Telegram Web
በማሕበራዊ ግንኙነት ውስጥ የአመኔታ አስፈላጊነት
14👍9
በማሕበራዊ ግንኙነት ውስጥ የአመኔታ አስፈላጊነት
(“አመኔታ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተቀነጨበ)

“በማሕበራዊና በፖለቲካዊ የአመኔታ ዘርፎች ውስጥ የተለያዩ ውጤቶችን የሚያስከትሉ ሂደቶች አሉ፡፡ ማሕበራዊ አመኔታ ከፍ ሲል ሕብረተሰቡ በሕይወት እርካታን የማግኘት፣ የእድሜ መርዘም፣ ራስን ከማጥፋት የመቆጠብ፣ የመኪና አደጋ የመቀነስና የመሳሰሉ ማሕበራዊ ጤንነቶችን ይለማመዳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ ደም ግፊት የመሳሰሉት የጤና ቀውሶችን የመቅረፍ አቅም አለው” (Uslaner)፡፡

አመኔታ ማንኛውም ሕብረተሰብ እርስ በርስ ተጣብቆ እንዲኖር የሚያደርግ ሙጫ ነው፡፡ ከአመኔታ ውጭ ሕብረተሰብ ይፈርሳል፡፡ እድሩ፣ እቁቡ፣ ሽምግልናው፣ ማሕበሩ፣ መዋጮው፣ መጎራረሱ፣ የቡና እንጠጣው ግብዣና የመሳሰሉት የሃገራችን እንቁ ባህሎች ከአመኔታ ውጪ ባዶና ተሰባሪ ናቸው፡፡

ይህ አመኔታ የተሰኘ ማሕበራዊ ምጣኔ ሃብት ሲራቆት የገንዘብ አቅማችንን፣ ጤንነታችንንና ሌሎችም ለህልውናችን የሚጠቅሙንን ሁኔታዎች ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፡፡

ትልቁ ስእል:-

አመኔታ በነገሰበት ሕብረተሰብ ውስጥ በስህተት ትክክል ያልሆነ ነገር ተናግረህና የተሳሳተ ተግባር ስታደርግ ተገኝተህ እንኳን ሕብረተሰቡ ይህ ነው የማይባል ትእግስትን ያሳይሃል፡፡ በተቃራኒው በአለመተማመን ማጥ ውስጥ የሚገኝ ሕብረተሰብ ጥቃቅን ነገሮችን እየለቀመ ሲነካከስ የሚታይ ሕብረተሰብ ነው፡፡

እንዲህ አይነቱ አናሳ አመለካከት ያለው ሕብረተሰብ “ነገር” የማያገኝበት ሁኔታ የለም፡፡ የተነገረው ለምን ተነገረ፣ ያልተነገረው ለምን ዝም ተባለ፤ የተሰራው ለምን ተሰራ፣ ያልተሰራው ደግሞ ለምን አልተሰራም ከማለት ውጪ ምንም ስራ የለውም፡፡

የሕብረተሰቡ አባላት ከጥቃቅንና ደቃቃ ጉዳዮች ወጣ ብሎ ትልቁን ማሕበራዊ ስእል እንዲመለከቱ ካስፈለገ አመኔታ ዋናው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ትልቁ ማሕበራዊ ስእል፣ አንድነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምንና እድገትን ያካተተ ነው፡፡

ማህበራዊ ሰላም:-

አመኔታ በሌለበት ሰላም የለም፡፡ እርስ በርስ መተማመን በጠፋበት ስፍራ ሰላም የለም፡፡ ይህ እውነታ ከቤት ወደ መንደር፣ ከመንደር ደግሞ ወደ ሃገር የሚዘልቅ ጉዳይ ነው፡፡ የአንድ ግቢ ነዋሪዎችን ንትርክ እንመልከተው፤ በየሰፈሩ ያለውን የጎረቤት አለመግባባት እናጢነው፤ በወዳጆች መካከል ያለውን ክስ እንከታተለው … በእያንዳንዱ ማሕበራዊ ሕመም ውስጥ የአለመተማመንን ወይም የአመኔታ መጉደልን ዘር እናገኛለን፡፡

ሕብረተሰብ ወደመጨረሻው አዘቅት ውስጥ የሚወድቀው ኢኮኖሚ ሲወድቅ ወይም የውጭ ጠላት ሲመጣበት አይደለም፣ ሕብረተሰቡ የሚያከትምለት እርስ በርስ መተማመን ሲጠፋ ነው፡፡

አመኔታ ሲጨምር ሰላም፣ መረጋጋትና ጸጥታ ስፍራቸውን ይይዛሉ፡፡ በተቃራኒው አመኔታ ሲጎድል ደግሞ ሁከትና ረብሻ ይበራከታሉ፡፡

ወደቀድሞው የእርስ-በርስ መተማመን ብንመለስስ ??? !!!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
48👍29
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ችግሮቻችን!

በሕይወት እስካለን ድረስ የተለያዩ ችግሮች እንጋፈጣለን፡፡ ከእነዚህ ችግሮች የአንዳንዶቹ መነሻ “ውጫዊ” ሲሆን፣ የሌሎቹ መነሻ ደግሞ “ውስጣዊ” ነው፡፡

“ውጫዊ” መነሻ ማለት የኑሮ ችግር ሲያጋጥመን፣ ሁኔታዎች በጠበቅናቸው መልኩ አልሄድ ሲሉን፣ ያልጠበቅናቸው ነገሮች ሲከሰቱና የመሳሰሉትን የሚያጠቃልል ሃሳብ ነው፡፡

“ውስጣዊ” መነሻ ማለት በውስጣችን ካለን አመለካከትና የስነ-ልቦናም ሆነ የስሜት ቀውስ የሚነሳ ችግርን አለመልካች ነው፡፡

እነዚህ የችግር መነሻዎች ይወራረሳሉ፡፡ ይህ ማለት፣ የውጪ ችግር ሲኖርብንና በሚገባ ካልያዝነው የውስጥ ችግር ማስነሳቱ አይቀርም፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የውስጥ ችግር ካለብንና ተገቢውን ትኩረት ካልሰጠነው ነገሮችን አያያዝ ላይ ቀውስ ስለሚፈጥር ውጫዊ ችግር ማስከተሉ አይቀርም፡፡

ችግር መጋፈጥ ሰው ሁሉ የሚለማመደው ሁኔታ ነው፡፡ ችግር ግን በሚገባ ካልተያዘ ወደ ቀውስ ያልፋል፡፡
ችግር ወደ ቀውስ ደረጃ ሲደርስ፣ ግራ መጋባት፣ ድብርት፣ በአንድ ነገር ላይ ማተኮር አለመቻል፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ጉጉትን ማጣት፣ “ምን ሆኜ ነው?” የሚል ስሜትና የመሳሰሉትን ምልክቶች ልናይ ችንችላለን፡፡

ችግሮቻችን ወደ ቀውስ ደረጃ የሚደርሱት

1. ችግሮች በራሳቸው ይሄዳሉ ብለን ችላ ስላቸው . . .

2. እርዳታን ለመጠየቅ ማፈር ወይም አለመፈለግ . . .

3. የሰውን ድጋፍ በሚጠይቁና በማይጠይቁ ሁኔታዎች መለየት አለመቻል እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ችግራችሁ ወደ ቀውስ ደረጃ ሳያልፍ የምክር አገልግሎትን አግኙ፡፡

ለምክር አገልግሎት ዶ/ር ኢዮብም ለማግኘት
በዚህ 👉🏽 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ inbox በማድረግ ወይም በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡
51👍22🔥1😱1
የሕዳር ወር challenge!!!

የሕዳርን አራት ኃሙስ ምሽቶች
የጊዜ አጠቃቀማችንን የምንገመግምበት፣ ስለ ስኬታማ የጊዜ አጠቃቀም የምንማርበትና በአዲስ ምልከታ ወደፊት የምንቀጥልበት ወር እንዲሆን አቅደናል፡፡

ብዙዎ ለመሰልጠን በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
23👍9
የባከነ ጊዜ እና ጸጸት!

በሕይወታችን ተጽእኖ አምጪ ከሚባሉ ስሜቶች መካከል “ጸጸት” ይገኝበታል፡፡

የጸጸትን ስሜት በሁለት ከፍለን ስናየው

1. “የማድረግ” ጸጸት ማለት ከዚህ በፊት ያደረግነውን ነገር አስበን፣ “ምነው ባላደረኩት ኖሮ” ብለን ስንጸጸት ማለት ነው፡፡

2. “ያለማድረግ” ጸጸት ማለት፣ ከዚህ በፊት ማድረግ ሲገባን ያላደረግነውን ነገር አስበን፣ “ምነው ባደረኩት ኖሮ” ብለን ስንጸጸት ማለት ነው፡፡

ዓለም አቀፍ ጥናቶችም ሆኑ የግል ልምምዳችን እንደሚጠቁሙን፣ አብዣውን ጊዜ ረጅም ርቀት የሚከተለንና ወደ ኋላ የሚጎትተን የጸጸት አይነት፣ ባላደረግናቸው ነገሮች ላይ የምንጸጸተው ጸጸት ነው፡፡

ጊዜያችንን እና ተግባራችንን በሚገባ ያለመጠቀም ሁኔታ የሚያስከትልብን የጸጸት አይነት ከዚህ ጥናት ውጤት ጋር ይገናኛል፡፡ በእቅድና በትክክለኛ የጊዜ አጠቃቀም ስልት ካለመኖራችን የተነሳ በርካታ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች ሳይከናወኑ ያልፋሉ፡፡ የዚህ ሁኔታ ጸጸት ደግሞ ረጅም ጊዜ ይከተለንና አቅም ያሳጣናል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ በሚገባ እንድትሰሩ የሚግዛችሁ ስልጠና ተዘጋጅቷልና ተጠቀሙበት!

የስልጠናው ርእስ፡-
“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
34👍34😢1
ጠቃሚ ነኝ!

ምንም እንኳ ከዚህ በፊት ብዙ ነገር ያበላሸሁና የተሳሳትኩ ብሆንም፣ ፈጽሞ ጥቅም-የለሽ ሰው ግን አይደለሁም፡፡

ቢያንስ ቢያንስ፣ ካበላሸኋቸውና ከተሳሳትኳቸው ነገሮች እኔ ራሴም ሆንኩ ሌሎች ሰዎች ትምህርት የምናገኝበትን፣ እንዲሁም የሚደረገውንና የማይደረገውን ነገር የመለየትን ጥቅም እሰጣለሁ፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
71👍8😢3
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የጊዜ አጠቃቀማችሁ ጉዳይ!

⏱️ እናንተ ለጊዜያችሁ እቅድ ካላወጣችሁ፣ በእቅድ የሚኖረውን ሰው ዓላማ እንዳስፈጸማችሁ ትኖራላችሁ፡፡

⏱️እናንተ ጊዜችሁን በአግባቡ ካልተጠቀማችሁበት፣ ጊዜአቸውን በሚገባ በሚጠቀሙ ሰዎች ስር ጥገኛ እንደሆናችን ትኖላችሁ፡፡

⏱️ጊዜያችሁን በሚገባ ሳትጠቀሙ ስታባክኑት በእጃችሁ ያለውንም ሆነ ገና ልታስገቡት የሚገባችሁን ገንዘብ ታባክናላችሁ፡፡

⏱️የራሳችሁን ጊዜ ካላከበራችሁ፣ የሌሎችንም ሰዎች ጊዜ አታከብሩም፤ የሰዎችን ጊዜ ካላከበራችሁ ደግሞ ሰዎች እናንተን አያከብሯችሁም፡፡

⏱️ጊዜያችሁን በተደራጀ መልኩ ካልመራችሁት ራሳችሁንም ሆነ ስራችሁን በተደራጀ መልኩ መምራት አትችሉም፡፡

ኑሯችን የማያድገውና የማይሻሻለው አነዚህን የማይለወጡ ሕጎች ችላ ስለምንላቸው ነው፡፡

በዚህ ርእስ ላይ ነቃ ያለ ሕይወት መኖር ከፈለጋችሁ የተዘጋጀውን ስልጠና መውሰዳችሁን አትዘንጉ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
28👍15
ጊዜ እንዳያመልጠን!

ጊዜ እያለን ልክ እንደሌለው የምንኖረው፣ ያንን ያለንን ጊዜ በሚገባ የማንጠቀምበት ከሆነ ነው፡፡

ጊዜያችን ሲባክን ደግሞ ባለን ጊዜ ሰርተን ማግኘት የሚገባንን ገንዘብም ሆነ ሌሎች የገንዘብ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች አብረው ይባክናሉ፡፡ ስለሆነም፣ ጊዜ ባከነ ማለት ሁሉም ነገር ባከነ ማለት ነው፡፡ ጊዜ አተረፍን ማለት ደግሞ ብዙ ነገር አተረፍን ማለት ነው፡፡

ማንኛውንም ነገር የምናተርፈው በቅድሚያ ጊዜያችንን ስናተርፍ ነው፡፡ አንድ ሰው ጊዜውን በትክክል ሲጠቀምና ጊዜ ሲተርፈው፣ ተጨማሪ ገንዘዝን ለማትረፍ የማሰቢያ እና የመስሪያ ጊዜ ያገኛል፡፡

የብዙ ነገራችን መዘባረቅ መነሻው ጊዜያችንን በትክክል ስለማንጠቀም ይሆን?

ጊዜያችሁን በውጤታማነት እንድትጠቀሙ የሚያግዛችሁ ወሳኝ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና አያምልጣችሁ፡፡


የስልጠናው ርእስ፡-
“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
22🔥4👍3
2025/10/12 18:07:33
Back to Top
HTML Embed Code: