው ያለፈበት እርዳታ እንዳልቀረበ ገለፀ።
በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው በደሴ ለሚገኙ ዜጎች ድጋፍ እየተደረገ ነው።
ተፈናቃዮቹ ከሚቀርበው እርዳታ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ የዱቄት ኬሻዎች ላይ የመጠቀሚያ ጊዚያቸው 2 ወር ያለፈበት እንዳለ ገልፀዋል።
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚሰራጩት የምግብ ቁሳቁስ ቀጥታ ከፋብሪካ የተገዙ በመሆናቸው በአንዳንድ ኬሻዎች ላይ የሚታየው በህትመት ችግር ምክንያት እንጂ መጠቀሚያ ጊዚያቸው ያለፈባቸው የምግብ ቁሳቁስ #እንዳልሆኑ ገልጿል።
የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ድጋፍ እየቀረበ ነው የሚለውም ትክክል እንዳልሆነ አሳውቋል።

ያለአንዳች ምክንያት ምርቶች ላይ በሚጨመረው ዋጋ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች እየተማረሩ ይገኛሉ።
ይህን ድርጊት የሚፈፅሙ አንዳንድ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር አብረው አንድ ላይ የማይኖሩ ይመስል በዚህ የፈተና ወቅት ዋጋ በመጨመር ዜጎች እያማረሩ ነው።
የዚህ ድርጊት ፈፃሚ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባም ዜጎች እያሳሰቡ ነው።
የተለያዩ የክልል መንግስታት ፣ የከተማ አስተዳደሮች ያለአግባብ ዋጋ እየጨመሩ ህዝቡን የሚያማርሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ እያስጠነቀቁ ነው።
ዛሬ የአርባምንጭ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በተለያዩ የእህል ምርቶችና ሸቀጦች ላይ አላስፈላጊ ዋጋ በሚጨምሩ አንዳንድ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ጀምሪያለሁ ብሏል።
ምክንያቱ ባልታወቀ መልኩ ፣ ምንም ዓይነት የምርት እጥረት በሌለበት በመሠረታዊ ሸቀጦች፣ በኢንዱስትሪ እና ግብርና ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አንዳንድ ነጋዴዎችና ድርጅቶችን በመለየት የዋጋ ማስተካከያ እንዲያደርጉ እየተደረገ መሆኑን አሳውዋል።
ትክክለኛውን የመነሻ ዋጋ በማጣራት አላስፈላጊ ዋጋ የጨመሩ ነጋዴዎች ዋጋ እንዲያስተካክሉና ቀድሞ ይሸጥ በነበረው ዋጋ ለሸማቹ ምርቶችን እንዲያቀርቡ እየተደረገ ነው ተብሏል።
ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ያልታረሙ 12 የንግድ ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
- በሩዝ፣
- ምስር፣
- ፓስታ፣
- ማካሮኒ ፣
- ጨውና የመሳሰሉ ምርቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ በመኖሩ የዋጋ ቅናሽ ተደርጎባቸዋል ተብሏል።
የግብርናና የተለያዩ ምርቶችን ያለአግባብ በመጋዘን ያከማቹ ግለሰቦች ላይ ክትትል ይደረጋል ተብሏል።
ህብረተሰቡ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ሲያጋጥሙት ጥቆማ እንዲያደርግ ፅ/ቤቱ ጥሪ አቀርቧል።

ፎቶ : የአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር የታወጀውን የሰዓት እላፊ ገደብ ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች።
የከተማው ህዝብ በየአካባቢው ተደራጅቶ ሰላሙ እንዳይደፈርስ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
እገዳው ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ህብረተሰቡ የተላለፈው መመሪያ አክብሮ ወደየቤቱ እየገባ ነው።
የባህር ዳር ከተማ ሰላም እና ህዝብ ደህንነት ጉዳዮች መምሪያ ምክትል ኃላፊ አደራ ጋሼ እንዳሉት ፥ ሰዓት ከገቡ ከተላለፈ በኃላ (ምሽት 2 ሰዓት ከተባለ በኃላ) ሰው ፣ ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ አይታዩም ብለዋል።
የከተማው ፀጥታ እንዲሁም ጥበቃ ከሚያስተባብሩ፣ ፍተሻ ከሚያደርጉ ወጣቶች፣ ከፀጥታ ኃይሎች ውጭ ሁሉም ወደቤቱ በመግባት ሰዓት እላፊውን ተቀብሎ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ማህበረሰቡ በመናበብ፣ አካባቢውን ፣ ሰፈሩን የጠበቀ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
Photo Credit : ባህር ዳር ኮሚኒኬሽን

#Afar
በአፋር ክልል በራህሌ ወረዳ ጥቃት ተፈፀመ።
የአፋር ክልል መንግስት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ' ህወሓት ' በክልሉ ኪልባቲ ረሱ በራህሌ ወረዳ በኩል ሰርጎ በመግባት ጥቃት መፈፀሙን ገለፀ።
የክልሉ መንግስት ህወሓት ፥ "በፈንቲ ረሱ በኩል ያደረገው ወረራ አልበቃ ብሎት ትናንትና ዛሬ በኪልበቲ ረሱ/ዞን በራህሌ ወረዳ በኩል ሰርጎ ለመግባት ሙከራ አድርጎ ወደ ንፁሀን አርብቶ አደር ማህበረሰብ ላይ ጦርነት ከፍቷል" ብሏል።
በትናንትናው ዕለት የህወሓት ቡድን በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ (ዞን) በራህሌ ወረዳ ዓላ ቀበሌ ዓሰ ዳ የተባለ ቦታ ላይ ጥቃት መፈፀሙን የገለፀው የአፋር ክልል "ጥቃቱን ለመመከት የአፋር ልዩ ሀይል እና ሚሊሽያ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት የያዘውን መሳሪያ አንጠባጥቦ እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጦ ነበር" ሲል አስታውሷል።
በዛሬው ዕለት በተመሳሳይ ቦታ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ ድጋሚ ወረራ በማካሄድ ወደ አርብቶ አደር ማህበረሰብ ሴቶችና ህፃናት ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ተኩስ ከፍቷል ሲል ከሷል።
የአፋር ልዩ ሀይል እና ሚሊሽ ዛሬም ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ወረራውን የመመከት ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ ሲል የአፋር ክልል መንግስት ገልጿል።
የአፋር ክልል መንግስት ፥ ' ህወሓት ' አሁንም በተለያዩ አቅጣጫዎች ትንኮሳ የማድረግ ሙከራ እያደረገ በመሆኑ ህዝቡ በአቅራቢያው ከሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመተባበር በንቃት በመጠበቅ ሰላሙን ሊያረጋግጥ ይገባል ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

አሜሪካ ዜጎቿን ከካቡል ማስወጣቷን ቀጥላለች።
የአሜሪካ ፕሬዜዳንይ ጆ ባይደን በሰጡት መግለጫ አሜሪካ እስካሁን ድረስ 13,000 ሰዎችን ከአፍጋኒስታን ማስወጣቷን፤ ይህ በታሪክ ትልቁ እንዲሁም አስቸጋሪው እንደሆነ ተናግረዋል።
ፕሬዜዳንቱ አሜሪካ እያካሄደችው ያለው ዜጎቿን በአየር የማስወጣት ዘመቻ በታሊባን እንቅፋት እየገጠመው አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል።
ይህም ከመከላከያ ኃላፊያቸው ጋር የተቃረነ ንግግር መሆኑ ጥያቄ አስነስቷል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስቲን አርብ ዕለት ለህግ አውጪዎች እንደተናገሩት ፤ አሜሪካውያን አፍጋኒስታንን ለመልቀቅ በሚሞክሩበት ወቅት በታሊባን ታጣቂዎች እንደተደበደቡ ነው ብለው ነበር።
የእረፍት ጊዜያቸውን አቋርጠው ወደ ሥራ የተመለሱት ጆ ባይደን ትላንት በሰጡት መግለጫ ፥ "ወደ አገራችሁ መመለስ የሚፈልጉ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ቤታችሁ እንመልሳችኋለን" ብለዋል።
ከአሜሪካዊያን በተጨማሪ ከ50 እስከ 65 ሺ የሚደርሱ ከአሜሪካ ጋር ሲሰሩ የነበሩ አፍጋኒስታናውያንንም ለማስወጣት ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዳለ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
ባይደን በትላንቱ መግለጫቸው ፥ ታሊባን #የአሜሪካን_ፓስፖርት የያዘ ማንኛውም ሰው ወደ አውሮፕላን ማረፊያው እንዲገባ እየፈቀደ መሆኑን ጠቅሰው የአሜሪካ ወታደሮችን ወደ ካቡል መላክ አስፈላጊ አይሆንም ብለዋል።
#ቢቢሲ በካቡል የአሜሪካ ዜጎች ወደ አውሮፕላን ማረፊያው ለመግባት እንቅፋቶች እየገጠማቸው እንደሆነ በርካታ ከካቡል የሚወጡ ዘገባዎች ያመላክታሉ ብሏል።

ዶላር እናትማለን በማለት ወንጀል ሲፈጽሙ የተገኙ የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በአዲስ አበባ የአሜሪካን ዶላርን እናትማለን በማለት የማታለል ወንጀል ሲፈጽሙ የተገኙ ሁለት የኮትዲቯር ዜጎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የደህንነትና የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።
የውጭ አገር ዜጎቹ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ፍላሚንጎ በተባለ ሥፍራ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የጋራ ግብረ ኃይሉ ገልጿል።
ዤያ ሼዬዣክ እና አው ማሪ የተባሉት ሁለቱ የኮትዲቯር ዜጎች ከአንድ ግለሰብ ብቻ 260 ሺህ ብር በመቀበል ሀሰተኛ የአሜሪካን ዶላር ሰርተው ለመሥጠት ስምምነት በማድረግ የማጭበርበር ሥራ ሲያከናውኑ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡ #ኢብኮ

#Ethiopia
ከሳዑዲ አረቢያ 378 ዜጎች ወደ አገራቸው 🇪🇹 ተመለሱ።
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራችው ለመመለስ የሚደረገው ጥረት መቀጠሉን ገልጾ በትናንትናው ዕለት 231 ሴቶች እና 147 ህጻናት በአጠቃላይ 378 ዜጎቻችን ከሪያድ፣ ሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው እንዲሚለሱ ተደርጓል ብሏል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ተገልጿል።

የኮቪድ-19 ክትባት ሲገበያዩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት በህገ ወጥ መንገድ ሲገበያዩ የነበሩ 3 ተጠርጣሪዎች ከነ ኤግዚቢቱ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ነሃሴ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ደጃች ውቤ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 9 ሰዓት ገደማ ነው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው አንድ ግለሰብ በህገ ወጥ መንገድ የኮሮና ቫይረስ ክትባት በቦርሳ ይዞ በህገ ወጥ መንገድ ለመሸጥ እየተደራደረ ስለመሆኑ ህብረተሰቡ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠቱና ፖሊስ ክትትል በማድረጉ 10 ብልቃጥ የቻይና ሲኖ ፋርም (sino pharm) እና 3 ብልቃጥ የአሜሪካ ጆን ኤንድ ጆንሰን (john and jonson) የተባሉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት መድሀኒቶችን እንዲሁም የክትባቱ መስጫ 12 መርፌዎች እና 3 የማቀዝቀዣ ቁሶችን ግብይቱ ለመፈፀም ሲስማሙ ከነበሩ 3 ተጠርታሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሏቸው ምርመራ እያደረገ ነው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ክትባቶቹ ከየት ተሰርቀው እንደወጡ ለማወቅ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
በህገ ወጥ መንገድ ለገበያ የሚቀርቡ መድሀኒቶች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ከጤና ተቋማት እና ከህጋዊ መድሃኒት መሸጫ መደብሮች ውጪ ማንኛውንም መድሃኒት ገዝቶ ባለመጠቀም ጤናውን እንዲጠብቅ እንዲሁም እንዲህ አይነት ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት እንዲቀጥል ፖሊስ አሳስቧል፡፡