Telegram Web
የትኩረት ለውጥ አምጡ!
25👍3
የትኩረት ለውጥ አምጡ!

እንቅፋትና መሰናክል እቅዳችሁን ሊያቋርጠው ቢችልም በውስጣችሁ ያለውን ግለት እንዲያቋርጠው ግን በፍጹም አትፍቀዱ፡፡

እንቅፋቱና መሰናክሉ ከእናንተ ቁጥጥር ውጪ የሆነ የውጪ ኃይል ነው፡፡ የውስጣችሁ ያለው አመለካከታችሁ ግን በውስጣችሁ ያለና በእናንተ ቁጥጥር ስር የሆነ ነገር ነው፡፡

ትኩረታችሁን መለወጥና መቆጣጠር በማትችሉት ነገር ላይ ማድረግ በማቆም መለወጥና መቆጣጠር በምትችት ላይ አደርጉ፡፡

1. መቆጣጠር ወይም መለወጥ የማንችላቸው

ይህ ማለት፣ ምንም ብናስብና አልፎም ብንጨናነቅ እንኳን ምንም ነገር ማድረግና ለውጥን ማምጣት የማንችላቸው ነገሮችን አመልካች ነው፡፡

ለምሳሌ . . . አስተዳደጋችን፣ ስህተቶቻችን፣ ሰዎች ያደረጉብና እና ያላደረጉልን፣ የሃገር ኢኮኖሚ ሂደት ተለዋዋጭነት፣ በድንገት ሊከናወኑ የሚችሉ ክስተቶች እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች፡፡

እነዚህን ሁኔታዎችን አስመልክቶ ማድረግ ከምንችላቸው ነገሮች መካከል፣ ጸሎት ማድረግ፣ ካለፈው መማር፣ እውነታን መቀበል፣ ከሁኔታዎች በላይ ሆኖ ለመኖር ራስ ላይ በመስራት መሻሻልና በተለይም የራእይ ሰው በመሆን ወደፊት መገስገስ ነው፡፡

2. መቆጣጠር ወይም መለወጥ የምንችላቸው

ይህ ማለት፣ በማሰብ፣ በማቀድ፣ ትክክለኛ ምርጫና ውሳኔን በማድረግ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድና ሆን ብለን ለውጥን ማምጣት የምንችላቸው ነገሮችን አመልካች ነው፡፡

ለምሳሌ . . . የሕይወት ገጠመኞችን በስሜታዊነት ሳይሆን በምክንያዊነት ምላሽ መስጠት፣ አመለካከታችንን የመቆጣጠራችን ሁኔታ እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች፡፡

እነዚህን ሁኔታዎችን አስመልክቶ ማድረግ ከሚገቡን ነገሮች መካከል፣ ሕይወትን በዲሲፕሊን መምራት፣ እቅድ በማውጣት ሕይወትንና የኑሮ ደረጃን ማሻሻል፣ ባለን የሰው-ለሰው ግንኙነት መብሰል፣ ራእይን መቅረጽና እሱን መከተል ነው፡፡

ይህንን ሂደት መገንዘብ እና መለማመድ ለውጥ በማናመጣባቸው ነገሮች ላይ በማተኮር ጊዜን ከማባከን፣ ገንዘብን ከመክሰር፣ የስሜት ቀውስ ውስጥ ከመግባት እና ከዋና የሕይወት ዓላማ ከመገታት እንድንጠበቅ ይረዳናል፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
108👍34🎉1🤩1
የሕልማችሁ እውነተኛነት ማረጋገጫ!

➫ ሕልማችሁ ካላችሁ የገንዘብ አቅም በላይ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡

➫ ሕልማችሁ ካላችሁ የእውቀት ደረጃ በላይ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡

➫ ሕልማችሁ ካላችሁ የሰው-ለሰው ግንኙትና የእውቅና ብዛት ያለፈ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡

➫ ሕልማችሁ አሁን ካላችሁበት የኑሮ ሁኔታ ያለፈ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡

➫ ሕልማችሁ ያለ የሌላችሁን አቅም ተጠቅማችሁ እንኳን የሚወጥራችሁ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡

የሕልማችሁ ጉዳይ ከባድ ሆኖ ሲታያችሁ፣ የማትደርሱበት ሲመስላችሁና ሩቅ እንደሆነ ስታስቡ እውነትም ሕልማችሁ “ሕልም” ነውና ደስ ይበላችሁ፡፡

ዝም ብላች አቅዱ፣ ራሳችሁን አሻሽሉ፣ ወደ ሕልማችሁ ተራመዱ!

ይሆናል! ይሳካል!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍119101🔥4😁4😢2🎉1
Day of Appreciation!

“አዲሱን ጫማችሁን ለመግዛት ስትሄዱ እዚያ ለመድረስ አድርጋችሁት የነበረውን አሮጌ ጫማ በፍጹም አትርሱ” - Daily Wisdom

አሁን ለደረሳችሁበት ደረጃ መዋጮ ያደረጉትን ሰዎች ውለታ appreciate የማድረጊያ ቀን እንዲሆንላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡

መልካም ቅዳሜ!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
166👍50😱3🎉1
💲በ ቪዲዮ ኢዲቲንግ የዶላር ተከፋይ ይሁኑ!

ምዝገባው ሊጠናቀቅ 1 ቀን ብቻ ይቀረዋል!


🗓 ስልጠናው ነገ ሰኞ ነሃሴ 26 ማታ 3፡30 ይጀምራል

⚡️ ስልጠናው ለአንድ ወር ይቆያል ፤ እየሰለጠኑ በጎን ስራውን መስራት የሚጀምሩበት ሁኔታ ተመቻችቷል!

——
ለመመዝገብ በዚ አካውንት ያናግሩን👇
🔗
@AddisGrind
——

ስልጠናው ምን ያካትታል?

🔹 ቪዲዮ ኢዲቲንግ የምንሰራበት ፕላትፎርሙ ላይ እንዴት ገንዘብ መስራት እንደምትችሉ ሙሉ መረጃ
🔹 ባንክ አካውንታችሁን ከ ፕላትፎርሙ ምታገናኙበትን ሂደት እናሳያችኋለን
🔹 በየቀኑ ለአንድ ሰዓት ለ አንድ ወር ያክል LIVE Training + Record የተደረገ ቪዲዮ ታገኛላችሁ
🔹 ሙሉ የ CapCut Advanced Video Editing
🔹 ሙሉ የ YouTube እና TikTok Viral Short Stagey
🔹 እኛ ያለፍንበትን እያንዳንዱን ሂደት Tips በስፋት ታያላችሁ
🔹 የምትሰሩት ስራ ላይ አስተያየት እና እገዛ ታገኛላችሁ
🔹 ክፍያችሁን ወደባንክ እስከምትልኩ ያልተቋረጠ እገዛ እናደርጋለን

ዛሬውኑ ተመዝገቡ

——
ለመመዝገብ በዚ አካውንት ያናግሩን👇
🔗
@AddisGrind
——

©️ Addis Grind | ለጥያቄ፡ @AddisGrind
40👍13😁1
የመርከባችሁ ጉዳይ!

አንድ ሰው እንደዚህ አለ፣ “ወደ መርከብህ ውስጥ ማንን እንደምታስገባ ተጠንቀቅ፡፡ አንዳንድ ሰዎች የመርከቡ ዋና ካፒቴን የመሆን ፍላጎታቸው ስላልተሳካላቸው ብቻ መርከቡን ሙሉ በሙሉ ከማስጠም አይመለሱም”፡፡

በገቡበት የግንኙነት መስክ ሁሉ ተሰሚዎቹ እነሱ፣ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላላፊዎቹ እነሱ፣ የበላይ እነሱ፣ ሙሉ ለሙሉ ተጠቃሚዎቹ እነሱ . . . መሆን እንዳለባቸው ከሚያስቡሰ ሰዎች ራሳችሁን ጠብቁ፡፡

እንደዚህ አይነት ሰዎች የፈለጉትን ካላገኙ ማንም ሰው እና ምንም ነገር ቢጠፋ ምንም ችግር የለባቸውም፡፡

የፍቅር ሕይወት መርከባችሁ፣ የስራ መርከባችሁ፣ የራእይና የሕልም መርከባችሁ፣ የንግድ መርከባችሁ . . . ይጠበቅ፡፡

እነዚህንና መሰል የሕይወታችሁን ክፍሎች ለመጠበቅ ከፈለጋችሁ ሰዎችን በሚከተሉት ፈተናዎች መፈተንን ተለማመዱ፡፡

1. የተግባር ፈተና

ሰዎች የሚነግሯችሁን ቃላት ብቻ በመስማት ከማመናችሁ በፊት የየእለት ተግባራቸውን በሚገባ ተመልከቱ፡፡

2. የጊዜ ፈተና

ጊዜ የማይገልጠው ነገር ስለሌለ ሰዎች ሲቀርቧችሁ በችኮላ ወደጠለቀ ግንኙነት ከመግባታችሁ በፊት በቂ ጊዜ አሳልፉ፡፡

3. የግልጽነት ፈተና

ሰዎች የሚደብቋችሁን እና በግልጽ የሚነገሯችሁን ሁኔታዎች በሚገባ ካጠናችሁት ስለማንነታቸው በሚገባ ያሳያችኋል፡፡

እነዚህን ፈተናዎች እንዳንጠቀም የሚያደርጉን . . .

• የብቸኝነት ስሜት ካለብን፣

• ጊዜ እያለፈብን እንደሆነ ከተሰማን ብቻችንን፣

• በሰዎች የተገፋን ከሆንን እና ተቀባይነት የሚጠማን ከሆነ፣

ለቀረበን ሰው ሁሉ ተጋላጭ እንሆናለንና እነዚህና መሰል ቀውሶች መስመር ሊይዙ ይገባቸዋል፡፡

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
155👍35😁1🎉1
💲በ አንድ ወር ስልጠና በቪዲዮ ኢዲቲንግ የዶላር ተከፋይ መሆን ይችላሉ!

ምዝገባው ዛሬ ማታ 3 ሰዓት ይጠናቀቃል!


🗓 ስልጠናው ማታ 3፡30 ይጀምራል ፤ ለአንድ ወር በየቀኑ የሚሰለጥኑ ሲሆን ስልጠናውን እየወሰዱ በጎን ስራውን መስራት የሚጀምሩበት ሁኔታ ተመቻችቷል!

——
ለመመዝገብ በዚ አካውንት ያናግሩን👇
🔗
@AddisGrind
——

ለተጨማሪ ጥያቄ ፡
📞 +251709920368

ስልጠናው ምን ያካትታል?

🔹 ቪዲዮ ኢዲቲንግ የምንሰራበት ፕላትፎርሙ ላይ እንዴት ገንዘብ መስራት እንደምትችሉ ሙሉ መረጃ
🔹 ባንክ አካውንታችሁን ከ ፕላትፎርሙ ምታገናኙበትን ሂደት እናሳያችኋለን
🔹 በየቀኑ ለአንድ ሰዓት ለ አንድ ወር ያክል LIVE Training + Record የተደረገ ቪዲዮ ታገኛላችሁ
🔹 ሙሉ የ CapCut Advanced Video Editing
🔹 ሙሉ የ YouTube እና TikTok Viral Short Strategy
🔹 እኛ ያለፍንበትን እያንዳንዱን ሂደት Tips በስፋት ታያላችሁ
🔹 የምትሰሩት ስራ ላይ አስተያየት እና እገዛ ታገኛላችሁ
🔹 ክፍያችሁን ወደባንክ እስከምትልኩ ያልተቋረጠ እገዛ እናደርጋለን

ዛሬውኑ ይመዝገቡ

——
ለመመዝገብ በዚ አካውንት ያናግሩን👇
🔗
@AddisGrind
——

©️ Addis Grind | ለጥያቄ፡ @AddisGrind
36👍13😁2
ሕይወት እንደ አይሮፕላን በረራ ነች!

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ አይሮፕላን በረራ ያደርጋታል፡፡ የአይሮፕላን በረራ አደገኛው፣ ለመከስከስ ተጋላጭ የሆነውና እጅግ ትልቅ ጥንቃቄ የሚስፈልገው ጊዜ ሁለት ነው፡፡

1) የመነሻው (የመጀመሪያ) ጊዜ፣

2) የማረፊያው (የመጨረሻው) ጊዜ፡፡

ማንኛውንም ግንኙነት፣ ንግድ፣ ስራ፣ ራእይ . . . ስትጀምሩ በጥንቃቄ አስባችሁበት ጀምሩ፡፡ በችኮላ፣ በመላ-ምትና በግድ የለሽነት የተጀመረ ነገር ለመከስከስ አደጋ የተጋለጠ ነው፡፡ ትክክለኛ ነገር እየጀመርን እንኳን በጥንቃቄ ካላደረግነው ከአደጋው አናመልጥም፡፡

ማንኛውም ግንኙነት፣ ንግድ፣ ስራ፣ ራእይ . . . ወደማብቂያው እንደደረሰ ሲገባንና “ማሳረፍ” ስንፈልግም ታላቅ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡ በስሜታዊነትና በችኮላ ነገሮችን ከማቋረጥ መጠንቀቅንና ስናቋርጠው ደግሞ በጥበብ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ አሳርፉት እንጂ አትከስክሱት!

ይታሰብበት!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
182👍61🔥5🎉2
ሰዎች ሲሳሳቱ!
20👍7🎉2
ሰዎች ሲሳሳቱ!

በሕይወታችን በሚዛናዊነት ልንይዛቸው ከሚገቡን ወሳኝ ነገሮች መካከል በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎች፣ በተለይም የየእለት የኑሮ ስምሪታችን የሚያገናኘን ሰዎች ስህተት ሲሰሩ የምንሰጠው ምላሽ ቀንደኛው ነው፡፡ ከሰዎች ጋር የምናሳልፈው ጊዜ በበዛ ቁጥር ሰዎቹ ስህተት ሲሰሩ ማየታችን አይቀርም፡፡

የቤተሰብ አባሎቻችን፣ የትዳር አጋራች፣ የቅርብ ጓደኞቻችን፣ የስራ ባልደረቦቻችን፣ አለቆቻችን፣ የሃገር መሪዎቻችንና . . . ካለማቋረጥ ስህተትን ይሰራሉ፡፡ ለዚህ አይቀሬ ግላዊም ሆነ ማሕበራዊ ሂደት የምንሰጠው ምላሽ ሚዛናዊነት ለግልም ሆነ ለማሕበራዊ ስኬታችን እጅግ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡

አብዛኛዎቻችን ከአስተዳደጋችን ለስህተታችን ምህረት ሳይደረግልን ከላይ ከላዩ ተጠብጥበን ስላደግን ሁኔታው አሁን ለሰዎች ስህተት ምህረት-የለሽ እንድንሆን ተጽእኖ አድርጎብናል፡፡ ስለዚህም፣ ለሁሉም ስህተት ጨከን ማለት ሚዛናችንን ስለሚያስተን መቼ ጠንከር፣ መቼ ደግሞ ለስለስ ማለት እንደሚገባን ማሰብ ታላቅ ሚዛናዊነትን ይሰጠናል፡፡

በቃ! የለመድነው መውቀስና መወቀስ፣ መምታትና መመታት፣ ማማትና መታማት፣ ስም ማጥፋትና ስም መጥፋት . . . ስለሆነ ስህተትን አይቶ በቀላሉ የማለፍን ጉዳይ ሆን ብለን ለራሳችን ካላስተማርነው በስተቀር ያስቸግረናል፡፡ ምንም ስህተትን በማያሳልፍና በተሳሳተን ሰው ላይ ልክ እንደወደቀ ዛፍ ሁሉም ሰው መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ሕብረተሰብ መካከል ስንኖር የምህረት፣ የይቅርታና አንዳንድ ጊዜ “ይሁን” ብለን አለፍ የምንል አይነት “አብሪ ኮከቦች” እንድነሆን የሚከተሉት ሃሳቦች ያግዙናል ብዬ አስባለሁ፡፡

አብዛኛውን ጊዜ ስህተት በሰሩ ሰዎች ላይ የመጨከን ዝንባሌችን የሚገናኘው ከማናውቃቸው ነገሮች የተነሳ ነው፡፡ ሶስቱን ዋና ዋና የማናውቃቸውን ነገሮች እንመልከት . . .

1. ይህ ሰው ይህንን ስህተት ላለመስራት ምን ያህል እንደታገለ አናውቅም፡፡

ሰዎች ስህተትን ሲሰሩ ያንን ስህተት ላለመስራት ምን ያህል እንደታገሉና እንደሞከሩ ብናውቅ ትንሽ ለስለስ እንልላቸው ነበር፡፡ እኛው ራሳችንም ብንሆን አንዳንድ ጊዜ አንድን ስህተት ላለመስራትና ላለመድገምም ጭምር ብዙ ታግለን ስላቃተን ብቻ ራሳችንን ስህተት ላይ እንደምናገኘው ማሰብ አለብን፡፡

2. ይህ ሰው ይህንን ስህተት እንዲሰራ ጫና ያሳደረበትን ከአቅሙ በላይ የሆነን ሁኔታ አናውቅም፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አንድን ስህተት እንዲሰሩ የሚያስገድዳቸው የራሳቸው የሆኑ ሁኔታዎችና የሚያልፉበት ነገር ይኖር ይሆናል፡፡ የሰዎቹ ጾታ፣ የእድሜ ደረጃ፣ የገንዘብ አቅም፣ የእውቀት ብቃት፣ ያለፈ ልምምድና የመሳሰሉት ሁኔታዎች የራሱ ውህደት (Chemistry) ስላለው ማንም ሰው ያንኑ ችግር በእነሱ ሁኔታ ሊጋፈጠው አይችልም፡፡ ይህንን ማሰብ ትንሽ ሰፋ እንድንልና ሚዛናዊ እንድንሆን ያግዘናል፡፡

3. ይህ ሰው በሚያልፍበት በተመሳሳይ ሁኔታ ብናልፍ እኛ ራሳችን ምን ያህል ስህተት ልንሰራ እንደምንችል አናውቅም፡፡

ሰዎች በመሪነት የውሳኔ ስህተት ሲፈጽሙ እኔ እንደ አንድ ዜጋ የፍርድ ቃል መናገር ሊቀለኝ ይችላል፤ መሪ ስላለሆንኩኝ፡፡ እኔ መሪ ብሆንና እሱ በሚያልፈበት ሁኔታ ባልፍ ግን ምን አይነት ስህተት እሰራ እሆን? በተመሳሳይ ሁኔታ ባልና ሚስቶች፣ ሴቶችና ወንዶች፣ መሪና ተመሪዎች፣ ነጋዴዎችና ገበያተኛዎች . . . ሊያስቡ የሚገባቸው እነሱ በዚያኛው ሰው ቦታ ቢሆኑ ሊሰሩ የሚገደዱት ስህተት ሊኖር የመቻሉን ጉዳይ ነው፡፡

በተቻለን መጠን ስህተትን ላለመስራት የመታገላችንን ጉዳይ ስናሰምርበት፣ ከዚያው ጋር በተቻለን መጠን ሰዎች ስሀተት ሲሰሩ የፍርድና የወቀሳ ሃሳብ ከመሰንዘራችን በፊት ግራና ቀኙን የማየት ሰፊነት የማዳበርንም ጉዳይ እንድናሰምርበት አሳስባለሁ፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
152👍56🔥9🎉6
ከፍርሃት ባሻገር!

“ለማድረግ ስትፈልጉት የነበራችሁት ነገር በሙሉ ከፍርሃታችሁ በሻገር ቁጭ ብሎ ይገኛል” - Wisdom For Living

ተራመዱ እንጂ!!!


https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍7744🤩4🎉3😢2
ብዥ ሲልብኝ

• የሚወዱኝ ሰዎች የማይወዱኝ፤ የማይወዱኝ ሰዎች ደግሞ የሚወዱኝ እየመሰለኝ ራሴን ለብቻው አገኘዋለሁ - እስክባንን ድረስ!

• የሚያስኬደው መንገድ የማያስኬድ፤ የማያስኬደው መንገድ ደግሞ የሚያስኬድ እየመሰለኝ ሩቅ ተጉዤ እመለሳለሁ - እስኪጠራልኝ ድረስ!

• ማመን የሚገባኝን ሰው ባለማመን፤ ፈጽሞ ማመን የማይገባኝን ሰው ደግሞ በማመን ብዙ እጎዳለሁ - እስኪገባኝ ድረስ!

• ጊዜ መስጠት በሚገባኝ ነገር ላይ በመቸኮል፤ ጊዜ መስጠት በማይገባኝ ነገር ላይ ደግሞ በማዝገም ብዙ አባክናለሁ - እስከነቃ ድረስ!

• ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ላይ አጉል በመዳፈር፤ ድፍረት በሚጠይቀው ነገር ላይ በመፍራት እወዛገባለሁ - ቆፍጠን እስክል ድረስ!

• “እሺ” ማለት ለሚገባኝ ሰውና ሁኔታ “እምቢ”፤ “እምቢ” ማለት ለሚገባኝ ሰውና ሁኔታ “እሺ” በማለት እተራመሳለሁ - እስክረጋጋ ድረስ!

ምን ሆኛለሁ?! ለምንድን ነው ነቃ የማልለው?! ምን ሆኜ ነው የምፈዘውና የምደነዝዘው?!

. . . ይቀጥላል!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
169👍44😢14🔥4🎉1
ብዥ ሲልብኝ . . .

የሚወዱኝ ሰዎች የማይወዱኝ፤ የማይወዱኝ ሰዎች ደግሞ የሚወዱኝ እየመሰለኝ ራሴን ለብቻው አገኘዋለሁ - እስክባንን ድረስ!

ስባንን . . .

1. የማንነቴን መለኪያና የደስታዬን መጠን በወደዱኝና ባልወደዱኝ ሰዎች ላይ ማስደገፍን በማቆም ከሰውም ጋርም ሆነ ከሰው ውጪ ሙሉና ደስተኛ ሰው እንደሆንኩኝ አምናለሁ፡፡

2. ሰዎች ለእኔ የሚያሳዩኝ ሁኔታ እውነተኛ ሆኖ የሚፈተነውና የሚለየው በጊዜ እንደሆነ ስለማውቅ በችኮላ ለሰዎች ልቤን ከመስጠቴ በፊት በቂ ጊዜን እሰጣቸዋለሁ፡፡

3. ለሚወዱኝ ሰዎች ተመጣጣኝ ምላሽ በመስጠት መቅረብ፣ ለማይወዱኝን ደግሞ ለሰው ሁሉ የሚገባውን ክብር በመስጠት ርቀትን መጠበቅ፣ እየተለዋወጡ ግራ ለሚጋቡኝ ሰዎ ደግሞ ለወቅቱ ሁኔታቸው የሚመጥንን ጊዜያዊ ምላሽ በመስጠት አላማዬ ላይ አተኩራለሁ፡፡

ምንም አልሆንኩም! ንቁ ሰው ነኝ! አልፈዝምም አልደነዝዝምም!

. . . ይቀጥላል!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
150👍53🔥10🎉4
ውድቀት ለእድገት!

ስህተታችሁን የማወቅ ብስለት፣ ከስህተታችሁ የመማር ትህትና፣ እንዲሁም ስህተታችሁን ያለመድገም ብርታት እስካላችሁ ድረስ ከውድቀት ይልቅ እድገትን መለማመዳችሁ አይቀርም፡፡

Sweet dreams!!!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
95👍45🔥1😁1🎉1
ብዥ ሲልብኝ . . .

የሚያስኬደው መንገድ የማያስኬድ፤ የማያስኬደው መንገድ ደግሞ የሚያስኬድ እየመሰለኝ ሩቅ ተጉዤ እመለሳለሁ - እስኪጠራልኝ ድረስ!

ሲጠራልኝ . . .

1. የሕይወቴን ራእይን ዓላማ መለየቴንና ማወቄን እርግጠኛ እሆናለሁ፡፡

2. የምከተለው መንገድ በሙሉ ከዋናው የሕይወቴ ራእይና ዓላማ ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን ሳላረጋግጥ አልንቀሳቀሰም፡፡

3. የተሳሳተ መንገድ እንደያዝኩኝ ሲገባኝ ምንም ጊዜ ሳላባክን እንደገና በመመለስ አቅጣጫዬን አስተካክላለሁ፡፡

ምንም አልሆንኩም! ንቁ ሰው ነኝ! አልፈዝምም አልደነዝዝምም!

. . . ይቀጥላል!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
125👍35🔥4🎉2🤩1
ብዥ ሲልብኝ . . .

ማመን የሚገባኝን ሰው ባለማመን፤ ፈጽሞ ማመን የማይገባኝን ሰው ደግሞ በማመን ብዙ እጎዳለሁ - እስኪገባኝ ድረስ!

ሲገባኝ . . .

1. ሰውን ከማመን ውጪ ሕይወት ትርጉም እንደሌላትና ምንም ነገር ለማድረግ እንዳልችል እገነዘባለሁ፡፡

2. ሰዎችን ከማመኔ በፊት ማጣራት የምችለውን ነገር ሁሉ የማጣራትና በማመኔ ምክንያት ላገኝ የምችለውን ጥቅማነ ሊደርስብኝ የሚችለውን ጉዳት አመዛዝናለሁ፡፡

3. ያመንኳቸው ሰዎች ሲጎዱኝ ምንም እንኳን ለጊዜው ስሜቴ ቢዛባም በእነሱ ምክንያት አልቆዝምም፣ ተስፋም አልቆርጥም፡፡
ምንም አልሆንኩም! ንቁ ሰው ነኝ! አልፈዝምም አልደነዝዝምም!

. . . ይቀጥላል!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
128👍21😢5🔥3
ብዥ ሲልብኝ . . .

ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ላይ አጉል በመዳፈር፤ ድፍረት በሚጠይቀው ነገር ላይ በመፍራት እወዛገባለሁ - ቆፍጠን እስክል ድረስ!

ቆፍጠን ስል . . .

1. ሕይወት ማለት ሃምሳ በመቶ ጥንቃቄ፣ ሃምሳ በመቶ ደግሞ አደጋና ስጋትን የመጋፈጥ እርምጃ እንደሆነች በማመን እንደአስፈላጊነቱ ማድረግ ያለብኝን ከማድረግ አልመለሰም፡፡

2. ቆፍጣናነት ማለት ጥንቃቄ ለሚያስፈልገው ነገር ሰብሰብ ማለት ብልሀነት እንጂ ፈሪነት እንዳልሆነ፣ ድፍረት ለሚያስፈልገው ነገር ደግሞ ጥበብ የተሞላበት እርምጃ መውሰድ ማለት አጉል ሞኝነት እንዳልሆነ እገነዘባለሁ፡፡

3. ፈርቶና ተደብቆ ምንም ሳይሰሩ ከሞት ያልናነሰ ሕይወት ከመኖር ደፍሮና ቀና ብሎ ከባባድ ሁኔታዎችን መጋፈጥ ሁል ጊዜ የተመረጠ እንደሆነ አስባለሁ፡፡

ምንም አልሆንኩም! ንቁ ሰው ነኝ! አልፈዝምም አልደነዝዝምም!

. . . ይቀጥላል!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
127👍29🔥7🎉3😱1
ከራሳችሁ ይጀምር!

• ለራሳችሁ ያልሰጣችሁትን ክብር ከሰዎች አትጠበቁ፡፡ ራሳችሁን ስታከብሩ፣ በሰዎች ትከበራላችሁ፡፡ ባትከበሩም እንኳን፣ የሰዎችን ንቀት አልፋችሁ የመሄድ አቅምታ ታገኛላችሁ፡፡

• ለራሳችሁ ያልሰጣችሁትን ፍቅር ከሰዎች አትጠብቁ፡፡ ራሳችሁን ስትወዱ፣ በሰዎች ትወደዳላችሁ፡፡ ባትወደዱም እንኳን የሰዎችን ጥላቻ አልፋችሁ የመሄድ ጉልበት ታገኛላችሁ፡፡

• ራሳችሁ ያላሰመራችሁትን የቀይ መስመር ሰዎች እንዲያከብሩላችሁ አትጠብቁ፡፡ የግል ቀይ መስመር ሲኖራችሁ ሰዎች ያንን መስመር ያከብሩላችኋል፡፡ ባያከብሩላችሁም፣ ተገቢውን ምላሽ የመስጠት ብርታት ታገኛላችሁ፡፡

የሰላም እንቅልፍ ተመኘሁላችሁ!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
157👍46🔥9😁2🎉1
ብዥ ሲልብኝ . . .

“እሺ” ማለት ለሚገባኝ ሰውና ሁኔታ “እምቢ”፤ “እምቢ” ማለት ለሚገባኝ ሰውና ሁኔታ “እሺ” በማለት እተራመሳለሁ - እስክረጋጋ ድረስ!

ስረጋጋ . . .

1. ተገቢ ለሆነ ነገርም ሆነ ላልሆነ ነገር እሺም አልኩ እምቢ ሁሉም ነገር ከችግር ውጪ እንደማያደርገኝ በማወቅ ራሴን አዘጋጃለሁ፡፡

2. ተገቢ ላልሆነ ነገር “እምቢ” በማለት ከሚመጣው ችግር ይልቅ “እሺ” ማለትና ለመጣው ነገር ሁሉ ክፍት መሆን የሚያመጣው ችግር አደገኛ እንደሆነ እገነዘባለሁ፡፡

3. ተገቢ ላልሆነ ነገር “እምቢ” ስል የሚያስከትለው ችግር ሁል ጊዜ የኋለ ኋላ መልካም ፍሬን እንደሚያፈራና በራሴም ላይ ያለኝን አመለካከት ጤናማና ሚዛናዊ እንደሚያደርገው አውቃለሁ፡፡

ምንም አልሆንኩም! ንቁ ሰው ነኝ! አልፈዝምም አልደነዝዝምም!

. . . ይቀጥላል!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍7555🔥3🎉3
ብዥ ሲልብኝ . . .

ጊዜ መስጠት በሚገባኝ ነገር ላይ በመቸኮል፤ ጊዜ መስጠት በማይገባኝ ነገር ላይ ደግሞ በማዝገም ብዙ አባክናለሁ - እስከነቃ ድረስ!

ስነቃ . . .

1. ማንኛውም ምርጫና ውሳኔ ከማድረጌ በፊት ለሁኔታው የሚመጥነውን ጊዜ በመስጠት ማሰብን፣ ማመዛዘንንና አስፈላጊ ከሆነ ምክርን መቀበልን እለማመዳለሁ፡፡

2. የወደፊቱን የሕይወቴን አቅጣጫ እስከወዲያኛው በሚቀይሩ ሁኔታዎች ላይ በጊዜያዊ ስሜት በመነሳሳት ከመወሰን በመቆጠብ በቂ ጊዜ እሰጣቸዋለሁ፡፡

3. ምንም ብጎብዝ፣ ብልህ ብሆንና ለነገሮች ገጊዜ ብሰጣቸውም አንዳንድ ጊዜ የተሳሳቱ ውሳኔዎችን ላስተናግድ እንደምችል አምኜ በመቀበል ስሳሳት ራስን ከመውቀስ ይልቅ መፍትሄው ላይ አተኩራለሁ፡፡

ምንም አልሆንኩም! ንቁ ሰው ነኝ! አልፈዝምም አልደነዝዝምም!

መልካም የአዲስ አመት ዋዜማ!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
89👍13🎉5
2025/10/12 20:29:17
Back to Top
HTML Embed Code: