[ታኅሣሥ 22 የአምላክ እናት ተአምሯን ለጻፈላት ለቅዱስ ደቅስዮስ በረከቷን የሰጠችበት]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ደቅስዮስ የተወለደው በ607 ዓ.ም. ሲኾን ከጊዜ በኋላ የቶሌዶ ጳጳስ የሆነው አጎቱ ዩጄኒየስ በወጣትነቱ ቃለ እግዚአብሔርን ያስተምረው ነበረ። ከዚያም በ632 ዓ.ም አካባቢ የቶሌዶ ኤጲስ ቆጶስ ኤላዲዎስ ዲያቆን አድርጎ ሾሞታል። ከፍ ካለ በኋላ በቶሌዶ አቅራቢያ ወደሚገኘው የአጋሊያ ገዳም በመግባት የገዳሙ አበምኔት ኾነ። ከዚያም በ657 የቶሌዶ ሊቀ ጳጳስ ኾኖ ተመረጠ።
💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በፍጹም ልቡ ከመውደዱ የተነሣ በተቻለዉም ኹሉ ያገለግላት ነበር “ወእምንደተ ፍቅሩ አስተጋብአ መጽሐፈ ተአምሪሃ” ይላል ከፍቅሩም ጽናት የተነሣ ክብሯን፣ ንጽሕናዋን፣ ቅድስናዋን፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋን፣ ወላዲተ አምላክነቷን፣ ተአምሯን የሚናገር መጽሐፍን ሰበሰበ።
💥 ደቅስዮስ መሰብሰብ ብቻ ሳይኾን ድርሰትም ደራሲ ነበረ። ከጻፋቸው ከደብዳቤዎቹ ሁለቱ እና አራቱ ጽሑፎቹ አሁንም ድረስ አሉ። በተለይ የመዠመሪያው እና ዋናው ክፍል ስድስት ድርሰቶችን ያቀፈና ልክ እንደ ጀሮም ርሱም ሄልቪደስን ተቃውሞ ስለ እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና የጻፈው "De virginitate perpetuâ sanctae Mariae adversus tres infideles" (On the Perpetual Virginity of Holy Mary) በመባል የሚታወቅ ሥራው ነው። ይኽ የደቅስዮስ መጽሐፍ ለ3 የተከፈለ ሲኾን "ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ" ዘላለማዊት ድንግል መኾኗን ይተነትናል።
💥 ቅዱስ ደቅስዮስ የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልናዋ የልጇ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት የሚገልጽ ምልክት እንደኾነ ሲገልጽ ልጇ እግዚአብሔር ነውና ብቻውን በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ሊወለድ ችሏል ብሏል።
💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በጽሑፉ ማርያም ብቻ ብሎ በስሟ አይጠራትም። ይልቁኑ ድንግሊቱ፣ የእኛ ድንግል ይላታል።
💥 ያን ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት “ይኽን መጽሐፍ ስለ ጻፍኽልኝ ደስ ብሎኛል” ብላው ባርካው ተሰወረች፡፡
💥 በተጨማሪም በ304 ዓ.ም. በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነትን በተቀበለችው በቅድስት ሊዮካዲያ (Saint Leocadia) የከበረ ዐፅም ፊት ሲጸልይ በተአምራት ተነሥታ የአምላክን እናት ስላከበራት አመስግናዋለች።
💥 ቅዱስ ደቅስዮስም ይኽነን ኹሉ ካየ በኋላ እጅጉን በመደሰት ለእመቤታችን ክብር ምን መሥራት እንዳለበት በማሰብ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠረበት መጋቢት 29 ቀን የዐቢይ ጾም በመኾኑ ምክንያት ሰዎች ማክበር ያልተቻላቸውን በዓለ ብሥራትን ከልደት በዓል ስምንት ቀናት ቀደም በማድረግ ታኅሣሥ 22 ዕለት እንዲከበር ሥርዐትን ሠራ። በቶሌዶ በተደረገ ጉባኤ ለአምላክ እናት ክብር የተለየ የበዓላቷን ቀን ተደነገገ።
💥 ምእመናንም እጅጉን በመደሰት በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ እግዚአብሔር በማሕፀነ ማርያም የተፀነሰበትን በዓል ለውጥ በማሰብ በዓሉን በድምቀት አከበሩ፡፡ ያን ጊዜ በወርኃ ታኅሣሥ በ665 ዓ.ም. በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ለደቅስዮስ ለብቻው ተገልጻለት “ወዳጄ ደቅስዮስ ባንተ ደስ አለኝ፤ ሥራኽንም ወደድኊ፤ በዓሌን አክብረኽ ስለ እኔ ሰውን ኹሉ ደስ አሰኝተኻልና እኔም ዋጋኽን ልሰጥኽ እወዳለኊ ትቀመጥበትም ዘንድ ይኽነን ወንበር አመጣኹልኽ” በማለት በወንበሩም ላይ ማንም ሊቀመጥባት የሚቻለው እንደሌለ ነግራው ከርሱ ተሰወረች፡፡
💥 በሌላ ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ደቅስዮስ ከምእመናን ጋር የእመቤታችንን መዝሙር ሲዘምሩ ከፍተኛ ብርሃን ወርዶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲከብባት አብዛኞቹ ምእመናን ፈርተው ሲሸሹ ደቅስዮስ ከጥቂት ዲያቆናት ጋር ብቻ ቀረ። ያንጊዜ ቅድስት ድንግል ማርያም ደናግልን አስከትላ ወርዳ በኤጲስ ቆጶስ ዙፋን ላይ ተቀምጣ አየ። እመቤታችንም ደቅስዮስን ለታማኝነቱ አመስግናው እጅግ የተለየ ልብሰ ተክህኖ በበዓላቷ ላይ ብቻ እንዲለብስ ሰጥታው በእመቤታችን በዓላት ይለብሰው ነበር።
💥 ቅዱስ ደቅስዮስም በ667 ዓ.ም. ከዚኽ ዓለም በሕይወተ ሥጋ በተለየ ጊዜ እመቤታችን የባረከችውን ልብስ በቤተ ክርስቲያን ዕቃ ቤት በክብር አኖሯት፤ ከርሱ በኋላ የተሾመው ኤጲስ ቆጶስ ግን ያችን ልብስ ሊለብሳትና በደቅስዮስም ወንበር ሊቀመጥ ወደደ።
💥 ቀሳውስትና መምህራን ግን የልብሷን ክብር በመንገር ይኽነን እንዳያደርግ ቢለምኑት ርሱ ግን ልክ እንደ ዖዝያን በድፍረት ልብሷን ለብሶ በወንበሩ በተቀመጠ ጊዜ ሐናንያና ሰጲራ በቅዱስ ጴጥሮስ ፊት ተቀሥፈው እንደሞቱ፤ ርሱም “ወድቀ በጊዜሁ እምላዕለ ውእቱ መንበር በቅድመ ኲሎሙ ሰብእ እለ ሀለዉ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወሞተ በእኩይ ሞት ወሕሡም ፈድፋደ” ይላል በዚኽ የድፍረት ኀጢአቱ ከዚያ ወንበር ላይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ኹሉ ፊት ወድቆ ክፉ አሟሟትን ሞቷል፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተደረገው ተአምር ሕዝቡ በመደነቅ ምስጉን እግዚአብሔርን በማመስገን አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችንን ስለ አደረገችው ተአምር እጅጉን አክብረዋታል፡፡ በግእዝ በብራና በተጻፉት ተአምረ ማርያም ላይ ይኽ የቅዱስ ደቅስዮስ ታሪክ ተሥሎ ማየት የተለመደ ነው።
💥 ከዚያ በኋላ የሰጠችው ልብስ ቢሰወርም ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ለደቅስዮስ ስትገለጥለት እግሯን ያሳረፈችበት ድንጋይ ግን በቶሌዶ ካቴድራል ጸሎት ቤት ውስጥ ይከበራል።
💥 ንጉሥ ዳዊትም እንደነ ደቅስዮስ ላሉ እመቤታችንን ለሚወዷት ኹሉ በምልጃዋ ከልጇ ስለምታሰጣቸው ታላቅ መንፈሳዊ በረከት መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ ገልጦለት “ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ” (በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ) በማለት ከገለጠ በኋላ “ወትሠይሚዮሙ መላእክተ ለኲሉ ምድር” (በምድርም ኹሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ) በማለት የሠያሜ ነገሥት፣ የሠያሜ ካህናት የክርስቶስ እናት መኾኗንና፤ ይኽነንም የአምላክ እናትነቷን ለመሰከሩ ለነ ደቅስዮስ ወንበር፤ ለነ ኒቆላዎስ ዐጽፍ፣ ለነ ቅዱስ ኤፍሬም “አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ” (አቤቱ የጸጋኽን ማዕበል ግታው፤ ወስነው) እስኪሉ ድረስ በቃል ኪዳኗና በአማላጅነቷ ያሰጠቻቸው ታላቅ በረከት መንፈሳዊ ሹመትና ብቃት መኾኑን አሳይቷል፡፡
💥 “ወይዘክሩ ስመኪ በኲሉ ትውልደ ትውልድ” (ለልጅ ልጅ ኹሉ ስምሽን ያሳስባሉ) በማለት በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በርሷ ወላዲተ አምላክነት በማመን የጸና ያለፈውና የሚመጣው ትውልድ ኹሉ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) እያለ የተቀደሰ ስሟን ሳይጠራ የሚውል ማንም እንደማይኖር ቅዱስ ዳዊት በመንፈሰ እግዚአብሔር ገላጭነት ተናግሯል (መዝ ፵፬፥፱-፲፯)፡፡
💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በሕማማት ሰላምታው ላይ፦
“ማርያም ሀብኒ ልብሰ ትፍሥሕት ወተድላ
ከመ ወሀብኪዮሙ ቅድመ ምስለ መሐላ
ለደቅስዮስ ወለኒቆላ ሰላም ለኪ"
(ለኒቆላና ለደቅስዮስ ከቃል ኪዳን ጋራ አስቀድመሽ እንደሰጠሻቸው ሰላምታ የተገባሽ ማርያም የፍጹም ደስታና ተድላ ልብስን ስጪኝ) በማለት ተማፅኗታል፡፡
💥 የነገረ ማርያም ሊቃውንት የነበሩት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ እመቤታችን ተአምሯን ሰብስቦ ላዘጋጀላት ለደቅስዮስ ታላቅ ጸጋን በቃል ኪዳኗ እንዳሰጠች ሲገልጹ፦

“ሶበ ጸሐፈ ደቅስዮስ ተአምረኪ ቅዱሰ
መንበረ ወዐጽፈ ዕሤተ ጻማሁ ወረሰ
ማርያም ድንግል ዘታብእሊ ፅኑሰ
ዐስበ ማሕሌትየ ዐቅመ ልብየ ኀሠሠ
ጸግውኒ አትሮንሰ ወጽጉየ ልብሰ”
(ደቅስዮስ ልዩ የኾነ ተአምርሽን በጻፈ ጊዜ የድካሙን ዋጋ ልብስንና ወንበርን አገኘ፤ ድኻውን ባለጠጋ የምታደርጊ (ነዳየ አእምሮውን በቃል ኪዳንሽ ባለ አእምሮ የምታደርጊ) ድንግል ማርያም ልቡናዬ በፈለገ መጠን የምስጋናዬን ደሞዝ ወንበርንና የክብር ልብስን ስጪኝ) በማለት የሿሚ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግልን በረከት ልክ እንደ አባ ጊዮርጊስ ሽተዋል፡፡

❤በቤተ ክርስቲያን 5 አይነት አክሊላት አሉ❤
1 አክሊለ ሰማዕት
ይህ አክሊል ሰማእታት በተጋድሎ የሚያገኙት አክሊል ነው ቅዱስ
ጳውሎስም ስለዚህ አክሊል ሲናገር ሃይማኖቴን ጠብቄለው ሩጫዬን ጨርሻለው ወደፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ብሎ ጠቅሶታል
2 ጢሞ 4+6-7
በተመሳሳይ ባለራዕዩ ቅዱስ ዮሐንስም እስከሞት ድረስ የታመንክ ሁን የሕይወት አክሊል እሰጥሃለው ብሎ የተናገረው ስለ ሰማእታት አክሊል ነው ራዕ 2+10 ክርስቶስም አክላሎሙ ለሰማእት ተብሏል እመቤታችንም አክሊለ ሰማእት ትባላለች
2 አክሊለ ሶክ (አስኬማ መላእክት)
ይሄ አክሊል የአባ እንጦንዮስ አክሊል ሲሆን መነኮሳት የሚያደርኩት አክሊል ነው ይሄ አክሊል በምንኩስና ዓለምን ከናቁ በኋላ የሚገኝ ነው ክርስቶስ በዕለተ አርብ የተቀበለው አክሊለ ሶክ የሚታሰብበት ሲሆኔ ይሄን አክሊል ያደረጉ መነኮሳት እንደ መላእክት በንጽሕና በቅድስና ስለሚኖሩ አስኬማ መላእክት ተብሏል
3 ተክሊል (የተክሊል አክሊል)
ይህ አክሊል በድንግልና ኑረው ለሚጋቡ ኦርቶዶክሳውያን የሚደረግ የድንግልና ምልክት የሆነ አክሊለ ከብካብ ነው ደናግል ላልሆኑ ፈጽሞ የማይደረግ ነው
4 አክሊለ ነገሥት ይህ አክሊል ለነገሥታት ብቻ የሚደረግ ነው ሰሎሞን ሲነግሥ ሲቀባ የተደረገለት አክሊል ነው አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ወአክሊሉ ለሰሎሞን የሰሎሞን አክሊል ነሽ ብሎ የተናገረው የነገሥታት አክሊል እመቤታችን እንደሆነችና ነገሥታት ሲነግሢ ተቀብተው አክሊል እንደሚያደርጉ ለመግለጽ ነው
5 አክሊለ ካህናት
ይህ አክሊል በክህነት የሚያገለግሉ ካህናትና ዲያቆናት የሚያደርርጉት አክሊል ነው
ክህነት ለሌለው ፈጽሞ የማይደረግ ሲሆን የካህናት አክሊል አሰራሩ ከላይ 4 ማዕዘን ሲሆን የዲያቆናት አክሊለም በአሰራር ከካህናት የተለየ ክብ ነው ዲያቆን የቄሱን አክሊል ፈጽሞ ማድረግ አይችልም አምስቱ አክሊላት እነዚህ ናቸው
አሁን አሁን ግን የካህኑን እና የዲያቆኑን አክሊል ሴቶች ሳይቀር አድርገውት እየታየ ስለሆነ እጅግ የሚያሳዝን ነው
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እየተጣሰ ቸል ተብሎ እየታየ ነው ስለዚህ የሊቃውንት ጉባኤ ይሄን ጉዳይ እልባት ሊሰጥበት ይገባል ።

ጾመ ሰብአ ነነዌ
ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡
ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም የካቲት ፫ ቀን ትጀመራለች፡፡
‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሚለው የጽሑፋችን ርእስ እንደሚያስረዳው ይህቺን የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/ ፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር። በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡
ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡
ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛ ነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኔታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡
እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡
እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ ንብረታችሁን ሳይኾን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡
እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡
ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡
እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡
ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል። ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡
የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/። ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡
ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡
ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው። ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ። የነነዌ ሰዎች የተነሳ ሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡
ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡
ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
ለተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE

Telegram
ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
#ዐብይ_ጾም
#ዐብይ_ጾም ፦ማለት ምን ማለት ነው በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹አበየ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡
የዐብይ ጾም የተለያየ ስያሜዎች ዐብይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ ጾሙ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡
#ጾመ_ሁዳዴ፡- ሁዳድ ማለት ሠፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡ ይህም ጾም ደግሞ በቀኑ ብዛት ትልቅ (ሠፊ) በመሆኑ የሁዳዴ ጾም ይባላል፡፡
#የካሳ_ጾም፡- እንዲህ የተባለበት ምክንያቱ ደግሞ አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሳ ጾም ተብሎሏል
#የድል_ጾም ፡-ይህም ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡
#የመሸጋገሪያ_ጾም ፦ጌታችን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ሊያሸጋግረን የጾመው ጾም በመሆኑ የመሸጋገሪያ ጾም ተብሏል።
#ጾም_አስተምህሮ፡- ይህ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለበት ምክንያት ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የተለያዪ ስያሜዎች አሉት
‹‹የመሸጋገሪያ ጾም ››
‹‹የስራ መጀመሪያ ጾም ››
ይህ ፆም ታላቅ መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መፆሙና ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር
መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ
ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ፆምም
በመሆኑ ነው።
ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሶስቱ ርዕሰ ኃጢአት የሚባሉት
#ትዕቢት፣
#ስስት
#ፍቅረ_ነዋይ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል የተመቱበት ስለሆነ ይህ ጾም አብይ (ታላቅ) ተብሏል፡፡
የአብይ ጾም ሳምንታት 8 ናቸው፤
1. #ዘወረደ
2. #ቅድስት
3. #ምኩራብ
4. #መጻጉዕ
5. #ደብረዘይት
6. #ገብርሔር
7. #ኒቆዲሞስ
8. #ሆሣዕና
አቢይ ጾም ሦስቱ ክፍሎች
1. ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል)፤ ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሑድ ያረስ ያለው 7 ቀን ነው።
2. የጌታ ጾም፤ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው።
3. ሕማማት፤ ይህም ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጠበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው።
ይህም 7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነው።
የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስየተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅም በፆም ድል ማድረግን ለእኛ አስተምሮናል። እኛምበዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀርእንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ። በፆም የተጠቀሙ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳንእናቶች እንዳሉን እናስተውል።
ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

#መጻጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛው እሑድ)
➯በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡
➯መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡
➯«38 ዓመት የታመመውን መጻጉዕን ኢየሱስ አዳነው» እንዲሁም ልጁ የታመመበት የመቶ አለቃው «ጌታዬ በቃልህ እዘዝ ልጄ ይድናል፡፡ በቤቴ ጣርያ ሥር አንተ ልትገባ አይገባህም» አለው:: «ጌታ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ዕውር ፈውሰኝ» ብሎ ጮኸ የሚመሩት ሰዎች ዝም በል አሉት፡፡ ዕውሩ ግን እምቢ ብሎ «የዳዊት ልጅ ጌታ ይቅር በለኝ ዕርዳኝ» እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡
➯«በሰንበት ኢየሱስ መጻጉዕን ተነሥ አልጋህን ተሸከም ባለው ጊዜ ቀኑ ሰንበት ነበረ፡፡ መጻጉዕም አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ገባ የእግዚአብሔር ልጅ በሰንበት ፈውሷልና «በሰንበት ድውያንን ፈወሰ የዕውራንንም ዓይኖች አበራ እያለ 38 ዓመት በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዞ ሲማቅቅ የኖረውን መጻጉዕንና ሌሎቹን በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙትን ሕሙማን መፈወሱን በጠቅላላው ለምፅ ማንጻቱን፣ ዕውር ማብራቱን፣ አንካሶችን ማርታቱን፣ ልምሾዎችን ማዳኑን፣ አጋንንትን ማውጣቱን፣ወዘተ እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ዕለቱና ሳምንቱ መጻጉዕ ተብሏል፡፡
➯ስለዚህም ይህ ሰንበት የሕሙማን ፈውስ መታሰቢያ ዕለት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በነዚህ ሁሉ ታሪኮች የመጻጉዕንና የሌሎቹን ሕሙማን ሁሉ ደኅንነት ታሪክ እንረዳለን፡፡ የሰንበቱም ስያሜ ልብ ወለድ አጠራር ሳይሆን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢርና የጾመ ድጓውን ይትበሀል ተከትሎ የተሰየመ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡
በዕለቱ በቅዳሴ ላይ የሚነበቡት
ምንባቦች የሚከተሉት ናቸው፦
➯1ኛ. የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ገላትያ ሰዎች 5 ፡ 126
➯2ኛ. የሐዋርያው የቅዱስ ያዕቆብ መልእክት 5፡14-20
➯3ኛ. የሐዋርያት ሥራ 3፡1-12
እንዲሁም የዕለቱ ምስባክ፦
➯በመዝሙር 4ዐ ቁጥር 3 ላይ የሚገኘው
➯እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ላይ ሳለ ይረዳዋል፡፡ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ፡፡ የሚለው ይሆናል፡፡የዕለቱ የወንጌል ንባብም
➯በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ከቁጥር 1 እስከ 25 ድረስ ያለው ነው፡፡
➯ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፡፡
➯ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
#SHARE'
❤️🔥 🔗 🙅♂️ 👍
ˡᶦᵏᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ደብረ ዘይት
የዐብይ ጾም አምስተኛ እሑድ(ሳምንት)
(የዐብይ ጾም እኩሌታ)
ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው፡፡ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:- ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሠረት ነገረ ምጽአቱን እንድናስታውስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነው።
ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ ዳግም ምጽአቱ ምልክቶች ምን እንደሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ላይ በሦስት መሠረታዊ ክፍሎች ከፍሎ ጽፎልናል፡፡
፩. ሃይማኖታዊ ምልክቶች
"እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ" /ማቴ 24፥5/፡፡
፪. ፖለቲካዊ ምልክቶች
“ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ” /ማቴ 24፥6/ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና” /ማቴ 24፥7/
፫. ተፈጥሯዊ ምልክቶች
“ረሐብም ቸነፈርም የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል” /ማቴ.24፥7/
ከላይ ያየናቸውን ምልክቶች በዓለማችን ላይ ዕለት ዕለት የምናየው የምንሰማው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸውን ምልክቶች የቤተ ክርስቲያናችን አራት ዐይና ሊቃውንት የወንጌሉን ገጸ ንባብ እንዲህ ብለው ያመሰጥሩታል፡፡
“እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸው” /ማቴ.24፥8/
ምጥ ሲመጣ አስቀድሞ የምጡ መጀመሪያ ሕመም (ጣር) እንዳለ ሁሉ የዓለምም ፍጻሜ በጣር ነው የሚጀምረው። ይህንንም ጌታችን በግልጽ አስረድቶናል፦ ጦርና የጦር ወሬ መሰማት፣ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ መነሳት፣ ርሃብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ መታየት ለዓለም ፍጻሜ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸዉ። እነዚህ ነገሮች በሁሉም ቦታ በአንድ ጊዜ ላይከሰቱ ይችላሉ፤ ነገር ግን በልዩ ልዩ ቦታዎች ለብዙ ዘመናት ታይተዋል፤ እየታዩም ናቸው።
“ስለ ስሜ በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” /ማቴ.24፥9/
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለ ስሜ ክርስቲያኖች በመሆናችሁ በዓለም ዘንድ ትጠላላችሁ" ብሎናል። ዓለም ክፉ ስለሚሠራ የጥሩ ነገር ተቃራኒ ሆኖ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል። ጌታችን “ብርሃንም ወደ ዓለም ስለመጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፣ሥራዉም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል” /ዮሐ. 3፥19-21/ እንዳለን በክፉ ሥራ ውስጥ ያለው ይህ ዓለም በጎ ሥራ የሚሠሩትን የክርስቶስን ተከታዮች ይጠላል። ጨለማ ብርሃንን ብርሃንም ጨለማን እንደሚጠላ፤ ይህ ዓለም እኛን እንዲጠላን፣ እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ ይህንን ዓለም ልንጠላው ይገባል።
አሁን ባለንበት ዘመን ክርስትና እየተጠላ፣ እየተናቀ ነው ያለው። “ባደጉት” ዓለማት ባዶ አብያተ መቅደሶች ቀርተው እነሆ እንመለከታቸዋለን፤ ትውልዱ በዓለም ስሜትና በሥጋ ፈቃድ ብቻ እየሔደ ነው። ክርስቲያን ነን በሚሉትም አውሮፓውያን ዘንድ የአንገት በላይ የማስመሰል ክርስትና እንጂ እንደ ቅዱስ ቃሉ የሚጓዝ አማኝ ማግኘት አይቻልም። እውነተኞች አይወደዱም፤ ይገፋሉ፤ ይናቃሉ። ሁኔታው የዘመኑ ፍጻሜ እጅግ እየቀረበ መምጣቱን በእርግጥ ያስረዳል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህም በላይ “ስለ ስሜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል” ብሏል። ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ማንንም ሳይበድሉ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ በልዩ ልዩ ሀገራት ክርስቲያኖች ሰማዕትነትን እስከ አሁን ድረስ እየተቀበሉ ነው፡፡ቅዱስ ጳዉሎስ “ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” /ሮሜ 8፥36/ እንዳለው። ይህ በቅዱሱ በክርስቶስ ስም መጠላትና መከራ መቀበል ከዓለም የሚጠበቅ የፍጻሜዉ ዘመን ምልክት መሆኑን አውቀን መዘጋጀትና ከሐዋርያው ጋር “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” /ሮሜ 8፥37/ እያልን በእምነታችን ጸንተን መጋደል ይገባናል።
የክርስቲያኖች ቁጥር እያነሰ መምጣት፣ የአብያተ ክርስቲያናት መዘጋት፣ ሰው ሰው የሚያሰኘውን ክብርና ሞገስ ትቶ በግብሩ እንስሳትን ሲመስል የቅድስና ሕይወት ሲጠላና ሲናቅ፤ በአንጻሩ ደግሞ የሰው ልጅ ለረከሰው ለዚህ ዓለም ምኞትና ፈቃድ ሲገዛ ስናይ የዚህ ዓለም ፍጻሜ ጊዜው እየደረሰ መሆኑን አውቀን፤ ኖኅ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቢኖርም ራሱን በቅድስና ጠብቆ እንደኖረ /ዘፍ.6-8/፤ ሎጥም እንዲሁ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ሲኖር በነርሱ ኃጢአት እንዳልተባበረ /ዘፍ. 19/ ከዚህ ዓለም ክፉ ሥራ ተለይተን ራሳችንን በቅድስና በመጠበቅ እንጋደል። ዓለሙ ስለ እምነታችን ቢጠላንም እኛም ስለ ክፉ ሥራው ንቀነው መኖር የግድ መሆኑን እንወቅ እንጂ ስለ እምነት፣ ስለ ቅድስናም ከዓለም በጎ ነገር አንጠብቅ። በተለያዩ ሁኔታዎች የሚደርሱብንን ፈተናዎች ሁሉ በትዕግስት እንቀበላቸው እንጂ በማማረር አንዘን፤ ምክንያቱም ስለ ስሜ በዓለም ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ተብለናልና።
“የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል!” ማቴ.24፥15/
ዓለም ራሱን በማርከስ ብቻ ሳይወሰን በፍጻሜ ዘመን በተቀደሰው ስፍራ እንኳን ሳይቀር የጥፋትን ርኩሰት ያቆማል። የተቀደሰው ስፍራ የተባለው በተቀደሰ ሃይማኖት የሚኖሩትን ሀገራት፣ ሕዝቦች የሚመለከት ነው። እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉትን ሀገራት ዲያብሎስ በመልእክተኞቹ ላይ አድሮ በብዙ ርኩሰት ተፈታትኗቸዋል፤ እየተፈታተናቸውም ነው። የየሀገራቱን እምነትና ታሪክ ለማጥፋት ጥሯል፤ ብዙውንም የቅድስና ሥርዓት በርዟል፤ የቻለውንም ከነጭራሹ አጥፍቶታል። አሁን እንኳ አምልኮተ እግዚአብሔር በሚፈጸምባቸዉ ቅዱሳት መካናትና ገዳማት ሳይቀር በልዩ ልዩ ምክንያት የጥፋት ርኩሰት አዉጇል። ይህም የፍጻሜ ዘመኑ አንዱ ምልክት ስለሆነ አንባቢዉ እንደተባለ የዘመኑን መፍጠን የጊዜውን መድረስ በመረዳት መዘጋጀት ይገባናል።
“ብዙ ሐሰተኛዎች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ” /ማቴ.24፥11/፡፡
ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት በየዘመኑ ተነስተው እውነተኛይቱን ታግለዋታል፤ ሊያጠፏት ባይችሉም እንኳን ብዙ ልጆቿን ነጥቀው ወስደውባታል። የነዚህን ሠራተኞች አመጣጥ ከባድ የሚያደርገው በተአምራትና በድንቅ ምልክቶች መምጣታቸው ነው። ጌታችን እንደተናገረ “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” /ማቴ.24፥24/ ስለዚህ በምትሐታዊ ምልክቶቻቸው የብዙ የዋሃንን ልብ በማታለል ከተቀደሰ እምነታቸው እያስኮበለሉ አጥፍተዋቸዋል፤ በማጥፋትም ላይ ይገኛሉ። ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ “ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነዉ እንደሆነ መርምሩ”/1ዮሐ 4፥1-3/ አለን።

ቅዱስ ጳዉሎስም “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸዉን እየለወጡ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞ ሠራተኞች ናቸው። ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለዉጣልና” ብሏል /2ቆሮ.11፥13-15/። ሐዋርያት ሁሉ በየመልእክቶቻቸው ከሐሰተኞች አስተማሪዎች እንድንጠበቅ ደጋግመው አሳስበዋል። ብዙ ሰው ግን በየዋሕነት ስለሚጓዝ የነዚህ ተኩላዎች ሰለባ ሆኗል።
ጊዜው ክፉ ነውና የሐሰተኞች ነቢያት መረብ ጠልፎ ወደ ሐሰተኞች ክርስቶሶች እንዳይወስደን #በጥንቃቄ መጓዝ ይጠበቅብናል። ሐዋርያዉ ቅዱስ ይሁዳም በመልእክቱ ቁ.3 “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ” ሲል እንደመከረን በተቀደሰ እምነታችን እስከመጨረሻ ጸንተን እንጋደል።
#በቅዳሴ #ጊዜ# የሚነበቡ #ጥቅሶች፦
-፩ኛ ተሰ ፬፥፲፫ እስከ ፍጻሜ
-፪ኛ ጴጥ ፫፥፯-፲፭
-የሐዋ ሥራ ፳፬፥፩-፳፪
#ምስባኩም፦ መዝ ፵፱፥፫
"እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም #እሳት ይነድድ ቅድሜሁ"
"እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል"
#ወንጌል፦ ማቴ ፳፬፥፩-፴፮

#መጋቢት_27
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
እንኳን ለአባታችንና ለአምላካችን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!!
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
✞ መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም - ክ ር ስ ቶ ስ ✞
ጌታችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈፀመው የማዳን ስራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት።
ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና፤ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አስረው ሲደበድቡት አድረዋል።
ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት።
ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዘበቱበት።
ራሱንም በዘንግ መቱት።
እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ። በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት። በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ገረፉት።
ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት። ሰባት ታላላቅ ታአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ። ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ።
በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ። አስራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት።
በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ። ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍጹም ለቅሶን አለቀሰ። ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ።
ለእኛ ለኃጥአን ፍጡሮቹ ሲል ይህንን ሁሉ መከራ የታገሰ አምላክ ስለ አሥራ ሦስቱ ኀማማቱ፤ አምስቱ ቅንዋቱ፤ ስለ ቅዱስ መስቀሉ፤ ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን።
-------------------------------------------
"በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ። ሕማማችንንም ተሸክሟል። እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ። ስለ በደላችንም ደቀቀ። የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ። በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።" (ኢሳ ፶፫፥፬-፭)
<<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>
#ስንክሳር_ዘወርሃ_መጋቢት
ይቀላቀሉ ሌሎችንም ይጋብዙ!
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
እንኳን ለአባታችንና ለአምላካችን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!!
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
✞ መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም - ክ ር ስ ቶ ስ ✞
ጌታችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈፀመው የማዳን ስራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት።
ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና፤ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አስረው ሲደበድቡት አድረዋል።
ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት።
ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዘበቱበት።
ራሱንም በዘንግ መቱት።
እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ። በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት። በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ገረፉት።
ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት። ሰባት ታላላቅ ታአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ። ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ።
በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ። አስራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት።
በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ። ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍጹም ለቅሶን አለቀሰ። ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ።
ለእኛ ለኃጥአን ፍጡሮቹ ሲል ይህንን ሁሉ መከራ የታገሰ አምላክ ስለ አሥራ ሦስቱ ኀማማቱ፤ አምስቱ ቅንዋቱ፤ ስለ ቅዱስ መስቀሉ፤ ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን።
-------------------------------------------
"በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ። ሕማማችንንም ተሸክሟል። እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ። ስለ በደላችንም ደቀቀ። የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ። በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።" (ኢሳ ፶፫፥፬-፭)
<<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>
#ስንክሳር_ዘወርሃ_መጋቢት
ይቀላቀሉ ሌሎችንም ይጋብዙ!
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
Telegram
ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
ኒቆዲሞስ፡የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት
በመ/ር ጌታቸው በቀለ
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሠረት ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ በዚህ ሰባተኛው ሳምንት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኒቆዲሞስ ለተባለ የአይሁድ አለቃ ያስተማረው ትምህርት ይነበባል፣ ይተረጎማል፣ ይዜማል /ዮሐ ፫፥፩-፳፩/፡፡
ኒቆዲሞስ ማን ነዉ?
ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡: ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል /ዮሐ ፩-፪/፡፡ በአይሁድ አለቆች ፊትም “ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ እግዚአብሔርነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሣ መርምርና እይ” አሉት እንጂ አልተቀበሉትም /ዮሐ ፯፥፵፰-፶፪/። ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ /ዮሐ ፲፱፥፴፱/። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል።
ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ብቻ ሳይሆን የፈሪሳውያን አለቃ፣ የኦሪት መምህር ብቻ ሳይሆን የኦሪት ምሁርም ነበር፡፡ በእርሱ ደረጃ የነበሩ ታላላቅ የአይሁድ ምሁራን መንፈሳዊ ሥልጣናቸውና ሹመታቸው የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ረስተው በሕዝቡ ላይ የሚመጻደቁ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው ዕውቀትን የሚገልጥ እውነተኛ አምላክ፣ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም ሲገለጥ የአይሁድ ምሁራን የጌታን መገለጥ አልወደዱትም፡፡ የእርሱ ትሕትና የእነርሱን ትዕቢት የሚያጋልጥ ነበርና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሄዱትን ሁሉ ይነቅፉ ይከስሱ ነበር፡፡ ጌታችንም የፈሪሳውያን ሐሳባቸው በግብዝነት የተሞላና ከንቱም እንደሆነ ነግሯቸዋል፡፡ ለደቀመዛሙርቱም ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ የሚበልጥ ሥራን እንዲሰሩ አስጠንቅቋቸዋል /ማቴ.፭፥፳፤ማቴ.፲፮፥፮/፡፡
ኒቆዲሞስ ወደ ጌታችን በሌሊት የሄደዉ ለምንድነው? ለምን በቀን አልሄደም?
ኒቆዲሞስ በመጀመሪያ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው በቀን ሳይሆን በሌሊት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በሌሊት ወደ ጌታችን ከሄደባቸው ምክንያቶች አንዱ በቀን መሄድን ስለፈራ ነው። ለዚህም የቤተ ክርሰቲያን አባቶች በዋናነት ሁለት ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ፡፡ የመጀመሪያው የአይሁድ መምህር ሆኖ ሳለ በቀን በሕዝብ ፊት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መማር ስላፈረ ነው የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ አይሁድ “ከእኛ ወገን በክርስቶስ ያመነ ቢኖር ከምኩራብ ይሰደድ” የሚል ዐዋጅ ዐውጀው ነበርና ያንን ፈርቶ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ፍራቻዎች ኒቆዲሞስን ወደ ክርስቶስ ከመምጣት አላገዱትም፡፡
ኒቆዲሞስ በርቀት በአደባባይ ድንቅ ተአምራትን ሲያደርግ ያየውን ኢየሱስ ክርስቶስን ቀርቦ መጠየቅ መማር ፈልጓል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካደረጋቸው ተአምራት የተረዳው ነገር ቢኖርም ቀርቦ ደግሞ ከእርሱ ከራሱ ስለማንነቱ መስማት ፈልጓል፡፡ ወደ ክርስቶስም ቀርቦ “መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን” አለው /ዮሐ.፫፥፪/፡፡
ኒቆዲሞስ ግን ከእነዚህ ከፈሪሳዊያን መካከል የተገኘ ልዩ ምሁረ ኦሪት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ራሱን ለእውነት ልቡን ለእምነት አዘጋጅቶ ከሁሉ ቀድሞ በሌሊት ክርስቶስን ፍለጋ የመጣ ከእነዚህ ፈሪሳዊያን ወገን ተለይቶ ወደ ጽድቅ መንገድ የተጠራ ነው፡፡ ሹመት እያለው ሁሉ ሳይጎድልበት በዙርያው የነበሩት ከእኛ በላይ ማን አዋቂ አለ የሚሉ ከእውነት ጋር የተጣሉ ጌታችንን የሚያሳድዱ በእርሱም የሚቀኑና ጌታችንንም ለመግደልም ዕለት ዕለት የሚመክሩ ሁነው ሳለ ኒቆዲሞስ ግን እውነትን ለማወቅ እልቅናው ሳይታሰበው፣ ከአካባቢው ጋር መመሳሰልን ሳይመርጥ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሊማር በሌሊት መጣ፡፡ መምህረ ትሕትና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የኒቆዲሞስን ትሕትናውን ተቀብሎ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትውልድ ሁሉ የሚማርበትን ረቂቁን ምስጢረ ጥምቀትን አስተማረው፡፡
ዳግመኛ የመወለድ ምስጢር
ኒቆዲሞስ ዳግመኛ የመወለድን ምስጢርን ለማወቅ ልቡናውን ከፍ ከፍ አደረገ፡፡ ኒቆዲሞስ በመጀመርያ የጥምቀትን ነገር ሲሰማ ለመቀበል ተቸግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ግን የኒቆዲሞስን አመጣጥ በማየት ልቡናውንም ከፍ ከፍ ስላደረገ ምስጢረ ጥምቀትን ገለጸለት፡፡ “ቅዱሱን ማወቅ ማስተዋል ነው” ተብሎ በምሳሌ መጽሐፍ እንደተጻፈ /ምሳ 9፥11/ ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ኅብረት ወጥቶ በትሕትና ወንጌልን ለመማር፣ በሃይማኖት ልቡናውን ለእግዚአብሔር ቃል አዘጋጀ፡፡ ለአብርሃም የግዝረትን ጸጋ የሰጠ ጌታ በትሕትና ለቀረበው ኒቆዲሞስ የግዝረት ጸጋ ፍጻሜ የሆነች የልጅነት ጥምቀትን ነገር አስተምሮታል፡፡
ኒቆዲሞስ ወደ መድኃኔዓለም ለመማር የሄደው በሌሊት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በሚታሰብበት የዐቢይ ጾም ሰንበት በጸሎተ ቅዳሴ የሚዜመው የክቡር ዳዊት መዝሙር “በሌሊት ጎበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው፣ ፈተንኸኝ፣ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር” ይህን የሚያስረዳ ነው /መዝ.፲፮፥፫/፡፡ ሌሊት በባሕሪው ሕሊናን ለመሰብሰብ በተመስጦ ለመማር የሚመች ነው፡፡ ክርስትናም በተጋድሎ ሕይወት በመትጋት ሥጋን በቀንና ሌሊት ለነፍስ እንዲገዛ በማድረግ የሚኖር ሕይወት ነው፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱን “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ” ባለው መሠረት ቤተክርስቲያንም በቀንና በሌሊት በኪዳኑ በቅዳሴው በማህሌቱ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡
ዮሐንስ ወንጌላዊ ይህንን የኒቆዲሞስን ምስክርነት “ከእነርሱ አንዱ በሌሊት ቀድሞ ወደ እርሱ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው። እነርሱም መለሱና፡- አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ አሉት። እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ሄደ።” በማለት ገልጾታል /ዮሐ.፯፥፶-፶፪/፡፡ ኒቆዲሞስ ያለፍርሐትና ያለ ሀፍረት በካህናቱ ፊት እውነትን መስክሯል፡፡ ካህናቱን መጽሐፍ ጠቅሶ እውነትን ተናግሮ አሳፍሯቸዋል፡፡ ኒቆዲሞስ እስከ መጨረሻው በመጽናት ለታላቅ ክብር በቃ፡፡

ኒቆዲሞስም ከጌታችን በተማረው ትምህርት ጸንቶ ለመኖር የበቃ አባት ነው፡፡ የሃይማኖቱ ጽናትም በተግባር የተፈተነ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የአይሁድን ድንፋታ ሳይፈራ “እሱን ያገኘ ያገኘኛል” ሳይል በድፍረት የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን በንጹሕ የተልባ እግር በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር፣ በጌቴሴማኒ የቀበረ ሰው ነው /ዮሐ.፲፱፥፴፰/፡፡ ኒቆዲሞስ ከሐዲስ ኪዳን ካህናት ቀድሞ የጌታችንን ነፍስ የተለየው መለኮት የተዋሐደው ክቡር ሥጋ ለመገነዝ የበቃ አባት ነው፡፡ የጌታችንን ክቡር ሥጋ ገንዘው ሲቀብሩም በጸናች የተዋሕዶ እምነት ጌታ እንደገለጠላቸው “ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል፣ ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት” የሚለውን ቤተክርስቲያናችን እስከ ዕለተ ምጽአት የክርስቶስን ሥጋና ደም ስትባርክ የምትጠቀምበትን ጸሎት እስከ ፍጻሜው እየጸለዩ ነበር፡፡ በዚህም ኒቆዲሞስ ከሐዲስ ኪዳን ካህናት ቀድሞ ምስጢረ ጥምቀትን ከጌታ እንደተማረ፣ የሐዲስ ኪዳንን የምስጢራት አክሊል ምስጢረ ቁርባንንም እንዲሁ ተማረ፡፡ ይህንንም በሚመለከት ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ አብሮት ይቀድስ የነበረውን ንፍቅ ካህን በባረከበት አንቀጽ “በዚህ ምስጢር እየተራዳኝ ከእኔ ጋር ያለ ይህንን ካህን እርሱንም እኔንም ሥጋህን እንደገነዙት እንደ ዮሴፍና እንደ ኒቆዲሞስ አድርገን” /ቅዳሴ ማርያም፤ ቁ.115/ ብሏል፡፡
እንደ ማጠቃለያ
እኛም እንደ ኒቆዲሞስ በዕውቀታችን፣ በሥልጣናችን፣ በሀብታችን፣ ባለን ማንነት ሳንታበይ ራሳችንን ዝቅ በማድረግ የእውነተኛ አባቶችን ትምህርት፣ ምክርና ተግሣጽ ልናዳምጥ በተግባርም ልናውለው ይገባናል፡፡ ምድራዊ አመክንዮ ሳያሰናክለን በቀንና በሌሊት ወደ አማናዊት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለምስጋና መሄድ ይኖርብናል፡፡ ክርስትና ምድራዊ ስጦታና ተዓምራት በሚገለጥበት በገሊላ ባሕር አጠገብ ብቻ ሳይሆን መከራና ስቃይ ባለበት በቀራንዮም መገኘትን ይጠይቃል፤ በፈተናና በመከራ ጊዜም ቢሆን በእምነት ልንጸና የበለጠም በመታመን ልናገለግል ይገባል፡፡
ከኒቆዲሞስ ሕይወት ተምረን በሃይማኖት እንድንጸና የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል” /ማር.፲፮፥፮/ በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንሆን ዘንድ ይፍቀድልን፤ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፤ አሜን፡፡
ምንባባት ኒቆዲሞስ
መልዕክታት
✍️ ሮሜ ፯፥፩-፲፱
✍️ 1ኛ ዮሐ.፬፥፲-ፍጻ
ግብረ ሐዋርያት
✍️ ሐዋ.ሥራ ፭፥፴፬—ፍጻ
ምስባክ
✍️ መዝ.፲፮÷፫
ሐውጽከኒ ሌሊት ወፈተንኮ ለልብየ፥
አመከርከኒ ወኢተረክበ አመጻ በላዕሌየ፤
ከመ ኢያንብብ አፍየ ግብረ ዕጓለ እመሕያው
ትርጉም፦ ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም። የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፡፡
ወንጌል
✍️ ዮሐ.፫÷፩-፳
የዕለቱ ቅዳሴ
✍️ ቅዳሴ እግዚእ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቤ መጻሕፍት፡-
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ሃይማኖተ አበው
✍️ ቅዳሴ ማርያም
✍️ የቤተክርስቲያን መዝገበ ቃላት

Forwarded from Elohe pictures (Elohe pictures)
🌟ELOHE PICTURE
👍ㅤ ⬇️ㅤ ➡️ ✉️ Lᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
➪ ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ
🔻🔻ይቀላቀሉን 🔗🔗⏰
https://www.tgoop.com/+Ci5F1FcleWtlZThk
ተስፋ ቆርጠህ ቁጭ ብለህ እስከሚነጋልህ አትጠብቅ። እንደ ኒቆዲሞስ "በሌሊት ወደ ኢየሱስ ሒድ" ክርስቶስ ያለበት ሌሊት ከቀን ይልቅ ብሩሕ ነው።
👍ㅤ ⬇️ㅤ ➡️ ✉️ Lᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
➪ ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ
🔻🔻ይቀላቀሉን 🔗🔗⏰
https://www.tgoop.com/+Ci5F1FcleWtlZThk
Forwarded from Elohe pictures (Elohe pictures)
🌟ELOHE PICTURE
👍ㅤ ⬇️ㅤ ➡️ ✉️ Lᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
➪ ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ
#Elohe_picture #ኦርቶዶክስ #የተደረገለት
🔻🔻ይቀላቀሉን 🔗⏰
https://www.tgoop.com/+Ci5F1FcleWtlZThk
7ተኛ ሳምንት
መዝሙር 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም።
⁴ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።
👍ㅤ ⬇️ㅤ ➡️ ✉️ Lᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
➪ ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ
#Elohe_picture #ኦርቶዶክስ #የተደረገለት
🔻🔻ይቀላቀሉን 🔗⏰
https://www.tgoop.com/+Ci5F1FcleWtlZThk
ሆሣዕና በአርያም = እንኳን አደረሳችሁ!
☞ የዐቢይ ጾም ፰ኛ ሳምንት #ሆሣዕና
✔ የዕለቱ መዝሙራት፣ መልእክታት፣ ምስባክና ወንጌል
❖ የሆሣዕና ዋዜማ /የቅዳሜ ማታ መዝሙር
«ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ።»
ትርጉም፦
የፋሲካ በዓል ሳምንት ሲቀረው የእውነተኛ አምላክ ደቀ መዛሙርት የእግዚአብሔር ሀገር ወደ ሆነችው ደብረ ዘይት ቁልቁለት ሲደርሱ ወደ እርሱ ለመታዘዝ ቀረቡ፤ ብዙ ሕዝብ፣ ልጆችና ሽማግሌዎችም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ተጭኖ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸው ዘንድ በፍጹም ደስታ ኢየሩሳሌም ገባ።
#መልዕክታት
➊. ዕብራ. ፰:፩-ፍጻሜ /8÷1-ፍጻሜ
ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን። (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➋. ፩ኛ ጴጥ.፩÷፲፫ እስከ ምዕ ፪÷፲፩
ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➌. ግብረ ሐዋርያት
የሐዋ. ፰:፳፮-ፍጻሜ /8÷26-ፍጻሜ
የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን
ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው
መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
✞ ምስባክ
ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ፡፡
በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡
እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ፡፡
ትርጉም፦
በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዓቱ ነውና÷
(መዝ.፹÷፫)
.
✝ ወንጌል
ዮሐ.፲፪÷፩-፲፩
ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
፠ የሌሊት ሆሣዕና
+ ምስባክ
ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር።
ባረክናክሙ እምቤተ እግዚእብሔር፡፡ እግዚእብሔር እግዚእ አስተርአየ ለነ፡፡
ትርጉም፦
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤
ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ፡፡
ጌታ እግዚአብሔር ተገለጠልን፤
(መዝ.፻፩፯÷፳፮)
.
✝ ወንጌል
ሉቃ.፲፱÷፩-፲፩
ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢያራኮ ገብቶ በዚያ ያልፍ ነበር፡፡ እነሆ÷ የቀራጮች አለቃ ስሙ ዘኬዎስ የተባለ አንድ ሰው ነበር፤
(ተጨማሪውን ያንብቡ)
✞ ዘነግህ
(በጊዜ ዑደት ውስተ ቤተ መቅደስ)
+ ምስባክ
ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር።
ወቆማ እገሪነ ውስተ አዕፃድኪ ኢየሩሳሌም።
ኢየሩሳሌምሰ ሕንፅት ከመ ሀገር።
ትርጉም፦
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ስላሉኝ ደስ አለኝ፡፡
ኢየሩሳሌም ሆይ÷ እግሮቻችን በአደባባዮችሽ ቆሙ፡፡
ኢየሩሳሌምስ እንደ ከተማ የታነጸች ናት፡፡
(መዝ ፻፳፩ ፣ ፩ /121፥1)
+ ወንጌል
ማቴ. ፳፥፳፱-ፍጻሜ
ከኢያሪኮም በወጣ ጊዜ ብዙ ሰዎች ተከተሉት፡፡ እነሆ÷ ሁለት ዕውራን በመንገድ አጠገብ ተቀምጠው ነበር፤ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
✞ ምስባክ
ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር፡፡
ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን :-
እስመ አጽንዐ መናስግተ ኆኃትኪ፡፡
ትርጉም:-
ኢየሩሳሌም ሆይ÷ እግዚአብሔርን አመስግኚ÷
ጽዮንም ሆይ÷ አምላክሽን አመስግኚ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጸንቶአልና÷
መዝ.፻፵፯÷፩
.
★ ወንጌል
ማርቆስ ፲፥፵፮-ፍጻሜ
ወደ ኢያሪኮም ገባ፤ ከኢያሪኮም በወጣ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ብዙ ሰውም ነበረ፤ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
+ ምስባክ
ግበሩ በዓለ በትፍሥሕት፣
በኃበ እለ ያስተሐምምዎ፣
አስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ።
ትርጉም፦
ጌታ እግዚአብሔር ተገለጠልን፤
እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በሚያስተነትኑበት በደስታ በዓልን አድርጉ፡፡
(መዝ ፻፲፯፥፳፯)
.
+ ወንጌል
ማቴዎስ ፱፥፳፮ እስከ ምዕ ፲÷፲፰
.
☞መዝሙር => ዘምዕዋድ
አርእዩነ ፍኖቶ ወንሑር ቤቶ እስመ እምጽዮን ይወጽእ ሕገ ወቃለ እግዚአብሔር እምኢየሩሳሌም ንሣለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት ተቀበልዋ ለታቦት እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን
.
☞መዝሙር => <<ሰመያ አብርሃም>>
ሰመያ አብርሃም ወይቤላ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ በዕምርት ዕለት በዓልነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
.
☞መዝሙር => ወትቤ ጽዮን
ወትቤ ጽዮን አርኅው ሊተ አናቅጸ ይባኡ ሕዝብ ብዝዙኃን ወያዕትቱ ዕብነ እምፍኖት ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም
.
✝ መዝሙር => "ባርኮ ያዕቆብ"
ባረኮ ያዕቆብ ለይሁዳ ወልዱ ወይቤሎ ሀሎ ንጉሥ ዘይወጽእ እምኔከ ዘየሐጽብ በወይን ልብሶ ወበደመ አስካል ሰንዱኖ ንጉሦሙ ውእቱ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም
.
★+መልዕክታት
➊ ዕብራ ፱÷፲፩-ፍጻሜ
ክርስቶስ ግን ለምትመጣይቱ መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ÷ የሰው እጅ ወደ አልሠራት÷ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➋1ኛጴጥ ፬÷፩-፲፪
ክርስቶስ ስለ እኛ በሥጋው ከተሰለቀ÷ እናንተም ይህቺን ዐሳብ ጋሻ አድርጋችሁ ኑሩ፤ በሥጋዉ መከራ የተቀበለ ከኀጢአት ድኖአልና፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➌ የሐዋ/ሥራ ፳፰÷፲፩-ፍጻሜ
ከሦስት ወር በኋላም በዚያች ደሴት ወደ ከረመችው ወደ እስክንድርያ መርከብ ወጣን፤ በዚያች መርብ ላይም የዲዮስቆሮስ ምልክት ነበረባት፤ ይኸውም “የመርከበኞች
አምላክ” የሚሉት ነው፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
✞ ምስባክ
እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ፡፡
በእንተ ጸላዒ፡፡
ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡
ትርጉም፦
ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡
ስለ ጠላት÷
ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡
(መዝ ፰:፪ /8÷2)
.
+ ወንጌል
ዮሐንስ ፭÷፲፩-፴፩ /5÷11-31
እርሱም መልሶ÷ “ያዳነኝ እርሱ፡- አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ” አላቸው፡፡ አይሁድም... (ተጨማሪውን ያንብቡ)
✞ ቅዳሴ = ዘጎርጎርዮስ (ነአኵቶ) [በዕዝል ዜማ]
♦-♥ መልካም የሆሣዕና በዓል ♥ -♦

Forwarded from Elohe pictures (࿈ ᙘᴇꋊɪ ፲፮ ♱¹²)
ውድ የቻናላችን ተከታዮች
ከዚህ በፊት በጠየቃችሁን መሰረት የአብነት ትምህርት
ምርጫችሁን ያደረጋችሁ በመመዝገብ በብፁዕነታቸው አማካኝነት በነፃ አብነት መማር ትችላላችሁ
👉ቅኔ
👉አቋቋም
👉ጾመ ድጓ/ምዕራፍ ወይስ ሌላ...
ምን እከፍላለው ብለው ሳይጨነቁ ፣ ያለ ምንም ክፍያ ልናስተምሮት በonline ዝግጅታችንን ጨርሰናል !!!
ሰፊ ማብራርያ የምትፈልጉ
👇👇👇👇👇👇👇
@Kinfemikael12
ማነጋገር ትችላላችሁ
በተጨማሪ
👉 የፈለጉትን ትምህርት ቀለል ባለ መንገድ እና በአጭር ጊዜ ለማስጨረስ የራሳችን ማስተማሪያ መንገድ አዘጋጅተን እየጠበቅናችሁ ነው
👉 በእያንዳንዱ ጉባኤም ከ50 በላይ ተማሪ ስለማንቀበል ሳይሞላብዎት በፍጥነት ይመዝገቡ🙏
https://www.tgoop.com/Abnetschoolcalifornia

👉 ልዩ ዕለት
የዛሬቱ ዕለት ከሁሉም ዕለታት ልዩ ዕለት ናት የድንቅ ምሥጢር መገለጫ ልዩ ዕለት
ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት ለአሐዱ ብእሲ እንዲል ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይይዙታል ማለትም በሰባቱ ዕለታት ተፈጥረው የተመለኩ ፍጥረታት የአምላክን አምላክነት ይመሰክራሉ ማለት ነው የመሰከሩባት ልዩ ዕለት
አንድም ሰባቱ ተአምራት ተፈጽመው ጌትነቱን የሚሰብኩባት ልዩ ዕለት
➟ ፀሐይ የጨለመባት ልዩ ዕለት
➟ጨረቃ በደም የታጠበችባት ልዩ ዕለት
➟ከዋክብትም ጽናተቸውን የለቀቁባት ልዩ ዕለት
➟ካምስት መቶ ብቅ ከስድስት መቶ ዝቅ የሚሉ ሙታን ከመስቀሉ እግርጌ እንደ አሸን የፈሉባት ልዩ ዕለት
➟ መቃብራት የተከፈቱባት ሙታን የተነሱባት ልዩ ዕለት
➟ ድንጋዮች የተፈተቱባት ልዩ ዕለት
➟የቤተ መቅደሱ ከሦስት ካራት የተቀደደባት ልዩ ዕለት
➣ መድኀን ክርስቶስ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በፈቃዱ የለየባት ልዩ ዕለት
➣ ምእመንንም የሞሸረባት ልዩ ዕለት
➣ እጁን በደም ነክሮ ለኖረ ሽፍታ ወንበዴም ምሕረት የወረደባት
➣ገነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተችባት ልዩ ዕለት ወዘተርፈ
በአጠቃላይ ከሰው ልጆች ይልቅ ደግሞ ግዕዛን የሌላቸው ፍጥረታት እግዚአብሔርነቱን የመሰከሩባት ልዩ ዕለት ናት
➣ እኛስ የፀሐይን ያህል መስክረን ይሆን ?
የጨረቃን ያህልስ እንባ አልቅሰን ደም ደም አልቅሰን እዝኅ በማለቅስ በእንባ በደም በመራጨት መስክረን ይሆን ?
የከዋክብትን ያህልስ መስክረን ይሆን ?
የሙታንን ያህልስ
የድንጋዮችን ያህልስ ልባችን ተሰንጥቆ ይሆን ?
የመጋረጃውን ያህል ምን ያህል ተብሰክስከን ይሆን ?
➟ ነገሩስ ከእነዚህ ሁሉ እንደምናንስ ምንም እንደማይሰማን ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ገልጾታል
እስኪ እንስማው
"ፀሐይ ሰኢኖ ጽዕለተ እግዚእ ጸዊረ ብርሃኖ ለጽልመት ሜጠ ወንሕነሰ እም ጽልመት አከይነ ወኢ እምልብነ ንፈቱ ንትነሳሕ መንጦላዕተ ቤተ መቅደስ እንዘ አልቦ ዘአበሰ ርእሶ ሰጠጠ ወንሕነሰ በእንተ ኀጢአትነ ኢተነሳሕነ ወኢ በልብነ ንፈቱ አጻብአ ፈረስ ወፀር ተንሢኦሙ አማሰኑ ብሔረነ ከመ ለእግዚአብሔር ፈሪሀነ ውስተ ንስሓ ንግባእ ወበዘሂ ኢተነሳሕነ ወኢደንገፅነ ንትነሳሕ እንከ"
➟ትርጉም
ፀሐይ እንኳ የጌታውን ስድብ መሸከም ተስኖት ብርሃኑን ወደጨለማ ለውጧል እኛ ግን ከጨለማ ከፍተናል ከልባችንም ንስሓ ለመግባት አልወድም የቤተ መቅደሱም መጋረጃ በደል ሳይኖርበት ራሱን ቀዷል እኛ ግን ስለኀጢአታችን ከልባችን ንስሓ ለመግባት አንወድም እግዚአብሔርንም በመፍራት ንስሓ ወደንስሓ እንድንመለስ የጠላትና የፈረስ እጣቶች ተነስተው ሀገራችንን አጥፍተዋል በዚህም ንስሓ አልገባንም ንስሓ ለመግባትም እንግዲህ አልደነገጥንም ።
ወንበዴውን የማረ ጌታ ይማረን
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
የዛሬቱ ዕለት ከሁሉም ዕለታት ልዩ ዕለት ናት የድንቅ ምሥጢር መገለጫ ልዩ ዕለት
ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት ለአሐዱ ብእሲ እንዲል ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይይዙታል ማለትም በሰባቱ ዕለታት ተፈጥረው የተመለኩ ፍጥረታት የአምላክን አምላክነት ይመሰክራሉ ማለት ነው የመሰከሩባት ልዩ ዕለት
አንድም ሰባቱ ተአምራት ተፈጽመው ጌትነቱን የሚሰብኩባት ልዩ ዕለት
➟ ፀሐይ የጨለመባት ልዩ ዕለት
➟ጨረቃ በደም የታጠበችባት ልዩ ዕለት
➟ከዋክብትም ጽናተቸውን የለቀቁባት ልዩ ዕለት
➟ካምስት መቶ ብቅ ከስድስት መቶ ዝቅ የሚሉ ሙታን ከመስቀሉ እግርጌ እንደ አሸን የፈሉባት ልዩ ዕለት
➟ መቃብራት የተከፈቱባት ሙታን የተነሱባት ልዩ ዕለት
➟ ድንጋዮች የተፈተቱባት ልዩ ዕለት
➟የቤተ መቅደሱ ከሦስት ካራት የተቀደደባት ልዩ ዕለት
➣ መድኀን ክርስቶስ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በፈቃዱ የለየባት ልዩ ዕለት
➣ ምእመንንም የሞሸረባት ልዩ ዕለት
➣ እጁን በደም ነክሮ ለኖረ ሽፍታ ወንበዴም ምሕረት የወረደባት
➣ገነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተችባት ልዩ ዕለት ወዘተርፈ
በአጠቃላይ ከሰው ልጆች ይልቅ ደግሞ ግዕዛን የሌላቸው ፍጥረታት እግዚአብሔርነቱን የመሰከሩባት ልዩ ዕለት ናት
➣ እኛስ የፀሐይን ያህል መስክረን ይሆን ?
የጨረቃን ያህልስ እንባ አልቅሰን ደም ደም አልቅሰን እዝኅ በማለቅስ በእንባ በደም በመራጨት መስክረን ይሆን ?
የከዋክብትን ያህልስ መስክረን ይሆን ?
የሙታንን ያህልስ
የድንጋዮችን ያህልስ ልባችን ተሰንጥቆ ይሆን ?
የመጋረጃውን ያህል ምን ያህል ተብሰክስከን ይሆን ?
➟ ነገሩስ ከእነዚህ ሁሉ እንደምናንስ ምንም እንደማይሰማን ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ገልጾታል
እስኪ እንስማው
"ፀሐይ ሰኢኖ ጽዕለተ እግዚእ ጸዊረ ብርሃኖ ለጽልመት ሜጠ ወንሕነሰ እም ጽልመት አከይነ ወኢ እምልብነ ንፈቱ ንትነሳሕ መንጦላዕተ ቤተ መቅደስ እንዘ አልቦ ዘአበሰ ርእሶ ሰጠጠ ወንሕነሰ በእንተ ኀጢአትነ ኢተነሳሕነ ወኢ በልብነ ንፈቱ አጻብአ ፈረስ ወፀር ተንሢኦሙ አማሰኑ ብሔረነ ከመ ለእግዚአብሔር ፈሪሀነ ውስተ ንስሓ ንግባእ ወበዘሂ ኢተነሳሕነ ወኢደንገፅነ ንትነሳሕ እንከ"
➟ትርጉም
ፀሐይ እንኳ የጌታውን ስድብ መሸከም ተስኖት ብርሃኑን ወደጨለማ ለውጧል እኛ ግን ከጨለማ ከፍተናል ከልባችንም ንስሓ ለመግባት አልወድም የቤተ መቅደሱም መጋረጃ በደል ሳይኖርበት ራሱን ቀዷል እኛ ግን ስለኀጢአታችን ከልባችን ንስሓ ለመግባት አንወድም እግዚአብሔርንም በመፍራት ንስሓ ወደንስሓ እንድንመለስ የጠላትና የፈረስ እጣቶች ተነስተው ሀገራችንን አጥፍተዋል በዚህም ንስሓ አልገባንም ንስሓ ለመግባትም እንግዲህ አልደነገጥንም ።
ወንበዴውን የማረ ጌታ ይማረን
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
Telegram
ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
ቅዳሜ፡–
ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡
የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ።
ጠዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡
ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡
በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡
ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡
የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡
ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡
ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡
በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡
ምእመናን ሆይ፣ በአጠቃላይ ሥርዓተ ሕማሙን፤ ሰሙነ ሕማማት ብለው የተለየ ሥርዓት አውጥተው አባቶቻችን ተግተው ያቆዩልንን ሥርዓተ መላእክት ልንጠብቀውም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ የዕለታቱን ክብርና ስያሜ ከማወቅና ከመረዳት ጋር በዕለታቱ የታዘዙትን ሃይማኖታዊ ግዴታዎችን መወጣት ከሁላችንም ይጠበቃል።

ብቻህን ማሰብ ስትጀምር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የብቻችን የሆነ ትምህርት የለም። በማኅበር እንማራለን ፤ በማኅበር እንጸልያለን ፤ አንድ ሆነን የተዘጋጀልንን ማዕድ ቅዱስ ቊርባን እንቀበላለን ፤ በመጨረሻም የተዘጋጀልንን የተስፋ አገር እንቀበላለን።
ክርስቶስ ያስተማረ በጉባኤ ነው ፤ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ምንጊዜም ጉባኤአዊት ሆና ትቀጥላለች እንጅ ማንም ምንም ቢሆን የራሱን ትምህርት አምጥቶ ሊያስተምር የሚችልበት ዕድል የለውም።
የብቻው የሆነ ክርስቶስ ስለሌለው የብቻው የሆነ ትምህርትም ሊኖረው አይችልም።
ብቻህን ማሰብ ከጀመርህ ከጉባኤው የተለየ አስተምህሮ ማምጣትህ ስለማይቀር “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” የሚለውን የሃይማኖት መግለጫ አስቀድመን እንድናውቅ መደረጉ ስለዚህ ነው።
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚኖር ማንም ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ካስተማረችው ትምህርት የወጣ እንደሆነ መዐርጉ ፣ የዕውቀት ደረጃው ፣ የወገኑ የሀብቱ ብዛት ሊያድነው አይችልም። በመጀመሪያ ከቃሉ የሰሙ ሰዎች “የተናገርኸውን ትምህርት አስበኸው ከሆነ አትናገረው ተናግረኸውም ከሆነ አትድገመው” ብለው ይመክሩታል። ምክራቸውን ሰምቶ በዚህ ካቆመ ይተዉታል፤ ምክራቸውን አልሰማ ብሎ ከቀጠለ ግን ወደ መምህራን ያደርሱታል፤ መምህራንንም አልሰማ ካለ ወደ ጉባኤ {ሲኖዶስ} ይቀርባል። ሲኖዶሱን ካልሰማ ተወግዞ ይለያል።
በሰሞኑ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የሰጡትን ትምህርት በቪዲዮ አንዲት ወዳጄ ልካልኝ ተመለከትሁት፤ ምናልባት ከባልንጀሮቻቸው ጋር ተማክረውበት ከበታቾቻቸውም ጋር ተከራክረውበት የነበረ ጉዳይ ከሆነ “አስበኸው ከሆነ አትናገረው ተናግረኸውም ከሆነ አትድገመው” ሊሏቸው ይገባ ነበር።
አሁን ግን በሹክሹክታ ሳይሆን በሰገነት ላይ የተሰበከ የስሕተት ስብከት ስለሆነ ጉዳዩ ከዚህ ያለፈ ይመስለኛል። ከረፈደም ቢሆን ባየሁት መረጃ መሠረት ብዙ ሊቃውንት ሀሳብ ሰጥተውበታል ፤ ይሄ ለብፁዕነታቸው መልካም ዕድል ነው ብየ አምናለሁ። ሀሳባቸውን የገለጹ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን በሊቅነታቸው የምታምንባቸው ሊቃውንት እንደመሆናቸው መጠን ምክሩን ይቀበሉታል ብየ ስለማምን ነው። ሀሳቡን ሳይንቁ በቶሎ በሰገነት ላይ ያጠፉትን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በሰገነት ላይ ወጥተው ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። “አትደንግጡ” ብለውናል እንዳንደነግጥ ያድርጉን።
ይህንን ትምህርት አባቶቻችን አልነገሩንም መጻሕፍቶቻችን ላይ ተጽፎ አላገኘነውም።
ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ መጻሕፍቶቻችንን አባቶቻችንን ተቃውመዋል። ዛሬ መልስ አልጽፍም፤ ምክንያቱም መልሱን ከብፁዕነትዎ ስለምጠብቅ ነው።
ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ

Forwarded from ማኅቶት Wave
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ
መልካም ዕድል!!!
https://www.tgoop.com/addlist/hVsJ5h6oKyk1NDRk