Telegram Web
የክፍል 4 ትምህርት የክለሳ ጥያቄዎች


1 ቅዱስ ጳውሎስ ወልድን “ሁሉን ወራሽ” ብሎ የጠራው ለምንድር ነው?


2 በአምላክ ሰው መሆን ትምህርት ውስጥ “ተዋሕዶ” ሲባል ምን ማለት ነው?


3 ሐዋርያው “ዓለማትን በፈጠረበት” ሲል ምን እያለን ነው? “ፈጠረበት” የሚለውን ቃል እንዴት ነው የምንረዳው?
Live stream scheduled for
Live stream started
Live stream finished (58 minutes)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“የተሰቀለው ክርስቶስን የሚያይ እና እምነቱንም በእርሱ ላይ የሚያኖር፣ ከኃጢአት ቁስሎቹ ሁሉ ይፈወሳል”

የሂፖው ሊቀ ጳጳስ አውግስጢኖስ

አቤቱ መድኃኔዓለም ሆይ፥ በስቅለት በመከራህ የተዘራሁ፣ በደምህም ላይ የበቀልኩ ፍሬ ነኝና ጠውልጌ እንድቀር አትተወኝ።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tgoop.com/Dnabel

ስብከቱ፡ የክቡር ሊቅ አለቃ አታሌው ታምሩ
+++ ያለ እግዚአብሔር "እንደ እግዚአብሔር" +++

በእባብ ሥጋ ተሰውሮ ወደ ሔዋን የመጣው ሰይጣን ሴቲቱን ያታለለበት የሐሰት ቃል "ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው" የሚል ነበር።(ዘፍ 3፥5) ይገርማል! በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረ የሰው ልጅ እንደ እግዚአብሔር (እርሱን መስሎ) የመኖር ፍላጎት እንዳለው ሰይጣን ያውቃል። ይህ ውሳጣዊ ፍላጎቱ ላይ ለመድረስ በሃይማኖትና በበጎ ምግባር ከማደግ ይልቅ ባልተገባ መንገድ ፍለጋውን ያደርግ ዘንድ አዲስ ስብከት አመጣለት። ምን የሚል? "ያለ እግዚአብሔር 'እንደ እግዚአብሔር' ትሆናላችሁ" የሚል። በምን? በቅጠል።

ዛሬም ሰይጣን ያለ እግዚአብሔር "እንደ እግዚአብሔር" ትሆኑባችኋላችሁ ሲል የሚያሳየን እንደ ገንዘብ፣ ዕውቀት፣ ጉልበት ያሉ ብዙ ቅጠሎች አሉ። ነገር ግን እኛ ክርስቲያኖች እርሱን ወደ መምሰል የምናድግበት ብቸኛው መሰላላችን ረድኤተ እግዚአብሔርና የማይቋረጥ የእኛ ሩጫ ነው። እርሱ ሳይኖር እና ሳያካፍል እኛ በራሳችን የምንካፈለው ምንም አምላካዊ ምሳሌነት የለም።(2ኛ ጴጥ 1፥4)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tgoop.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
በኢያሪኮ መንገድ ቆመው ይለምኑ የነበሩ ሁለት ዓይነ ስውሮች ክርስቶስ በዚያ እያለፈ መሆኑን ሲሰሙ "የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን" እያሉ ፈውስ ይማጸኑት ጀመር። ነገር ግን ከጌታችን ፊት ቀድመው ይሄዱ የነበሩ ሰዎች እኒህን ነዳያን "ዝም በሉ!" ብለው ገሰጿቸው።(ሉቃ 18፥39) ልብ በሉ፤ የገሰጿቸው ሰዎች ጌታን ከኋላ የሚከተሉ ወይም ከአጠገቡ አብረው የሚሄዱት አልነበሩም። ከፊት ከፊት የሚቀድሙት እንጂ። በእርግጥም ከጌታው ፊት ቀደም ቀደም የሚል ሰው ጠባይ ይህ ነው። ራሱን ከባለቤቱ በላይ ዐዋቂ ያደርጋል። ምስኪኖችን "ዝም በሉ" እያለ የሚያሳቅ፣ የጌታውን ቸርነት የሚሸፍን አጉል ጠበቃ ይሆናል። እስኪ አሁን "ማረን" ማለት ምን ነውር አለው? ቃሉስ የስድብ ያህል የሚያስቆጣና "ዝም በሉ" የሚያሰኝ ነው? እነዚህ ሁለቱ ዕውሮች የገጠሟቸው እንዲህ ያሉ "በባለቤቱ ያልተወከሉ ጠበቆች" ነበሩ። ግን አልተበገሩም "ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ ማረን" እያሉ ከቀድሞው ይልቅ አብዝተው ጮኹ። እርሱም ልመናቸውን ሰምቶ ወደዚህ አምጧቸው አለ፣ ፈወሳቸውም።

እነ እገሌ ፊት ነሱኝ፣ ተቆጡኝ፣ አመናጨቁኝ ብለህ ከቤተ ክርስቲያን አትቅር ጸሎትህንም አታቋርጥ። ጉዳይህን ከባለቤቱ ጋር ብቻ አድርግ። ያኔ የልመናህን ድምፅ ይሰማል። ሊፈውስህም ወደ እርሱ የሚያቀርቡ ወዳጆቹን ይልክልሃል።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://www.tgoop.com/Dnabel
ክቡራን፣

ክፍል ስድስት ትምህርታችንን ዛሬ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ በዚህ https://www.tgoop.com/Dnabel የቴሌግራም ቻናል በlive stream ትምህርቱ ይሰጣል።

እንደ አማራጭ ይህን ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ደግሞ በzoom ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ።

https://us05web.zoom.us/j/84709079682?pwd=obn6Rc8YrJjSTaAAeRwKmNbMC2kY8n.1
ጥያቄ!

1. “እርሱም የክብሩ መንጸባረቅ” የሚለውን ቃል ይዘን ፀሐይን እንዴት በምሳሌነት እንዳነሣነው ዘርዝራችሁ ጻፉ።
Live stream scheduled for
Live stream started
Live stream finished (54 minutes)
የኃጢአት ሸክም ያጎበጠህ፣ በሁሉ የተናቅህ፣ አላፊ አግዳሚው ምራቁን ጢቅ እያለ ስድብ የሚያዋጣብህ ጎስቋላ ትሆናለህ። ሌሎች እነርሱን ስላልመሰልክ ይንቁህና ያንቋሽሹህ ይሆናል። ነገር ግን በፈጣሪህ ዘንድ ያለህን ተፈላጊነት ሰዎች በሚያሳዩህ ዝቅ ያለ አመለካከት አትለካ። ዛሬ የሚሰድቡህና የሚያዋርዱህ ሰዎች በአንተ መፈጠርና ሰው ሆኖ መኖር ላይ ምንም ዓይነት አስተዋጽዖ የላቸውም። የሕያውነት እስትንፋስ አልሰጡህም ሞተህ እንዳትቀር ስለ አንተ አልተሰቀሉልህም። ላንተ ሲሉ የከፈሉት ዋጋ ስለሌለ ለእነርሱ ከቁስ ያነስክ ልትሆን ትችላለህ።

ነገር ግን በእጁ የለወሰህ፣ ቁርበትና ሥጋ ያለበሰህ፣ በአጥንትና በጅማት ያጠረህ ሕይወት ሰጥቶ ሰው ያደረገህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚበልጥበት ሀብት የለውም። በፀሐይና በጨረቃ በሌሎች ብርሃናት ሁሉ ያላስቀመጠው በአንተ ውስጥ ብቻ የቀረጸውን መልኩን ፈጽሞ ሊረሳ የማይችል አምላክ ይፈልግሃል። ጥበቡን አፍስሶ ስለ ፈጠረህ ስትጠፋ ዝም አይልም። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ደሙን ስላፈሰሰልህ ፈጽሞ አይተውህም።

የሆሣዕና በዓል በሰዎች ፊት እንደ ምናምንቴ ለሆንን ለእኔ እና ለአንተ ነው። ጌታ ከኢያሪኮ ወደ ቤተ መቅደስ ይዟቸው የመጣው እንደ በርጤሜዎስ ያሉ የተናቁ ነዳያንን፣ እንደ ዘኬዎስ ያሉ የተጠሉ ኃጢአተኞችን ነበር። "ሆሣዕና በአርያም" የሚለው መዝሙራቸውም እንደዚያ ያማረው በመገፋት እና በመጠላት ልባቸው የቆሰሉትን በፍቅርና በምሕረቱ ፈውሶ መድኃኒትነቱን ስላቀመሳቸው ነው።

ለጌታ እናስፈልገዋለን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tgoop.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ላትሞት ነው የምትፈታው?
(የሆሣዕና ፍትሐት)

ቤተ ክርስቲያናችን በበዓለ ሆሣዕና ቀን ከምታከናውናቸው ነገሮች መካከል አንዱ ለክርስተ‍ኢያኖች ሁሉ ፍትሐት ማድረግ ነው። ይኸውም ከሆሳዕና ቀጥሎ ባሉት ቀናት ሌሎቹን አገልግሎት ሁሉ ለጊዜው አቁማ ልክ እንደ ሰጎን ዕንቁላል ከክርስቶስ ሕማም እና ሞት ላይ ዓይኗን ስለማታነሣ፣ በዚህ ሳምንት የሚያንቀላፋ ቢኖሩ ቀድማ በዕለተ ሆሳዕና ፍትሐት ታደርግለታለች።

ይሁን እንጂ የፍትሐቱ ዋናው ምሥጢር ያለው ግን እዚህ ላይ ነው። ክርስቶስ የተቀበለው መከራ እና ሞቱ በሚታሰብበት በመጪው ሳምንት ልጆቿ ምእመናን የሥጋ ፈቃዳቸውን በመስቀል ሰቅለው ስለ እነርሱ ሲል ለሞተው አምላክ፣ እነርሱም ለዚህ ዓለም ፍትወት የሞቱ ሆነው እንዲያሳልፉ ለማሳሰብ ነው። ስለዚህም ክርስቲያኖችን ሁሉ በቁማቸው ሳሉ እንደ መነኮሳቱ (ለዓለሙ ፈቃድ እንደ ሞቱት) ፍትሐት ታደርግላቸዋለች። ታዲያ በሆሣዕና ሰንበት ወደ ቤተ ክርስቲያን ለፍትሐት ስትመጣ ለራስህ ፈቃድ ሙት ሆነህ ለክርስቶስ ለመኖር ወስነህ ነው? ወይስ ላትሞት ነው ለመፈታት የምትሄደው?

“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ”

2ኛ ቆሮ 5:15

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://www.tgoop.com/Dnabel
ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የአይሁድ ፋሲካ ሊደርስ አምስት ቀናት ብቻ ቀርተውት ነበር። በእርግጥ አምስት ቀናት የቀሩት እስራኤል ከግብጽ ባርነት መውጣታቸውን ለሚያስቡበት እና የፋሲካውን በግ ለሚያርዱበት በዓል ብቻ ሳይሆን፣ ዓለም ሁሉ ግብጽ ከተባለ ሲዖል ነጻ ለሚወጣበት እና የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሠውቶ አማናዊው ፋሲካ ለሚደረግበትም የሥርየት ዕለት ነበር። ስለዚህ ሰውን ሁሉ ከሲዖል ወደ ገነት፣ ከባርነት ወደ ነጻነት የሚያሻግረው የፋሲካው በግ ክርስቶስ ወደሚሠዋባት ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ሕዝቡ በደስታ ተቀበለው። መድኃኒትነቱን ተጠምቶ በናፍቆት ሲጠባበቀው የነበረ ነፍስ ሁሉም “አቤቱ እባክህ አሁን አድን” እያለ ዘንባባ ይዞ ዘመረለት።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://www.tgoop.com/Dnabel
በእስራኤል ታሪክ አህያ ይጠብቅ እና በእርሱም ይጓጓዝ የነበረ እንደ ሳኦል ያለ ሰው ነግሥዋል። ይሁን እንጂ የሹመት ዘውድ ከደፋ በኋላ ግን ሳኦል በፈረስ እና በሠረገላ እንጂ በአህያ ዳግም አልተጫነም። ንጉሠ ሰላም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ሐዋርያቱን ፈረስ ወይም በቅሎ እንዲያዘጋጁለት አላዘዘም። ትሑት ሆኖ በአህያ ላይ ለመጫን አህያይቱን ከነግልገሏ ፈተው እንዲያመጡለት ላካቸው እንጂ። ምናልባት በፈረስ የተጫነ በሠረገላ የተፈናጠጠ ንጉሥ ይፈራ ይሆናል፣ ነገር ግን በአህያ ላይ ትሑት ሆኖ እንደ ተሳፈረ ንጉሥ ግን ሊወደድ እና ልብስ ሊነጠፍለት አይችልም። ክርስቶስ አስፈራርቶ ሳይሆን ተወዶ የሚገዛ ንጉሥ መሆኑን ያሳየው በዚህች በሆሳዕና ዕለት ነው። ሕዝቡ ለዚህ ትሑት አምላክ የጎበጠውን መሬት ማቅናት መደልደል፣ ቆሻሻውንም ማጽዳት ባይችሉ የለበሱትን ልብስ ትቢያ ላይ አንጥፈው “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” እያሉ አዳኛቸውን ተቀበሉ።

መሰናበቻ!

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም፥

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://www.tgoop.com/Dnabel
”በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጕር በዙ… ነፍሴ ስድብንና ኃሣርን ታገሠች፤ አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም፤ የሚያጽናናኝም አጣሁ”
መዝ 69:4፣ 20
Channel photo updated
2025/04/14 13:29:59
Back to Top
HTML Embed Code: