Telegram Web
#ክርስቲያናዊ_የሥነ_ምግባር_ትምህርት
#መግቢያ "መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያመሰግኑት ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ " ማቴ 5:16 ክርስቲያን የክርስቶስ ወገን ማለት ነው ። ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ማለት የክርስቶስ ወገን የሆነ ሁሉ ሊሰራው የሚገባ ያማረ ትክክለኛነትና አርአያነት ያለው ስራ ማለት ነው ። ክርስቲያናዊ ስነምግባር መገለጫው የተለያየ መልክ ሲኖረው ከስፋቱና ከአይነቱ አንፃር በ2 ከፍለን እንመልከተው ። እነሱም ግላዊ ስነምግባር እና ማህበራዊ ስነምግባር ናቸው ። #1ኛ_ግላዊ_ሥነ_ምግባር ፦ መንፈሳዊ ሰው በመጽሐፍትና በመምህራን የተላለፋለትን አምላካዊ ቃል በህሊናው ጽፎ በልቦናው ቀርፆ ከሰውነቱ ጋር አዋህዶ ሁልጊዜም ደግና መልካም የሆነውን ነገር እየፈፀመ ክፉ ከሆነው ነገር ደግሞ ተቆጥቦ እና ሸሽቶ በእለት ተእለት ህይወቱ የሚከተለው ( የሚተገብረው ) የሥነ ምግባር አይነት ነው። ግላዊ ሥነምግባር ገላጭ ባህርያት ከሆኑት በጥቂቱ፦
➊ በትህትና እና እራስን ዝቅ በማድረግ መኖር
➋ ቃሉን በመጠበቅ በትክክለኛው መንገድ በመራመድ
➌ እግዚአብሔርን ከመበደል በመጠበቅ
➍ ራስን መግዛት
➎ ፈቃደ ሥጋን ለፍቃደ ነፍስ ማስገዛት እና ወዘተ...
#2ኛ_ማህበራዊ_ሥነ_ምግባር፦ አንድ ክርስቲያን በዕለት ተዕለት ሥራውና በማህበራዊ ኑሮ ግንኙነቱ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ ሲኖር መተሳሰብን ፍቅርን አንድነትን የሚገልጥበት ፣ ሰዎችን አለአግባብ መቃወምን ግለሰቦችን መናቅን ቁጣን እና ራስ ወዳድነትን የሚያስወግድበት በአጠቃላይ ከሰዎች ጋር ተስማምቶ እና ተፋቅሮ የሚኖርበት የሥነ ምግባር አይነት ነው ። ከመገለጫዎቹ በጥቂቱ፦
➊ተግሳፅን መቀበል
➋ሌሎች ሰዎች ከእኔ የተሻሉ ናቸው ብሎ ማሰብ
➌ሰብአዊ ርህራሄ
➍ከግል ጥቅም ይልቅ ማህበራዊ ጥቅምን ማስቀደም
➎ይቅር ማለት እና ወዘተ... በአጠቃላይ ለክርስቲያናዊ ስነምግባር መሠረቱ ሕገ-እግዚአብሔር ቃለ-እግዚአብሔር ሲሆን ህጉን ለመጠበቅ እና እንደ ቃሉ ለመኖር ትልቁ ኃይል ፈሪሃ-እግዚአብሔር ነው ። 
https://www.tgoop.com/joinchat-aX7cWUYFhBNkNDE8
ለአስተያየት
https://www.tgoop.com/joinchat-Ww52B9j34AgyNDI0
#የአብይ ፆም5ኛ ሳምት ደብረ ዘይት ♥️

🌿♥️💒 ደብረ ዘይት ማለት🌿💐💒

🌿♥️💒 ደብረ ዘይት ጌታችን ያረገበትና ስለ ዓለም ፍጻሜ ምልክቶች ያስተማረበት በወይራ የተከበበ ተራራ ነው
ደብረ ዘይት ተብሎ በተራራው ስም ይጠራ እንጂ የጌታችን በዓለ ምጽአቱን የምናስበበት በዓል ነው
ደብረ ዘይት ከጌታችን ከ18ቱ በዓላት አንዱ ነው
በደበረ ዘይት ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ሶስት ዋና ዋና ነገሮችን አስተምሯቸዋል

1የምጽዓቱን ምልክቶች
2 የምጻቱን ምሳሌዎች
3 የአመጣጡን ሁኔታዎች

🌿♥️💒 1የምጽአቱ ምልክቶች
የሐሰተኞች ነቢያት በክርስቶስ ስም መነሳት
ልዩ ልዩ የጦር ዓይነት መሰራት
የጦርና የጦር ወሬ መብዛት
የርሀብ መከሰት
የቸነፈር ብዛት (አዳዲስ ህመሞች መምጣት)
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መነሳት
መንግሥት በመንግሥት ላይ መነሳት
ብዙ ሰዎች ሃይማኖታቸውን መካድ
የአመጻ መብዛት
ከሰው ልብ ውስጥ የፍቅር መቀዝቀዝ
ቅዱስ ወንጌል በዓለም መሰበክ
ርኩሱ በቅዱሱ ስፍራ መቆም
ደጋግ ሰዎች ለመከራ ተላልፈው መሰጠት መገረፍ መሞት
እነዚህና የመሳሰሉት የምጽአቱ ምልክቶች ናቸው

🌿♥️💒 2 የምጽአቱ መቅረብ ምሳሌ
የበለስ መለምለም
በለስ በክረምት አትለመልምም በበጋ ነው የምትለመልመው
የበለስ መለምለም የክረምቱን ማለፍ የበጋውን መምጣት ወይም የመከሩን መድረስ ታስረዳለች
የበለስ መለምለም የመከር መድረስ ምልክት እንደሆነ
የምጥ ጣር መጀመሪያም ምጽአት እንደ ቀረበ ያስረዳል

🌿♥️💒 3 የአመጣጡ ሁኔታዎች

1 እንደ መብረቅ
መብረቅ በዝናም ጊዜ ሳይታሰብ እነደሚመጣ ሁሉ
ክርስቶስም እንዲሁ ባልታሰበበት ሰአት ይመጣል

🌿♥️💒 2 እንደ ሌባ
ሌባ በሌሊት ባለቤቱ ባላሰበበት ባልጠበቀበት ሰአት ይመጣል የቤት ባለቤት ሌበው መቸ እንደሚመጣ ቢያወወቅ ተዘጋጂቶ ይጠብቅ ነበር
ክርስቶስም መቸ እንደሚመጣ አይታወቅም ተዘጋጅቶ መጠበቅ ያስፈልጋል

🌿♥️💒 3 እንደ ኖህዘመን የጥፋት ውሃ
የጥፋቱ ውሃ በኖህ ዘመን ለነበሩ ሰዎች ባላሰቡት ባልጠበቁት ሰዓት መጥቶ አጥፍቶቸውዋል
ክርስቶስም ባልታሰበበት ሰአት መጥቶ ይህን ዓለም ያሳልፈዋል

+ 🌿♥️💒 የምጻቱ ፍጻሜ
የፀሐይ መጨለም የጨረቃ ደም መሆን የከዋክብት መርገፍ (ማለፍ)
ያንግዜ የሰው ልጅ ምልክቱ በሰማይ ይታያል
ሰማይና ምድር ያልፋሉ ሙታን ይነሳሉ አውሬ የበላው ውሃ የወሰደው በጦር የሞተው በምንም ዓይነት ሞት የሞቱት ሁሉ ይነሳል ሴቶች እንደሄዋን 15 ዓመት ሁነው ወንዶቹ እንደ አዳም የ30 ዓመት ሁነው እንደ ዓይን ጥቅሻ እንደ ከንፈር ንክሻ ፈጥነው ይነሳሉ
ምድር አደራዋን ትሰጣለች
በነፋሳት እንደኳስ ትጠቀለላለች
ከነበረችብት ወዳልነበረችበት ይወስዳታል
የነፍስ ስራዋ ይገለጻል
ኀጥአን በገራው ጻድቃን በቀኙ ይቆማሉ
ስድስቱ ቃላተ ወንጌል ለመስክርነት በጥያቄ ይቀርባሉ
ለጻድቃን ይፈርድላቸዋል የአባቴ ቡሩካን ወደእኔ ኑ ይላቸዋል ከጸሐይ ሰባት እንጅ አብርተው አምላካቸውን መስለው ወደ መንግሥተ ሰማያት ይሄሉ;;
በኀጥአን ይፈረድባቸዋል
ይፈርድባቸዋል እናንተ ርጉማን ሂዱ ይላቸዋል ከቁራ ሰባት እጅ ጠቁረው አለቃቸው ዲያብሎስን መስለው ወደ ገሃነም ይሄዳሉ

💐🌿💒🌿💒🌿💒♥️
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
💐🌿💒🌿💐💒🌿💐
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ  ዐረፉ

ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ የሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት  መካከል አንዱ የሆኑት በቀድሞ ስማቸው  አባ ኃይለማርያም መለሰ ዶ/ር በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ  አህጉረ  ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ  ተለይተዋል።

በረከታቸው ይደርብን።
፨ ሰባቱ ኃጢአቶች  ፨

፨ ቅድስት ማርያም መግደላዊት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉም ሐዋርያቶቹ በፊት በቀዳሚነት ትንሣኤውን የገለጠላት ቅድስት ሴት ናት ጌታችን ቀድሞ ተቆራኝቷት የነበረውን ሰባት አጋንንት አስወጥቶላታል ሰባት በዕብራውያን አነጋገር የፍጹምነት ነው ፍጹም ኃጢአትን የሚያሰሩ አጋንንት ነበሩባት አንድም በቁሙ ሰባት ዓይነት ኃጢአት የሚያሰሩ አጋንንት ነበሩባት   እነርሱም

፩ መንፈሰ ትዕቢት
፪ መንፈሰ ጽርፈት(ስድብ)
፫ መንፈሰ ቅንዓት
፬ መንፈሰ ትውዝፍት (የምንዝር ጌጥ ማድረግ)
፭ መንፈሰ ዝሙት
፮ መንፈሰ ሐሜት
፯ መንፈሰ ሐሰት

፨ እነዚህን ኃጢአቶች ጌታችን አውጥቶላት ከ 36ቱ ቅዱሳት አንስት ተቆጥራ ያለፈች ሴት ናት ነሐሴ 6 በሰማዕትነት ዐርፋለች

፨ ነገርን ከስሩ  ለማምጣት ነው እንጂ ዋናው ሀሳባችን በእዚህ የጾም ወቅት ያቆሰሉን ኃጢአቶቻችንን  ፍትወቶቻችንን ቆርጠን ለመጣል ጾሙ ስለት እንዲሆነን እነዚህ ኃጢአቶች እኛ ውስጥ አሉ ወይ ብለን በጥቂቱ እንፈትሻለን

             ፩ መንፈሰ ትዕቢት

  የትዕቢት ሥሯ ተዘክሮተ ሞትን  ኀልዎተ እግዚአብሔርን መርሳት እና ወዘተ ናቸው
በመጽሐፍ እንደምናገኘው የፈርዖን የትዕቢት ጅማሬ እና ፍጻሜው እግዚአብሔር ማነው እግዚአብሔር የሚባል ነገር አለ ወይ ብሎ ማሰቡ እና ሞት አለ ብሎ አለማስተዋሉ ነው ትዕቢት ከሊቁ እስከ ደቂቁ በሦስት ቀዳዳዎች ይገባሉ በዕውቀት በጉልበትና በሀብት  እነዚህ ሰውን ከሰው ተበላልጦ እንዲታይ እና ልባችንን ተራራ አድርገን እንድናይ ያደርገናል እኚህ ሦስቱ ነገሮች በራሳቸው ጉዳት ያላቸው ሆነው ሳይሆን እንደምናጣቸው ባለማስተዋል አላግባብ ስለምንጠቀማቸው ነው  እኔ የነ እገሌ ዘር የነ እንትና የልጅ ልጅ የጃንደረባ አሽከር ፉከራ እስከ መቼ አይተወንም ፨ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ፨ ሲናገር ምን ይላል ( አንተ ሰው ክርስቶስ ከአብ ጋር ትክክል ሆኖ ሳለ አብ ይበልጠኛል ካለ ከብዙ ሰው የምታንስ አንተ እንዴት ከነእገሌ ጋር እኩል ነኝ ትላለሀ) እኛስ ከሦስቱ የቱ አለን በየትኛውስ እንታበያለን ?
      
        ፪ መንፈሰ ጽርፈት (ስድብ)

  እነዚህ 7 ኃጢአቶች ተያያዥ መሆናቸውን የምናስተውለው ትዕቢት የሌለበት ሰው ስድብ ከአፉ እንደማይወጣ ስናውቅ ነው ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል በትህትናው ከፍታን ያገኘ ስለ ሙሴ ስጋ ከዲያብሎስ ጋር በተነጋገረ ጊዜ እግዚአብሔር ይገስጽህ አለው እንጂ የስድብን ቃል ከአፉ አላወጣም እናስ እኛ ማንን አብነት አድርገን ነው ሰውን የምንሰድብ ከልባችን አንቅተን ሰውን ስንዘረጥጥ እንውላለን ዛሬ ግን ጾም ነው በቀደመው ግብራችን ነን ወይስ በጾም ልጓም ተይዘናል ?
               
፫ መንፈሰ ቅንዓት

     አይሁድ አስቀድመው ቅድስት ሐናን ያሳደዱበት ቀጥለው እመቤታችንን ማየ ዘለፋ ያጠጡበት እናት እና ልጇን ከሀገር ሀገር ያባረሩበት  የፍጻሜው መጀመሪያ ክርስቶስን  በመስቀል የሰቀሉበት አልበቃ ብሏቸው መስቀሉን የቀበሩበት ምክኒያት ምንስ ነው ብንል ግልጥ የሆነ ቃል (ቅናት) ነው ሌላው ቀርቶ ሰይጣን እኛን ከክብራችን እንድንወድቅ ያደረገን ቦታው ተነጥቆ ለእኛ ስለተሰጠን ነው  ዛሬም በዘመናችን የየጸበል ቦታው ኑዛዜ ይኽን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል ታዲያ እኛስ ይኽ መንፈሰ ቅናት አለብን ይሆን  ለባስያነ ክርስቶስ የተባሉ ክርስቲያኖች ላይ ይህን አድርገን ከአይሁድ እንተካከል ይሆን ?

         
፬ መንፈሰ ትውዝፍት (የምንዝር ጌጥ)

ይኽ ኃጢአት ሴት እህቶቻችንን ላይ ይዘወተራል ለኃጢአት ጾታ መስጠቴ ሳይሆን ሰይጣን ሴትን ሴት ወንድን የማሰናከል ሂደቱ ቀጥሎ ዛሬ ላለንበት መድረሳችንን ለማጠየቅ ነው እናም ሴት እህቶቻችን ላይ የሚታየው የምንዝር ጌጥ ከሀሳቡ ይጀምራል ለምን ? አላማ ተለበሰ ለመዘነጥ ከሚለው የኃጢአት ቅያሪ ስም ከመስጠት በቀር እና ስም ከመለዋወጥ በቀር ሀሳቡ የታወቀ የተረዳ ነው   ሴት ልጅ እንኳን አካላቷን ሜዳ አስጥታ ይቅርና በጥቂቱ ከእግሯ ቀሚሷን ሰብሰብ ካደረገች ወንድን እንደምታስት የታወቀ ነው እርሱም  ሳይበቃ የሚቀባ ተቀብታ ለሀገር ለሚበቃ ሽቱ ተነስንሳ ሲሆን ደግሞ እንኳን ወጣኒ ፍጹምም ሊያሰናክል እንደሚችል የታወቀ ነው ወንዶችም ባት እና ደረታችንን እያሳየን ስንሄድ ስንቱ ሴት ስቶብን ይሆን ? እናም እህት ወንድሞቼ ልብስን ጌጥን ስንጠቀም እውን በእዚህ አለባበሴ እግዚአብሔርን አስደስቼዋለውን ብለን ብናስተውል !

            ፭ መንፈሰ ዝሙት

ከላይ እንደጠቀስኳቸው እነዚህ 7 ኃጢአቶች ተያያዥነት አላቸው አሁን የምናየው ዝሙት ከላይ ባየናቸው ችግሮች የሚመጡ ናቸው ካየናቸው በተጨማሪ ዝሙት ከሚያመጡ ነገሮች   የዝሙት ፊልም መመልከት የምንዝር ጌጥ የለበሰችን ሴት ፎቶ መመልከት ወንድ ከሴት ጋር ሴት ከወንድ ጋር በጓደኝነት እና በመንፈሳዊ እህትነት ሰበብ አላስፈላጊ ንክኪ ማድረግ እነዚህ ነገሮች ስንጀምራቸው እንደ ጤፍ ፍጻሜያቸው እንደ ክምር ነው እኛስ በየቱ ይሆን የወደቅን ?

             ፮ መንፈሰ ሐሜት

መቼም ይሄ ንብ ያልነደፈው ወይ ከሰው ጋር አይኖርም ወይ ከሰው አይስማማም እንዴት ካላቹ ሰው ሐሜት ጀምሮ አረ ተው ሐሜት ነው እኮ ብላቹ ካስቆማቹት እንደ እናንተ ጠላት አይኖረውም ለምን? አንደኛ እራሳቹን እንደ ጻድቅ አይታቹ እርሱን እንደ ኃጢያተኛ የቆጠራቹት ስለሚመስለው ይነደዋል እናም መቼም እንደ ሀገር ከምንሰራው ኃጢአት መካከል ሐሜት ነው በዘር በጎሳ በጎጥ በተለያየንበት በእዚህ ዘመን እራሱ ኃጢአቶቻችን የጋራ ናቸው በዋናነት ደግሞ ሐሜት የኢትዮጵያዊነት መለያ እስከ መሆን ደርሷል እኛስ ተቀምጠን ወንድም እህቶቻችን እናማ ይሆን ?

                   ፯ መንፈሰ ሀሰት

  በእዚች ለሆድ በሚኖርባት የሰፊ ጠባብ ዓለም ከደረጃ ወደ ደረጃ ከክብር ወደ ክብር ከሚያወጡ ኃጢአቶች አንዱ ሀሰት ነው ዛሬ በየእስር ቤቱ በሀሰት ተመስክሮባቸው የተወረወሩ ቤት ይቁጠራቸው በሀሰት የተገደሉ በሀሰት ንብረታቸውን ያጡ በሀሰት ክብራቸውን ያጡ እልፍ ናቸው እኛስ ማንን ይሆን በሀሰት ያለ ስሙ ስም ያሰጠነው ከደረጃው አውርደን በትቢያ ያስጣልነው ?

ከላይ የተመለከትናቸው እያንዳንዱን ኃጢአት እውን ከመግደላዊት ማርያም ወጥቶ ከእኛ ቤት ገብቶ ይሆንን ይህን በማስተዋል መመልከት ይፈልጋል

አሁን ወቅቱ የጾም ነውና ተርቦ ከመዋል በዘለለ እነዚህ ከላይ ያየናቸው ኃጢአቶች ከጓዳችን የሰገሰግናቸው!  ጾም ቆሻሻ አውጡ እያለን ስለሆነ  በንስሐ መጥረጊያ ጠርገን መጣል አለብን ለማለት እወዳለሁ ።


  ፆም ከመላዕክት ጋር በአንድ መቀመጥ ነው>

   ቅዱስ አትናቴዎስ
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
➡️የሌሊቱ ተማሪ (ዮሐ 3:1)
    **
ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ከአይሁድ አለቆችና መምህራን አንዱ ነው። ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል አድራጊ ወይም አሸናፊ ማለት ነው። ኒቆዲሞስ በቀን የሚማር በማታ የሚያስተምር፤ በቀን ኦሪትን የሚያስተምር በማታ ወንጌል የሚማር ነው።

በአጭሩ ብሉይን አስመክሮ ደከመኝ ሳይል ሐዲስን የቀጠለ ትጉህ መምህርም ደቀመዝሙርም ነው። በአይሁድ ሸንጎ የታወቀና ረቢ እየተባለ ተከብሮ የሚጠራ በቀን ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈርድ በማታ ከወንበር ስር የሚማር ትሁትም ነው።በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እርሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ አምላክነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር ”አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሳ መርምርና እይ“ አሉት እንጂ አልተቀበሉትም። ዮሐ ፯፥፵፰–፶፪።

ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ”ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ። ዮሐ ፲፱፥፴፱። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለና ወደ ህገ ወንጌል የተሻገረ መሆኑንን እንረዳለን።
የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ ዮሃ ፫፤፪
ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው በሌሊት ወደ ጌታ እየሄደ ይማር ነበር ኒቆዲሞስ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ ?

፩/ ኒቆዲሞስ መምህር ስለነበር ሲማር ሰዎች ቢያዩኝ ውዳሴ ከንቱ መምህር መባል ይቀርብኛል ብሎ ነው። ውዳሴንም እውቀቱንም የፈለገ ሰው ነው። ብዙዎችቻን መወደስን አንቱ መባልን እንጂ ዝቅ ብሎ መማርን አናስተውልም አንቱ የሚያስበልን መማራችን እና እድሜ የሰጠን መድኃኔዓለም መሆኑን አንዘንጋ።
፪/ .ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ስለነበር እንዳያዩት ፈርቶ ሌሊት እየመጣ ይማር ነበር።
‹ፍፁም ፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና› ፩ዮሃ ፬፤፲፰ ፍርሃትን አስወግደን ለእውነት ልንቆም ይገባል።
፫/ ኒቆዲሞስ ከቀን ልብ ይልቅ የሌሊት ልብ የተካተተ ስለሆነ በሙሉ ልቡ በማስተዋል ለመማር ስለፈለገ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የማታውን መረጠ እኛም ዛሬ ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ከልብ ሆነን የምንማር የሰማነው ቅዱስ ቃል በህይወታችን ፍሬ እንዲያፈራ ቅዱስ ቃሉን ከልብ ሆነን በማስተዋል ልንሰማ ይገባናል ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ልብ መልካም መሬት ተብⶀል
‹ በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው› ማቴ ፲፫፡፳፫

፬/ ሌሊት ጨለማ ነው ብርሃን የለውም ይህም የኃጢአት ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስ በሌሊት መምጣቱ በኃጢአት እንዳለ ንስሃ እንደሚፈልግ ያስረዳናል አንድም ኦሪት ጨለማ ናትና ወንጌልን ይረዳ ዘንድ መጥቷል። አንድም ኦሪት ጨካኝ ህግ ናትና ምህረት ይቅርታ ወደሆነችው ወንጌል መጥቷል። እኛም ልክ እንደ ኒቆዲሞስ ከጨለማ ስራ ከጭካኔ ከጥላቻ ወደ ፍቅር ወደክብር ፀጋና በረከት ወደምናገኝበት መልካምነት ቀኑ ቢመሽም ሰዓቱ ያለፈ ቢመስልም እንድንመለስ ይርዳን።

፭/ ሌሊት የቆየው ኪዳን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስም እኔ ምሁረ ኦሪት እንጂ ምሁረ ወንጌል አይደለሁም ወንጌልን ካንተ እማር ዘንድ ያስፈልገኛል ሲል በሌሊት ይመጣ ነበር። ብሉያት ከሐዲሳት ጋር ተዋህደው ሲተረጎሙ ሰሙና ወርቁ ተጣምሮ የሕይወት ትምህርት ያስገኛል።ኒቆዲሞስ ሁለቱንም ኪዳናት ማለት ጥላ የተባለችውን ኦሪትን ተምሮ ያወቀ በመሆኑ አካል የሆነው ወንጌል ይረዳ ዘንድ መርጧል። ትንቢት ከሆነችው ኦሪት ፍፃሜ ወደሆነው ወንጌል ተሻግሯል። ሁላችንም ያለ ድካም እንደ ኒቆዲሞስ  በኦሪት ስርዓት ከመታሰር ወደመፈታት ወደ ህገ ወንጌል እንድንሻገር በወንጌልም እንድንኖር እርሱ ይርዳን።

ስለዚህ እንደኒቆዲሞስ ኦሪትንም ወንጌልንም ማወቅ ያስከብራልና አንዲት ቃል ሳናጎድል በጥበብና በጸሎት መረዳት ያስፈልጋል ይህ‹እውነት እላችኋለው ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከህግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አታልፍም› ማቴ፭፤፲፰ በማለት አበክሮ የተናገረው ኒቆዲሞስ ምንም እንኳን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ባይመቸውም በሌሊቱ ሰአት ለመማር ችሏል እኛም ከሱ ተምረን ምንም ውጣ ውረዱ ቢበዛብንም በትዕግስት ለሚበልጠው ፀጋ እንድንተጋ ይርዳን።

በመጨረሻም ኒቆዲሞስ ስለክርስቶስ ሲመሰክር እምነቱን ሳይሆን እውቀቱን ተናግሯል አንተ ከእግዚአብሔር ተልከህ እንደመጣህ እናውቃለን ብሏል እናምናለን ግን አላለም። የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ግን አንተ ከእግዚአብሔር ተለከህ እንደመጣህ እናምናለን ብሎ ዘምሯል። እኛም አሜን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ እንደታደገን እናምናለን እንመሰክራለንም። ሌላው ኒቆዲሞስ ይኖር የነበረው በመንፈሰ ረድኤት ነበርና ክርስቶስ ደግሞ የመጣው ወደ መንፈሰ ልደት ለማሻገር ነውና ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለድ ብሎ ስለምስጢረ ጥምቀት አስተምሮታል (ዮሐ 3:7) በአጭሩ ኒቆዲሞስ ስልጣን እውቀት ገንዘብ ያለው ሲሆን እነዚህም እስከዛሬ ዓለምን የሚያሾሩ ወሳኝ ነገሮች እያሉት ጌታን ፈልጎ የመጣ ተምሮ ያመነ አምኖ የመሰከረ መስክሮ የከበረ ታላቅ ሊቅ መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ነው። ከስልጣንም ከገንዘብም ከእውቀትም ጌታን ማወቅና ማግኘት የበረከት ሁሉ ራስ የነፍስ እረፍት የአዕምሮ ስኬት ነው።ለቅዱስ ቃሉ  ጊዜ ሰጥተን ቀን በስራ ቢደክመንም ማታ አንድ ምዕራፍ አንብበን ወይም አድምጠን እንድናርፍ እርሱ የሚያበረታታውን መልዐክ ይላክልን። ህይወት ለሚገኝበት ትምህርት ጊዜ ሰጥተን እንደኒቆዲሞስ ከመስቀሉ ስር መገኘት ብቻ ሳይሆን ታምነን እስከ መቃብር እንድናከብረው መድኃኔዓለም ይርዳን። ጾማችንን በሠላም ያስፈፅመን። ለሀገራችን ኢትዮጵያ እና ለሕዝቧ ፍፁም ሠላምና ፍቅርን ያድለን አሜን።ክብር ለመድኃኔዓለም ይሁን🙏
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ጌታችየየመየመድኃኒታየየኢየኢየስክርስቶችምአምላካችንንናድኃኒታችንንለምንዳኑንዛነትውንራባትንለተ አርብ ያደረገልንን ስለ እኛ ስፍር ቁጥር የሌለውን መከራ መቀበሉን የምናስብበት እና ለአምላካችን ምስጋና ውዳሴ የምናቀርብበት ዕለት ነው።

🔵👉 " ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ዮሐ ፲፭፥፲፫ "እኛ በገንዘብ ሳይሆን በክቡር ደሙ የገዛን ወገኖቹ ነንና።

🔴👉 ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን በዕለተ አርብ በስቅለቱ ፲፫--ሕማማተ መስቀልን ተቀብሏል እነሱም፦

፩ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
፪ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
፫ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
፬ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
፭ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
፮ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
፯ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
፰ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
፱ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
፲ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
፲፩ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
፲፪ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
፲፫ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት)

❖ አምላካችን ሆይ፤
❖ ጌታታችን ሆይ፤
❖ መድኃኒታችን ሆይ፤
❖ አማኑኤል ሆይ፤
❖ ኢየሱስ ሆይ፤
❖ ክርስቶስ ሆይ፤
❖ እግዚአብሔር ሆይ፦ ሥለ እኛ ስድሥት ሺህ ሥድሥት መቶ ጅራፍ ተገረፍህ፤ክፍዎች አይሁድ ምራቃቸውን ተፉብህ፤ በዘንግ እራሥህን መቱህ ፤እርቃንህን በመስቀል ላይ ሰቀሉህ፤ኦ!ወየው! ኢሳ፶፫፦፯,መዝ ፳፩,ማቴ፡፳፮:ዮሐ፳:ማር፲፭

🔴👉 " እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።" መዝ ፻፲፰፥፳፬ ተብሎ እንደተፃፈ በእውነትም እለተ አርብ የጌታስቃይ ቢያስለቅስም ከስራት የተፈታንበት ዕለት ስለሆነ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ናት ብለን መድኃኒታችንን ሥለማይነገር ስጦታው እናመሰግነዋለን እናመልከዋለን።

🔵👉 "ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ ፫፥፳፫ እንዳለ የሰውልጆች ፅድቅ እርቆን በግዞት ውስጥ ሳለን ከሰማያት ወርዶ በመስቀል ተሰቅሎ ደሙን አፍስሶ የጥልን ግድግዳ ሰብሮ ከኃጢያት ባርነት ነፃ ያወጣን መድኃኒዓለም ይክበር ይመስገን።"በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ። ገላ-፭፥፩

👉 እሚያሳዝነው ግን መድኃኒዓለም በመስቀል ላይ ስለ እኛ ሞቶልን ሳለ ግን አሁንም በኃጢያት ቀንበር ሆነን የሞተልንን ፈጣሪያችን እያሳዘነው ነው።

🔵👉 "እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል። ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል? ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።" ፩ኛ ዮሐ ፫፥፲፮

🔴👉 "እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ በልባችሁም። አብርሃም አባት አለን ማለትን አትጀምሩ፤ ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር እንዲችል እላችኋለሁና።ዮሐ ፫፥፰" ነው ያለን ጌታችን እራሱ። "ለንስሀ የተገባ ህይወት ይስጠን "እንደቸርነቱ ይማረን ፤ ተዋህዶኃይማኖታችንን ይጠብቅልን፤አፅራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን ፤ሀገራችን ኢትዮጵያን በቀደመ ክብሯ ያስብልን!

    🙏ሼር አድርጉ አይከፈልበትም🙏

።።።።
#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
    ።።።።።
#ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
     ።።።።።
#ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE

  
#የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ

#መርገመ_በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡

በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

#አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦

ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡

በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5 ሺ ከ5 መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

https://www.tgoop.com/tmhrteorthodox
ሐሙስ የምሥጢር እና የነጻነት ቀን

ይህ ዕለት ብዙ ምሥጢር እና ታሪክ የተፈጸመበት ዕለት ስለሆነ በብዙ ስሞች ይጠራል ጥቂቶቹን ከምክንያታቸው  ጋር እንዲህ አቅርበናቸዋል

ጸሎተ ሐሙስ:- የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ መኾኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ቀን ነውና ‹ጸሎተ ሐሙስ› ይባላል (ማቴ. ፳፮፥፴፮-፶፮)፡፡

ሕጽበተ ሐሙስ:- ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ዅሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ የንጽሕና፣ የቅድስና አምላክ መኾኑን ያጠይቃል፡፡ ስለዚህም ዕለቱ ‹ሕጽበተ ሐሙስ› ይባላል፡፡ ይህን

የምሥጢር ቀን:- ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ምሥጢረ ቍርባን በዚህ ቀን ተመሥርቷልና ዕለቱ ‹የምሥጢር ቀን› ይባላል፡፡ ይኸውም ጌታችን ኅብስቱንና ጽዋውን አንሥቶ ‹‹ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቈረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ፤ ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል ላይ የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ፤›› በማለት እርሱ ከእኛ፤ እኛም ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምሥጢር  ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመኾኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ:- መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመኾኑ ይህ ዕለት ‹የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ› ይባላል (ሉቃ. ፳፪፥፳)፡፡ ‹ኪዳን› ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ዅሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለ ኾነ ይህ ዕለት ‹የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ› ተባለ፡፡

የነጻነት ሐሙስ:- ይህ ዕለት ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ኾኖ መኖር ማብቃቱ የተገለጠበት፤ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለ ኾነ ‹የነጻነት ሐሙስ› ይባላል፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፡፡ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፤›› በማለት ከባርነት የወጣንበትን፤ ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመኾኑ ሊቃውንቱ ‹የነጻነት ሐሙስ› አሉት (ዮሐ. ፲፭፥፲፭)፡፡
ስለዚህ ይህን ዕለት ከኃጢአት እና ከዲያቢሎስ  ባርነት  በእግዚአብሔር ቸርነት ነጻ መውጣታችንን የምናስብበት ስለሆነ የተከፈለልንን ዋጋ አስበን ዛሬ ከታሠርንበት የኃጢአት ሠንሰለት በንስሐ ነጻ ሆነን ልናስበው ይገባል፡፡
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ሰባቱ የመስቀሉ ላይ ቃላቶች
ጌታችን አምላካችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀለ ላይ ሁኖ በዛ በቀራኒዮ ተራራ እጆቹን ለህማም ዘርግቶየእሾህ አክሊል ደፍቶያ ደረገው ሁሉ የማዳን ተግባር ሰው ሁሉ በዚህ ጥበብ ይድን ዘንድ እግዚአብሔር ስለፈቀደና ስለወደደ ለሚያምኑት ሰዎች ሁሉ ኃይል ቤዛ ሆነዋል። ለማያምኑት ሰዎች ግን በዚህ ቃል እየተሰናከሉ እንዲወድቁ ይሆንባቸዋል። ለሚስቱ ሰዎች መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል " የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:18)
" የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።"(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:8)
ብዙ ግዜ የሚስቱ ሰዎች የሚስቱት ቃሉን ሳያውቁ በመቅረት ሳይሆን ቃሉን በገዛ ፍላጎት በመተርጎም በሽታ ነው ። የእውነትን ወንጌል ወደማይሆን አቅጣጫ እያጣመሙ ብዙዎች ይጠፉበታል።ብዙዎች ይወድቁበታል።
ጌታ በመስቀል ላይ ሆኖ የተናገራቸው ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት እነማናቸው? ለምንስ ተነገሩተነገሩ?
1) ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? (የማቴዎስ ወንጌል 27:46)
ይህን ቃል አረማይክ ሲሆን ትርጉሙ ደሞ አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።"
ይህን ቃል የተናገረው አላማ ምንድነው?
አንደኛ ፦ ይህን ፀሎት የአባታችን የአዳማ ፀሎት ነው። አዳም በሲኦል ውስጥ ሁኖ አምላኬ ለምን ተውከኝ ይል ነበርና የአዳምን ጩኸት ጩኸት አድርጎ አዳምን ለማዳን የመጣ እንደሆነ ለማጠየቅ ነው።
ሁለተኛ ፦ በመዝሙረ ዳዊት መዝ 22 ላይ የተፃፈ ትንቢት አምላኬ አምላኬ ስለምን ተውከኝ ብሎ የሚጀምረው በጌታ ላይ በመስቀል የሚደረጉት ድርጊቶች የሚያመለክተን ትንቢት ነው።
ሦስተኛ ፦ እኛ በሽግር ውስጥ ስንወድቅ ወደ አምላካችን መጮህ እንዳለብን ሲያመለክተን ነው እንጂ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ አምላክ ነው አምላክን ፍለጋ አይደለም። ምክንያቱም ከእኔ ተማሩ ብለዋልና።ማቴ 11:29
2)አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (የሉቃስ ወንጌል 23:46)
ይህን የተናገረበት ደሞ በችግር ውስጥ ስንሆን ነፍሳችን ለእግዚአብሔር እንድንሰጥ ሲያመለክተን ነው እንጂ እሱ ለሌላ ነፍስ የሚሰጥ ሁኖ አይደለም። ምክንያቱም በዮሐ 10:30 ላይ እኔና አብ አንድ ነን ብለዋልና።
3) (አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ)፣( እናትህ እነኋት) (የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 19:26-27)
በዚህ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ ሁለት ነገሮች እንመለከታለን ፦
አንደኛ ፦ አሁን እዚህ ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ይወደው ለነበረው ለቅዱስ ዮሐንስ ለእናትነት እንደሰጠው ያሳየናል። ለማን ነው የሰጠው? ☞ (((ለሚወደው))) ለቅዱስ ዮሐንስ ነው ያለን።
አሁን እዚህ ላይ ልብ ማለት ይገባናል። መልእክቱ ለኛ ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናት እንድትሆነው የሚሰጠው ለማን ነው? መልሱ፦ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚወዳቸው እናቱን ለሚያከብሩለት ለኛ እናት እንድትሆነን ነው እየሰጠን ያለው እንጂ ለተሳዳቢዎች እናታቸው እንድትሆን አይሰጥም እነሱም(መናፍቃን) እናታቸው ብለው ሊቀበሏት አይችሉም። በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስትያናችን ግን ቅዱስ ዮሐንስን አብነት አድርገን የመስቀል ስር እናታችን ብለን እንጠራታለን እንቀበላታለን። ለቅዱስ ዮሐንስ እነኃት እናትህ ያለው መልእክቱ ለእኛ ነው እናታችን ብለን እንድንቀበል ነው እንጂ እንዳትራብ ነውን? እንዳትቸገር ነውን? በውነት እንደዚህ ብሎ ለሚያስቡ እግዚአብሔርን የማያቁ ናቸው። የሰማይ ወፎችን የሚመግብ እንዴት እናቱን መመገብ አይችልም?
" ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።"(መዝሙረ ዳዊት 87:5) ☞ ይህንን ትንቢት የመስቀል ስር እናታችን መሆኗን ለመግለፅ ነው። ዮሐ 16 : 26-27
ሁለተኛ ፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሌሎች ልጆች እንደሌላት ለቅዱስ ዮሐንስ ለእናትነት እንደተሰጠ ነው እየነገረን ያለው። ምክንያቱም መናፍቃን እንደሚሉት ሌሎች ልጆች ወልዳለች ለሚሉ ለምን መጥተው አይረከቡም ነበር? ለምን ለቅዱስ ዮሐንስ ለእናትነት ተሰጠ? እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግል መሆኗን እንዲነግረን ነው።
4) ተጠማሁ (የዮሐንስ ወንጌል 19:28)
ጌታችን በመስቀል ላይ ሁኖ ተጠማሁ ያለበት ምክንያት እርግጥ ነው በለበሰው ስጋ ቢጠማ ግን ውቅያኖስን የፈጠረ ውኃ ማድረግ አቅቶት ነው? አይደለም። ተጠማሁ ያለው ውኃን ሳይሆን ፅድቅን ነው። ከሰው ልጆች መልካም ምግባርን ተጠማሁ ነው። የሰው ልጆች ፍቅር እንዲኖራቸው ፣በንስሃ እንዲኖሩ ፣ ስጋ ወደሙ እንድንበላ እንድንጠጣ፣ፅድቅ እንድንሰጠው ነው ተጠማሁ ያለን።
5) እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ (የሉቃስ ወንጌል 23:43)
ይህን ለጥጦስ በቀኝ ለተሰቀለው ሽፍታ የተነገረ ቃል ነው። ጌታ ለጥጦስ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ ያለበት ምክንያት ምንድነው? ያ ሽፍታው ሁለት ነገር አምኖ ስለ ነበር ነው።
አንደኛው፦ ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ስላመነ ነው። እኛም ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው ፣ አምላክ ነው ብለን ማመን እንዳለብን እንጂ ነብይ ነው ፣ አማላጅ ነው ፣ ፍጡር ነው ማለት እንደሌለብን ሲያመለክተን ነው።
ሁለተኛው፦ ባለ መንግሥቱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ አምኖ ነው። (ሉቃስ 23:42) ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባለመንግሥት ነው። መንግሥት የሚያሰጥ አማላጅ አይደለም ፣ ነብይም አይደለም ፣ ፍጡርም አይደለም ፣ ዝምብሎ ተራ ሰውም አይደለም።
ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው ባለ መንግሥት ነው ብለን ማመን አለብን።
6) አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (የሉቃስ ወንጌል 23:34)
ጌታ በመስቀል ላይ ሁኖ የተፉበትም ፣ የቀለዱበትም ፣የሰደቡትም ሁሉ በይቅርታ ተመለከታቸው። እኛም ቂም ይዘን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንደሌለብን ፣ በይቅርታ ህይወት እንድንመለላለስ ፣ ይቅርታ እንድንጠይቅ ፣ ይቅርታ ተጠይቀን እንደገና ይቅርታ እንድናደርግ ነው። ካላደረግን ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ማየት አይቻልም። በይቅርታ መንፈስ እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን።
7) ተፈጸመ (የዮሐንስ ወንጌል 19:30)
ምን ተፈፀመ? የሰይጣን አገዛዝ ተፈፀመ ፣ ለ5500 አመታት የነበሩ ትንቢቶችና ምሳሌዎች ተፈፀመ ፣ ለ33 አመቱ በስጋዌ ዘመን ያደረገው የማዳን ተግባር ተፈፀመ ነው።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ሼር ይደረግ
ድንግል ሴት ትፈልጋለህ ?

ምንም እንኳን ሰዎች ሁሉም ባይሆኑም ብዙ ሰዎች ግን የሚያገቧት ሴት ድንግል እንድትሆን ይፈልጋሉ። አንዳንዶች ደግሞ መፈለግ ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያ መስፈርታቸው ያደርጉታል ። ይህ እጅግ ደስ የሚያሰኝ አቋም ነው። ምክንያቱም የኹሉም ሰው አቋም እንዲህ ቢሆን ኖሮ ሴቶች ኹሉ በንጽሕና መኖርን ለወደፊት ትዳራቸው መቃናት ሲሉ ስለሚለማመዱት ነው።

ታዲያ ሚስቱ ድንግላዊት ሆና ቢያገኛት የሚመኝ ሰው እርሱም ድንግልናውን የጠበቀ ሆኖ መገኘት እንዳለበት ለአፍታም እንኳን ቢሆን መዘንጋት የለበትም። ስለዚህ ይህን የሚመኝ ራሱን ይጠብቅ። ካላገባኻት ሴት ጋር አንሶላ መጋፈፍን አትሻ። ልታገባ አንድ ቀን የቀረህ ቢሆን እንኳን ሳታገባት ይኽን መሞከር የለብኽም። በሰዓታትና በቅጽበት ውስጥ በእቅፍኽ ያለች እጮኛህ ያንተ ሚስት መሆን የማትችልበት ሁኔታ ይፈጠር እንደሆነ አታውቅምና። አንተ ራስህ ከነድንግልናህ የምትፈለግበት ጋብቻ ከፊተህ ይጠብቅሀል ።

እርሷም በምትሄድበት ቦታ ባሏ ከነ ሙሉ ክብሯ ይሻታል። ታዲያ ካላገባሃት ሴት ጋር ለምን ትተኛለህ ? ካላገቧት ሴት ጋር ምንጣፍ መጋራት በሰው ቤት መግባትና ከባለ ትዳር ሴት ጋር እንደ ማመንዘር ነው። ያላገባች መሆኗ ልዩነቱ ባሏን መቅደምህ ብቻ ነው። አንተ በሰው ትዳር እንዲህ የምተገባ ከሆነ ሌሎች ደግሞ አንተ የምታገባትን ሴት ከክብር አስንሰው ንጽሕነዋን ገፈው ያቆዪሀል። አንተ ድንግል ሳትሆንና የብዙዎችን ሕግ አፍርሰህ ድንግል ሴት መፈለግህ አያስገርምም ?

ሰው የራሱን ድንግልና ቢጠብቅ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግልና የተጠበቀች ሚስት እንደ ፍላጎቱ ሊሰጠው ተስፋ ሰጥቷል። ሰው የራሱን ዕቃ ቢጠብቅ ለእርሱ የሚገባውን ዕቃ እግዚአብሔር በክብር ይጠብቅለታል ። በመጽሐፍ ቅዱስ ዕቃ የሚባለው አባለ ዘርዕ (ኀፍረተ አካል ) ነው። ቅዱስ ዳዊት በእውነት ከመጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሶስት ቀን ጠብቀናል የብላቴኖችም ዕቃ የተቀደሰች ናት ስለዚህ ዛሬ ዕቃቸው የተቀደሰች በመሆኗ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል 1ኛሳሙ 21:5 በማለት የተናገረው ቃል ኀፍረተ አካል ዕቃ እንደሚባል ያስረዳል።

የራሱን ንጽሕና የጠበቀ ሰው ለእርሱ የምትሆነው ሚስቱ ከነቅድስነዋ ከነንጽሕነዋና ከነሙሉ ክብሯ (ድንግልነዋ) እንደሚያገኛት ማወቅ አለበት ሲል ሐዋሪያው "ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን እቃ (ሚስቱ የምትሆነውን ) በቅድስናና በክብር (ከነድንግልነዋ) ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ" በማለት ይናገራል። "ዕቃ" የሚለው ኀፍረተ አካል መሆኑ ከላይ በማያሻማ መልኩ ተገልጿል። ስለዚህ ድንግልን ማግባት የሚፈልግ ሰው የራሱን ክብር መጠበቅ ይኖርበታል። (1ኛ ተሰሎንቄ 4÷5)
https://www.tgoop.com/tmhrteorthodox
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 1 ♥️
እግዚአብሔር በአካል ሦስት ስለመሆኑ የሚያስረዱንን ከአራቱ ጉባኤያት ለማየት እንሞክራለን።በብሉይ ምሥጢረ ሥላሴ ለጥቂቶች ካልሆነ በቀር ለብዙው አይታወቅም ነበር።እግዚአብሔር ግን ስለራሱ በብዙ አምሳል እና ትንቢት እንደተናገረ ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ.1፣1 ገልጾልናል።በብሉይ ዘፍ.1፥26 ላይ ሰውን በአርአያችን በምሳሌያችን እንፍጠር ይላል።በዚህ ቃል እንደምንረዳው መፍጠር የፈጣሪ ስራ።ይህ ፈጣሪ ግን እንፍጠር ብሎ የአካልን ከ2 በላይ መሆን ገልጾልናል። ሌላው ዘፍ.11 ላይ ንዑ ንረድ ወንክዐው ነገሮሙ ለከለዳውያን በሚለው ደግሞ ንዑ ባይ አካል አንድ እና።ንዑ የሚባሉ ደግሞ 2 ወይም ከዚያ በላይ አካላት ሊኖሩ እንደሚችሉ ይጠቁማል።ሥላሴ 3 ለመሆናቸው ደንበኛውን ምስጢር የምናገኘው ማቴ 28፣19 ላይ ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም ወአጥምቅዎሙ በአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ የሚለው ነው። መጠመቅ ደግሞ በፈጣሪ እንጂ በፍጡር አይደለምና የአካላትን ሦስትነት ያስረዳናል። ይህ አካለ ሥላሴ እንዴት ነው ቢሉ ለእግዚአብሔር ራስ እንዳለው ዳን.10፣4 ጆሮ ዓይን እንዳለው መዝ.10፥4 ጣቶች እንዳሉት ዘጸ.31፥18 እግር እንዳለው ኢሳ.8፥1 እጆች እንዳሉት መዝ.101 አፍንጫ እንዳለው ወአጼነው መዓዛ መሥዋእቱ ለኖኅ ሲል ይገኛል።ደረት እንዳለው ወጾሮሙ በእንግድዓሁ ይላል።አፍ እንዳለው ወትስማእ ምድር ቃለ አፉየ ይላል። በአጭሩ ይህ እግዚአብሔር በአካል 3 እንደሆነ እና የሰው አምሳል የእግዚአብሔር አምሳል እንደሆነ ራሱ በዘፍ.1፣26 ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ ብሎ ገልጾታል።ሌላው ለእግዚአብሔርም ለመላእክትም ለሰው ነፍስም የሴትም የወንድም ጾታ የላቸውምም አይነገርላቸውም።

ይህ አካለ ሥላሴ ግን በሁሉ ያለና የሚኖር ነው።በብዙ ገጸ ንባብ አብ ወልድን ወልድየ ሲለው ወልድም አብን አቡየ ሲለው ይስተዋላል።ይህ አብነት የባሕርይ አብነት ነው።ይህ ወልድነት የባሕርይ ወልድነት ነው።አብ አብ ስለተባለ ከወልድ አይበልጥም።ወልድም ወልድ ስለተባለ ከአብ አያንስም።ከአብ ያለ እናት ተወለደ ስንልም እንዴት ተወለደ ለሚለው ባሕርይ ዘእምባሕርይ አካል ዘእምአካል ነው።አብ ወልድን ወለደ ስለተባለ ከወልድ ቀድሞ የነበረበት ዘመን አልነበረም።ሃይ. አበ. አሐቲ ቅድምናሆሙ ለሥላሴ ወዕሩያን እሙንቱ በቅድምና እንዲል።የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ቅድምና አንድ ነው።በዘመን አንዱ ከአንዱ አይበልጥም። በመፍጠር በማዋሐድ በማጽናት በማንጻት አንድ ናቸው።ምንም እንኳ አንዱን ጉዳይ ለአንዱ ሰጥቶ ቢናገር በአካላዊ ግብር ካልሆነ በስተቀር በሥልጣናዊ ግብር አንድ ናቸው።ይህንንም የሚያሳየን ጌታ ስለ ትንሳኤው።ንሥትዎ ለዝንቱ ቤተ መቅደስ ወበሠሉስ እለት አነሥኦ... ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን አስነሳዋለሁ ብሎ ይኽውም ስለ ሥጋው እንደሆነ ተጽፋል።ስለዚህ ወተንሣእኩ በሥልጣነ ባሕቲትየ ይላል።በራሴ ሥልጣን ተነሣሁ ይላል። በሌላ በኩል ደግሞ አብ አስነሣው ይላል።በሌላ ገጸ ንባብ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ አስነሣው ይላል። ይሕ ሥልጣናዊ ግብር ስለሆነ ለአንዱ አካል አድሎ ቢናገርም በተገናዝቦ የሚሰሩት ስራ ነው። ተገናዝቦ የሌለበት አካላዊ ግብር ነው።አካላዊ ግብር የሚባለው የአብ መውለድ ማስረጽ ነው።የወልድ መወለድ ነው። የመንፈስ ቅዱስ መስረጽ ነው።

ሦስቱ አካላት ለየራሳቸው ናቸው ያሉ ነበሩ።ይህ ግን ስህተት ነው የሚያገናዝባቸው መለኮት አለና። እንደሰባልዮስ አንድ ገጽ ያሉም አሉ።ነገር ግን እፌኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሃ መንፈሰ ጽድቅ ካልዐ ዘይወጽእ እም አብ ብሎ።ካልዐ ብሎ በአካል ሦስት መሆናቸውን ስለሚያስረዳ።ጉዳዩ ፈራሽ ሆኖ ይገኛል
"""ይቀጥላል ነገ እለተ እሁድ ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ እንለቃለን። """"
ከ ሌላ ገፃ የተወሰደ

https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ሚያዝያ ፴
ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ

ሚያዝያ ሠላሳ በዚች ቀን ለእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት አለቃ የሆነ ወንጌልን የጻፈ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት አረፈ።

የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አርስጦቡሎስ ነው እርሱም ከአምስቱ አገሮች የሆነ የእናቱም ስም ማርያም ነው እርሷም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ተጽፋለች እርሱም አስቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ነው። በግብረ ሐዋርያት ማርቆስ በተባለ በዮሐንስ እናት ቤት ሐዋርያት ይጸልዩ ነበር ተብሎ እንደ ተጻፈ። እርሷም ባለጸጋ ነበረችና የዮናናውያንን የሮማይስጥን የዕብራይስጥን ትምህርት ለልጅዋ ለማርቆስ አስተማረችው።

በአደገም ጊዜ በርናባስ ወንጌልን ለመስበክ ከጳውሎስ ጋራ ሲሔድ ይዞት ሔደ በእነርሱም ላይ የሚደርስባቸውን መከራ አይቶ በጵንፍልያ ከተማ ሳሉ ትቷቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን አሕዛብ እንደ ተመለሱ እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ላይ ድንቅ ተአምራትን እንዳደረገ ተናገሩ። ይህ ብላቴና ማርቆስም ከእርሳቸው ስለ መለየቱ አዘነ ተጸጸተ።

ከዚያም አብሮአቸው ሊሔድ ፈለገ አስቀድሞ ትቷቸው ስለተመለሰ ጳውሎስ ሊአስከትለው አልወደደም በርናባስ ግን ወሰደው አጎቱ ነውና። በርናባስም ከአረፈ በኋላ ወደ ሮሜ አገር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሒዶ ለእርሱ ደቀ መዝሙሩ ሆነ በዚያም ቅዱስ ጴጥሮስ የተረጐመለትን ወንጌልን ጻፈ በሮሜ አገርም አስተማረበት። ከዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝና በሐዋርያትም ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ። በውስጥዋም የከበረ ወንጌልን አስተማረ ደግሞም በአፍራቅያና በአምስቱ አገሮች በርቃ በሚባልም አገር ወደ እስክንድርያ ከተማ በገባ ጊዜ ጫማው ተቆረጠ።

በዚያም በከተማው መግቢያ ጫማ ሰፊ ነበረ። ቅዱስ ማርቆስም እንዲሰፋለት ለርሱ ሰጠው ሲሰፋም ጣቱን ወግቶ ሰነጠቀው ከእርሱም ደም ፈሰሰ በዮናኒም ቋንቋ ኢታስታዖስ አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም ስሙን የምትጠራው አውቀኸው ነውን አለው እንጠራዋለን እንጂ አናውቀውም አለ።

እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ አባታችን አዳም ትእዛዙን እንደተላለፈ የጥፋት ውኃም እንደ መጣ ሙሴንም እንደላከውና እስራኤልን ከግብጽ እንዳወጣቸው ሕግንም እንደ ሠራላቸው ናቡከደነጾርም ወደ ባቢሎን ማርኮ እንደወሰዳቸውና ከሰባ ዓመት በኋላ ወደ አገራቸው ኢየሩሳሌም እንደ ተመለሱ ክርስቶስ ሥጋ በመልበስ ወደ ዓለም ስለ መምጣቱ ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩ ያስተምረው ዘንድ ጀመረ።

ከዚያም በኋላ ወደ ምድር ምራቁን ትፍ ብሎ ጭቃ አድርጎ ጣቱን ቀባው ወዲያው ዳነ በጌታችንም አመነ። ያም ሰፊ ስሙ አንያኖስ ነው። ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወስዶ ልጆቹን ዘመዶቹንም ወደ ርሱ አቀረበ እርሱም አስተምሮ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።

በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሰዎች በበዙ ጊዜ የቅዱስ ማርቆስን ዜና ሰምተው የአገር ሰዎች ሊገድሉት ተሰበሰቡ እርሱም አንያኖስን ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሹሞ ልጆቹን ቄሶችና ዲያቆኖች አድርጎ ከዚያም ወደ በርቃ ወደ አምስቱ አገሮችም ወጥቶ አስተማረ። በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው በእርሳቸውም ዘንድ ሁለት ዓመት ኖረ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው።

ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ተመለሰ ምእመናንም ተጨምረው በዝተው በታወቁ ቦታዎች ሁሉ በባሕሩም ዳር በላሞች መካበቢያ በሚባለውም አብያተ ክርስቲያን ሠርተው አገኛቸው።

ከሀድያንም የከበረ ሐዋርያን ይገድሉት ዘንድ በብዙ ድካም ፈለጉት እርሱም አምስቱን አገሮች ሲጐበኝ በሥውር ወደ እስክንድርያ ከተማ ይገባ ይወጣ ነበር። በአንዲትም ዓመትም ከአምስቱ አገሮች ተመልሶ ሚያዝያ ዐሥራ ሰባት ቀን በመድኃኒታችን የትንሣኤ በዓል ወደ ቤተክርስቲያን ገባ ሕዝቡም ሁሉ በዙሪያው አሉ። ከሀድያንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በአንገቱ ውስጥ ገመዶችን አድርገው በከተማው ሁሉ ጎተቱት። እነርሱም ገና እንደፍየል ሙክት እንጎትተዋለን እያሉ ይጮኹ ነበር። በላሞች መካበቢያና በሀገሪቱ አደባባይ በከተማውም ዙሪያ በየቀኑ ሲጎትቱት ኖሩ።

ሌሊትም በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያት ጋራ በነበረበት አርአያ ሁኖ ተገለጠለት ሰላምታም ሰጥቶ አጽናናው ቃል ኪዳንም ሰጠው። እነሆ አንተ ከወንድሞችህ ሐዋርያት ጋር ተካከልህ አለው። እርሱም በልቡናው ፈጽሞ ደስ አለው። በማግሥቱም ሁለተኛ ገመዶችን በአንገቱ አድርገው በአገሮች ሁሉ ጎተቱት በቀኑም መጨረሻ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።

ከሀዲዎችም ታላቅ እሳትን አንድደው የቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ከውስጡ ጨመሩ። በክብር ባለቤት ጌታችን ፈቃድም ንውጽውጽታ ጨለማ ቀዝቃዛ ነፋስ መብረቅና ነጐድጓድ ሆነ። ፀሐይም ጨለመ ከሀዲዎችም ሸሹ ምእመናንም መጥተው የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ወሰዱ ምንም ጥፋት ሳይደርስበት ደኀና ሆኖ አገኙት በመልካም ልብስም ገንዘው በጥሩ ቦታ አኖሩት መታሰቢያውንም አደረጉ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ማርቆስ ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ቅዱስ ሲኖዶስ በ2ኛ ቀን ውሎው የተከፋፈለ  ሲኖዶስ እንደሌለ እና ከዚህ ሐሳብ ውጪ የሆነ አካል ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ውጪ ገለጸ !

ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

የ2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የሁለተኛው ቀን ውሎን አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባባቢዋ  አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማብራሪያ ተሰጥተዋል ።

ብፁዕነታቸው በሁለተኛው ቀን በነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሁለት ርዕሰ ጉዳዮች መወያያየቱን ገልጸዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በቀዳሚነት በሀገር ሰላም ዙሪያ በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ጉባኤው ብዙ ሲወያይ  ከቆየ በኋላ በመጨረሻም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁሉን ማድረግ ትችላለች ፣ ምእመናንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ይሰማሉ የሚለው ሐሳብ አሸንፎ ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስን ወክለው  የሚሰሩ ሦስት ብፁዓን አባቶች ተመርጠው  የሀገር ሰላምን በተመለከተ ረዥም ርቀት በመሔድና ከሚመለከተው አካል ጋር ሁሉ በመነጋገር   በሀገር ሰላም ዙሪያ  ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉና አሁን ካለንበት መከራ የምንወጣበትን  መፍትሔ እንዲያመጡ ተመርጠዋል።

በቀጣይነት በወቅታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ችግር አስመልክቶ በትግራይና በኦሮሚያ አህጉረ ስብከት የነበሩትን ችግሮች መነሻ በማድረግ

ሀ) በክልል ትግራይ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የትግራይ አባቶችና  አባላቱን በአካል የሚያነጋግሩ  ብፁዓን  አባቶች ተመርጠው  ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

- በተጨማሪም ተቋርጦ የነበረው በጀት እንዲለቀቅ
- የማጽናኛ  መርሐ ግብር  እንዲካሄድና በተቻለ መጠን   አስቸኳይ  እርዳታ እንዲደረግ በጉባኤው ተወስኗል።

ለ) በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የተከሰተውን የቤተ ክርስቲያን ፈተና በተመለከተ ሰፊ ውይይት ከተደረገ እና ወደ መግባቢያ ሐሳቦች መደረሱን ገልጸው
በስድስት አህጉረ ስብከቶች ምንም ዓይነት  የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እየተሰጠ አለመሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ
የማያዳግም የመፍትሔ ለመስጠት ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ከሦስቱ ብፁዓን አባቶች  ጋር አራት ብፁዓን አባቶችን ተጨማሪ በማድረግ በቀጥታ የነበረው ችግር ሙሉ በሙሉ መቀረፉንና ከአንድ ሲኖዶስ ውጪ ሌላ አለመኖሩን ለመንግሥት አካላት  በጋራ ሔደው  የተደረሰበትን  ስምምነት  ተገቢውን  መረጃ እንዲሰጡ
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን
ብፁዕ አቡነ  ሩፋኤልን
ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን
ብፁፅ አቡነ  ሳዊሮስን
ብፁዕ  አቡነ ዜና ማርቆስን
እና ብፁዕ  አቡነ ኤውስጣቴዎስን
በመመደብ እነዚህ ሰባት ብፁዓን  አባቶች  በአንድ  ላይ  ከመንግሥት  ጋር በመነጋገር  ፍጹም በሆነ የመግባባት ስምምነት መፈጠሩን ገልጸው
ከእንግዲህ በኋላ የተከፋፈለ ሲኖዶስ እንደሌለ እና ከዚህ ሐሳብ ውጪ የሆነ አካል ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ውጪ የሆነ መሆኑን በአንድነት ለመንግሥት  እንዲያሳውቁ  መወከላቸውንም ገልጸዋል።

በቀጣይም ያሉንን የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች በዚህ መልኩ በመግባባትና በመተማመን በመፍታት  በሀገርና በቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነትን በማያዳግም ሁኔታ የሚያውጅ ቆይታ ይሆን ዘንድ መላው ሕዝበ ክርስቲያን በጸሎት አስቡን በማለት ብፁዕነታቸው አባታዊ መልእክታቸውንና ቡራኬአቸውን በመስጠት የሁለተኛውን ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ አጠር ባለ መልኩ ገልጸውልናል ሲል ኢኦተቤ ቴቪ ዘግቧል።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ቅዱስ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እና ብፁዕ አቡነ ቶማስ ቀደም ሲል ሲያገለግሉባቸው በነበሩባቸው አህጉረ ስብከት አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ወሰነ !

ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሎ ዕለታዊ ማብራሪያ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በሦስተኛ ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡብ ትግራይ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና መተከል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቀደም ሲል ያገለግሉባቸው በነበሩባቸው አህጉረ ስብከት አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ጉባኤው ወስኗል።

ጉባኤው በዛሬው ውሎው እንዲነጋገርበት ተይዞ የነበረው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ጉዳይ የጉባኤው የመጨረሻ አጀንዳ እንዲሆን የአጀንዳ ሽግሽግ አድርጓል። እንዲሁም የዋልድባ ዳልሻህ ኪዳነምሕረት ማኅበረ ደናግል ገዳምን በተመለከተ ፣ የያዘው አጀንዳ ላይ መወያየቱን እና ለውሳኔ በይደር መቆየቱን ገልጾ ኢኦተቤ ቴቪ ዘግቧል ።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ውስብስብ የሆነውን የቤተ ክህነት ችግር እንደሚያቃልል ተስፋ የተጣለበትን መሪ ዕቅድ መርምሮ ማጽደቁ ተገለጸ !

ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ በስድስተኛ  ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በተለያዩ ጉዳዮች ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል። የመጀመሪያው ለረጅም ጊዜ የቤተ ክህነቱን ውስብስብ ችግሮች ይፈታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የመሪ ዕቅድን በተመለከተ ሲሆን  በዚህ ውስጥ መንፈሳዊ ልማት ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና አስተዳደር ጉዳዮችን ተመልክቷል ። በዚሁ አጀንዳ (ሀ) የመንፈሳዊ ልማት ዓላማ የቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ጉዳይ በምድሪቱ ላይ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ መፍጠር ፣ መገንባት የሚያስችል ሆኖ መጽደቁን የተናገሩት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በዚሁ መሠረት ወደ ሥራ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዚሁ አጀንዳ (ለ) ቤተክርስቲያን በብዙ የልማት ሥራዎች ውስጥ የምትሳፍበት  እድል መኖሩ የተመላከተ ሲሆን ይኸው  ወደ ተግባር እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሁሉም ሰው በመሪ ዕቅዱ ትግበራ  ላይ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል ።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ግንቦት ፲፩
ቅዱስ ያሬድ ካህን ወማኅሌታይ

ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅዱስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያናት ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት።

ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ።

ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው።

ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ።

በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊያቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ።

ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ።

ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ።

ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው።

የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም።
በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም።

ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው።

ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበረሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ።

ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል።

የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች
፩. ድጓ
፪. ጾመ ድጓ
፫. ዝማሬ
፬. መዋሥዕት
፭. ምዕራፍ  ናቸው።

የዜማ ዓይነቶች
፩. ግዕዝ
፪. ዕዝል
፫. አራራይ ናቸው።

የቅዱስ ያሬድ ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
የይቅርታ  እናት  ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ   !

✍️-የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የተጋድሎ ታሪክ እንደ ባሕር አሸዋ፣እንደ ሰማይ ክዋከበት ተቆጥሮ ተሰፍሮ ከማያልቀው ነገረ ቅዱሳን  መካከል አንዱ ነው።
      -ነገረ ቅዱሳንን መረዳት፣ማስረዳት ፣ማወቅና ማሳወቅም የወንጌልን አዝመራ መሰብሰብ ነው።
     - ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዚህ ዓለም ከከበሩ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ደጋግ ባልና ሚስት የተገኘችና የተመረጠች እናት ናት።
✍️የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የአባቷ ስም ደራሳኒ፣የእናቷም ስም እሌኒ ይባላሉ። በሸዋ ክፍለ ሀገር በቡልጋ አውራጃ ጌየ በተባለች አካባቢ እንደ ተወለደች ታሪኳ ያስረዳል።(
#ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘወርኃ መስከረም -ቊጥር-፪ )

    ደረሳኒ እና ዕሌኒ ልጃቸውን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን በሃይማኖታዊና ሥነ-ምግባራዊ ሥርዓት አሳደጓት(ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘመስከረም -ቊጥር፬ ) መጽሐፈ ገድሏ" ልጅቱ ክርስቶስ ሰምራ ባደገችና ዐቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ የንጉሥ ባለሟል የሆነ••••የኢየሱስ ሞዓ ልጅ ለሠምራ ጊዮርጊስ በሕግ አጋቧት"ይላል።( ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘመስከረም -ቊጥር፮ )እግዚአብሔር በረድኤት ከሚገለጥባቸው የቅድስና መንገዶች አንዱ ቅዱስ ጋብቻ ነው።

✍️- ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለሠምረ ጊዮርጊስ ፲፩ ልጆች ወለደችለት ከነዚህም መካከል ፱ ወንዶች፣ ፪ቱሴቶች ነበሩ።(ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘመስከረም -ቊጥር- ፲፬) ልጆቿንም ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች በክብርና በሥርዓት አሳደገቻቸው።

✍️- ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትዳሯ ሰላማዊነት፣የባሏ አክብሮትና ፍቅር፣የልጆቿ መብዛት ፣የሀብትና ንብረቷ መድለብ እየሠመረ ቢሄድም የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልብ ግን የሚያስበው ግን ምናኔ ነበር።ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ፣ከዚያም በኋላ ልብሰ ምንኲስናዋን፣ ማለትም ቆቧን፣ ቀሚሷን፣ አጽፏን፣መታጠቂያዋን፣ አዘጋጀች።

✍️ ያልተለመደ ነገር ሲደረግ የተመለከቱት ቤተሰቦቿ ለምን እንደ ምታዘጋጀው ፣ለጠየቋት ጥያቄ "
#ሃይማኖት ያስተማሩኝ አባቴ ልብስ አልቆባቸዋል፣ሲሉ ሰምቼ ለእርሳቸውም ነው የማዘጋጀው ፣"አለቻቸው።

      ከዚህ ላይ ሃይማኖታዊ ጥበብ ያልተከሰተላቸው አስመሳዮች ለምን የሌላ ነው አለች" ሊሉ ይችላሉ።ይህ ሥርዓት ግን ለ፪ ነገር ይጠቅማል።

፩•የምናኔ ጉዞ ገና ሳይጀመር በውዳሴ ከንቱ ላለመጠለፍ፣
፪•ይህን ርምጃዋን ዲያብሎስ በተለያዩ ሰዎች አድሮ ሊያደናቅፈው ስለሚችል ከዓላማዋ ሊገታት ስለሚችል መልካም ጥበብ ነው።በሌላ በኩል ልማደ መጻሕፍትም ነው።
-✍️ ከዕለታት አንድ ቀን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አገልጋዮችን " ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሂድ" ብላ ይዛቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደች ።የምናኔው መጀመሪያ ነበር።

✍️- ከዚያም ቤተ ክርስቲያን ጥቂት እንደምትቆይ ለቤተሰቦቿ አንዲት ፣ሠራተኛና አንድ ሕፃን ብቻ አስቀርታ
ሌሎችን አሰናብታ ምናኔው ተጀመረ፣የወላድ መናኝ የሚያልፈውን በማያልፈው ዓለም ለመለወጥ ልጇን አዝላ እግሬ አውጭኝ ብላ ገሠገሠች።እግሮቿ በደም ታጠቡ፣የራስ ፀጒሯ ተላጭቶ ወደቀ።የገዳማውያን አለባበሷን ለብሳ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገባች።ማቴ 10÷37 በተግባር ላይ ሲተረጎም ተመለከትን።

✍️የተጋድሎ ሕይወቷ እየቀጠለ ኼዶ ከመከራዋ ብዛት ከገድሏ ጽናት ሰውነቷ ተበሳስቶ የዓሣ መመላለሻ እስኪሆን ድረስ ከባሕሩ ገብታ ወደ ግራና ቀኝ ሳትል ፲፪ ዓመት ሙሉ በጣና ባሕር ውስጥ ቆማ ትጸልይ ዘንድ ኃይለ እግዚአብሔር ተሰጣት።፲፪ ዓመት ሙሉ በባሕር ውስጥ መቆየት የሚቻለው ማነው? የሚል ጎደሎ እምነት ያለው ወገን ካለ: ባሕረ ኤርትራ እንደ ግድግዳ ቆሞላቸው እስራኤላውያን ማሻገር ይችላሉ ወይ?" ለሚያምን ሁሉ ይቻላል"(ማር 9÷22)

✍️መሴ በሲና ተራራ 40መዓልትና 40 ሌሊት ያለምግብ መቆየት ይችላል ወይ?ሠለስቱ ደቂቅ እሳት ውስጥ ገብተው ሳይቃጠሉ መውጣት ይችላሉ ወይ? ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን መጠየቁ የተሻለ ይሆናል።

✍️" ከአቤል ጀምሮ እስከ ዛሬ የሞቱት ከዛሬም በኋላ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚሞቱትን አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው "አለችው ( ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘግንቦት -ቊጥር፲፯ )

√ የአማላጅነት ጸጋዋ:
የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ሕይወት የቅድስና ሕይወት በመሆኑ ለአማላጅነት የተመቸ ነው።

✍️ጌታ ምን አደርግልሽ ዘንድ ትሻለሽ? አላት ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ " አቤቱ ፈጣሪየ ሆይ ! ፈቃድህስ ቢሆን የአዳም ልጆችን ከሥቃይ ከኵነኔ ይድኑ ዘንድ ዲያብሎስን ይቅር ትለው ወይም ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ:የኃጥእን መመለሱን እንጂ የጥፋቱን አትወድምና አለችው ፣ የምለምንህ ወይም ማረው የምልህ ዲያብሎስን ወድጄው አይደለም ነገር ግን እሱ ከተማረ በአዳም ልጆች ላይ ሥቃይና ኵነኔ ሊኖር አይችልም ብየ በመገመት ነው እንጂ " ( ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘግንቦት -ቊጥር36 -38 )ይህን ልመና ጌታችን የሚያስደንቅ ልመና ብሎታል።ይህ መልካም ሐሳብ የሚመነጨው የእምነት ፍቅር ካላቸው ሰዎች ልብ ውስጥ ብቻ ነው።
- የዲያብሎስን ተንኮል የሚያውቅ መድኃኔዓለም የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን የአማላጅነት ነጻነት አልገደበውም።
√ የተሰጣት ቃል ኪዳን
"ሥጋሽን እንደ እናቴ እንደ ድንግል ማርያም ሥጋ እቀድሰዋለሁ" ማለት የእመቤታችን ሥጋ በኅሊና አምላክ የተቀደሰ ሲሆን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ሥጋ ደግሞ በገድል ፣በትሩፋት ተቀጥቅጦ ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ያመልክታል።ነሐሴ 24 የዕረፍት መታሰቢያዋ ይከበራል።
  
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ወርቃማዋ ፎገራ(The Golden lans scape of Fogera)  በደሴተ ጓንጉት ደብረ ምሕረት ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ክብረ በዓል ዓመታዊ በዓሏ በየዓመቱ ግንቦት ፲፪ ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡ከወረታ ከተማ በስተ ምዕራብ በኩል  25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጣና ዳር ዋገጠራ ቀበሌ ትገኛለች ፡

- የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ  በረከቷ ፣ረድኤቷ ፣አማላጅነቷ አይለየን!
#ምንጭ
- ሐመር መጽሔት ግንቦት /ሰኔ 1997ዓ/ም
- ነገረ ቅዱሳን -፪ ( ገጽ-68)
- ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ(በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት- 1992ዓ/ም )
- ልሳነ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ ሚያዝያ 7ቀን 1993 ቁ 53
የይቅርታ  እናት  ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ   !

✍️-የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የተጋድሎ ታሪክ እንደ ባሕር አሸዋ፣እንደ ሰማይ ክዋከበት ተቆጥሮ ተሰፍሮ ከማያልቀው ነገረ ቅዱሳን  መካከል አንዱ ነው።
      -ነገረ ቅዱሳንን መረዳት፣ማስረዳት ፣ማወቅና ማሳወቅም የወንጌልን አዝመራ መሰብሰብ ነው።
     - ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዚህ ዓለም ከከበሩ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ደጋግ ባልና ሚስት የተገኘችና የተመረጠች እናት ናት።
✍️የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የአባቷ ስም ደራሳኒ፣የእናቷም ስም እሌኒ ይባላሉ። በሸዋ ክፍለ ሀገር በቡልጋ አውራጃ ጌየ በተባለች አካባቢ እንደ ተወለደች ታሪኳ ያስረዳል።(
#ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘወርኃ መስከረም -ቊጥር-፪ )

    ደረሳኒ እና ዕሌኒ ልጃቸውን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን በሃይማኖታዊና ሥነ-ምግባራዊ ሥርዓት አሳደጓት(ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘመስከረም -ቊጥር፬ ) መጽሐፈ ገድሏ" ልጅቱ ክርስቶስ ሰምራ ባደገችና ዐቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ የንጉሥ ባለሟል የሆነ••••የኢየሱስ ሞዓ ልጅ ለሠምራ ጊዮርጊስ በሕግ አጋቧት"ይላል።( ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘመስከረም -ቊጥር፮ )እግዚአብሔር በረድኤት ከሚገለጥባቸው የቅድስና መንገዶች አንዱ ቅዱስ ጋብቻ ነው።
2025/07/14 02:06:30
Back to Top
HTML Embed Code: