Telegram Web
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ወንድም እህቶቼ  ዛሬ እስኪ  አንድ መንፈሳዊ ስራ እንስራ 🙏

በመጀመሪያ ይህ መንፈሳዊ ቻናል  እየጠቀሞት ነው

አዎ  ከሆነነ መልሱ  ወደ ፊትም ብዙ ነገር ይጠብቀናል   በእምነት የደከመውን ሰው ማጽናት፣ የተበተነውን መንጋ መሰብሰብ   ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን ማስፋፋት 
ታዲያ እርሶም አላፊነቶን  ይወጡ  ቢያንስ   1 ሰው  ብንጋብዝ  እግዚአብሔርን ቃል በዛኑ ልክ እናስፋፋለን    ታዲያ  ያ ነገር  ያቅተናል 
ስልካችን ላይስ ስንት ዓለማዊ ቻናል አለ   መንፈሳዊስ  

ወዳጆቼ  ከስጦታዎች  ሁሉ ስጦታ  የእግዚአብሔርን ቃል መጋበዝ  ነው    እርሶም   ይህን  ቻናልና  ተመሳሳይ የኦርቶዶክስ አስተምህሮ  የያዙትን ቻናሎችን  ይቀላቀሉ🙏

ብዙ ስራ ይጠብቀናል

ቻናሉን  ለመቀላቀል


☞︎︎︎ https://www.tgoop.com/eotcy
☞︎︎︎ https://www.tgoop.com/eotcy
☞︎︎︎ https://www.tgoop.com/eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለ2 ደቂቃ ቦታ ሰጥታችሁ አንብቡት

ከዕለታት አንድ ቀን ምድር የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰባት፤ መንቀጥቀጡ መሬት ላይ ያለውን ሁሉ ማነቃነቁ አይቀርምና ሁሉም ተናወጠ። በወቅቱ ከዛፍ ላይ አንድ የወፍ ጎጆ ነበረች፤
ይህች የወፍ ጎጆ በውስጧ እንቁላሎችን ይዛ ነበር። መሬቱ ሲንቀጠቀጥ ግን እንቁላሎቹን ይዛ ከነበረችው ጎጆ ውስጥ አንዱ እንቁላል ከዶሮዎች መንደር ወደቀ። ዶሮዎቹ እንቁላሉን እንደ እራሳቸው ተንከባክበውና ታቅፈው እንዲፈለፈል አደረጉ። ወፉ እንደ ዶሮ ዶሮዎቹ ጋር ተቀላቅሎ ማደግ ጀመረ። እነሱን መስሎ ዶሮነቱን አምኖ ኑሮውን መግፋቱን ቀጠለ። አንድ ቀን ከዶሮ ቤተሰቦቹ ጋር አንድ ላይ ሆነው በመሬት ሺንሸራሸሩ ወፎች በሰማይ ሲበሩ ተመለከቱ። ይሄኔ ወፉ, እኒህ በሰማይ በነፃነት የሚበሩት ወፎች ምንኛ የታደሉ ናቸው፤ ምናለ እኔም እንደነሱ መብረር ብችል "ሲል እራሱን እየተመለከተ ተናገረ። አብሮ አደጎቹ ዶሮዎች በወፉ ተሳለቁበት "አንተ እኮ ዶሮ ነህ እንደት እንደወፍ ለመብረር ታስባለህ ብለው ሃሳቡን አጣጣሉበት።
ወፉ ምንም እንኳን መብረር የሚችል ወፍ ቢሆንም እንደ ዶሮ ከዶሮ መሃል ስላደገ ዶሮ ነኝ ብሎ አምኗል። ማንነቱን ለውጦ አቅሙን አሳንሶ እራሱን ሳያውቅ ሌሎች ዶሮዎች በነገሩት ብቻ አለመብረሩን አምኖ ኖረ። ክንፎቹን ታቅፎ ሌሎች ወፎች ሲበሩ እየቀና እድሉን እያማረረ ኖሮ ሞተ።
መብረር ተፈጥሮው ሆኖ አልበርም ብሎ በማመኑ ብቻ ወፍ ሆኖ ተወልዶ ዶሮ ሆኖ ምድርን ተሰናበታት። የዚህ ወፍ ታሪክ የሁላችንም ታሪክ ነው። የምንመኘውን ነገር ለማድረግ ሁሉ ተሰጥቶን እያለ ሌሎች አይቻልም ስላሉን ብቻ አንችልም ብለን በማመን የፈለግነውን ኑሮ ሳንኖር እንሞታለን። እንደዛ ምስኪን ወፍ ከሌሎች መሃል ወድቀን ሌሎችን እንሆናለን። ማንነታችን ሌሎች እየነገሩን ራሳታችን ሳናውቅ እድሜያችን ይገፋል። አቅማችንን ሌሎች እየለኩት ችሎታችንን እና ተሰጥዖዋችንን ሳንጠቀምበት ህይወታችን ያልፋል። እስቲ እራሳችሁን ጠይቁት የወደቃችሁት ከማን መካከል ነው
ይቻላል ይሳካል ከሚሉት ወይስ አይቻልም አይሳካም ከሚሉት ወፍ መብረር እየቻለ ከዶሮ መሃል ስላደገ እና ዶሮ ነኝ ብሎ ስላሰበ መብረር ምንም እንኳን ቢመኝ ሳይበር ቀረ።
የብዙዎቻችን ሕይወት ከዚህ ብዙም አይለይም። ሁሉ ነገር እያለን ሌሎች ሲሞክሩት ስላላየን ብቻ የማይቻል መስሎን ምኞታችን ምኞት ብቻ ይሆንብናል።
ይህን ነገር አስታውስ በባነነበት ሰዓት የሮጠ ሁሉ አረፈደ አይባልም። ነቅተን ዙሪያችንን እንመልከት፤ የከበቡንን እናስተውል። በዙሪያችን ያሉት አይቻልም ስላሉ ብቻ አይቻልም ብለን እራሳችንን ወደ ኋላ አናስቀረው። ከዶሮ መሃል እንደ ወደቀ ወፍ አትሁን። አቅምህን ተጠቀምበት፤ ፍላጎትህን ኑረው፤ ምኞትህን እውን አድርገው፤ ራስህን መመልከት ከቻልክ አንተ ከምታስበው በላይ ታላቅ ሰው መሆንህን ትደርስበታለህ። ማህበረሰብ ፣ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ባወጣልህ መስፈርት እና መመዘኛ እራስህን አትመዝን፤ ይልቁንም እራስህን በራስህ ፈትነው። ብዙዎች እንደ ወፍ ተወልደው እንደዶሮ ሞተዋል። ያ ክፉ እድልእኛን እንዳይገጥመን ሁላችንም የወደቅንበትን እንመልከት.....ሌሎች መብረር ካልቻሉ አንተ መብረር አትችልም ማለት እኮ አይደለም።
#ኦርቶዶክሳዊ_ትምህርቶች

አስተማሪ ሁኖ ካገኙት Like Share አስተያየትዎ
💚 https://www.tgoop.com/eotcy 💚
💛 https://www.tgoop.com/eotcy 💛
https://www.tgoop.com/eotcy
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር!
አንዱ ድንግል ሌላዋ ድንግልና ባይኖራት ጋብቻው በምን ይፈጸማል

ተክሊልን በተመለከተ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል ከተጣማሪዎቹ /ከተጋቢዎቹ/ መካከል ሴቷ ወይም ወንዱ ድንግል ባይሆኑ ጋብቻ እንዴት ባለሥርዓት ነው የሚፈጸመው የሚለው አንዱ ነው።

ሥርዓተ ጋብቻ ለመፈጸም ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ ሦስት አይነት ጥንዶች አሉ። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱም ድንግልና የሌላቸው ሲሆኑ ሁለተኞቹ ደግሞ ሁለቱም ድንግልና ያላቸው ጥንዶች ይሆናሉ። የእነዚህ ከላይ ያነሳናቸው ሁለቱ ተጣማሪዎች የሚያስቸግር ነገር የለውም ድንግልና ለሌላቸውም በቅዱስ ቁርባን ያለ ተክሊል ድንግልና ላላቸውም የተክሊል ሥርዓት ይፈጸምላቸዋል። ለጥያቄ የሚያጋልጠው ከላይ የተነሳው ከሁለት አንዳቸው ድንግልና የሌላቸው ሁነው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለሥርዓተ ጋብቻ ሲመጡ ነው።

እዚህ ላይ መረዳት ያለብን አንድ መሠረታዊ ጉዳይ አለ። እርሱም ተጋቢዎች የአንድነታቸው ምስጢር ማኅተሙ ሥጋ ወደሙ እንጂ ተክሊሉ አይደለም።  ተክሊሉ አላማው ሽልማትና እውቅና መስጠት ነው። ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን እስከ ጋብቻ ድረስ በንጽሕና በድንግልና ለጸኑት ልጆቿ የምትሰጠው የሰማያዊ አክሊል አምሳል የሆነ ሽልማት ነው ተክሊል። አንዳንድ ሰዎች ተክሊል በተጋቢዎች መካከል አንድነት የሚያመጣ እርሱ ነው ብለው ያስባሉ ይህ ግን ስህተት ነው። በተጋቢዎች መካከል የአንድነት ፀጋ የሚያሰጠው ተክሊል ከሆነ ያለ ተክሊል ጋብቻቸውን በመአስባን የሚፈጽሙ ክርስቲያኖች አንድነት ጸጋ አያገኙም እያልን ነው በተጋቢዎች መካከል የአንድነት ጸጋ የሚያሰጠው ሥጋ ወደሙ ነው።

ሰለዚህ ተጋቢዎች መካከል በድንግልና ልዩነት ቢኖር ድንግልና ላለው አካል ተክሊል ሥርዓቱ ይፈጸምለታል። የድንግልና ሽልማቱን ያገኛል። ድንግልና የሌለው አካልም ለደናግላን የሚፈጸመው ሥርዓት አይመለከተውም። ምክንያቱም የወጣትነትን ክፉ ፈተና ተቋቁሞ ድንግልናውን ጠብቆ እስከ ጋብቻ መዝለቅ አልቻለምና ። ተክሊል አይፈጸምለትም /ለሴት ከሆነ አይፈጸምላትም/ ። ተክሊል የሚደረግለት ድንግልናውን ለጠበቀ ድንግልናዋን ለጠበቀች ብቻ ነው። ፍትሃ ነገሥት ላይ ይሄንን በተመለከተ እንዲህ ይላል ፦ " የሚያገቡ ፈቶች ቢሆኑ ተክሊል አያድርጉላቸው። ይህ ተክሊል በጋብቻ ጊዜ ለድንግል ወንድና ለድንግል ሴት ይገባቸዋልና። ከሚያገቡት አንዱ ድንግል ቢሆን ብቻውን ይባረክ።" 24:906

ይህ በግልጽ የተቀመጠ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ነው። ነገር ግን ተክሊል የሚፈጽመው አካል ራሱን ዝቅ በማድረግ ያለ ተክሊል ሥርዓተ ጋብቻውን መፈጸም ይችላል። ለምሳሌ ቄስ የዲያቆንን ቦታው ሸፍኖ መቀደስ ይችላል ዲያቆን ግን ቀና ብሎ እንደ ቄስ በመሆን ልቀድ ማለት እንደ ማይችል ሁሉ ድንግልና የሌለው አካል ልመሳሰል ብሎ ተክሊል ልፈጽም ማለት ትዕቢት ነው። ቄሱ የዲያቆንን ቦታው ሸፍኖ መቀደስ እንደሚችል ሁሉ ድንግልና ያለው አካልም ዝቅ ልበል ካለ ያለ ተክሊል መፈጸም ይችላል።

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤
የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል



በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ ... የተራ ቀለማት መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም
❗️

የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ስለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡

እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር? እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ! ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ!

ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤
የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል? ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳልሆንሁ በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ መናገር ያምረኛል፡፡...


ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን ከንፈሮች በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት❗️ ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች።

          ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ


𝚓𝚘𝚒𝚗 👉  https://www.tgoop.com/eotcy
እናቶቻችን አሃዱ ሳይባል ውስጥ ለመግባት ነው  የሚሮጡት
እኛሳ ወደዬት ይሆን የምንሮጠው ፡፡

ልሩጥ አይደክመኝም!
©ታደለ ሲሳይ
==============
ጉልበቴ ቢደክም፣ ቢዝል ሰውነቴ
የነፍሴ ብርታቷ፣ ናት እና እመቤቴ
ልሩጥ ወደ ቤቷ፣ ትቀደስ ሕይወቴ።
....................
ልሩጥ አይደክመኝም፣ ልሂድ ስሟን ልጥራ
የጨለመው ልቤ፣ በእመቤቴ ይብራ።
......................
ነፍሴ ብትቆሽሽ፣ ቢከስም ምግባሬ
አኑሮኛልና፣ ከዱሮ እስከዛሬ
ከእናቱ ጋራ ነው፣ ውሎዬና አዳሬ።
..................
ልሩጥ አይደክመኝም፣ ልጓዝ ወደ ቤቱ
ነፍሴን ያድሳታል፣ ቅዳሴ ማእጠንቱ።
.................
ቢዘል ከንቱ ጉልበት፣ ቢደክም ተፈጥሮ
ያፈረ ሰው የለም፣ ከእርሷ ጋራ ኖሮ።
......................
ሞት መጥቶ ሳይቀድመኝ፣ ሥጋ ሳይሆን አፈር
ነፍሴ ከሥጋዬ፣ በዕድሜ ሳትባረር
ልሩጥ አይደክመኝም፣ ልሂድ ወደ እግዚአብሔር።
...................
ሞት መጥቶ ሳይቀድመን፣ ሳንሆን ሬሳ
ኑ አብረን እንሩጥ፣ አብረን እንነሳ።😍🙏


https://www.tgoop.com/eotcy
እውነተኛ ደቀ መዝሙር መሆን የጀመርኩት አሁን ነው

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቅዱስ አግናጢዮስ ወደ ሞት እየተወሰደ ወደ ሮም የተላከ ጥቅልል ( ደብዳቤ )

      በሰውነቴም በልቤም ሀይል እንዳገኝ ጸልዩልኝ በእርግጥ ክርስቲያን ሆኜ ለመገኘት እንጂ በስም ብቻ ክርስቲያን መባል አይበቃኝምና በአፍ ብቻ ሳይሆን በእውነት ፈቃደኛ መሆን ያስፈልገኛል እውነተኛ ክርስትና ብርቱ በመሆን የሚገለጥ ነው እንጂ በዝምታ አይደለም ።

    እናንተ ካልከለከላችሁኝ ለአምላኬ ለመሞት መሆኔን በሰው ሁሉ ፊት እመሰክራለሁ ስለዚህ አላግባብ እንዳታስቡልኝ እለምናችኋለሁ ወደ እግዚአብሔር እንድደርስ የአራዊት ጉርሻ ብሆንም እንኳ የእግዚአብሔር የስንዴ ቅንጣት ነኝ የአራዊትም ጥርሶች ቢፈጩኝ ለኢየሱስ ክርስቶስ ንፁህ እንጀራ እሆናለሁ ።

  ካንቀላፋሁ በኋላ ለማንም ሰው ሸክም እንዳልሆን ሰውነቴ በሙሉ ይለቅ አራዊት መቃብሬ እንዲሆኑ ይምጡብኝ እንዲይዙኝም እናንተ አነሳሷቸው በመሞቴ በክርስቶስ ነጻነት አገኛለሁ ስለዚህ አንዳች ምድራዊና አላፊ ነገር መመኘት እንደማያስፈልገኝ ተረድቻለሁ ።

     ገና በመንገድ ላይ ሳለሁ በባህር በየብስም ሌትና ቀን አሁንም ከአራዊት ጋር እየታገልኩ ነኝ የአስር ነብሮች ቁራኛ ነኝ ማለት ከወታደሮች ጋር ነው ያለሁት እነርሱም መልካም ነገር ቢያደርጉላቸው የባሰውን ክፋት የሚያሳዩ ናቸው ይሁንና በእነርሱ ማጉላላት ልምምድ አገኛለሁ በዚህ ግን እጸድቃለሁ ማለቴ አይደለም ።

    እውነተኛ ደቀ መዝሙር መሆን የጀመርኩት አሁን ነው የሚታይም ሆነ የማይታይም ማንም ሰው በምቀኝነት ዓይን አይመልከተኝ ልድረስ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እሳት መስቀል የአውሬ ብዛት መጨፍጨፍ የአጥንቶቼ መበታተን የብልቶቼ መሰባበር የሰውነቴ መጨፍጨፍ ሁሉ የሰይጣን ስቃይ ይምጣብኝ ብቻ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ልድረስ ።

   የቅዱስ አግናጢዎስ በረከቱ ይደርብን አሜን
https://www.tgoop.com/eotcy
በጣም አስተማሪ  ታሪክ🙏

ይነበብ ‼️

አንድ ሰው በበረሃ እየተጓዘ እያለ የያዘው ውሃ አልቆበት በውሃ ጥም ይያዛል ቀስ በቀስ ውሃ ጥሙ ሰውዬውን እያደከመው ይመጣል በስተመጨረሻ ከአንድ የውሃ ጉርጓድ ጋር ይደርሳል ጉርጓዱ በጣም ጥልቅ ነበረ ውሃ ይኑረው አይኑረው አይታይም፡፡
ከዚያም ከጉርጓዱ ጎን አንድ አሮጌ የውሃ መሳቢያ ሞተር አለ ሞተሩ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል፡፡ ‹‹ይህ የውሃ መሳቢያ ሞተር የሚሰራው በውሃ ነው›› ይላል፡፡
ከሞተሩ ጎን አንድ ጆግ ሙሉ ውሃ ተቀምጧል ጆጉ ላይ እንዲሁ አንድ ጽሁፍ ሰፍሯል ‹‹ወዳጄ ሆይ ይህንን ጆግ ውሃ ሞተሩ ውስጥ ጨምረው ሞተሩ ብዙ ውሃ ያወጣልሃል ታዲያ አደራ አንተም እንዳንተ ላለ ሌላ መንገደኛ ይጠቅማልና ውሃው ከጉርጓዱ ሲወጣልህ ጆጉን ሞልተህ ማስቀመጥን አትርሳ›› ይላል፡፡
በጆግ ያለውን ውሃ ሞተሩ ውስጥ ልጨምረው ወይስ ልጠጣው እዚጋር ሰውዬው በሁለት ሃሳብ ተወጠረ ‹‹አንደኛ ይህ ሞተር አርጅቷል ጨምሬው ባይሰራ ይህንንም ውሃ አጣሁ ማለት ነው ሞትኩ ማለት ነው☹️ ስለዚህ ልጠጣውና ህይወቴን ላድን ፡ ደሞ ማሳሰቢያውስ ውሃው ያለሞተር አይሰራም እንደኔ ውሃ የተጠማ ሰው ቢመጣ ይህንን ማንቀሳቀሻ ከጠጣሁት ይሞታሉ›› 😭😭ብሎ ለራሱም ለሌሎቹም አሰበና በሃሳብ ተወጠረ በስተመጨረሻ በብዙ ጭንቀት ተወጥሮ ትልቅ ውሳኔ ወሰነ እንዲህ አለ ወደሞተሩ ብጨምረው ይሻላል ከሰራ ጥሩ ካልሰራ ግን እሞታለሁ እንጂ በፍፁም ‹‹ውሃውን ይህንን ጆግ ውሃ ጠጥቼ ሄጄ ዘለዓለሜን ስለዚህ ጉርጓድና ይህንን ውሃ አተው ስለሚሞቱ ሰዎች እያብኩ መኖር አልፈልግም›› አለ፡፡
ከዚያም የጆጉን ውሃ ወደ አሮጌው ሞተር ውስጥ ጨመረውና የሞተሩን ማስነሻ ተጫነው፡፡ ሞተሩም ድምፅ እያሰማ ውሃ የማውጣት ስራውን ጀመረ፡፡ ሰውዬው ተደነቀ🤭 የሚፈልገውን ያህል ጠጣ አካባቢው በሙሉ በውሃ እራሰ ከጠበቀው በላይ አካባቢው ሁሉ ውሃ በውሃ ሆነ😃 ከዚያም በተባለው መሰረት እሱም ጆጉን በውሃ ከሞላው ቦሃላ ጆጉ ላይ ፅሁፍ ጨመረበት ‹‹እመኑኝ በትክክል #ይሰራል›› አለ፡፡

🟢🟡🔴
እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ለራስ ማሰብ በህይወት መኖር ነው ለሌላው ማሰብ ግን ሰው መሆን ነው‼️ያለህን ሳትሰስት ከሰጠህ በእጥፍ ድርቡ ፈጣሪ ይሰጥሃል፡፡ ሰውዬው ጆግ ውሃ ሰቶ አካባቢን የሚያርስ ውሃ እንደተቸረው አንተም የምትሰጣት ጠብታ  ከልብህ ከሆነ በእጥፉ ይሰጥሃል፡
ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲ ይለናል 

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል። 1ኛ ቆሮንቶስ 13÷1-8

  መስጠትን ብቻ ሳይሆን አሰጣጥህ ወሳኝነት አለው፡፡ አንዳንዴ ከመንጠቅ የማይተናነስ መስጠትም አለ‼️

ምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በፍቅር ይሁን

መልካም ቀን

꧁  ይ🀄🀄ሉ ꧂

https://www.tgoop.com/eotcy
ውድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የቴሌግራም ቻናል ተከታዮቻችን እንደምን ቆያችሁ በፍልሰታ ጾም ምክንያት ተቋርጦ የነበረው አገልግሎታችን ከዛሬ ጀምሮ ባማረና ከበፊቱ በሰፋ ወደ አገልግሎቱ ተመልሷል እርሶም ለወዳጆ በማጋራት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን ያስፋፉ

https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
እግዚአብሔር ዝም ይላል

👉አልአዛር ሲታመም ዝም
👉ሲሞት ዝም
👉 ሲቀበር ዝም
👉ከተቀበረ ሦስት ቀን ሆነው ዝም በአራተኛው ቀን መጣ ከሞት አሰነሳው።
✍️ መፃጉዕ 38 ዓመት ያልጋ ቁራኛ ሆነ ዝም ሰው የለኝም እያለ ጮኸ አሁንም ዝም ግን ሰዓቱ ሲደርስ እራሱ የማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሸከመችውን አልጋውን አሸከመው። እረስቶናል ብለን ተስፈ ስንቆርጥ በሰው ያለን ተስፋ ሲሟጠጥ እግዚአብሔር በዝምታ ይመጣል እግዚአብሔር ለነብዬ ኤልያስ በምን አይነት ሁኔታ እንደተገለጸለት እናስታውስ 4 ነገሮች ተከስተው ነበር. ።
(1ነገ 19÷11)
1.ትልቅና ብርቱ ነፍስ ተራሮችን ሰነጠቀ አለቶችንም ሰበረ
2.የምድር መናወጥ ሆነ
3.እሳትም ሆነ በእነዚህ በሶስቱ ውስጥ እግዚአብሔር አልነበረም አራተኛው ትንሽ የዝምታ ድምጽ ሆነ በዚህ በዝምታ ድምጽ ውስጥ እርሱ እግዚአብሔር ነበር እግዚአብሔር ዝም ብሎ ይመጣል በእርሱ ብቻ መደገፋችን እርግጠኛ ሲሆን ይመጣል ቢዘገይም የሚቀድመው የለምና ከዓይን ጥቅሻ ፈጥኖ ይመጣል እርሱም አይዋሽም ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሡ እርሱ አይዘገይም።
(ትንቢተ ዕንባቆም 2:3፤)
✍️እግዚአብሔር ዝም ብሎ የሚያክም ሐኪም ነው።
✍️እግዚአብሔር ዝም ብሎ የሚፈውስ ባለ መድኃኒት ነው።
✍️ሰው በንግግር ያደክማል እግዚአብሔር ግን በዝምታ ያክማል።
✍️ ለሁሉም ጊዜ አለው እግዚአብሔር የሚናገርበት ጊዜ አለው።
✍️ ደግሞም እግዚአብሔር ዝም ብሎ ሰው የሚናገርበት ጊዜም አለ የበረሃው ኮከብ ቅዱስ እንጦንስ "እኔ ስናገር እግዚአብሔር ዝም ይላል እግዚአብሔር ሲናገር ደግሞ እኔ ዝም እላለሁኝ "እንዳለ በተደነቀ ዝምታ የምትኖር አስታዋሸ እግዚአብሔር ሆይ እናመሰግንሃለን።
✍️አንተ በዝምታ ውስጥ መልስ አለህና እናከብርሃለን።
✍️እንደማይሰማ ዝም ብትልም እንደማይሰጥ ብትዘገይም እንደማይገደው ብታልፍም ዓላማ አለህና ተመስገን።
✍️ የቀኑን ምልክት በማየት አለባበሴን ባስተካክልም የዘመኑ ምልክት ግን ሳይገባን በአንደበታችን  በከንቱ ሸንግለንሃልና ይቅር በለን።
✍️ ዓለም ስትንጫጫ ዝም ማለትን አስተምረን እንደ ኃጢአታችን ሳይሆን እንደ  ቸርነትህ ማርን።
✍️የሰው ልጅ በሰው ልጅ የሚያደርገውን መጨካከን ከኢትዮጵያ ሀገራችን አስወግድልን።
✍️የድሆችን እንባ የሚያብስ ጠፍቷልና እግዚአብሔር  አንተ በቸርነትህ ይቅር ብለህ ከመከራ ፣ከሰቆቃ ታደገን ከአንተ ውጭ የሚታደገን ማንም የለንምና።
👉አባ ኒሉስ የተባሉ አባት የዝምትን ጥቅም ሲያስረዱ፦ ጸጥታን የሚወድ ሰው የጠላት ቀስት ሊነካው አይችልም።
👉 ነገር ግን ወደ ጭንቅንቅ የሚጓዝ ኹል ጊዜ ይቆስላል።"
👉  ጸጥታን በማፍቀር የጠላትን ቀስት ማምለጥ እንደሚቻል የሚያስረዱን።
👉ዲያብሎስን በዝምታ ማራቅና ማሰር እንችላለን በንግግር ግን ሊያቆስለንና በሞትና በሕይወት መካከል አድርጎን ሊሔድ ይችላል። 👉ዝምታ ጠላትን የማራቅና ወጥመዱን የማፍረስ ኃይል አለው።
👉ከዚህ በተጨማሪ  ጳጳሱ አንጄሎስ "አንዳንዴ ዝምታ ስለኾነ ጉዳይ ለመናገር ያለን እጥረት የሚያመለክት አይደለም።
👉ነገር ግን እግዚአብሔር ትክክለኛውን የመልስ ዕድል እስኪሰጥ የሚደረግ ብልሀት ያለበት ማቋረጥ ነው እንጂ።" በማለት ዝምታ ያለውን ጥቅም ያስረዱናል።
👉በዚህ አባት ትምህርት መሠረት ማንም ሰው ስለኾነ ጉዳይ በማወቁ ምክንያት ብቻ መናገር የለበትም።
👉በእርግጥ የእርሱ አለመናገር ለጥቅም እንጂ ለሌላ አይደለም።
👉 እኛ ብዙ ጊዜ የሚቸግረን ስሜታችንን ተቆጣጥረን፤ ውስጣችንን መርምረን፤ በመናገራችን መጠቀም አለመጠቀማችንን በደንብ አለመፈተሻችን ነው።
👉 በመናገራችን ብቻ የምናስበው ነገር የሚሳካ ስለሚመስለን፤ ከመጠን አብዝተንና ቸኩለን ተናግረን ጉዳትን ራሳችን ላይ እናመጣለን።
👉ይህ ጉዳት ምናልባት ለጊዜው ላይታየን ይችላል፤ ቀስ እያልን ስንሔድ ግን ልንረዳው እንችላለን።
👉ከዚህ ኹሉ በላይ ደግሞ ዝምታን ሽንፈት አድርገን ማሰባችን በራሱ ትልቅ ችግር ነው።
👉ወዳጄ ሆይ! ዝምታ ጩኽት የሌለው ነው ብለህ ካሰብክ ተሳስተሀል።
👉ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ዝምታን እንዲህ ይገልጹታልና፦” (ዝምታ ጮኽ ያለ ለቅሶ ነው።
👉እንግዲህ ወንድሜ በዝምታ ውስጥ ያለው ጩኽት ታላቅ መኾኑን በመረዳት ተለማመደው። 👉የዝምታ ጩኽት እስከሰማይ የመድረስ ኃይል ያለው ብርቱ ነው።
👉 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው ለምን ትጮኽብኛለህ? ዘጸ 14፥15 በማለት ሙሴ በዝምታ የጮኽው ጩኽት በእግዚአብሔር ዘንድ መሰማቱን መጽሐፍ ያስረዳናል።
👉 በመናገር ከምንፈጽመው ይልቅ በዝምታ የምንፈጽመው ጩኽት በእግዚአብሔር ዘንድ የበለጠ ተወዳጅነት አለው።
👉ዝምታ ወዴት እንደምትመራ ብናውቅ ኖሮ የምንወዳጃት ይመስለኛል።
👉ዝምታ ወደ በጎ ምግባር የምትመራ ከኹሉም ፈጣኗ መንገድ ናት።
👉በዝምታ የሚሳፈሩ ሰዎች የቅድስናን ተራራ ፈጥነው ይወጡታል።
👉 ዝምታ ወደቅድስና ለመግባትም በር ከፋች ናት።
👉የዚህችን ታላቅ መሣርያ ኃይል ባለመረዳታችን ምክንያት ቀኑን በሙሉ የማይጠቅሙንን ነገሮች ስንናገር እንውላለን።
👉ልበ አምላክ የተባለው ቅዱስ ዳዊት ስንኳ "በአንደበቴ እንዳልስት አፌን እጠብቃለሁ አልሁ፥ ለበጎ እንኳ ዝም አልሁ፣ እንደማይሰማ ደንቆሮና በአፉ መናገር እንደማይችል ድዳ ኾንኹ።" በማለት ይናገራል ።
      መዝ 38፥1-2።
👉 እንግዲያውስ አሳክቶ መናገር የሚችለው ቅዱስ ዳዊት በአንደበቴ እንዳልስት ብሎ ከመናገር ራሱን ከከለከለ።
👉 ከኃጢአት በቀር የማንናገር እኛማ እንዴት የበለጠ ዝም ልንል እንዲገባን መገንዘብ አለብን።

💠 @eotcy
በምጸልይበት ጊዜ ሐሳቤ አይሰበሰብም
እንዲህ ከሆነ መጸለይ ቢቀርብኝስ
       አጭር አስተማሪ ታሪክ ነው አንብቡት
https://www.tgoop.com/eotcy
   
☞︎︎︎ ልቡናውን ሰብስቦ መጸለይ ያቃተው አንድ ደቀ መዝሙር አረጋዊውን አባት እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል፡- “አባቴ የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ስጸልይ ልቡናዬ አይሰበሰብልኝም፤ አፌ ቢያነበውም ልቡናዬ ግን ይበታተናል፡፡ እኔ ደግሞ ዝም ብዬ ሳስበው፦ ቅዱሳን በፍጹም ሐሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የጻፉትን እኔ በልቤ ሌላ እያሰብኩ በአፌ ብቻ ባነበንበው እንደ ገደል ማሚቶ ፊደሉ አፌ ላይ  እየነጠረ ይሄዳል እንጅ ጸሎትም አይሆንልኝም ፡፡

☞︎︎︎ ስለዚህ አባቴ የአፍ ብቻ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል?" ብሎ ጠየቃቸው። አረጋዊው አባትም እንዲህ ሲሉ አስረዱት፡-

☞︎︎︎ “አየህ ልጄ ዐይነ ስውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው የበትሩን ድምጽ ሰምቶ ይመታኛል ብሎ ይሸሻል እንጅ ዐይነ ስውር ነው አላየኝም ብሎ ባለበት አይጠብቀውም። ስለዚህ አንተም አስተውለህ ብትጸልይ መልካም ቢሆንም ለጊዜው ግን ጭራሽ ከምታቆመው  በአፍህ ውስጥ ያለው የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት የሚሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና መቼም ቢሆን ጸሎትህን አትተው፡፡ አጋንንትንም ማባረር አንድ ታላቅ ጥቅም ነውና፡፡ ብዙ ከመጸለይህም አንጻር አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር ታደርስሃለች።

☞︎︎︎ እናም ልጄ ልብህ ምንም ዝርው ቢሆንም አፍህም የልዑል እግዚአብሔር ፍጥረትነውናይህንንምእንዳታቆመው። አሁን አንዱን ይዘህ ወደፊት ደግሞ ሁለቱንም ለማገናኘት መጣር ይኖርብሃል እንጅ አንተው በዳይ አንተው አኵራፊ ሆነህ ጭራሽ ከአምላክ ርቀህ የጠላት ሰይጣን መጫወቻ እንዳትሆን በማለት መለሰለት:: ስለዚህ እኛም በምጸልይበት ጊዜ ልቤ አይሰበሰብም  እንዲህ ከሆነ መጸለይ ቢቀርብኝስ ብላቹሁ እንዳታቆሙ እህት ወንድሞቼ

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

https://www.tgoop.com/eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ዓይነ ሥውር በእጁ ደማቅ ብርሃን ያለው ፋኖስ ይዞ በጨለማ በመንደር ውስጥ እየሔደ ነው:: አንድ ሰው ድንገት ሲያልፍ አየውና ፋኖሱን ሲያይ ተገርሞ ጠየቀው::

"ይቅርታ ወንድሜ:: በእጅህ ፋኖስ አብርተህ ይዘሃል:: እንዳትደናቀፍ ነው እንዳልል እንደማይህ ዓይነ ሥውር ነህ:: የማታይ ከሆነ የፋኖሱ ብርሃን ምን ይጠቅምሃል?" አለው::
"ልክ ነህ የፋኖሱን ብርሃን አላይም:: የምይዘው እኔ በጨለማ ውስጥ ስሔድ እንዳልደናቀፍ አይደለም:: ሆኖም በጨለማ ውስጥ ብርሃን ሳልይዝ ከሔድኩ ሰዎች እኔን ስለማያዩኝ ከእኔ ጋር እንዳይጋጩ ወይንም እንዳይደናቀፉ ነው:: ፋኖሴንን ከያዝሁ በብርሃኑ እኔን ያዩኛል" ብሎ መለሰለት::

ወዳጄ በዚህች ጨለማ ዓለም ስትሔድ የልብህ ዓይን በመታወሩ ምክንያት የማታያቸው ብዙ እንቅፋቶች አሉ:: "ኸረ እኔ ዕውር አይደለሁም" ካልክ "ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም፡ የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ" ነው:: (ራእ 3:17)

#በጨለማው_ዓለም_ስትሔድ_ለራስህ_ብቻ_ሳይሆን_ለሌሎችም_ማሰብ_ትገደዳለህ:: እውነተኛውን ፋና #ክርስቶስን በጉያህ ከያዝክ ሰዎች እሱን አይተው በአንተ ከመሰናከል ይድናሉ:: አለዚያ ግን በአንተ ምክንያት የሚደናቀፈው ሰው ብዙ ነው::
.......እነሆ የተወደደችው ሰዓት አሁን ነው፥ የመዳን ቀን አሁን ነው
--1ኛ ቆሮ 6፥2

🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/02/15 22:39:36
Back to Top
HTML Embed Code: