Telegram Web
Mark your calendars for October 27 and get ready for an eye-opening Mental Health Awareness event hosted by Ubuntu Psychological Services in collaboration with Why Global and Rotaract club of Lewet!☺️

We’re excited to introduce two outstanding panelists:

• Dr. Dawit Assefa (MD, Psychiatrist)—former CEO of Amanuel Mental Specialized Hospital, past President of the Ethiopian Psychiatric Association, and the brilliant mind behind the novel “YeHulu.”

• Petros Hagos, a senior clinical psychologist at Erq Maed and Lebeza Psychiatry Clinic, with a wealth of experience in guiding mental wellness.

Join us as they take you on a journey to uncover the secrets of resilience and how to thrive through life’s challenges. 🤗

This is one event you won’t want to miss!😌

📅 Date: Sunday, October 27, 2024
Time: Begins at 1:00 PM |7:00LT
📍 Location: Atmosphere, Bole behind Alem Cinema
http://surl.li/bftgdy

Follow Us 👇
Instagram | Facebook | Linkedin | Telegram
#EmbracingChange #MentalHealthAwareness #Resilience
የምስራች --- ምክር ብሉ!
================

የምስራች ሲባል "ምስር " ብሉ ማለት ቀርቶ "ምክር" ብሉ መባል በጀመረበት ወቅት ደፍሬ የምስራች ለምስራቅ ኢትዮጲያ እንዲሁም ለድሬደዋ ነዋሪዎች በሙሉ እላለው፡፡ ምንም እንኳን የአዕምሮ ህመም በምስራቁ የሀገራችን በብዛት ቢታይም ይህንን ያማከለ እና ለአእምሮ ህክምና ታስቦ የተዘጋጀ ህክምና ማዕከል አለመኖሩ ብዙውን የምስራቅ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ እንዲያማትር ሲያስገድደው አስተውለናል፡፡ ይህንን መጉላላት ለመቅረፍ ቤካንሲ ልዩ የአዕምሮ ህክምና ለምስራቅ ሀረርጌ እንዲሁም ድሬደዋ "ምክርም ምስርም ብሉ" ብሎ በተዳረጀ ምልክ ብቁ ከሆኑ የአእምሮ ህክምና እና ስነልቦና ባለሞያዎች ድሬደዋ ላይ ከትሞ ይጠብቆታል፡፡

አድራሻ፡- ኢትዮጲያ ፣ ድሬደዋ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
+251920016898
ማህበራዊ ድህረገፃችንን ተቀላቀሉ
Telegram:- https://www.tgoop.com/Bekansipsyc
Tiktok:- https://www.tiktok.com/@bekansi01?_t=8rf7RzbOksx&_r=1
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61568832854930
የጭንቀት ህመም ስሜቱ ምን ይመስላል?
==========================
ወንበር ላይ ተቀምጠህ የወንበሩ የጀርባ መደገፊያ ላይ ጀርባህን አስደግፈህ በአንድ እጅህ የጠረጴዛ ጫፍ ይዘህ የወንበሩን የፊት እግሮች ከመሬት ከፍ እያደረግህ ወደ ኋላ ለጠጥ ትላለህ። ለጠጥ ለጠጥ ስትል የሆነች ነጥብ ላይ ስትደርስ ልትወድቅ የሚመስል ልብን ስውር የምታደርግ ቦታ አለች። እሷን ስሜት አወቅሀት? Generalized anxiety disorder (የአጠቃላይ ጭንቀት ህመም) ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜ እንደሱ ነው የሚሰማቸው።

ፈተና ልትገባ ስትል ያለው ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት፣ ሰውነት መወጣጠር፣ ሀሳብ ብትንትን ማለት...ወዘተ እሱን ስሜት አስታወሴከው ? GAD ያለባቸው ሰዎች ቀን በቀን የሚሰማቸው እንደዛ ነው። ይዜ ስሜት Apprehensive expectation ይባላል። 'የሆነ አደጋ ሊደርስ እንደሆነ ታውቆኛል' ስሜት ልንለው እንችላለን።

ይሄ ስሜት ለአንድ ቀን ከሆነ ኖርማል ነው። ለሳምንታት ከዘለቀ አሳሳቢ ነው። ለ6 ወራት እና ከዛ በላይ ከቆየ ግን መታከም ያለበት ህመም ነው።

ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ከባድ የጭንቀት ስሜት ከተሰማችሁ ቀአቅራቢያችሁ ያለ የአእምሮ ሀኪም ጋር ቀርቦ መታየት ጥሩ ነው። GAD ውጤታማ ህክምና አለው!

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!
ከሚያስገርሙኝ ሀኪሞች-ግብፃዊው ዶ/ር አብዱልረዛቅ ከድር
==========================
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ ግብፃውያን መምህራን ነበሩ። በተለይ የሚያስተምሩት ከሆስፒታል በፊት ያሉትን ሳይንሶች (Pre-clinical sciences) ነው። አብዛኞቹ በጣም ጎበዞች ነበሩ። በተለይ ዶ/ር አብዱልረዛቅ ለማስተማር ያለው ፍቅር፣ የሚሰጣቸው ምሳሌዎች፣ ጨዋታ አዋቂነቱ፣ ፅንሰ ሀሳብ ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ ፋይዳ (Clinical implications) እያስደገፈ ፊዚዮሎጅን (Human physiology) ሲያስተምር ያለው ሁኔታ ከስንት አመታት በኋላ አሁንም አይረሳኝም።

ዶ/ር አብዱልረዛቅ አንደኛው ክፍል ሲያስተምር ሌላኛው ግብፃዊ( ስሙ ጠፋኝ) ደግሞ ሌላኛውን ክፍል ያስተምር ነበር። ሌላኛው አስተማሪ ለተማሪዎች ከረሜላ ይሰጥ ነበር። ዶ/ር አብዱረዛቅ በነገር ሸንቆጥ ሲያደርገው "እኔ የማስተምረው አንደ አንዳንድ አስተማሪዎች ከረሜሎ-Vascular ሳይሆን ካድዲዮ ቫስኩላር (Cardio vascular ) ነው።" ይል ነበር።

በነገራችን ላይ ህክምና ትምህርት ቤት በየዲፓርትመንቱ ጎበዝ የሆኑ ነገር ግን የማይዋደዱ ሲንየሮች አሉ። እደግመዋለሁ በየዲፓርትመንቱ!!!!! (እሱን ሌላ ጊዜ በዝርዝር 'የዝሆኖቹ ትግልና የሬዚደንቶች መከራ' በሚል ርእስ እመለስበታለሁ።😂😂)

ዶ/ር አብዱልቃድር ፊዚዮሎጂን ፈትፍቶ ነው የሚያስተምረው። እሱ አቴንዳንስ አይዝም። የሱን ትምህርት ብትቀር አንተ ይጎልብሀል። ፊዝዮሎጂን ብዙዎች እንዲወዱ ያደረገ መምህር ነው። የምታስታውሱ እስቲ ጨምሩበት።

Fond rememberances!!!!!
ረጅም እድሜ ከጤና ተመኘሁ!!!
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::

የዚህ ወር ርዕስም፡- “ቦርደርላይን ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደርን መረዳት” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን አቶ ጴጥሮስ ሃጎስ ናቸው፡፡

ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡
https://forms.gle/ErdfV7uCCR2Y3Lzs8

የማስታወሻ መልእክት እና የቦታውን አቅጣጫ ምልክት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡፡
https://www.tgoop.com/mhaddisababa
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2017 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::

የዚህ ወር ርዕስም፡- “ናርሲስቲክ ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደርን መረዳት” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን አቶ ጴጥሮስ ሃጎስ ናቸው፡፡

ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡
https://forms.gle/mNTB3tYLfjXekzPu6

የማስታወሻ መልእክት እና የቦታውን አቅጣጫ ምልክት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡፡
https://www.tgoop.com/mentaladdis
We're thrilled to announce that Ease mind care a facility providing in person and online mental health services has made it to the finals of the Great Rift Valley Summit competition!
• Vote for Ease mind care
Please take a moment to vote for us at: https://vote.grvsummit.com/
Every vote brings us closer to making a bigger impact in a mental healthcare and achieving our vision. Thank you for your continued support together, we can make this happen!
2025/02/11 08:14:05
Back to Top
HTML Embed Code: