Telegram Web
#AD

     ያኪን ሜካፕ እና ጥፍር

ፕሮግራም አለቦዎት🤔?  እንግዲያውስ  ወደኛ ዘንድ ብቅ ይበሉና አምረው ተውበው ይመለሳሉ..

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
➟ Makeup 💄       ➟ Gel polish 🧫
➟ Nalis💅             ➟ Aclyric 🎀
➟ Pedicure🦶

በስራችን እጅጉን ይደሰታሉ 👌

➫For Wedding 👰
➫For Birthday 🎂
➫For Bridal 🧝‍♀️
➫ For any programs

ለግቢ ተማሪዎች ብቻ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ አድረገናል። ሳያመልጦ በእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ‼️ 

Location :-📍ደ/ብርሃን ሆስፒታል ፊት ለፊት
                  (የድሮ መናኸሪያ) ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ

ለበለጠ መረጃ    ☎️  0907445803 
                        ☎️  0902516515  ይደውሉልን
👍20😁7
‘’ለአከባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥ ማሽን ገዝቻለሁ’’ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ 


ደ/ብ/ዩ አዲስ የመውቂያ ማሽን በመግዛት ለዩኒቨርስቲውና ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል።

ዩኒቨርስቲው   በ2016/17 ዓ.ም የአዝመራ መሰብሰቢ ወቅት በዋናው ግቢና አንጎለላ በሚገኘው ቴክኖሎጅ ካምፓስ  በ27 ሄክታር መሬት ላይ 600 ኩንታል በላይ  ይመረታል ተብሎ የሚገመተውን ስንዴና ገብስ የመሰብሰብ ስራ ያከናውነው መሆኑን ገልጦ ፣ ለዚሁ አገልግሎትና የአካባቢውን ማህበረሰብ እንዲያገለግል በማሰብ የእህል መውቂያ ማሽን በመግዛት በትናንትናው እለት የሙከራ ስራው ተጠናቆ በዛሬው እለት መደበኛ የመውቃት ስራ እየተሰራ ይገኛል።

@DBU11
@DBU11
👍31😁6👏4
የፈጠራ ሀሳብ ላላችሁ አዲስ ሀሳብ ማሳደግ ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ:- የ ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ፣ኢንኩቤሽን እና ሽግግር ማእከል ባስተላለፈው ማስታወቂያ ideal hub ን በመቀላቀል ሀሳባችሁን ወደተግባር ለመለወጥ እገዛ ማግኘት ትችላላችሁ።
ለመመዝገብ👉 @DBU_ideal_bot
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት👉
https://www.tgoop.com/Ideal_hub
ሁለቱንም ስትሪሞች ማለትም ማህበራዊ እና ተፈጥሮ ሳይንስ ከ አዲስ ገቢ እስከ መጨረሻ አመት ተማሪዎችን በሙሉ ያካትታል።






@DBU11
@DBU11
👍8
የኮሮና ወረርሽኝ እና ጦርነቶች የጫና በትሩን በልዩነት የ2013 ባች የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ያሳረፈ ይመስላል።

በዚህ ሰዓት (ዛሬ ማለትም ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም) የ 2013 ባች ጁንዬር (2014 ባች) ተማሪዎች ሲንዬሮቻቸውን(2013 ባቾችን) ቀድመው የ GC birthday ceremony እያከበሩ ይገኛሉ። 2013 ዎች ደግሞ ከጁንዬሮቻቸው በመቀጠል በሚቀጥለው ሳምንት ceremony እንደሚያደርጉ ተናግረዋል በመሆኑም ዩንቨርስቲው በዚህ አመት ሁለት ተከታታይ(2013 እና 2014)entry ዎችን ያስመርቃል ማለት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ
በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች የ2013 ባች ተማሪዎቻቸው አንድ አመት ላግ (ወደ ሗላ እንዲቀሩ) በማድረግ በዚህ አመት ያስመርቃሉ።

አዲስ አበባን ጨምሮ ከአማራ ክልል ውጭ ያሉ አቻ ዩንቨርስቲዎች የክረምት ትምህርት መርሀ ግብር በማውጣት ጭምር የባከነውን የትምህርት ጊዜ በማስተካከል የሚፈለገውን የትምህርት ክፍል የትምህርት አመት በመጨረስ ማስመረቃቸው ይታወሳል።

በአዲሱ እና በተከለሰው የትምህርት ስርዓት አንድ ተማሪ በበፊቱ የትምህርት ስርዓት(curriculum) 3 ዓመት የሚፈጅበትን አንድ የትምህርት ክፍል ጥናት 4 ዓመት ይወስድበታል በአማራ ክልል የተፈጠረው ሁኔታ ደግሞ 2013 ባቾችን አምስት አመት ወስዶባቸዋል።

የእኛ ዩንቨርስቲ ከህግ ተማሪዎች ጋር ተያይዞ የተነሳበትን የቅሬታ ጥያቄ መልሷል።

ሁላችሁም ሰላማችሁ ይብዛ ለፈጣን እና አስተማማኝ መረጃ daily news ን ይቀላቀሉ ሰናይ ቅዳሜ እና እሁድን ተመኝተናል።


@dbu11
@dbu111
👍49😁11
የተማሪዎች ጥያቄ እና የአስተዳደሩ ምላሽ

በዛሬው እለት ከዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች በተለያየ መልኩ ለዩኒቨርሲቲው ሲሰነዘሩ የቆዩ ጥያቄዎችን በይፋ ይዘው ወጥተዋል።

በዚህም የፀጥታ አካላት እና የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን አቶ አለምነው መልካሙ ተማሪዎችን ቀርበው አነጋግረዋል።

ተማሪዎቹ በዋናነት በተደጋጋሚ ሲያነሱት የነበረው የአግልግሎት ችግር

👉1. ከምግብ (ካፌ) አገልግሎት ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄ
ከትምህርት ሚኒስቴር ለዩንቨርስቲዎች ተሻሽሎ የተላከው የምግብ ሜኑ ተግባራዊ ይሁን(ይሻሻል)።

# የመመገቢያ አዳራሹ(ካፌ) ወንበሮች እና የመመገቢያ (ዕቃ) ሳህኖች ንፅህና ይጠበቅ።

# የእራት መመገቢያ ሰዓት ይሻሻል።

በምግብ ቤት ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል ሲሆኑ

#2 መብራትን በተመለከተ
# በዋና ዋና መንገዶች የምሽት መብራት
# ቀን ላይ በፕሮጀክተር በመማር ሂደት የመብራት መቆራረጥ

3 . የምግብ ግዥ እና ዝግጅት ላይ የተማሪ ተወካይ ተሳትፎ ።

4.የወጭ መጋራት ሒሳብ በዩንቨርስቲ ቆይታችን ልክ እንዲሰላ ።

4. የዋይፋይ አገልግሎት ይስተካከል እንዲሁም

5. የጥር ተፈታኞች የመመረቂያ ጊዜ በይፋ (በግልፅ) ይነገረን
የሚሉ ጥያቄዎች ሲሆኑ

ጥያቄዎቹን ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች የነበሩ ሲሆኑ daily newsም በቀደሙት ዜናዎቹ ዘግቧቸው ነበር።

የተማሪዎች ዲን አቶ አለምነው ጥያቄያችሁን ስነ ስርዓት በጠበቀ መልኩ ጠይቁ እኔም ስራዬን (ሀላፊነቴን) በመወጣት መልኩ እሰራለሁ።
# ፍላጎቴም ስራየም የእናንተን ምቹ የትምህርት አካባቢ መፍጠር ነው እንጅ ሌላ ጉዳይ የለኝም።

👉 የምግብ ሜኑን በተመለከተ የተጠቀምኩት ከተላከልን የሜኑ መስፈረት በጀቱ የሚፈቅድልንን ዝቅተኛውን ሬሾ ነው።

አካባቢው የሚፈቅደውን የግብዓት ግዥም ከግምት አስገብተን እንሰራለን መተግበር የምንችለውን እንተገብራለን ብለው የመለሱ ሲሆን በዛው ቅፅበት ብዙሀኑ ተማሪ ስብሰባውን አቋርጦ ወጥቷል።

ነገር ግን ዲኑ ከጥቂት ተማሪዎችጋ ተጨማሪ ነገሮችንም ለመነጋገር ሞክረዋል።




@dbu11
@dbu111
👎81👍59😁10
የተማሪዎች ጥያቄ ምንድነው?

👉የካፌ የምግብ ሜኑ እና የምግብ ጥራት

👉 የመመገቢያ ሰዓት ውስንነት

👉 የመግቢያ ሰዓት ማጠር

👉 የኮስትሼሪንግ ጉዳይ (በዩኒቨርሲቲው በኮሮና እና በጦርነት ምክኒያት ያልተኖሩ ዓመታት በእዳ መያዝ)

👉 ተማሪን በተመለከተ የሚወጣ እቅድን አስቀድሞ አለማሳወቅ።
(የመግቢያ፣የመውጫ እና የመመረቂያ እቅድ )

👉 የተማሪዎች ህብረት ተሳትፎና ተቀባይነት።

👉በምሽት ሰዓት የመንገዶች መብራት አለመኖርና መቆራረጥ

👉 የዋይፋይ አገልግሎት መቋረጥ


እነዚህንና መሰል ጥያቄዎች ከተማሪዎች ቀርበዋል።


@DBU11
@DBU111
👍126👎7👏2😁1
የደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ይዘን የወጣነው የአገልግሎት ጥያቄ በትላንትናው እለት በቂ ምላሽ አላገኘንም በማለት በዛሬው እለት ቀጥሎ በይፋ የተካሔደ ሲሆን የዞን እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የኮማንድ ፖስት አመራሮች ጨምሮ የፀጥታ አካላት በተገኙበት የዩንቨርስቲው ከፍተኛ አመራር አቶ አለባቸው እና የተለያዩ የስራ ክፍል ሓላፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች ቅሬታ ከተነሳበት ከትላንትናው መልስ የተሻለ ምላሽ ሰጥተዋል።

የተነሱት ጥያቄዎች ትላንት daily news የዘገባቸው ሲሆን ዛሬ ደግሞ አዩ ዘሐበሻ በቴሌግራም ገፁ አስነብቧቸዋል daily news የተለያዩ የግል ሚድያዎችም ሽፋን እንደሰጧቸው ተመልክቷል።

የዩንቨርስቲው የስራ ክፍል ሐላፊዎች (አመራሮች) በሰጡት ምላሽ

1. ከምግብ ሜኑ ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄ ከትምህርት ሚንስተር የተላከው የምግብ ሜኑ ይተገበራል።
2. የዋይፋይ አገልግሎትን በተመለከት ለአገልግሎት የተዘጋጁትን ነገር ግን የማይሰሩ የዋይፋ ሮውተር ሞደሞችን እናስተካክላለን ነገር ግን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የውል ሒደት ላይ ስለሆንን በትንሽ ጊዜያቶች በየብሎኮች የዋይፋይ አገልግሎት ያለ እንከን ታገኛላችሁ።

3 .ከመብራት ጋር ተያይዞ በአሁኑ ወቅት በሀይል መቆራረጥ ምክንያት ዳታ ሴንተሩ ተቃጥሎብናል( ለችግር ምክንያት የሆነ ጥፋት አጥፍቶብናል )ነገር ግን በቅርቡ ይስተካከላል። የመንገድ ዳር መብራቶችም ይስተካከላሉ።

4.በህክምና አገልግሎት የተነሱት ጥያቄዎችም ግዴታ ክሊኒክ መስጠት ያለበትን አገልጎሎት ይሰጣል ከአቅሙ በላይ ከሆነ መድሐኒት አቅርቦቱም ከሌለው ሪፈር ያደረጋል ሰራተኞችም በዲስፕሊን አገልግሎት ይሰጣሉ ይህ እንዲሆን እንከታተላለን።

5 . የግቢው አገልግሎት ሰጭ ሰራተኞችም ሰነ ምግባር በተሞላበት መልኩ ይሰራሉ።

6. የወጭ መጋራት ጋር በተገናኘ ለሚመለከታቸው ሓላፊዎች ጥያቄ ልከናል እየተነጋገሩበት ነው መልስ ነገ ይዘው ይመጣሉ። ኢንተርንሽፕ ግን ትምህርት ክፍሉ የትምህርት ስርዓቱ የሚያዘውን መተግበር ግዴታ አለበት ተፈፃሚ ይሆናል።

7.የመመገቢያ እና መግቢያ ሰዓት ተነጋግረን እናንተን በሚጠቅማችሁ መልኩ ለውጥ የሚኖረው ከሆነ እናያለን።

8. ላውንጅ እና ሱቅ ከዋጋ ማጭበርበር እና ጥራት የእናንተን ጥቆማ እና መረጃ አድርሱን እንጅ የምንወስደውን እርምጃ እንወስዳለን።
9. calendar issue በዩንቨርስቲያችን ሶስት አይነት ካላንደር አለ የተፈጠረውም ከአቅማችን በላይ በሆነ ምክንያት ነው የሆነው ሆኗል ወደፊት የሚሆነው ግን መሆን ያለበት ይሆናል።

የሚል ምላሽ ሰጥተዋል ከምንም በላይ ግን ጥያቄያችሁን አንድም ጥፋት ሳታጠፉ በዚህ መልኩ በማቅረባችሁ እናመሰግናለን ኮርቸባችሗለሁ ነው ያሉት።
ተማሪዎችም ይኽንን በተግባር አውርዳችሁ አሳዩን ካልሆነ ግን ጥያቄያችንን እንቀጥላለን ነው ያሉት።

@DBU11
@DBU111
👍146👏12👎10😁8
#Gc_2017

አንድን ዝግጅት እንዲህ ባማረ መልኩ አጠናቆ ማቅረብ ጥበብን ይጠይቃል።አንድ ሆኖ ለደስታ መናበብንም።

ለተማሪዎች እንኳን አደረሳችሁ።
     አዘጋጆችም ክብር ይገባችኋል!

የዝግጅቱ ቪዲዮ ከላይ ተያዟል
Credit
📼📽️ by  #Eyuel_belay

@DBU11
@DBU11
👍36👏4😁4
update
የኮዲንግ ሥልጠና ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች!

በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉ ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ ይመዝገቡ፡፡

የኦንላይን ስልጠናውን በተሰጡት 8 ሳምንታት ለሚያጠናቅቁ ብቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትላቸዋል፡፡




@DBU11
@DBU111
👍26👎8
#ማስታወቂያ👆👆👆👆

ለሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን መደበኛ ተማሪ የክፍል ተወካዮች በሙሉ ነገ በቀን 18/04/17 ዓ/ም ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር ስብሰባ ስለሚኖር ከጧቱ 3፡00 ሰዓት አስተዳደር ህንፃ እንድትገኙ።




@DBU11
@DBU111
👍10
ማስታወቂያ ከሴቶች፣ህፃናት፣ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ቡድን ቢሮ 👆👆👆👆👆👆

@DBU11
@DBU111
👍26😁2
ስለ አዲሱ የምግብ ሜኑ ከክፍል ተወካዮች ጋር ምክክር እየተደረገ ይገኛል።

በምክክሩም በቅርቡ ተግባራዊ የሚሆነው የምግብ ሜኑ ይፋ ተደርጓል።

@dbu11
@dbu111
👍48😁31👎2
ከ2017 ጀምሮ በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ተግባራዊ የሚደረግ የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ይፋ ተደረገ።

በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ  በቅርቡ ተግባራዊ የሚደረገው የተማሪዎች አዲስ የምግብ ሜኑ ይፋ ተደርጓል ።

ከክፍል ተወካዮች እንዲሁም ከተማሪ ህብረት አባላት  ጋር በተደረገው ውይይት የበፊቱ ሜኑ በጀት አጠቃቀም እንዴት እንደነበርና አዲሱ  የምግብ ሜኑ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን ከዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ዲን አቶ አለምነው መልካሙ ሰፊ ገለፃ ተደርጓል።

ይሁን እንጂ የተማሪዎች ጥያቄ የምግብ ና ተያያዥ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን አካዳሚያዊ (cost sharing, calender, intership,exit exam etc.) ጭምር እንደነበር ተማሪዎቹ አነስተው ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በጥያቄው መሠረት በሁለተኛ ዙር ከአካዳሚክስ ጉዳይ ተጠሪ ዶ/ር ጌትነት ጋር ውይይት ተደርጓል።

ከዶ/ር ጌትነት ጋር በነበረው ውይይት ስለኮስት ሼሪንግ ለተነሳው ጥያቄ ሒሳቡ የሚሠላው ተማሪው በቆየበት ጊዜ እንደነበረው የገንዘብ መጠን  የሚሰራ ይሆናል።

የ2013 ባች ተማሪዎች ከexit exam በፊት ያሉባቸውን ቀሪ ኮርሶች እንዲጨርሱ ያ ካልሆነ ግን የምርቃት ጊዜያቸው ከየካቲት አልፎ ወደ ሰኔ እንደሚጠጋ አመላክተዋል።

ከዛ ውጪ ግን የአካዳሚክ ካሌንደሩ ከዚህ በፊት ተገልጾ እንደነበረው ይቀጥላል የሚል መልስ ተሰቷል።

Reporter :ፅዮን መሉነህ

@DBU11
@DBU11
👍48👎35
#Ad
GC Birthday Party ከእኛ ጋር በጃዝሚን
ከዲጄ አጫዋች ጋር...


መግቢያ 100 ብር
አድራሻ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ታክሲ ተራ ጃዝሚን ባር (ማርካን)

@DBU11
@DBU111
👎22👍16😁3
2025/07/12 10:10:00
Back to Top
HTML Embed Code: