ማሳሰቢያ ለሁሉም የዩንቨርሲቲያችን ተማሪዎች፦
ውድ ተማሪዎች፣ ሁላችሁም እንደምታውቁት
ዩንቨርሲቲያችን በተማሪዎች ውጤት አያያዝ ላይ አዲስ የውጤት አያያዝ ለመከተል በዝግጅት ላይ እንደነበር ይታወቃል። ይህም ደግሞአንድ ተማሪ ኮርሱን ለማለፍ በኮንቲኒየስ አሴስመንት(continuous assessment) ቢያንስ 20 ከ50 እና በፋይናል ፈተና(final exam) ቢያንስ 20 ከ 50 ማምጣት እንደሚጠበቅበት መግለፁ ይታወቃል።
ነገር ግን ይህ ለውጥ በብዙ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እና ቅሬታ ፈጥሯል። በምላሹም የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንቱ እና ሌሎች የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ትናንት ከክፍል ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በዚህም ምክንያት የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በሚቀጥለው ሳምንት አዲሱን የምዘና ዘዴ እንደገና እንዲገመገም እቅድ ተይዟል እና የመጨረሻውን ውሳኔ ከስብሰባው በኋላ ያሳውቃል።
👉 ስለሆነም ሁሉም ተማሪዎች የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ እንደተለመደው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በጥብቅ አሳስበዋል።
የደ/ብ/ዩ ተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
Telegram
DBU የተማሪዎች ህብረት!!
የደ/ብ/ዩ የተማሪዎች ህብረት የመረጃ አውታር !!!