የአዲስ አበባ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን ሊከስ መሆኑ ተሰማ።
በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አማካኝነት እየፈረሱ የሚገኙት በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ጉዳይ አሳስቦኛል ያለው የአ.አ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኮርፖሬሽኑን ልከስ ነው ብሏል።
በቅርስነት የተመዘገበው የራስሃይሉ ተክለሃይማኖት መኖሪያ ቤት ያፈረሰው ወደ ፍርድቤት ለመውሰድ በሂደት ላይ መሆኑንም የአ.አ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
ቤተእምነቶችን፤ ድልድዮችና ሃውልቶችን ጨምሮ በከተማዋ ከ440 በላይ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን 316 የሚሆኑ ቤቶችን በቅርስነት መዝግቦ የቅርስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለመስጠት በሂደት ላይ መሆኑንም ነው ቢሮው የገለጸው፡፡
ከነዚህም መካከል ፒያሳ ሰባራ ባቡር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የራስሃይሉ ተክለሃይማኖት መኖሪያ ቤት ተጠቃሽ ነው፡፡
ነገርግን በቅርስነት የተመዘገበው ይህ ታሪካዊ መኖሪያ ቤት ከቢሮው እውቅና ውጪ በቤቶች ኮርፖሬሽን ሙሉ ለሙሉ መፍረሱን በቢሮው የቅርስና ጥገና እንክብካቤ ዳይሬክተር ደረጀ ስዩም ለባላገሩ ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡፡
ባላገሪ ቴሌቭዥን በስፍራው ተገኝቶ እንዳረጋገጠው ይህ ታሪካዊ መኖሪያ ቤት ሙሉ ለሙሉ የፈረሰ ሲሆን ዙሪያውም ታጥሮ ተመልክተናል፡፡
እንደ ራስሃይሉ ተ/ሃይማኖት ያሉ አብዛኞቹ ቅርሶች ጉዳት የሚደርስባቸው በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አማካኝነት መሆኑን የገለጹት አቶ ደረጀ፤ ተቋሙ ቤቶቹን በባለቤትነት የማስተዳድረው እኔ ነኝ በማለት ቅርሱ እሴቱን እንዲያጣ የማድረግ ዝንባሌ መኖሩንም አንስተዋል፡፡
በአሰራርጥበቡ፤ የተሰራበት ጊዜና ቁስን መሰል መስፈርቶችን አሟልቶ መኖሪያ ቤቱ በቅርስነት መመዝገቡን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ አሁን ግን መፍረሱን ተከትሎ ቢሮው ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት ለመውሰድ በሂደት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ለቀጣይ የተመዘገቡት ቅርሶች በፕላን ውስጥ የማካተት ስራ እየተሰራ መሆኑን በማንሳት ቅርሶችን መጠበቅ የሁሉም ሃላፊነት ሊሆን እንደሚገባም አቶ ደረጀ ተናግረዋል ጨምረው ተናግረዋል፡፡
#ባላገሩዜና
@Dire_Tube_news

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከ200 በላይ ንጹሃን ሰዎችን እንደገደሉ ዶቸቬለ ዘግቧል፡፡ በጥቃቱ ከ40 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ታጣቂዎቹ የክልሉ ልዩ ኃይል ከአካባቢው በወጣ ማግስት ነሐሴ 12 በወረዳው 6 ቀበሌዎች እድሜና ጾታ ሳይለዩ የአማራ ብሄር ተወላጆችን ለይተው እንደገደሉ የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ኮምንኬሽን ቢሮ በበኩሉ ጥቃቱን ያደረሱትን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ለማደን ልዩ ኃይል እንደተሠማራ ለጣቢያው ተናግሯል፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የሐረሬ ክልል መንግሥት አሳማኝ ያልሆነ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር በምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጣሪያ እንደወሰነ ፎርቹን ዘግቧል፡፡ የዋጋ ጣሪያ ከተጣለባቸው ሸቀጦች መካከል፣ የምግብ ዘይት፣ ጤፍ፣ ስጋ እና ሲምንቶ እንደሚገኙበት ዘገባው ጠቅሷል፡፡ የዋጋ ጣሪያው ከተያዘው ወር መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል ተብሏል። ሌሎች ክልሎች ግን ሸቀጦችን ያላግባብ የሚያጠራቅሙ ነጋዴዎችን ከማስጠንቀቅ አልፈው እስካሁን የዋጋ ጣሪያ ለመወሰን አልሞከሩም፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የዋንጫ ሽልማት ተሸለሙ፡፡
የውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በዛሬው እለት የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ሽልማቱን ያበረከተላቸው የኢትዮጵያ የታሸገ ውሀ የለስላሳና የአትክልት ፍራፍሬ ማቀነባበርያ አምራቾች ኢንዱስትሪ ማህበር ነው፡፡
ማህበሩ ሽልማቱን ያበረከተላቸው ሚኒስትሩ የህዳሴን ግድብ በተለመከተ ለአለም ማህበረሰብ እያሳዩት ካለው የበሰለ አመራር እና የህዳሴ ግድቡ ሁለተኛ ዙር የውሀ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ በመከናወኑ ነው ተብሏል፡፡
የማህበሩ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጌትነት በላይ እንደተናገሩት፣በፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን አቋም እውቀት በታከለበት መንገድ የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ያንጸባረቁት እና ያደረጉት ንግግር በታሪክ መዝገብ መቀመጥ የሚችል ነው ብለዋል፡፡አሁን ላይ የህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 80 ከመቶ መድረሱ የተነገረ ሲሆን የግድቡ ግንባታ የሲቪል ሥራዎች አፈጻጸም ደግሞ 91 በመቶ ደርሷል ተብሏል።
Ethio FM

በመንግስት ውሳኔ እንዲዘጉ የተደረጉ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ወደ ሃገራቸው እየገቡ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደ አዲስ ባዋቀረው አሰራር ብቁና ወጭ ቆጣቢ የዲፕሎማሲ ግንኙነትን መፍጠሪያ ብሎ ካስቀመጣቸው ውሳኔዎች መካከል በአንዳንድ ሃገራት የሚገኙ ኤምባሲዎችን መዝጋት ነበር።
በውሳኔውም መሰረት በርካታ ዲፕሎማቶች ወደ ሃገራቸው እየገቡ እንደሚገኙ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። በበረራ ትኬት መስተጓጎል እና በአንዳንድ ችግሮች ያልገቡ ዲፕሎማቶች እንዳሉ የተናገሩት አምባሳደር ዲና እስከ ነሃሴ 21-2013 ዓ.ም ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል። ይህ የለውጥ ሂደት ውጤታማነቱ ይታያል ያሉት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ ውጤታማነት ከሌለው ይቀየራል ብለዋል።
“በተለያዩ ምክንያት ዲፕሎማቶቹ ካሉበት ሃገር ወደ ኢትዮጵያ ላይመለሱ ይችላሉ” ያሉት ቃል አቀባዩ “በዚህ ሃገር በተፈተነችበት ወቅት አውሮፓ ካልቆየሁ፤ አሜሪካ ካልተኛሁ የሚል ዲፕሎማት ይኖራል ብዬ አላስብም” በማለትም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ኢትዮጵያ በአንዳንድ ሃገራት የሚገኙ ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ እንደምትችል ፍንጭ መስጠታቸው አይዘነጋም።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት አዲስ አበባ ገብተዋል
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት አዲስ አበባ ይገኛሉ።
ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ የተገኙት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት መሆኑ ተነግሯል።
በቆይታቸውም ሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ለመመከር ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልና የመከለከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታን እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሹማምንት ለፕሬዝዳንቱ አቀባበል አድርገውላቸዋልም ተብሏል።

ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ የመፍታት አቅም ስላላት የውስጥ ጉዳይዋ ተደርጎ ሊታይ እንደሚገባ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት አመለከቱ።
@Dire_Tube_news
በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ በመከረው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ከቋሚና ተለዋጭ አባል አገራት ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷው አቅም ልትፈታው ይገባል ብለዋል።
በተለይ ሩሲያ እና ህንድ አሸባሪው ህወሓት የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ተላልፎ በአጎራባች የአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ የፈጸመውን ግፍ አውግዘዋል።
ሩስያ በተወካዩዋ በኩል "ሰኔ ላይ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠና አቅም ያለው መንግስት በኢትዮጵያ ስላለ ችግሩን ራሳቸው ኢትዮጵያውያን ይፈቱታል" ብላለች።
ቻይና በበኩሏ"በሰብአዊ እርዳታ ስም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመጣስ መሞከርን ቻይና በፍፁም አትቀበለውም፤የአለም ሀገራት በሙሉ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን ሊሆኑ ይገባል፤ በእርዳታ ስም ችግር ለመፍጠር የሚሞክሩ ቡድኖች የተመድን ህግ ሊያከብሩ ይገባል" በማለት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን እንደምትቆም አስታውቃለች።
የኢትዮጵያ መንግስት ችግሩን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ ያስታወቀችው ህንድ ደግሞ፣ "ችግሩን ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግስት በቂ ነው" ብላለች።
ኬንያም ኢትዮጵያ ላይ ለመጣል የሚታሰብ ምንም አይነት ማዕቀብ እንደማትደግፍ አመልክታለች።
በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የሞከሩት የአሜሪካና እንግሊዝ ሀሳብ ኢትዮጵያ ችግሯን ለመፍታት በምታደርገው ጥረት የውጭ ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም በሚል በሌሎች አገራት በተነሱ ሀሳቦች ተቃውሞ ቀርቦበታል።

ኢትዮጵያ ነጻነቷን እና ሉአላዊነቷን ለማስጠበቅ በምታደርገው የህልውና ዘመቻ እየደረሰባት ያለውን የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበሉት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።
ሳልቫ ኪር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር በትላንትና እለት ከተወያዩ በኋላ ህወሃት እያደረሰ ያለውን ጥቃት ኮንነዋል ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትር የፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል።
“የጉብኝቱ ትኩረት ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና የክልል ጉዳዮች ላይ በጋራ መነጋገር ነበር” ሲሉም አክለዋል፡፡
ኪር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቢትሪስ ዋኒ-ኖህን ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የልዑካን ቡድን ጉብኝት ላይ “በተለይ ትኩረት የሰጠው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን እና የጋራ የመሠረተ ልማት ግንባታን ማጠናከር ነበር” ማለታቸውን ሱዳን ፖስት ዘግቧል፡፡
አሸባሪውን ህወሃትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጎን እንቆማለን ያሉት ፕሬዝዳንቱ በሰኔ ወር የተከናወነው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መጠናቁንና በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተም እንኳን ደስ አለዎት ሰሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 117 ሚሊየን መድረሱ ተነገረ
የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 117 ሚሊየን መድረሱና ከአለም 14ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኘ ተገለፀ፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በዛሬው እለት የስነ ህዝብ እና የአካባቢ ጥበቃ ድርጅት ከኮንሰርቲየም ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመተባበር የአለም ስነ ህዝብ ቀንን አክብረዋል፡፡
በፈረንጆቹ ከ1987 የአለም የህዝብ ብዛት 5 ቢሊየን የደረሰበትን ወቅት ምክንያት በማድረግ እስካሁን ድረስ እየተከበረ የሚገኝው የአለም ስነ ህዝብ በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ደረጃ መከበሩ ተገልጿል፡፡
በቦታው የተገኙት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባሁኑ ሰአት የአለም ህዝብ ብዛት 7 ነጥብ 8 ቢሊየን መድረሱን ተናግረዋል፡፡
የአለም የስነ ህዝብ ላይ ጥናቶች የሚያደርገው ፖፑላሽን ሪፈረንስ ቢሮ መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 117 ሚሊየን እንደደረሰ ዶ/ር ሊያ ታደሰ መናገራቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ በየአመቱ የ2 ነጥብ 6 ሚሊየን እድገት እንደሚያሳይ የተገለፀ ሲሆን የስነ ህዝቡ መጠን በዚህ አይነት መንገድ የሚቀጥል ከሆነ በ2035 ዓ.ም 160 ሚሊየን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በሚቀጥሉት 30 ዓመታት የዓለም የህዝብ ቁጥር ዕድገት ከፍተኛውን ቁጥር ከሚይዙ ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ልትሆን እንደምትችልም ተገልጿል፡፡

በኤካ ኮተቤና ሚሊኒየም አዳራሽ ያሉ የጽኑ ህክምና አልጋዎች ሙሉ ለሙሉ በህመምተኞች መያዛቸው ተገለጸ
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ፤ወደ ጽኑ ህክምና የሚገቡ እና ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዕለታዊ ሪፖርት ያስረዳል።
ዜጎች ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከቫይረሱ እንዲጠብቁ ጤና ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት በማሳሰብ ላይ ይገኛሉ።በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው የለይቶ ህክምና ከሚደረግባቸው ማዕከላት መካከል ኤካ ኮተቤ እና የሚሊኒየም ኮቪድ 19 ህክምና ማእከል ተጠቃሽ ናቸው።
አል አይን አማርኛ በነዚህ ማዕከላት የኮሮና ቫይረስ ህመምተኞች አገለግሎት ምን ይመስላል ሲል የማዕከላቱን አመራሮች ጠይቋል።
የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ተጠባባቂ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ዮናስ ገብረእግዚያብሄር ለአልአይን እንዳሉት ካለፉት ሶስት ሳምንታት ጀምሮ በቫይረሱ ተይዘው ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው ብለዋል።
Via Al Ain

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን እንዲከሰሱ ተጠየቀ
ብሊንከን የተከሰሱት የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም አላስጠበቁም ተብለው ነው
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የገቡትን የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ማስበር ባለመቻላቸው እንዲከሰሱ ተጠይቋል፡፡
ሚኒስትሩ እንዲከሰሱ የጠየቁት የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ምክር ቤት የገቡ አባላት መሆናቸውን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡
አንቶኒ ብሊንከን ወደ ኃላፊነት ሲመጡ የገቡትን ቃል ማሳካት እንዳልቻሉ የገለጹት አባላቱ በዚህም ምክንያት መከሰስ አለባቸው በሚል የሀገሪቱን ሕጎች እየጠቀሱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ብዙ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት በብሊንከን ላይ ጥያቄ ቢኖራቸውም የሚሪላንድ ተወካዩ አንዲ ሃሪስ እና የደቡብ ካሮላይና ተወካዩ ራልፍ ኖርማን ግን የሕግ አንቀጾችን ሳይቀር እያጣቀሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒትሩ መከሰስ እንዳለባቸው መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
የአፍጋኒስታን ጉዳይ እንዲሻሻል መሰራት ቢገባውም ይህንን ማድረግ ባለመቻሉ ከፍተኛ መቅሰፍት መድረሱን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡
የአፍጋኒስታንን ጉዳይ ማስተካከል በፕሬዝዳንት ባይደን ትከሻ ላይ የወደቀ ቢሆንም በዋናነት ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን የማማከር ኃላፊነት ነበረባቸው ተብሏል፡፡
ከትናንት በስቲያ በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል ሃሚድ ካርዛይ ዓለም አቀፍ አወሮፕላን ማረፊያ ውጭ ላይ በተከሰተው ፍንዳታ 13 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው እና ምስቅልቅል የበዛበት ወታደሮችን የማስወጣት ተግባርም አንቶኒ ብሊንከንን ሊያስጠይቅ እንደሚችል የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ፤ የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት በሚጠበቅባቸው ልክ አለማማከራቸው እና አሜሪካ በአፍጋኒስታን ያላትን ብሐየራዊ ጥቅም በተገቢ ሁኔታ ማሳወቅ አለመቻላቸው ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ነው የተገለጸው፡፡
የምክር ቤት አባላት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንዲከሰሱ ቢጠይቁም ፤ ሌሎች ደግሞ በካቡል ሃሚድ ካርዛይ ዓለም አቀፍ አወሮፕላን ማረፊያ ውጭ ላይ በተከሰተው ፍንዳታ 13 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው በተለያየ ደረጃ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ተናግረዋል፡፡
በአሜሪካ ሕገ መንግስት መሰረት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት በተመለከተ ለኮንግረንሱ እና ለሕዝቡ ማሳወቅ እንዳለባቸው ቢደነግግም አንቶኒ ብሊንከን ግን ይህንን አለማድረጋቸውን የምክር ቤቱ አባላት ጠቅሰዋል ተብሏል፡፡
በታሊባንን ቁጥጥር ስር ባለ ሀገር የአሜሪካን ዜጎች ለአደጋ አጋልጦ በመውጣት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ተጠያቂ እንዲሆኑ ክስ ይቅርብባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ፎክስ ኒውስ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ምክር ቤት የገቡ አባሎች አንቶኒ ብሊንከን እንዲከሰሱ ፍላጎት አላቸው፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትም ሆነ ከራሳቸው ከአንቶኒ ብሊንከን የተሰማ አስተያየት አለመኖሩንም ፎክስ ኒውስ ጽፏል፡፡
#አል-ዐይን

በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ለ90 ቀናት ታገደ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በቀን 18/12/13 ባደረገው መደበኛ ስብሰባው የቤት ኪራይ ጭማሪን ለ90 ቀናት ለማገድ በቀረበ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
በዚህም መሠረት ደንቡ ከፀደቀበት 18/12/13 ዓ.ም ጀምሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ለ90 ቀናት የተከለከለ ሲሆን በቀጣይም ታይቶ ለተጨማሪ ቀናት ክልከላው ሊራዘም ይችላል ብሏል::
ደንቡን በመተላለፍ ጭማሪ የተደረገበት ተከራይ አቤቱታውን በፅሑፍ ለወረዳው ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት በማቅረብ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚቻልበት ሥርዓት በደንቡ ተደንግጓል ተብሏል፡፡
ሙሉ መግለጫዉ የሚከተለዉ ነዉ፡-
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪን ለመገደብ በወጣ ደንብ ላይ የተሰጠ መግለጫ፡-
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማችን የኑሮ ውድነት እየተባባሰ እንደመጣ የሚታወቅ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ በአብዛኛው አሳማኝ እና ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው በሰውሰራሽ ምክንያቶች የተፈጠረ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱም የከተማችንን ነዋሪ ለከፍተኛ ችግር ዳርጓል፡፡
በሰሜን የሃገራችን ክፍል ሃገር በማፍረስ ተግባር ላይ የሚገኘውን የአሸባሪው ህወሃት እንቅስቃሴ ለማክሸፍ እየተደረገ ካለው ዘመቻ ጋር ተያይዞ የከተማችን ነዋሪ በገንዘብ መዋጮ፤ ለሠራዊት የሚሆን ስንቅ በማዘጋጀት፤ ደም ልገሳ እስከ ህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ባለበት በዚህ ወቅት ጥቂት ስግብግብ ግለሰቦች በተቃራኒው ቆመው ከኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ፍፁም ባፈነገጠ መልኩ አሁን ካለው ችግር ላይ አላግባብ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የተለያዩ ተግባራት ውስጥ ገብተው ይገኛሉ፡፡
መንግሥት እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከውጭና ከውስጥ ያሉ ጫናዎችን ተቋቁሞ ሀገር የማፍረስ ተግባር እንዲከሽፍና የዜጎች የኑሮ ጫና እንዲቀንስ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም መሠረት እስከታችኛው የማኅበረሰብ ክፍልን የሚያሳትፍ የኢኮኖሚ አሻጥሩን ለመቀልበስ የተቋቋመው ግብረይል በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በአጭር ጊዜ ውስጥም ግብረሃይሉ ባካናወናቸው ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች በመታየት ላይ ይገኛል፡፡
ከመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ባሻገር አለግባብና የወቅቱን ሁኔታ ያላገናዘበ የቤት ኪራይ ጭማሪ የነዋሪውን ሕይወት በእጅጉ እየፈተነው ይገኛል፡፡
ይህም ወቅታዊ ሁኔታን በመጠቀም አላግብ ለመክበር የሚደረግ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነትና መተሳሰብ ጋር በፍፁም የሚቃረን ተግባር ነው፡፡
በ2012 ዓ.ም የኮቪድ 19 ወረርሽ በሀገራችን መገኘቱ ተከትሎ በርካቶች ችግር ውስጥ በገቡበት ወቅት የከተማችን ነዋሪዎች እርስ በእርስ ከመረዳዳትና ማዕድ ከመጋራት አልፎ በርካታ ቤት አከራዮች የወራት የቤት ኪራይ ዋጋ ለተከራይ በራሳቸው ተነሳሽነት ቀንሰው ችግሩን በጋራ ለመፍታት ኢትዮጵያው የመረዳዳት እሴታችን የታየበት እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይህም በወቅቱ በሕግ ተቀምጦ የነበረውን የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር የሚከለክለውን ድንጋጌ ሳይጨምር ነው፡፡
አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት በቤት ክራይ ላይ ዋጋ ጭማሪ መታየቱን ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው፡፡
ስለሆነም አሁን እየታየ ያለውን አላግባብ የሆነ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ የነዋሪውን ቅሬታ ምላሽ ለመስጠት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በቀን 18/12/13 ባደረገው መደበኛ ስብሰባው የቤት ኪራይ ጭማሪን ለ90 ቀናት ለማገድ በቀረበ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
በዚህም መሠረት ደንቡ ከፀደቀበት 18/12/13 ዓ.ም ጀምሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ለ90 ቀናት የተከለከለ ሲሆን በቀጣይም ታይቶ ለተጨማሪ ቀናት ክልከላው ሊራዘም ይችላል፡፡
ደንቡን በመተላለፍ ጭማሪ የተደረገበት ተከራይ አቤቱታውን በፅሑፍ ለወረዳው ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት በማቅረብ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚቻልበት ሥርዓት በደንቡ ተደንግጓል፡፡
በዚሀ መሰረት በሚቀርቡ አቤቱታዎች ላይ ማጣራት ተደርጎ ጭማሪ ባደረገ አካል ላይ በደንቡ ተዘርዝሮ በተቀመጠው መሰረት ተጠያቂ የሚደረግ ይሆናል፡፡
ምንም እንኳን ይህ ደንብ የወጣው ዜጎችን ካላስፈላጊ ጫና ለመከላከልና ጥፋተኞችን ተጠያቂ ለማድረግ ቢሆንም ህብረተሰባችን በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ችግሮችን በመተሳሰብና በመደጋገፍ ለማለፍ ያሳየውን ኢትዮጵያዊ የጨዋነትና አብሮነት እሴቶቹን በማዳበር ይህን ወሳኝና አስቸጋሪ ጊዜ በጋራ ማለፍን ማዕከል በማድረግ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም

1 ሺህ 886 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ።
• 657 ድርጅቶች የንግድ ፈቃዳቸውን ተሰርዟል።
• ከ64 በላይ በወንጀል ተከሰዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲሠሩ በነበሩ የንግድ ድርጅቶች ላይ ከማሸግ ጀምሮ በወንጀል እንዲጠየቁ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።
በዚሁ ጉዳይ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ መግለጫ ሰጥተዋል።
በከተማዋ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲሠሩ የነበሩ ፦
- 1 ሺህ 886 የንግድ ድርጅቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስድቦባቸዋል።
- ከንግድ ህግ ውጪ ሲሰሩ በተገኙ 657 ድርጅቶች የንግድ ፈቃዳቸው የመሠረዝ እርምጃ ተወስዷል።
- ከ64 ላይ የሚሆኑ በወንጀል እንዲከሠሡ መደረጉን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ 369 መጋዘኖችን የመፈተሽ ስራ መሰራቱን እና በ20 መጋዘኖች ከፍተኛ የምርት ክምችት በመገኘቱ ታሽገዋል፤ የተከማቹት ምርቶችም ለተጠቃሚ እንዲደርስ ተደርጓል።
በነዚህ መጋዝኖችም ከፍተኛ መጠን ያለው የግንባታ ዕቃዎች በተለይም፦
- ፌሮ ብረት፣
- የምግብ ሸቀጦች፣
- ጨው፣
- በርበሬ፣
- ዘይት፣
- ጥራጥሬ የመሣሠሉት ክምችት የተገኘ ከመሆኑም ባሻገር ለጤና ደህንነት ጠንቅ የሆኑ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው የጁስ ምርቶች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
አቶ አብዱልፈታ በመግለጫቸው አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው ስግብግብ ነጋዴዎች ትክክለኛ ባልሆነ የመስፈሪያ መሣሪያዎች ምርቶሮችን እየሸጡ መሆኑ ተደርሶበት ሲሠሩበት የነበሩ 19 የመስፈሪያ መሣሪያዎች ተሠብስበው እንዲወገዱ መደረጉን አሳውቀዋል። #AAPS

በቪትስ መኪና አምስት ክላሽንኮቭ ከ132 ጥይት ጋር ሲያጓጉዙ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ
@Dire_Tube_news
ቪትስ በሚል ስያሜ በሚታወቅ በቤት መኪና ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ አምስት ክላሽንኮቭ ከ132 ጥይት ጋር ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎችን መያዙን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዋና ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ኢየሩስ አስማረ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት በከተማው ልዩ ስሙ አየር ጤና በተባለው አካባቢ ነው፡፡
ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥሩ A76390 አዲስ አበባ በሆነ ቪትስ የቤት መኪና ውስጥ አምስት ክላሽንኮቭ ከ132 የክላሽ ጥይት እና 43ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ በድብቅ ሲያጓጉዙ መንገድ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ሊያዙ ችለዋል፡፡
አሽከርካሪውን ጨምሮ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ኢንስፔክተር ኢየሩስ አስታውቀዋል፡፡
“በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ለጥፋት ተልእኮ ለሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ተልዕኮ ማሳኪያ ሊውል እንደሚችል ፖሊስ ጥርጣሬ አለው” ብለዋል፡፡
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የአካባቢን ሰላምና የህዝቦችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ወንጀል በመሆኑ ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር የጀመረውን ግንኙነት አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
ኢዜአ

የሱማሌ ክልል ታጣቂዎች በአፋር ክልል ገቢ ረሱ እና አውሲ ረሱ ዞኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ሲል የአፋር ክልል መንግሥት ሰሞኑን በኮምንኬሽን ቢሮው ፌስቡክ ገጽ ባወጣው መግለጫ ከሷል፡፡ ኡንዳ ፎኦ በተባለች ቀበሌ በርካታ የክልሉ አርሶ አደሮች ተገድለዋል ያለው መግለጫው፣ የሟቾችን ቁጥር ግን አልገለጸም፡፡ በግጭቱ የአዲስ አበባ-ጅቡቲ ባቡር መስመር ተዘግቶ እንደነበር ክልሉ ጨምሮ ገልጧል፡፡ ሱማሌ ክልል በበኩሉ የአፋር ክልልን ውንጀላ ሐሰት ያለው ሲሆን፣ ፋና ብሮድካስት ይህንኑ የአፋር ክልል መግለጫ በማሰራጨቱ ይቅርታ ይጠይቀኝ ሲል ትናንት በይፋ ጠይቋል፡፡
Wazema
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
Wazema
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለስራ ጉብኝት ዩጋንዳ ይገኛሉ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዩጋንዳ ገብተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ግብዣ ወደ ሀገሪቱ ማቅናታቸው ታውቋል።ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍም በዛሬው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መቀበቻለውን እና እየተወያዩ መሆኑን አስታውቀዋል።
Via Alain

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከካቢኔ አባላት ጋር በመሆን የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ጎበኙ
@Dire_Tube_news
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከካቢኔ አባላት ጋር በመሆን የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ በአየር ኃይሉ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርም እና ለውጥ ለማየት እና የከተማ አስተዳደር የሚችለውን ድጋፍ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል።
“የኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን የአየር ኃይላችን ከዚህ ቀደም ትኩረት ያልተሰጠው እና ከአቅሙ በታች ይሠራ የነበረ ተቋም ነበር” ያሉት ወ/ሮ አዳነች፣ አሁን ላይ መሠረታዊ ሪፎርም ተደርጎለት በዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት በሚችል ደረጃ ላይ መሆኑን መመልከት ችለናል ብለዋል።
የአየር ኃይላችን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ አኩሪ ገድል እየፈጸመ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩም ለአየር ኃይል አባላት ደጀንነቱን ለመግለጽ የሰንጋ በሬዎችን ድጋፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ጽ/ቤት አስታውቋል።
በኢትዮጵያ አየር ኃይል በተካሄደው የጉብኝት መርሐ-ግብር የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የካቢኔ አባላት ተሳትፈዋል።

ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ሶስት አገራት አንዷ ናት አሉ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን
@Dire_Tube_news
የቱርክ ፕሬዝዳንት እንዳሉት ቱርክ በዘርፉ ከቀደምት ከሆኑ እና በከፍተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጡ ሶስት ሀገራት ውስጥ አንዷ ናት ማለታቸውን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል።
በሰሜን ምዕራብ ባለች አንድ ግዛት በተከናወነ ወታደራዊ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን “ቱርክ ሰው አልባ በሆነው የአየር ላይ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ ውስጥ ከሦስቱ እጅግ የተራቀቁ አገሮች አንዷ ሆናለች” ብለዋል።
ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቀዳሚ አገር ለመሆን ቆርጣ መነሳቷን ያስረዱት ኤርዶጋን ቱርክ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማዘጋጀት አለባት ሲሉ መደመጣቸውን አናዶሉ ዘግቧል።
የአገሪቱ ግብ በውጭ ሀገራት የአውሮፕላኖች ተልእኮ ውስጥ ለአገልግሎት የሚውሉ አጫጭር ማኮብኮቢያዎችን የሚይዙ እና በአውሮፕላን ተሸካሚዎች ላይ ሊያርፉ የሚችሉ የታጠቁ ድሮኖችን ማልማት ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 284 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
አዲስ አበባን የሽብር ቀጠና ለማድረግ የአሸባሪው ህወሓት ቡድንን ዓላማ ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 284 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።
199 ሽጉጥ ከ2 ሺህ 453 ጥይት ጋር፣ 32 ክላሽንኮቭ 5 ሺህ ከሚልቅ ጥይት ጋር እንዲሁም 4 የጦር ሜዳ መነፅር ከተጠርጣሪዎቹ እጅ፣ ከስራ ቦታቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው መያዝ መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ለአሸባሪው ህወሓት ሃገር የማፍረስ ተልዕኮ የገቢ ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግል ያከማቹት ከአንድ ኪሎ ተኩል በላይ ወርቅ እንዲሁም 37 ሺህ 294 ነጥብ 8 ግራም የብር ጌጣጌጥ መያዙን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ ለሽብር ተግባር የሚጠቀሙባቸው የአዲስ አበባ ፌዴራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ የማረሚያ ቤትና የራሱ የህወሓት የሽብር ቡድን አልባሳት መያዛቸውንም አስረድተዋል።
በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ 123 የምርመራ መዝገብ መደራጀቱንም ነው የገለጹት።የጥፋት ቡድኑ የትኛውንም ዓይነት ሽብር ከመፈፀም ስለማይቦዝን ህብረተሰቡ አካባቢውን ከመጠበቅ ባለፈ መረጃ በመስጠት ከፖሊስ ጋር የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
Via EBC

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሀገር አቀፍ የጸሎት ጥሪ አስተላለፈች።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምእመናን በወርሃ ጳጉሜ ስለሀገራችን ሰላም በልዩ ሁኔታ ጸሎት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፋለች።
የጸሎት ጥሪው የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቅዋማት ጉባኤ ያስተላለፈውን ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የጸሎት ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ ታልሞ የተላለፈነው።
በጥሪው በተለይ ጳጉሜ አንድ ቀን ሥራ ዝግ ሆኖ ምእመናን በየቁምስናዎቻቸው የሰላም ጸሎት እንዲያደርጉ አደራ ጭምር ተጠይቀዋል።
እንዲሁም በዕለቱ የሚሰበሰቡ የዓይነትም ሆነ የገንዘብ መባዕ በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣብያው ለሚገኙ ወገኖቻችን የሚሰራጭ በመሆኑ ምእመናን ይህንኑ ተገንዝበው ንቁ ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም ጊዜው የኮቪድ 19 ስርጭት ያገረሸበት በመሆኑ በጋራ የሚከናወኑ መርሃግብሮች በሙሉ የጥንቃቄ መመሪያዎችን የተከተሉ መሆናቸውን ክቡራን ቆሞሳት እና የሚመለከታቸው አካላት እንዲያረጋግጡ ጥሪ ተላልፏል።