Telegram Web
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟐]

በሥነ ሕይወት(Biology) ዙርያ “Argyroneta aquatica” በመባል የምትታወቅ የውኃ ሸረሪት በኩሬዎች ፣ ጅረቶች እና ሌሎች ጥልቀት በሌላቸው የንፁህ ውኃ አካላት ውስጥ ሙሉ ሕይወቷን የምታሳልፍ ብቸኛው ሸረሪት ስትሆን መኖርያዋን በተመለከተ —


➛ የውኃ ሸረሪት በውኃ ውስጥ ባሉ እፅዋቶች ወይንም ሌሎች ነገሮች ላይ ድሯን ትጠቀልላለች ፣ ቀጥሎ በሆዷ እና እግሮቿ ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ፀጉሮቿን በመጠቀም ወደ ወኃው ወለል ወጥታ የአየርን አረፋ በመያዝ እንደገና ወደ ታች በመጥለቅ አረፋውን አንድ ላይ አጠራቅማ መኖርያዋን ትሰራለች።

➛ ቀስ በቀስም በአየር የተነፋው ድሯ ይፈርሳል በየቀኑም አንድ ጊዜ ቤቷን በአየር ለማሳደስ ወደ ውኃው ወለል መውጣት ይኖርባታል።
[🔗 https://www.britannica.com/animal/water-spider]


🎯 አላህ ﷻ ከ1,400 ዓመታት በፊት እነዛን የካህዳይን ረዳቶችን ስንኩልነት ለመግለፅ ይህን የመሰለ ደካማ ቤት ከሚሰሩ ሸረሪቶች ጋር አነፃፅሮ ወደዚህ አስደናቂ እውነታ ጠቁሟል —

۞ {የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር)፡፡}
  — አል-ዐንከቡት 29÷41


“እርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፡፡” (Qur’an 41÷53)


ሰደቀሏሁል ዐዚም...

https://www.tgoop.com/EAAAresponse
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟑]

በሥነ ከዋክብት (Planetology) ዙርያ “Pulsar star” የሚባል ኮከብ በ1967 ዓም ሁለት ተመራማሪዎች ከሬዲዮ ቴሌስኮፕ ያልተለመደ ድምፁን አስተውለው በ1968 ላይ ሙሉ መረጃውን ይፋ አረጉት። 

➛ “Pulsar star” በሁለት ተቃራኒ ጎኖቹ ኃይለኛ ጨረር አመንጪና በእንጨት ላይ እንደማንኳኳት ይመስል ድምጽ አሰሚ ከ ‹nutron star› ክዋክብቶች የሚመደብ ደማቅ ኮከብ ነው።
[🔗 https://imagine.gsfc.nasa.gov/science/objects/neutron_stars1.html#:~:text=Pulsars%20are%20rotating%20neutron%20stars,very%20powerful%20beams%20of%20light.]


🎯 አላህ ﷻ በቅዱስ ቃሉ ከሺህ አራት መቶ ዓመት በፊት «በሰማዩ *በጧሪቅም(በአንኳኪው)* እምላለሁ፡፡» ብሎ ቀጥሎ «ጨለማን ቀዳጁ #ኮከብ ነው፡፡» (Qur’an 86÷1-3) በማለት ስለዚህ ግሩም ኮከብ አስቀድሞ ነግሮናል።

➛ "አጥ-ጣሪቅ/ الطّارق/ At-Tariq" የሚለው ቃል ‘ጠረቀ’ ወይንም ‘አንኳኳ/ he knocked’ ከሚል ግስ የረባ ሲሆን ትርጉሙ «አንኳኪ, knocker, striker» ማለት ነው።
[🔗 https://m.name-doctor.com/tarik/]


“እርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፡፡” (Qur’an 41÷53)


ሰደቀሏሁል ዐዚም...

https://www.tgoop.com/EAAAresponse
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟒]

በሥነ ጠፈር(Spaceology) ዙርያ አስትሮኖመሮች ወደ ጠፈር ጉዞ ሲያደርጉ (space blindness or VIIP) የሚባል ቅምረ ህመም በእይታቸው ላይ የዓይን እክልነትን/ስውርነትን አስከተሏል። እዛ ስበተ ቁስ(gravity) ስለሌለ በአንጎል እና በአይን ጀርባቸዉ ላይ ጫና ተፈጥሮ ነው ተብሎም ይታሰባል።


➛ ‘Julie Robinson’ እንዳለችው :- ‹ባለፉት 10 አመታት ውስጥ ከደረስንባቸው ነገራቶች አንዱ የተወሰኑ ጠፈርተኞች ወደ ህዋ ሲሄዱ ዓይናቸው ጠፋ...ጥቂቶቹ ወደ ምድር ሲመለሱ የማይቀለበስ ቋሚ የእይታ እጦት ደረሰባቸው።”›
[🔗 https://m.lasvegassun.com/news/2017/dec/02/space-blindness-must-be-solved-before-mission-to-m/]

➛ አንዳንዶችም እንደ ‘Scott Kelly’ እና ‘John Phillips’ ከጠፈር ጉዞ ከተመለሱ በኃላ በአጭር ጊዜ ውስጥ እይታቸው ላይ ችግር እንደተፈጠረ ታውጇል።
[🔗 https://www.sciencealert.com/we-finally-know-why-astronauts-lose-their-vision-in-space-and-it-s-bad-news-for-mars-missions]


🎯 አላህ ﷻ በቅዱስ ቃሉ ቁርአንን ያስተባበሉ ከሃድያን የሰማይን ደጃፍ (ozone layer) ከፍቶላቸው ወደ ላይ ቢያርጉ ኖሮ ‘space blindness’ ያጋጥማቸው እንደነበር ወደዚህ አስደናቂ ክስተት አስቀደሞ ጠቁሞናል—

۞ «በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ በዋሉ ኖሮ»

۞ «#የተዘጉት_ዓይኖቻችን_ናቸው፡፡ እንዲያውም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነን» ባሉ ነበር፡፡»
  — አል-ሒጅር 15÷14-15


ሰደቀሏሁል ዐዚም...

https://www.tgoop.com/EAAAresponse
AEMerge1641706886795
Convert To Voice
📚 Sahih Al-Bukhari⁵⁷⁷ & Muslim¹⁸²

❍ በዚህ ላይ ለሚነሱ አንዳንድ ሹብሃዎች ማብራሪያ

➊▸ አላህﷻ በተለየ ገጽታ ይገለጣል ሲባል?
➋▸ ሁለቴ በመገለጡስ ያለው ጥበብ ምንድ ነው?
➌▸ በተለየ ገጽታ መገለጥስ መቀያየርን ያመላክታልን?


🔊 በወንድም ‘𝖒𝖆𝖍𝖉𝖎 مهدي’ 🪔
https://www.tgoop.com/A3E1response
Audio
አላህ ስለ ራሱ ሲናገር ለምን "እሱ" የሚለውን ተውላጠ ስም ተጠቀመ?
www.tgoop.com/religionandphylosophy
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
◉ በረመዳን ወር ልናውቃቸው የሚገቡን ነገራቶች🪔

➀, “የጾም ትሩፍቶች” ➟ (00:27)
➁, “ጾምን የሚያበላሹ” ➟ (01:53)
➂, “ልንሰራቸው የሚገቡ” ➟ (02:36)


🎤 ▹ ወንድም እስሚዝ
⌛️ ▹ 03:42 min
💾 ▹ 91.9 MB

───────────────
📎 https://www.tgoop.com/EAAAresponse

📎 https://vm.tiktok.com/ZMLHbX18X/
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳንም ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላምና በጤና አብሮ አደረሰን 🎉🎊

▹ በአዲስ ምዕራፍ ጀምረን
▹ ይቅር ተባብለን
▹ በዒባዳ ጸንተን
▹ የተከበረውንም ወር ሕያው ከሚያረጉ ባሮቹ አላህ ያርገን።

አሚን!

───────────────
📎 https://www.tgoop.com/EAAAresponse
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🍁 Soothing Qur'an Recitation [25÷71-75]


أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ 🥀🥀🥀
───────────────
📎 https://www.tgoop.com/EAAAresponse
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🍁 Soothing Qur'an Recitation [Surah Noah]


أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ 🥀🥀🥀
───────────────
📎 https://www.tgoop.com/EAAAresponse
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟻]


በመጀመርያ ደረጃ የሱረቱል በቀራ አንቀፆች ብዛት = [𝟐𝟖𝟔] መሆኑን ልብ እንበል!

➛ እነዚህን ሦስት ቁጥሮችም (𝟐..𝟖..𝟔) ብናስተነትናቸው ግርምት ወደሚያጭር ድምዳሜ ይጥሉናል...


⓵) የሦስቱን ቁጥሮች (𝟐..𝟖..𝟔) የመጨረሻዋን ቁጥር(𝟔) ለይተን ብንቀንሳት ሃያ ስምንት ይሆናል...

𝟐𝟖
= የመደኒያ (በመዲና የወረዱ) የቁርአን ምዕራፎች ብዛት ነው!


⓶) የሦስቱን ቁጥሮች (𝟐..𝟖..𝟔) የመጀመርያዋን ቁጥር (𝟐) ለይተን ብንቀንሳት ሰማንያ ስድስት ይሆናል...

𝟖𝟔 = የመኪያ (በመካ የወረዱ) የቁርአን ምዕራፎች ብዛት ነው!


⓷) ሁለቱንም አንድ ላይ ስንደምራቸው ደግሞ...

𝟐𝟖 + 𝟖𝟔 = 𝟏𝟏𝟒 (ጠቅላላ የቁርአን ሱራዎች ብዛት ይሰጠናል!)



الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ

አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርኣን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው፡፡
— ሁድ 11÷1 📖

ሰደቀሏሁል ዐዚም... ✍️

───────────────
📎 https://www.tgoop.com/EAAAresponse
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍁 Soothing Qur'an Recitation [19÷61-63]


أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ 🥀🥀🥀
───────────────
📎 https://www.tgoop.com/EAAAresponse
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟼]

በንብ አናቶሚ(Anatomy of Honey bee) መስክ ከ1,400 ዓመታት በፊት ሊታወቁ የማይችሉ አላህ ﷻ በቅዱስ ቃሉ ካስተዋወቀን እውነታቶች የተወሰኑትን ስናውሳ —


ወንዱን ንብ በተመለከተ ዘረመል ክሮሞዞሙ (chromosome) «𝟏𝟔» ሲሆን¹ አስደናቂው ነገር ሱረቱል ነሕል ቅድመ ተከተሉ በ «𝟏𝟔» ኛው የቁርአን ምዕራፍ ላይ እናገኘዋለን፣ በተጨማሪም “ንብ” ብሎ የተጠቀሰበት ብቸኛው ቦታ በ [۞ Qur'an 16÷68] ሲሆን አንቀፁ ላይ «وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى ٱلنَّحْلِ» “ንብ” እስከሚለው ድረስ ብንቆጥር ጠቅላላ «𝟏𝟔» ፊደላት ናቸው።
🌐 «Click here»


ሴቷንም ንብ በተመለከተም ከአበባዎችና መሰል እፅዋቶች በቀሰመችው ቅመም ማር የምታዘጋጀዋ እሷ ስትሆን² አላህ ﷻ ቀድሞ ይህን እውነታ ባማረ ሁኔታ ንብን በ [۞ Qur'an 16÷68-69] ላይ «ٱتَّخِذِى/ያዢ፤ كُلِى/ብይ፤ فَٱسْلُكِى/ግቢ» ብሎ በእንስታይ መደብ እያዘዛት ወደ ጾታዋ ጠቁሞናል!
🌐 «Click here»


➛ በመጨረሻም በቅርብ ጊዜ በሳይንሳዊ ምርምሮች መሰረት ንቦች ሁለት ሆድ (stomach) እንዳላቸው መረጋገጥ ተችሏል።³ እንኪያስ ቁርኣን እንደለመደበት ወደዚህም እውነታ እጥር ምጥን ባለች አንቀፅ ላይ «#ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ [۞ Qur'an 16÷69]» በማለት ከአንድ ሆድ በላይ እንዳላቸው ጠቁሞን ተአምራቱ ዘላቂነትን እንዳገኘ ነው!
🌐 «Click here»



ሰደቀሏሁል ዐዚም... ✍️

───────────────
📎 https://www.tgoop.com/EAAAresponse
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟽]


ቁርኣን ወደር የሌለው ቃላቶቹም በጥንካሬ የተሰካኩ ጥርት ያለ የአለማቱ ጌታ ቃል መሆኑ ምንም ጥርጥር የሌለበት ሲሆን፣ ያማረ ቅንብሩን ሳይለቅ ቃላቶቹ በምጥቀትና በልቀት ከመከወናቸው ባሻገር ሒሳባዊ ተዓምራትንም ጭምር ማየት የምን ጊዜም አስገራሚ ነገር ነው!
ለዛሬው ስለ አጭሯ የቁርኣን ምዕራፍ(ሱረቱል ከውሰር) ሒሳባዊ ተዓምሯን ስንመለከት...


➛ ሱረቱል ከውስር የቃላቶቿ ብዛት አሥር (10) ናቸው።
{إنا، أعطيناك، الكوثر، فصل، لربّك،...}

➛ የመጀመሪያው አንቀጽ አሥር (10) የተለያዩ ፊደላትን ያዋቀረ ነው።
{أ، ن، ع، ط، ي، ك، ل، و، ث، ر}

➛ ሁለተኛውም አንቀጽ አሥር (10) የተለያዩ ፊደላትን ያዋቀረ ነው።
{ف، ص، ل، ر، ب، ك، و، أ، ن، ح}

➛ ሦስተኛውም አንቀጽ አሥር (10) የተለያዩ ፊደላትን ያዋቀረ ነው።
{أ، ن، ش، ك، ه، و، ل، ب، ت، ر}

➛ ያለ መደጋገም አንዳንድ ጊዜ ብቻ የተጠቀሱት ፊደላት አሥር (10) ናቸው።
{ع، ط، ي، ث، ف، ص، ح، ش، ه، ت}

➛ ሶስቱም አንቀፆች በ “ራእ(ر)” ተጠናቀዋል፤ እሱም አስረኛው (10) የዐረብኛ ፊደል ነው።
{أ، ب، ت، ث، ج، ح، خ، د، ذ، ر}

➛ በመጨረሻም ሱረቱል ከውሰር በራሷ ከአሥር (10) ፊደላት የተዋቀረች ናት!
{س، و، ر، ة، ا، ل، ك، و، ث، ر}



۞ ይልቁንም «(ቁርኣንን) ቀጣጠፈው» ይላሉን፡- «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን ዐስር የተቀጣጠፉ ሱራዎች አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን (ረዳት) ጥሩ» በላቸው፡፡
— Qur'an 11÷13 📖


ሰደቀሏሁል ዐዚም... ✍️

───────────────
📎 https://www.tgoop.com/EAAAresponse
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟾]


በሥነ ምድር(Geoscience) ዙርያ ከብዙ ጥናቶች ቡኃላ በመሬታችን ገጽ ላይ በአየሩም ሆነ በውኃ መጠን ቋሚ የጉድለት ክስተቶች መታየታቸው በቅርቡ ሳይንስ ተቃኝቷል...ለምሳሌ —


➛ ባሕርን አስመልክቶ መርማሪዎች “ውቅያኖሶች ከመጀመሪያው የምድር ዘመናት አንጻር ዛሬ አንድ አራተኛ የሚሆን የውሃ መጠናቸውን አጥተዋል።” ይላሉ!
🌐 «Click here»

➛ በተጨማሪም ሳይንቲስቶች ከብዙ ጥናቶች ቡኃላ “በየዓመቱ 95,000 ቶን የሚሆን ሃይድሮጂን ጋዝ ከምድር ከባቢ አየር(Atmospher) ወደ ውጫዊው ጠፈር እንደሚቀነስ አረጋግጠዋል።”
🌐 «Click here»


🎯 አላህ ﷻ በፍጥረተ ዓለሙ አስተንትነው ለሚገሰጹ ሕዝቦች በቅዱስ ቃሉ ከ1,400 ዓመታት በፊት ወደዚህ የምድር ጉለት እንዲህ ሲል ጠቁሟል...

۞ «እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎላት ኾነን ስንመጣባት አያዩምን እነሱ አሸናፊዎች ናቸውን?» (Qur'an 21÷44)

۞  «እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ኾነን የምንመጣባት መኾናችንን አላዩምን...፡፡» (Qur'an 13÷41)


ሰደቀሏሁል ዐዚም... ✍️

───────────────
📎 https://www.tgoop.com/EAAAresponse
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟿]


በክፍል 𝟻 ላይ “የቁርአን ምዕራፎች ብዛት = 114” ከሱረቱል በቀራ ጋር የነበረውን ትይይዝ እና ሒሳባዊ ተዓምሩን አውሰናል... ዛሬም በአላህ ፈቃድ ወደ “ቁርአን አንቀፆች ብዛት = 𝟔𝟐𝟑𝟔” ዘወር ብለን ወደ ሌላ ግሩም ሒሳባዊ ተዓምር እንሻገራለን...


➛ “አል-ቁርኣን/ٱلۡقُرۡءَان” የሚለው ቃል ለመጀመርያ ጊዜ በሱረቱል በቀራ (2÷185) ላይ የተጠቀሰ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜም በሱረቱል ኢንሺቃቅ (84÷21) ላይ ተገልፇል...

እነዚያን ቁጥሮቹ ጎን ለጎን አርገን ስናቀናንሳቸውም

𝟐𝟏𝟖𝟓 - 𝟖𝟒𝟐𝟏 = 𝟔𝟐𝟑𝟔 ይመጣልናል!


➛ በተጨማሪም የቁርአን ረጅሟን ሱራ (ሱረቱል በቀራ) እና የቁርአን አጭሯን ሱራ (ሱረቱል ከውሰር) የምዕራፍ ቁጥራቸውን እና የቃላቶች ብዛታቸውን ስንደምር...

የሱረቱል በቀራ ምዕራፍ = 2
የሱረቱል በቀራ ቃላቶች = 6116
የሱረቱል ከውሰር ምዕራፍ = 108
የሱረቱል ከውሰር ቃላቶች = 10

𝟐 + 𝟔𝟏𝟏𝟔 + 𝟏0𝟖 + 𝟏0 = 𝟔𝟐𝟑𝟔 እናገኛለን!


۞  «አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርኣን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው፡፡» (📖 Qur'an 11÷1)


ሰደቀሏሁል ዐዚም... ✍️

───────────────
📎 https://www.tgoop.com/EAAAresponse
2025/03/28 09:32:02
Back to Top
HTML Embed Code: