Telegram Web
#የመውጫፈተና


ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ብሄራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) መያዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) " የ2017 የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 /2017 ዓ.ም. በ51 ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ይሰጣል " ብለዋል።

ፈተናውን በ238 የትምህርት መርሃ ግብሮች ለ190 ሺ 787 ቅድመ መደበኛ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በበይነ መረብ ለመስጠት  አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

ለፈተናው 102 ሺ 360 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ፤ 88 ሺ 422 ተማሪዎች ደግሞ ዳግም የሚፈተኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲመጡ አገር አቀፍ ፋይዳ /ብሄራዊ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸውም ኃላፊው አስገንዝበዋል፡፡

በፈተና ወቅት ፦
- ተንቀሳቃሽ ስልክ ፣
- ሜሞሪ ያለው የእጅ ሰዓት ፣
- የራስ ያልሆነ መታወቂያ፣
- ያልተፈቀዱ ሂሳብ ማሽኖች፣
- አጫጭር ማስታወሻዎች፣
- የተጭበረበሩ ሰነዶች
- ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ክልክል መሆኑን አስገንዝበዋል።

ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ፦
° አደንዛዥ ዕጽ ተጠቅሞ መምጣት፣
° ከፈተና አስፈጻሚዎች ጋር አሉታዊ ተጽእኖ ያላቸው ውዝግቦችን መፍጠር ፣
° ያለመታወቂያ ካርድ ወደ ፈተና ማእከል መሄድ ፣
° ያለፈቃድ ፈተና ማዕከል መገኘት
° ለሌላ ሰው መፈተን ፍጹም የተከለከሉ ዲሲፒሊን ጥሰቶች መሆናቸውን አሳስበዋል።

ከሰኔ 2 እስከ 10/ 20017 በሚሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና 4 ሺ 17 ፈተና አስፈጻሚዎች እንደሚሳተፉ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል።

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ተኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!!


https://www.tgoop.com/DBUstudent
ማስታወቂያ

ውድ የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የ 2017 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎቻችን የምርቃት ቀንን በተመለከተ እስከ አሁኗ ሰዐት ድረስ ባለን መረጃ መሠረት ቀኑ እሁድ 15/10/17 ዓ/ም እንዳልተቀየረ ለማሳወቅ እንወዳለን ።

አዲስ መረጃ ሲደርሰን የምናሳውቃችሁ ይሆናል

የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
የምርቃት ቀናችንን በበጎ ስራ እናሳልፍ !
ስለ መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአይምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ምን ያህል ያውቃሉ 🤔 ?

ዛሬ ስለ መቄዶንያ ትንሽ እንበል

-ከ 8,200 በላይ አረጋውያን እና አይምሮ ህሙማንን  በስሩ አቅፎ እንደያዘ
- በመላው ሀገሪቱ በስሩ 45 ቅርንጫፉች እንዳሉት
-2,500 የሚሆኑት ህሙማን በቀን ቢያንስ 3 የአዋቂ ፓምፐርስ እንደሚጠቀሙ
- በቀን ከ 2.5 ሚሊየን ብር በላይ ለመድኃኒት ፣ለምግብ እና ለሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንደሚያስፈልገው ....
እንዲሁም ይህ ሁሉ ያለ ምንም የውጪ እና የመንግስት ድጋፍ የሚከወን መሆኑን በመረዳት በቅርቡ በግቢያችን ለዚህ የሀገር ኩራት ለሆነው ማዕከል እርዳታ የሚውሉ የተወሰኑ ተግባራት በቅርብ ቀናት ውስጥ ስለሚከናወኑ እንድትዘጋጁ እየጠየቅን ።  ለጊዜው በአቅማችን የመቄዶንያን እና የሰይፎ ሾው የዩትዩብ ቻናል Subscribe , Like , share እንድታደርጉ እንዲሁም
⋕በ8161 ላይ ok በማለት በቀን 1 ብር እንድትደግፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን 🙏

Links
የመቄዶንያ 👉  https://youtube.com/@mekedonia?si=kLvP7hGIBAoLEvzm

የሰይፉ ሾው  👉 https://youtube.com/@seifufantahun?si=BJglkVUzR4XY2f3f

ከላይ ባሉ ማስፈንጠሪያዎች ሰብስክራይብ በማድረግ screenshots ከስር ሀሳብ መስጫው ላይ ያጋሩን  🙏

<< ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው >>


የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
ማስታወቂያ

በነገው ዕለት በቀን 15/10/17 ዓ/ም የምርቃት ፕሮግራም 1:30 መጀመሩን ተከትሎ የቁርስ ሰዐት እስከ 2:00 ሰዐት ስለሆነ በጊዜ ተመግባችሁ ወደ ፕሮግራሙ ገብታችሁ እንድትሳተፋ ለመግለጽ እንወዳለን።

  የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
🎓🎉 መልካም የምረቃት ቀን ለሁሉም የ2017 ዓ.ም ተመራቂዎች 🎉🎓
ከደብረ ብርሃን  ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

ውድ ተመራቂዎች

በቅድሚያ እንኳን ለዚች ለምትናፍቋት እና በጉጉት ስትጠብቋት ለነበረችው ውድ ቀን በሰላም አደረሳችሁ።

ዛሬ የደስታ እና ድል አንድ ቀናችሁ ነው። ከብዙ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችና  ዓመታት እንዲሁም ከሌሎች ብዙ አስቸጋሪ የህይወት ውጣ ውረድ በኋላ በመጨረሻም ከዛሬው እለት ደርሳችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።

እናንተ ማለት ለበተሰቦቻችሁ ብርሃን፣ ላሳደጋችሁ እና ላኖራችሁ ማህበረሰብ ተስፋ እንዲሁም ለሃገራችሁ የወደፊት ተረካቢ ናችሁ፤ ይህንንም ደግሞ እስከዛረዋ እለት ድረስ በዘለቀው ጥረታችሁ አረጋግጣችኋልናልና ከልብ እናመሰግናለን።

📚 ከመጀመሪያው ወደ ግቢ ከገባችሁበት እለት እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ያሉት እያንዳዷ እርምጃ በሁላችሁም ህይወት ውስጥ መቼም የማይፋቅ ትውስታ፣ ጓደኝነት እና ቤተሰባዊነትን ጥለው አልፈዋል።

ሁሉም መጨረሻ ለሌላ አዲስ መዕራፍ መጀመሪያ ነውና ይህም ምርቃት ለሌላ አዲስ ተለዕኮ መጀመሪያ ነው ከዚህ ግቢም ወጥታችሁ ቤተሰባችሁንና ሃገራችሁን የምትጠቅሙና ስራ ፈጣሪዎች ሆናችሁ ለሌሎች የምትተርፉ ጥሩና መልካም ዜጋ እንድትሆኑ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።



በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ፤እንኳንቭተመርቃችሁ!!!
እንኳን ደስ አለሽ ተማሪ ፈቲሃ አሕመድ

ከኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል 4.00 ነጥብ በማምጣት የዩኒቨርስቲውን 🏆 ዋንጫ ወስዳዋለች ።
የሴቶች ዋንጫም ወስዳዋለች በድጋሚ እንኳን ደስ አለሽ በርቺልን

የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
ማስታወቂያ 

ለሁሉም በዩኒቨርስቲው ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎቻችን ከነገ ማለትም ረቡዕ ቀን 18/10/17 ዓ.ም  6:00 ሰዐት በኋላ  ግቢው ውሰጥ አገልግሎት ስለማታገኙ አስፈላጊ ነገሮችን በተቻለ ፍጥነት እንድትጨርሱ ለማሳወቅ እንወዳለን።

የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
Notice to All Class Representatives
Dear Class Representatives,
This is to inform you that the Field Choice Orientation Program is scheduled for Saturday, 10/01/2018 E.C., at 2:30 Local Time in the Graduation Hall.
Attendance is required for all students enrolled in 2017 E.C. from the following categories:
•  Other Natural Sciences
•  Other Social Sciences
•  Computing College
•  Free Engineering
We kindly ask you to arrive on time at the designated venue and to communicate this information to the students in your respective classes.
Thank you for your support and cooperation.

የደ/ብ/ዩ የተማሪዎች ሕብረት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
የ2018ዓ_ም_የመደበኛ_ተማሪዎች_የመኝታ_ህንፃዎችii2018.docx
24.6 KB
ለደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ የ2018ዓ.ም የዶርም ምደባና ዝርዝር መረጃ ይፋ ሆኗል!

የደ/ብ/ዩ የተማሪዎች ህብረት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
ተማሪ አቤል ተካ ሰርተፍኬትህን ጊቢ ውስጥ ወድቆ ያገኙት ተማሪዎች ወደ ተማሪዎች ህብረት ቢሮ ስላመጡት መጥተህ እንድትወስድ ስንል እናሳስባለን፡፡


https://www.tgoop.com/DBUstudent
የ2018 ዓ/ም የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ ተደረገ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከመስከረም 20 - 25/2018 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን አሳውቋል።

አመልካቾች የመመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ እንደሚችሉ ገልጿል።

ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ አመልክቷል።

አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ጥያቄ ዘውትር በስራ ሰዓት በ0920157474 ወይም 0911335683 እንዲሁም በኢሜይል አድራሻ [email protected] በኩል ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም አመልካቾች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳስቧል።

የምዝገባ እና የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በTeleBirr በኩል ብቻ መከፈል እንደሚኖርበት አስገንዝቧል።

#MoE

@tikvahethiopia
ለአዲስና ነባር የሜካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች በሙሉ የሜካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር አዲስ ወደ ሜካኒካል ምህንድስና የተመደቡ ተማሪዎችን የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራምና ከነባር የሜካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች ጋር የትውውቅ መርሀግብር ስለተዘጋጀ በቀን 25/01/2018 ዓ.ም ማለትም እሁድ 8:30 SE 13 F2 04 እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የሜካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር

https://www.tgoop.com/DBUstudent
ማስታወቂያ
notice

ተማሪ ብርቱካን ኤርሚያስ ት/ት ክፍል IS
ተማሪ ሀና ተስፋዬ ት/ት ክፍል  Agro Economics
የሆናችሁ ተማሪዎች የ Non-Cafe መረጃችሁ የተማሪዎች ምግብ ቤት ሄዳችሁ እንድታስተካክሉ እናሳውቃለን።

የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
2025/10/10 15:15:59
Back to Top
HTML Embed Code: