Telegram Web
የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በአፍዴራ የኢትዮጵያን ህዝብ ለቀጣይ 5 ዓመታት ሊመግብ የሚችል የምግብ ጨው ክምችት መኖሩን አስታወቀ፡፡

ሰሞኑን ተፈጥሮ የነበረው የጨው ዋጋ መጨመር ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡

አፍዴራ ላይ ጨው ወደ መኪና ላይ በሚጭኑ ማህበራት የመጫኛ ዋጋ ይጨመርልን ጥያቄ በማንሳታቸው ጨው አምራች እና ጨው ወደ መኪና ላይ በሚጭኑ ማህበራት መካከል ጊዜያዊ አለመግባበት ተፈጥሮ ነበር፡፡

ይህን ተከትሎ ጨው ለአንድ ወር ሳይጫን በመቅረቱ ምክንያት በገበያ ውስጥ የጨው ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ እንደነበር ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡

ሆኖም በአምራቾቹና በጫኞቹ መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት የተፈታ በመሆኑ በቂ የጨው ምርት ወደ ገበያ እየቀረበ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት አፍዴራ ላይ 30 ሚሊየን ኩንታል የጨው ክምችት መኖሩን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

የሀገሪቱ ወርሃዊ የጨው ፍጆታ 500 ሺህ ኩንታል መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ በአፍዴራ የሚገኘው የጨው ክምችትም ለቀጣይ 5 ዓመታት ፍጆታ የሚበቃ መሆኑን አመላክቷል፡፡

አሁን ላይ በሀገሪቱ 6 ህጋዊ ጨው አምራች ፋብሪካዎች መኖራቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
በመጪው መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ስድስተኛው ዙር የመንግስት ምስረታ እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ።
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ባንኮች ለአጭር ጊዜ የሚገጥማቸውን የገንዘብ እጥረት ለመፍታት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ የወለድ ምጣኔ ከፍ እንዲል ተወሰነ!
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
በኢኮኖሚ ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ ስርጭት ለመቀነስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁጥብ የገንዘብ ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ ወስኗል፡፡

ስለሆነም እ.ኤ.አ ከመስከረም 1 ቀን 2021 ጀምሮ ባንኮች ከሚሰበሰቡት የተጣራ ቁጠባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዲያስቀመጡ የሚገደዱትን የመጠባበቂያ መጠን ከነበረበት 5 በመቶ ወደ 10 በመቶ ከፍ እንዲል ተወስኗል፡፡

ባንኮች ለአጭር ጊዜ የሚገጥማቸውን የገንዘብ እጥረት ለመፍታት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ ወለድ ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 16 በመቶ ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡

በባንኮች በኩል የውጭ ምንዛሬ አጠቃቀም ላይም ማሻሻያ እንደተደረገ ብሔራዊ ባንክ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

Via EBC
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት (USAID) መጋዘኖችን በአሸባሪው ህወሓት መዘረፋቸው ተገለጸ

አሸባሪው ህወሓት የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት መጋዘኖችን እንደዘረፈ በኢትዮጵያ የድርጅቱ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ተናገሩ፡፡

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ህወሓት ሁኔታውን ያለአግባብ እየተጠቀመበት እንደሆነ እናምናለን ብለዋል፡፡

ከተረጂዎች ላይ እርዳታን በሃይል እየነጠቀ እንደሆነ ይሰማናል ያሉት ዳይሬከተሩ እርግጠኛ ሆነን መናገር የምንችለው ግን የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላት ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ ያሉትን የእርዳታ መጋዘኖቻችንን ዘርፈዋል፤ ይህ የምናውቀው ሀቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አሁን በግልጽ የምናውቀው ነገር የህወሓት ወታደሮች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል፣ መኪኖችን ሰርቀዋል በየመንደሮቹ ብዙ ውድመትን አድርሰዋልያሉት ዳይሬክተሩ ይህ ለተጎጂዎቹም ሆነ ለእኛ ለረጂዎቹ እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንቀሳቀሰው ሀገሪቱ አሁን ችግር ላይ ስላለች አይደለም ብለዋል፡፡

ይልቁንም ኢትዮጵያ ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ አጋሮቻችን መካከል አንዷ ነች ያሉት ዳይሬክተሩ ከኢትዮጵያ ጋር ስላለን አጋርነት በእጅጉ እንጨነቃለነ ነው ያሉት፡፡

አንዳንድ ጊዜ ህብረተሰቡ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚሰራጩትን ያልተረጋጋጡ ወሬዎች በመያዝ የኢትዮ አሜሪካ ግንኙነት እንደሻከረ ያስባሉ ያሉት ዳይሬክተሩ ነገር ግን እንደአሁኑ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብረን የሰራንበት ጊዜ የለም ሲሉም ለኢብኮ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማዔል ኡመር ጌሌህ ጋር ዛሬ በስልክ እንደተወያዩ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። የሁለቱ መሪዎች የስልክ ውይይት በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያጠነጠነ እንደነበር ኢምባሲው ገልጧል።

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
*ኢንሹራንስ እና ባንኮች ቦንድ እንዲገዙ ተወሰነ
*የዋጋ ግሽበቱን ለመግታት ብሄራዊ ባንክ አዳዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ውሳኔ አሳልፏል
*
ኢንሹራንሶች ከአመታዊ ገቢያቸው 15% የልማት ባንክ ቦንድ እንዲገዙ ተወሰነ። ውሳኔው ከነሃሴ 26 ጀምሮ ይተገበራል።
ባንኮች ከጠቅላላ አመታዊ የብድር ክምችት 1% የልማት ባንክ ቦንድ መግዛት ይጀምራሉ።
የባንኮች መጠባበቂያ መጠን ከጠቅላላው ተቀማጭ 10% እንዲሆን ተወሰነ። ቀደም ሲል 5% እንደነበር ይታወሳል።
ከወጪ ንግድ፣ ከግለሰብ ሃዋላ እና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች የሚገኝ የውጭ ምንዛሬ 50% ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ይደረጋል። ቀደም ሲል 30% በመቶ ነበር።
የውጭ ምንዛሬ ያስገኘ ደንበኛ ያለገደብ የሚቀመጥለት የውጭ ምንዛሬ መቶኛ 40% እንዲሆን ተወስኗል። ይህ መጠን 31.5% ነበር።
Via Capital Newspaper

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ኢትዮጵያ 22 ሚሊዮን ለሚጠጉ ዜጎች የኮቪድ-19 ክትባት ልትሰጥ ነው፡፡

ኢትዮጵያ እስከ ፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ድረስ ለ22 ሚሊዮን ዜጎች ኮሮና ቫይረስ ክትባት ልትሰጥ መሆኗን አስታውቃለች፡፡የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እስከ ፈረንጆቹ 2021 ድረስ 20 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ ለመከተብ ታቅዷል ብለዋል፡፡እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ 2.4 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎቿን የከተበች ሲሆን በኮቫክስ ጥምረት አማካኝነት 22 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች እስከ 2021 ድረስ ይከተባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን በአንድ ሳምንት ብቻ እስከ 10ሺህ ያህል ዜጎች በቫይረሱ እየተያዙ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 308ሺህ 134 የደረሰ ሲሆን 276 ሺህ 842 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።እንደዚሁም 4 ሺህ 675 ያህል ዜጎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡

Via Ethio FM
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህገ-ወጥ ድርጊትን ለሚጠቁም ማበረታቻ ለመስጠት ደንብ አወጣ።

ማበረታቻው የሚሰጠው እንደ ጥቆማው ውጤታማት ነው ተብሏል።ደንቡ በከተማዋ ህገ-ወጥነትን ለመከላከል የወጣ መሆኑን የከተማው ከንቲቫ ፅ/ቤት ዛሬ ይፋ ባደረገው መግለጫ አስታውቋል።ህገ ወጥ ተግባራት ይፈፀምባቸዋል ብሎ የዘረዘራቸው ተግባራትም ከመሬትና ከግንባታ ጋር፣ከጦር መሳሪያ፣ከውጭ ምንዛሬ ዝውውር፣ ከሀሰተኛ ሰነድ እና የገንዘብ ህትመት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ነው።

በእነዚህ ተግባራት ላይ በመደበኛ ሕጎች የሚፈጸመው እንዳለ ሲሆን፤ ይህ ደንብ በቅርብ ጊዜያት እየተንሰራፉ የመጡ በመንግስትና በሕዝብ ንብረት ላይ የሚሰሩ እና ነዋሪውን የሚያማርሩ ሕገወጥ ተግባራት ላይ እንዲያተኩር መደረጉን አብራርቷል ደንቡ የጥቆማዎቹን አቀራረብ ሥርዓት እና ለጠቋሚዎቹ ስለሚሰጥ ማበረታቻ ምጣኔ የሚገልጹ ድንጋጌዎችን ይዟል፡፡ያም ሆኖ ለማበረታቻው የሚከፈለው ገንዘብ እንደ ጥቆማው ውጤታማት መሆኑን አስተዳደሩ ዛሬ ይፋ ባደረገው ሰነድ ተመልክቷል።

DW

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደምትደግፍና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል ኤርትራ አስታወቀች
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news

የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደሚደግፍ እና በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደሚያወግዝ የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር አስታወቀ፡፡

የግንባሩ ዋና ፀሐፊ አል-አሚን ሙሐመድ አሊ ይህን ያስታወቁት የኤርትራ አብዮትን 60ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው፡፡

አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ በምትከተለው የተዛባ ፖሊሲ እና በምታደርገው ጣልቃ ገብነት ምክንያት የቀጣናው ሀገራት በግጭት መታመሳቸውን ቀጥለዋል ብለዋል፡፡

ሀገራቸው ኤርትራ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደምትደግፍ እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበለው አረጋግጠዋል፡፡

"የአፍሪካ ቀንድን ለመበታተን ይፈልጋሉ፤ በሶማሊያ ያደረጉትን እና ዛሬም በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለውን ተመልከቱ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ስላለው ነገር ምን ያገባቸዋል፤ ይህ የውስጥ ጉዳይ አይደለምን?" ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

አሜሪካ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገባች ያለችው አሸባሪው ህወሓትን ዳግም ወደስልጣን ለማምጣት ያላትን ፍላጎት ስለማይቀበሉ ነው በማለት ይመልሳሉ፡፡

በኢትዮጵያ የሚፈጠር አለመረጋጋት በጥቅሉ በቀጣናው ሰላም ላይ በተለይ ደግሞ በኤርትራ ሰላም ላይ ቀጥተኛ ስጋት ይደቅናል ነው ያሉት፡፡

የአሜሪካ አጀንዳ የአፍሪካ ቀንድን መበታተን ነው፤ የእኛ ምርጫ ደግሞ ከኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ጅቡቲ ጋር በትብብር በመስራት ሰላምን ማረጋገጥ ነው ብለዋል የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ዋና ፀሐፊ አል-አሚን ሙሐመድ አሊ፡፡

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነገ፤ ነሐሴ 27/2013 ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ተገለፀ፡፡

ሚኒስተሯ ሪይቸል ኦማሞ፤ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ዋልታ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ሚኒስትሯ ባለፈው ግንቦት 30/2013 በተመሳሳይ ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ መምጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የነበረውን የኢ-ቪዛ አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል። ኢ-ቪዛዎን በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።
www.evisa.gov.et

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የአምስት ቀናት የጾምና የጸሎት ምህላ አዋጅ መታወጁን የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ገለጸ
@Dire_Tube_news

የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አገር አቀፍ የጾምና የጸሎት ምህላ አዋጅ መታወጁን አስታውቋል፡፡
የጾምና ጸሎት ምህላው ከጳጉሜን 1 እስከ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
“ሸኔ” በምእራብ ወለጋ ዞን 10 ሰዎችን ማገቱን መንግስት አስታወቀ

ባንክ እና ፍርድ ቤትን ጨምሮ ከ34 በላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ተቋማት ላይም ዝርፊያ ፈጽሟል።

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የፈረጀው “ሸኔ” በምእራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ በፈፀመው ጥቃት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን መንግስት አስታወቀ።

የቆንዳላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ቡላ ደመረ በወረዳው “ሸኔ” በፈጸመው ጥቃት የንጹሃን የተገደሉ ሲሆን፣ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተዘርፈው በእሳት ተቃጥለዋል ማለታቸውን ኢዜአ በአፋን ኦሮሞ ገጽ አስነብቧል።

“በጥቃቱ ሸኔ 10 ሰዎችን አግቶ ወስዷል” ያሉት አቶ ቡላ ደመረ፤ 24 ንጹሃን ዜጎችን መግደሉንም አስታውቀዋል።

ቡድኑ የወረዳውን ፍርድ ቤት እና የአቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሙሉ በሙሉ በእሳት ማጋየቱን በመጥቀስ፤ 4 የመንግስት አመራሮች መኖሪያ ቤቶችንም አቃጥሏል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆንዳላ ቅርንጫፍን አንዲሁም በ34 የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ተቋማት ላይ ዝርፊያ መፈጸሙን ያስታወቁት የወረዳው አስተዳዳሪ፤ በወረዳው የሚገኝ የ2ኛ ደረጃ ትምህት ቤት ንብረት እና የተማሪዎችን ማስረጃ ማውደሙንም ተናግረዋል።

የ“ሸኔ” ታጣቂዎች በአጠቃላይ በወረዳው ከነሃሴ 9፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በፈጸሙት ጥቃት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የቆንዳላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ቡላ ደመረ ገልጸዋል።

“ህብረተሰቡ የሸኔ የሽብር ብድን የጥፋት ተግባርን ተረድቶ በአንድነት በመሆን የቡድኑን የጠላትነት ተግባር ሊያጋልጥ ይገባል” ሲሉም ዋና አስተዳዳው ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ኢትዮ ቴሌኮም ከአፍሪካ የቴሌኮም አገልግሎት ኩባንያዎች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ መቀመጡ ተሰማ።

በአፍሪካ 195 የቴሌኮም ኦፐሬተሮች ያሉ ሲኾን፤ ኢትዮ ቴሌኮም በግዝፈት፣ በደንበኛ ቁጥር እና በአገልግሎት ደረጃ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ያለው ግሎባል ሲስተምስ ፎር ሞባይል ኮሙኒኬሽንስ ወይም በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል GSMA የተባለ ተቀማጭነቱ እንግሊዝ ሀገር የሚገኝ ተቋም ያወጣው ሪፖርት ነው።

GSMA በዓለም ዙርያ ከ750 በላይ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋሞችን በአባልነት አቅፎ የያዘ እና ኩባንያዎቹን በሥራቸው ልክ ጥራት እና ደረጃ ሰፍሮ የሚናገር ዓለም አቀፍ ተቋም ነው።ይኸው ድርጅት ኢትዮ ቴሌኮምን ከአፍሪካ ሁለተኛ ከዓለም ደግሞ 28ኛ እንዳለው የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

ቻይና፣ አሜሪካ እና ሕንድ የመሳሰሉ ሀገሮች በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ እና በሌላውም ቀዳሚ በመሆናቸው፣ በእነዚህ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች ከ1 እስከ 27ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።በዛሬው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ቀጠና ማስፋፍያ ያደረገው ኢትዮ ቴሌኮም፣ የ4G እና LTE Advanced የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራውን አጠናቆ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ አስጀምሯል።

በቀጠናው 28,000 ደንበኞች የዳታ ተጠቃሚዎች ናቸው ተብሏክል።የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበጀት አመቱ 106 ከተሞች የላቀውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማስፋፊያ እየተሰራ ነው ብለዋል።ኢትዮ ቴሌኮም የዴታ አጠቃቀም በብርቱ በሚታይባቸው የሐገሪቱ ከተሞች የላቀውን የኢንተርኔት አገልግሎት እያስጀመረ መሆኑ ተሰምቷል።

Via Sheger FM
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ኢትዮጵያ በአልጀርስ ያለው ኤምባሲዋ ቢዘጋም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንደሚቀጥሉ ተገለፀ፡፡

ኢትዮጵያ በአልጀርስ ያለው ኤምባሲዋ ቢዘጋም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንደሚቀጥሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፁ፡፡

ኤምባሲው የሚዘጋው በሪፎርምና ከኮቪድ _19 ጋር በተገናኘ እንደሆነ ቢነገርም፤ መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሠው በፋይናንስ ዕጥረት መሆኑን አሻም ዘግባለች፡፡

@Dire_Tube_news
አንጋፋው ሙዚቀኛ አርቲስት አለማየሁ እሸቴ አረፉ

ተማር ልጄ፣ አዲስ አበባ ቤቴ እና በሌሎች ታዋቂ ስራዎች የሚታወቁት አርቲስት አለማየሁ እሸቴ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ዛሬ ነሀሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አርፈዋል

ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መፅናናትን ይመኛል

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ከሱዳን በመግባት የግድቡን ግንባታ ለማደናቀፍ የሞከረ “ቅጥረኛ” ኃይል መደምሰሱ ተገለጸ

መከላከያ በወሰደው እርምጃ “50 የሽብር ቡድን አባላት መደምሰሱንና ከ70 በላይ የሚሆኑትን ማቁሰሉን” መግለጫው ጠቅሷል


@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ ራስወዳድ ቡድን ነው፡- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ እና ራሱን ብቻ ከሌሎች ነጥሎ የሚወድ ስግብግብ ቡድን መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል አባላት ምረቃ ላይ ተገኝተዋል፡፡
በዚሁ ጊዜ እንዳሉት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለኢትዮጵያ እንቅርት ሆኖባታል፡፡
ይህን ፈተና ለማለፍ ብልሃት፣ አንድነት እና ቆራጥነት ያስፈልጋል ያሉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይህንን መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ባለፉት ወራቶች በተደረጉ ኦፕሬሽኖች አሁንም ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር መሆኗን አይተናል ብለዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና አንድነቷን ለመበተን አስቦ እየሰራ ቢሆንም በተቃራኒው ኢትዮጵያ ዳግም አንድ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል፡፡

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ ራስወዳድ ቡድን ነው፡- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ እና ራሱን ብቻ ከሌሎች ነጥሎ የሚወድ ስግብግብ ቡድን መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል አባላት ምረቃ ላይ ተገኝተዋል፡፡
በዚሁ ጊዜ እንዳሉት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለኢትዮጵያ እንቅርት ሆኖባታል፡፡
ይህን ፈተና ለማለፍ ብልሃት፣ አንድነት እና ቆራጥነት ያስፈልጋል ያሉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይህንን መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ባለፉት ወራቶች በተደረጉ ኦፕሬሽኖች አሁንም ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር መሆኗን አይተናል ብለዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና አንድነቷን ለመበተን አስቦ እየሰራ ቢሆንም በተቃራኒው ኢትዮጵያ ዳግም አንድ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል፡፡

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
መጭውን በዓላት ምክንያት በማድረግ 108 አማራጭ የገበያ ቦታዎች ማዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡

ቢሮዉ ቀጣዩን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ እየሰራ ካለው ስራ አንዱ ህብረተሰቡ አማራጭ እና ተደራሽ የገበያ ስፍራ እንዲያገኝና የሚፈልጋቸውን ምርቶች በቀጥታ ከአምራች ገበሬው ማግኘት እንዲችልና እየተስተዋለ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑን ቢሮዉ ለጣቢያችን በላከዉ መግለጫ አሳዉቋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ 108 የመገበያያ ቦታዎችን እና ከ250 ሺህ ኩንታል በላይ ተጨማሪ የግብርና ምርት የተዘጋጀ መሆኑን ቦሮዉ ጠቁሟል፡፡

በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ የጀመሩት መሸጫዎቹ በከተማዋ የሚስተዋለዉን የኑሮ ዉድነት በማረጋጋት በተለይም የግብርና ውጤት የሆኑ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እንዲሁም ለበዓል አስፈላጊ የሆኑ እንደ እንቁላል እና አይብ ያሉ የእንስሳት ተዋጽኦ አቅርቦትን ይበልጥ ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፆ እንደሚኖራቸውም ተገልጿል።

ከነዚህም ውስጥ 56 የቁም እንሰሳት የገበያ ስፍራዎች ሲሆኑ 52ቱ የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫዎች ናቸው ተብሏል፡፡አዳዲስ የግብይት ቦታዎቹ በሁሉም ክፍለ ከተሞች አገልሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን መሸጫ ስፍራዎቹ ከአርሶ አደሩ በቀጥታ ተቀብለዉ ለሸማቹ ህብረተሰብ ምርት በቀጥታ ከአርሶ አደሩ ከማቅረባቸው በተጨማሪ ምርቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ እንዲችሉ የተዘጋጁ አማራጭ የገበያ ስፍራዎች መሆናቸዉ ተነግሯል፡፡

Via Ethio FM

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
2025/02/11 15:10:36
Back to Top
HTML Embed Code: