Telegram Web
ደብረብርሃን የከተማ ውስጥ ትራንስፖርት

የተሻሻለው የታክሲ ትራንስፖርት ታሪፍ ከላይ የሚመለከተውን ይመስላል።

@DBU11
@DBU111
👍7
መልዕክት ከተማሪዎች ህብረት

ውድ ተማሪዎቻችን ሰሞኑን በተከሰተዉ የእንጀራ ብልሽት ይቅርታ እየጠየቅን ችግሩን ለማስተካከል ሲባል አዲስ ዱቄት ተፈጭቶ በአዲስ ተጋግሮ እንዲቀርብ ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ስለሆነ ዛሬ ምሳ ሰዓት ዳቦ እንዲሁም እራት ሰዓት ላይ አዲሱን ቡኮ ተጋግሮ /አፍለኛ/ ከ አማራጭ ዳቦ ጋር ስለሚቀርብ ችግሩ እስኪፈታ ድረስ የቀረበዉን አማራጭ በቅን ልቦና እንድንጠቀምና  ችግሩ እስኪፈታ በትዕግስት እንድትጠብቁን ስንል በትህትና እንጠይቃለን፡፡


       የደ/ብ/ዩ/ተ/ህ ጽ/ቤት

@dbu11
@dbu111
👏26👎17👍7🤔4
ይህን ፖስት ከለቀቅንበት ሰዓት ጀምሮ 18 ሰዓታት ብቻ ይቀራሉ

የመጀመሪያው (first session examinees)ሀገር አቀፍ የዩንቨርስቲ መውጫ ፈተናቸውን ለመውሰድ ነገ 2:30 AM local time exam room ይቀመጣሉ።
በነገው ዕለት የሚጀምረውን መውጫ ፈተና ሚወስዱት በተለያየ መሰናክል ውስጥ ያለፉ
ከአዲግራት ዩንቨርስቲ ህግ ትምህርት ቤት በዝውውር የዩንቨርስቲው ህግ ተማሪዎች የሆኑት ህግ ተማሪዎችን ጨምሮ በተከለሰው ስርዓተ ትምህርት አራት አመት የትምህርት ዘመን የዩንቨርስቲ ቆይታ ያላቸው 2013 ባች ተማሪዎች ናቸው።

ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲን በመቅደም ከጅማ ዩንቨርስቲ ቀጥሎ 2248 holding capacity በመያዝ የመጀመሪያው ፈተና ላይ ሚቀመጡት Accounting and finance ትምህርት ክፍልን በአንድ session ያስፈትናል።በአጠቃላይ 3516 ተማሪዎችን የሚያስፈትን ሲሆን።በ 1086 የተማሪ ብዛት ከፍተኛውን ቁጥር የሚወስደው ትምህርት ክፍል Management ነው።

daily news መልካም እና ጥሩ ውጤት ምታስመዘግቡበት ፈተና ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።



@dbu11
@dbu111
👍52👌2
#EXITEXAM #Note

ከትምህርት ሚንስቴር ቴሌግራም ገፅ ያገኘነው መረጃ 👇👇👇

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከጥር 26 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ይሰጣል።

🌀በፈተና ወቅት ከተፈታኝ ተማሪዎች ምን ይጠበቃል ?


👉🏾 ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

👉🏾 ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

👉🏾 ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

👉🏾 ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

👉🏾 ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች  መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 በድጋሚ ተፈታኞች የፈተና መግቢያ ትኬት (Exit Exam Entry Ticket) መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

NB.  ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

🌀 ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ

👉🏾 የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

👉🏾 ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

👉🏾 የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

👉🏾 በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

👉🏾 ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

👉🏾 ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

👉🏾 የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ




@dbu11
@dbu111
👍44🤬12👌1
ለተማሪዎች የማስጠንቀቂያ መልዕክት

ከሰሞኑን ለfinal እንዲሁም የexit ጥናትን ተከትሎ ሌሊት ላይ ከቤተ መፅሃፍት አምሽታችሁ  የምትወጡ ተማሪዎች ወደ ዶርም ስትገቡ አልያም ከ ዶርም ወደ ቤተ መፅሃፍት ስትሄዱ በተቻላችሁ መጠን ሁለትና  ሶስት እየሆናችሁ  አካባቢያችሁን በንቃት እየቃኛችሁ እንድትሄዱ ስንል እናሳስባለን።

👉እንደ earphones,airpod የመሳሰሉ የአካባቢ ድምፆችን ከመስማት የሚከለከክሉ ነገሮችንም ከመስማት ተቆጠቡ።

በሌላ በኩል የወንዶች ብሎክ ላይ የስርቆት ስራዎች (መስኮት ሰብሮ መግባትን ጨምሮ ለምሳሌ ብሎክ 34 ና 41 )ተበራክተዋል ።

👉ተማሪዎች በተለይም የታችኛው ወለል( Ground ) ላይ የምትገኙ ስልካችሁን በአቅራቢያችሁ እንድታደርጉ  እንዲሁም በራቹንና መስኮታችሁን ከመተኛታችሁ ፤ከመውጣታችሁ በፊት መዝጋታችሁን እንድታረጋግጡ ስንል በአፅንኦት እናሳስባለን።

👉ከዚህ በተጨማሪ ጨለማን ተገን አድርጋችሁ ወንጀል የምትሰሩ ተማሪዎች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያስጠነቀቅን ከድርጊታችሁ ለማትቆጠቡ ተማሪዎች ግን ከፍተኛ ክትትል እያደረግን እንደሆነ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።

ይህንን ተግባር የሚፈፅሙ አካላትን ያያችሁ ፣የምታውቁ ተማሪዎች  ሠላም ለሁላችንም ነውና ተጠርጣሪዎቹን ለሚመለከታቸው አካላት እንድታሳውቁ ስንል እናሳስባለን ።


የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ሰላምና ደህንነት ስራ አስፈፃሚ

@dbu11
@dbu111
👍49🤬6👌1
ለተመራቂዎች

የወጪ መጋራት መረጃ ለማሟላት 2 ጉርድ ፎቶ ይዛችሁ እንድትቀርቡ የሬጅስትራል ጽ/ቤት አስታውቋል።

@dbu11
@dbu111
🤔9👍6🤬2
ለመሃል ሜዳ ካምፓስ ለወጣው የቅጥር ማስታወቂያ የተወዳደራችሁ ውጤታችሁን ከዚህ በላይ ባሉት ምስሎች ተያይዘው ታገኛላችሁ።

@DBU11
@dbu111
👍4
👍7
2025/07/13 12:42:06
Back to Top
HTML Embed Code: