ምስል#
ትዝታ ደስታ አለው... ሲቀጥልም እንባ.. የቀደመን ከአሁን ይልቅ እንድንመርጥ ያስገድደናል።
የአመታቶች ፍጥነት በዱንያ ሂወታችን የራሱን አሻራ እያኖረ ሲያልፍ ሊያስቆመው የሚደፍር አንድም ፍጥረት የለም፤ ይህ የፈጣሪው እንጂ የተፈጣሪው ጉዳይ አይደለምና!
ከልጅነት... ወጣትነት... ወደጉልማሳነት... ለእርጅናዬ መንደርደሪያ ነበሩ፤ ትላንት ለዛሬ ቦታዉን እንደሚለቅ ሁሉ የኔም እድሜ ከዛ እርክብክቦሽ የተረከብኩት ነው፤ ዱንያ ላይ ባገኘነው ልክ የምናጣውም ብዙ ነገር አለ ወይስ ያጣነው ከአገኘነው የሚበልጥ ስለሚመስለን ነው?
ያኔ በብዙ በረሃ አቋርጭ ከተውኳት የበፊት ከተማዬ... በብዙ እውቀት ላጠመድኩት አይምሮዬ... ከትላንት እኔነቴ ጋ የቀበርኳት ልቤ... በደቂቃት ውስጥ ወደ ጥንት መለሰችኝ።
በድንገት ከእጆቼ መሃል የተገኘችው አንዲት አበባ ነብሴን ወደ መጣችበት መለሰችብኝ... እንደው ነገረ አለሙ ሁሉ የሚገርም አይደል? ከጊዜያት ኋላ እቺም ከትዝታ መዝገብ ልትሰፈርም ነውሳ አጀብ!!
ዛሬ ለተገኘንበት መዳረሻ የትላንት መነሻ ስለመኖሩ አይዘንጋን!

ፈገግታ
ወጣቱ በአንዲት አሮጊት ጥቆማ ያገኛትን ልጃገረድ ሽማግሌ ይልክላትና በቀናት ውስጥ ትዳር ይመሰርታሉ።
በሳምንቱ የጠቆመችውን አሮጊት ክስ መሥርቶባት የመንደሩ ቃዲ ጋር ያቆማታል።
•ዳኛ ሆይ ያገባኋት ልጅ አንካሳ እንደሆነች ያወቅሁት ጋብቻውን ከፈጸምኩኝ በኋላ ነው - ይህች ሴትዬም ስለ አንካሳነቷ ምንም አልነገረችኝም•
ዳኛው ፊቱን ወደ አሮጊቱ አዞረ - ሴትዪዋ መልስ ሰጡ
•ቃዲ ሆይ ስሙኝ አሏህ ይባርክዎትና
እኔኮ የሚገናኛትን ሚስቱን እንጂ ለሓጅ የሚጋልባትን አህያ አላስተዋወቅሁትም•
😊 የቃዲው ፈገግታ.....
መልካም ቀን😁

ስንፍና ባንተ አያምርም!
ወጣት ሆነህ ካልተለወጥክ መቼ ልትለወጥ ነው?አቅም ባለህ ሰዓት ካልሰራህ መቼ ልትሰራ ነው? ካልዘራህ እኮ አታጭድም፤ ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ይሄን ወርቃማ ዕድሜዬን ተዓምር እሰራበታለው በል!
ከ 10 ዓመትም በኋላ ከሰው መጠበቅ ነው የምትፈልገው? ከራስህ አልፈህ የምትወዳቸውን ሰዎች መቀየር አትፈልግም? እርግጠኛ ነኝ ትፈልጋለህ! ስለዚህ ተነስ! የምትችለውን ሁሉ አድርግ! ቁጭ አትበል! የማይጠቅምህን ፕሮግራም አትይ! ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም ንቃ ወዳጄ! ስንፍና ባንተ አያምርም!

'ጥረት ማድረግ'
.
ጥረት ማድረግ ወደ ስኬት ከሚመራን መንገድ ዋና ቁልፍ ነው፡፡ ጥረት መሀይሙን ያስተማረ፤ ድሃውን ያከበረ፤ ደካማውን ያጠነከረ፤ የተበላሸውን ያስተካከለ፤ የደፈረሰውን ያጠለለ፤ የተጣላውን ያስታረቀ፤ ጦርነትን ወደሰላም የቀየረ፤ የተበተነውን የሰበሰበ፤ የተቆረጠውን የቀጠለ፤ በመሆኑ በሁሉም ነገር ላይ የጥረትን አስፈላጊነት እንዲህ በማለት አላህ በቁርኣን ውስጥ ይናገራል፡
وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَمَعَ الْمُحْسِنِينَ
"እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡"
*አንከቡት-69*
በሌላ አንቀፅ ደግሞ እንዲህ ይለናል።
فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ
"የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡"
*አዝ_ዘልዘላህ-7*
የጣረበትን ውጤት የማያገኝ ሰው የለም። ጥረት የስኬት ብቸኛው መንገድ፣ የፈጣሪ ትዕዛዝ፤ የሰባአዊነት መገለጫ፤ የነብያቶች ሱና የኢማን አካል፤ በሆኑ ስለጥረት የአላህ መልዕከተኛﷺ - እንዲህ ይላል:
★ለሰው ሁሉ በላጩ እድሜው የረዘና ስራው ያማረ ነው (ቲርሚዚ)
★ኃያሉ አላህ - «ባሮቼ ሆይ ይህ ስራችሁ (ጥረታችሁ) ነው ከኔ ጋር እርሱኑ አስቀምጥላችኋለሁ መልካም ነገር ያገኘ አላህን ያመስግን ከዚህ ውጭ የገጠመው ደግሞ እራሱን እንጂ ማንንም መውቀስ የለበትም አለ። (ሙስሊም)
መልዕክተኛ ﷺ «በሚጠቅምህ ነገረ ላይ ትጉ ሁን። በአላህ መታገዝን ፈልግ፡ ደካማ አትሁን፡ አንዳች ነገር ቢደረስብህ እንዲህ አድርጌው በነበር እንዲህ ይሆን ነበር አትበል ነገር ግን አላህ ወሰነው የሻውም ተከሰተ በል ‹ነበር› (የሚለው) የሸይጧንን መንገድ ይከፍታል» (ሙስሊም)
ታላቁ ሰው አስ-ሰቃፍ ስለ ጥረት ታላቅነት ሲነግረን እንዲህ ይላል።
"ሁሉም ባለውና ባገኘው ነገር ቢረካ ኖሮ ጀግና የሚባል ነገር አይኖርም ነበር።"
ሁሌም ስኬታማ የመሆን ሚስጥሩ ሁሌም ወደ ፊት መሄድ ነው።" (ኢምሳሉል-አርብ)

«ጠንካራ ሁኚ !
ሀብታም ብታገቢ በሱ አለፈላት ላትባዪ ፣ ድሃ ብታገቢ አብረሺው ከፍ ለማለት ብርቱና ጠንካራ ሁኚ ። ገንዘብ መሰብሰብ የወንድ ብቻ ሳይሆን የሴትም ነው ። ግብሽ ትዳር ብቻ አይሁን ። ትዳሬን እንዴት አቀናዋለው በይ ! አይበለውና ባልሽ ልጆችሽን በትኖብሽ አኸራ ቢሄድ የልጆችሽ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል ? ሁሉን ማድረግ በምትችዪበት ወቅት ሁለንተናዊትን ተላበሺ ። በስራ ፣ በቤተሰብ አስተዳደር ፣ በት/ት ፣ በሸሪዓዊ ዒልም ፣ በማህበራዊ ግንኙነት ብቻ በሁሉም ጠንካራ ሴት ሁኚ።»
منقول

ከሙሉነት ጥቂቱን..
:
#የማህበራዊ_ህይዎት_አመላካች
የኛ ነቢ ሙሉ ናቸው ስንል የምናወጣባቸው አይብ ስለሌለ ነው። በምላሳቸው የወጣን በተግባር ለመከወን የሚቀድማቸው አልነበረም። ማህበራዊ ህይዎት...መተዛዘንና መተሳሰብ ካስማዎቹ ናቸው። ይህ የሚታየው ደግሞ 'የኔ' ከምንለው ስብስብ ውጪ ካለ ሰው ጋር ባለን መስተጋብር ነው። ከኔ ሀይማኖት...ብሔር...ቀለም...ሌላም ሌላም።
የኛ ረሱል አይሁድን ጀናዛ ቁመው አላሳለፉምን? ሲነገራቸውስ <ፍጡራንን ለፈጣሪያቸው ስትል ውደድ> የሚል ዘመን አይሽሬ አብረቅራቂ መርህን አልነገሩምን?
ደግሞ ሰሃባዎች ሙስሊም ባልሆኑ ሰዎች የሚደርስባቸውን ጫና መቋቋም ቢጠናባቸው... እነሱን እንዲረግሙላቸው ወደ ነብያችን ያቀናሉ። ብለው ያሏቸው ግን ከሳቸው ሙሉነት የሚጠበቅ...ለኛዋ ነፍስ የሚከብደውን ነው... <እኔ ለእርግማን አልመጣሁም ለእዝነት እንጂ። ጌታዬ ሆይ እነርሱ አያውቁምና አቅናቸው።>
ከዚህ ጣፍጭ ባህር አንድ እናክል:
የምናውቀው አብደላህ ኢብን ኡበይ ሙናፊቅ ነበር። መሪያቸውም ጭምር። ያጠፋውን የመፅሀፍ ገፆች ላይ አናጣውም። በተቃራኒው ልጁ እጅግ ታሚኝና ዓቢድ ነበር። አብደሏህ በሚሞትበት ወቅት ልጅዬው ነብያችን ጋር መጥቶ ቀሚሳቸውን ጠየቀ-ለአባቱ መገነዣነት። የልጁን ቀልብ ላለመስበር ...የተወዳጅ ባለቤታቸውን የእናታችን ዓኢሻን ስም ያጎደፈውን ሰው እንዲገነዝበት ሳያቅማሙ ሰጡ። ዓጂብ!!
ﷺ

አንዳንድ ትዝታዎች ውስጥ በአብዛኛው ጊዜ ህመም ፣ ጸጸት እና ምሬት... አንዳንዶቹ ላይ ደግሞ የደስታና የእርካታ ስሜት ሊኖር ይችላል። የአንዳንዱ ደሞ ጭራሽ ሊያስገርመን ይችላል ምክንያቱም ምንም የቀረ ትዝታ እስከማይኖራቸው ድረስ እየጠፉ ስለሆነ።
አሁን ላይ ስላለፈው ማሰብ ምንም ነገር የማይፈጥርባቹ እና ወደ ኋላ ለመመልከት የማትፈሩበት ደረጃ ላይ እንደደረሳቹ፣ ባለፈው ነገር ላይ መጥፎ ስሜት ከመሰማት ያለፋቹበትን መንገድ በመገንዘብ እና በውጤቱ የበለጠ የምደሰቱበት ቦታ ላይ እንዳላቹ ፣እና ባለፈው ጊዜያቶች ውስጥ በነበራቹ ማንነት በተሰማቹ ደካማነት ፍርሃት እና ተስፋ የቆረጣችሁበትን ስሜቶች ለራሳቹ ይቅርታን አድርጋችሁ ዛሬ ላይ አተኩራቹ ራሳችሁን እንዳጠነከራቹ ተስፋ አለኝ።
አሁንም ደካማ ልትሆኑ ትችላላቹ ፣ ነገር ግን ድክመታቹን እንደምታሸንፉት ታውቃላቹ ፡፡ አሁንም ተሰባሪ ልትሆኑ ትችላላቹ ነገር ግን ስባሪውን እንዴት እንደምትጠግኑት ታውቃላቹ ምክንያቱም አሁን ላይ ስለራሳቹ የበለጠ ታውቃላቹ።ካለፈው ሕይወታቹ ብዙ ተምራቹሀል። አሁንም የበለጠ ልትማሩ ትችላላችሁ ምክንያቱም ሕይወት ማስተማሯን አታቆምም፡፡
ሁል ጊዜ የሕይወትን መሰናክሎች ካለፋቹ ወይ ደግሞ ደጋግሞ ከመውደቅ ተስፋ ካልቆረጣቹ ከፈተናዋ መትረፍ እና መውጣት ትችላላችሁ፤ እናም ውድቀቶቹን ማደግያ፣ በጠባሳዎቿ ውስጥ ደግሞ ብርሃን ማያ እና የአዲሱ ማንነታችሁን ውበትን መመልከቻ ይሆናቹሀል፡፡
እራሳችሁን ወደ አዲስ ሰው ወይም ወደ ተሻለ ሰው መለወጥ ቢጎዳም ወይንም ቢከብድም እሱ ሊፈውሳቹ፣ አዲስ እና የተሻለ ሕይወትንም ሊፈጥርላቹ ይችላል።There is still a lot to discover in you JUST በራሳችሁ ላይ እምነት ይኑራቹህ!
#ሸግዬ_ምሽት 🥰

ደሞ ፈራሁ! ላለማውራትም ፈለኩ... ግን ደግሞ ውስጤ እንደ ተወጠረ አፉፋ ሆኖብኛል...ማውራት አለብኝ! አንደበቴ አልተሳሰረም ረጋ ብዬ ማውራቴን ቀጠልኩ።
አብዛኛውን ሳወራ በእንባ ታጅቤ ነበር፤ አይኖቼ በጉም እንደተሸፈኑ ሁሉ ለማየት እየተቸገሩ በተደጋጋሚ ልጠርጋቸው ጣቶቼን ወደ አይኖቼ እሰድ ነበር፤ አልፎ አልፎ ንግግሮቼ በሲቃ የተሞሉም ነበሩ፤ በየመሃሉ ትንፋሽ እያጠረኝ.. አንድ ሁለት ሶስቴ እያቋረጥኩ ዝም እል ነበር፤ በሆዴ የቀበርኩትን የአመታት እሮሮ ሁሉ በነፃነት አወራሁኝ፤ ያስቀረሁት ነገር ትዝ አይለኝም።
ወደራሴ ተመልሼ ከአካባቢዬ ጋ ስዋኸድ ከጉኔ የተቀመጠውን (በውል እንኳን ያላወኩት) የህመሜን ሃያልነት ሳስቆጥረው የነበረው ለዚህ ነው እንዴ?...ሁኔታው ገረመኝ፤ እንደመብሸቅም አደረገኝ። በደበዘዘ በፈዘዘ ሁነት ሲያየኝ... ከዚህ ቀደም እንደሆኑት ሁሉ ለምን አብሮኝ አልተንሰቀሰቀም...?
<< እህቺ ህመም ናት ብለን ልናነባላት አይገባም ይልቁኑ ስለነገ ተግዳሮቶች እያሰብህ በርታ በል>> ከተቀመጥንበት ብድግ አለ። እስካሁን ያላነበብኳቸው አይኖቹ አባቡኝ የተሸከሙት ሃዘን ከደመና ጥላ ባላነሰ ፊቱ ላይ አንዣቧል... እጆቹ እርስ በእርስ ይፋተጋሉ...ከዚህ በላይ ላየው አልደፈርኩም። ላቅፈው መንደርደር ፈለኩ... እጄን ወደ እርሱ እንደመጣልኝ ዘረጋሁ.. አልተቻለውም፣ ፈገግ ለማለት ሲዳዳ አይኖቹ ቀደሙት። ፊቴ መቆም አልሆነለትም... እንደ መርበትበት... እንደ መታነቅ... እንደ መስመጥ... እንደ ማዞር ሁሉ ያደረገው መሰለኝ... ዞሮ ከኔ ሲሸሽ ይበልጥ ገፅታው ውስጤን አላወሰው ደግሜ ማንባት ፈለኩ። በአሁኑ ግን ለእሱ!
ከእኛ ልናስቀድማቸው የሚገቡ ጥልቅ ህመሞች በእርግጥም አሉ!

ካቆሰሉኝ ኋላ ምን ሊፈይዱኝ
አይዞህ እያሉ ከንፈር የሚመጡልኝ?
ሁሉ እንዳልነበረ በአንድ ክስተት ለአመታት የተገነባውን ያፈራርሱታል፤ በአንዲት ጥፋት ምንም መልካም ነገር እንደሌለን አድርገው ያንቋሹናል፤ ልክ እንደ እቃ በፈለጉ ሰዐት አውጥተው ሊጥሉን ይከጅላሉ፤ <<አይንህን ለአፈር>> ለማለት ይሽቀዳደማሉ።
እርግጥ ነው ብዙ ስብራቶች አሉ። ግን በምንም መልኩ ሊድን አልያ ሊጠገን የማይችል ስብራት ከተዉልን በኋላ ድጋሚ ሊያስታምሙን ይቋምጣሉ፤ ከተሰበረው እኛነታችን ጋ አብረን እንደቀበርናቸው አያውቁምና ነው..?

'በራስ መተማመን'
.
በአንድ ወቅት፣ በሙስሊሙ አለም አንድ የዳኝነትን ሹመት የተሰጠው
መሃይም ሰው ነበር። እና አንድ ቀን ሁለት ሰዎች ተጣሉና ለፍርድ ወደዚህ
ሰው ይመጣሉ። በመጀመሪያ ከሳሹ ክሱን ለዳኛው አቀረበለት። የተናገረው ሁሉ ዳኛውን አሳምኖት ነበርና አምኖ ተቀበለው። “ማሻ አላህ! ሐሳብህ ጥሩ ነው። ወላሂ አንተስ እውነትም ተበድለሃል። እውነቱ ያለው አንተ ጋር ነው!” አለው።
አሁን ተከሳሹ ተራ ደረሰውና ራሱን ለመከላከል፣ ንጽህናውን ለማረጋገጥና
ክሱን ውድቅ ለማድረግ ንግግሩን አቀረበ። አሁንም የዚህ ሰዉየ ንግግር
ዳኛውን አሳመነው። ሃሳቡ ተዋጠለት። ስለዚህ ለዚህኛውም ሰውየ፣ “ትክክል
ነህ፣ ሀቁ ያለው ካንተ ጋ ነው።” አለው።
እውነቱ ያለው ከተበዳዩ ወይም ከበዳዩ ሆኖ ሳለ ለሁለቱም ፍርድ ሰጠ።
ይህን የፍርድ ሂደት ከመጋረጃው ጀርባ ሆና ትክታተል የነበረችው የዳኛው
ሚስት፦ “አንቱ ሰውየ! ምን አይነት ፍርድ ነው የምትሰጡት፣ የመጀመሪያውን አንተ ነህ ትክክል አልኩ፣ ሁለተኛውንም እንደዛው። ይህ እዴት ይሆናል?” አለች። ሰውየውም፣ “ወላሂ፣ አንችም ትክክል ነሽ። የተናገርሽው በጣም ልክ ነው።” አላት።
ግፍ የተሰራበትም ትክክል ነው፣ በዳዩም ትክክል ነው፣ ፍርዱን የነቀፈችውም
ሴት ትክክል ናት። ሌላም አራተኛ ሰው መጥቶ ቢናገር ትክክል ነው። እንዲህ
አይነቱ ሰው እንግዲህ በራሱ ውሳኔ የማይተማመን እና በሰዎች ሃሳብ ብቻ
የሚመራ ሰው ይባላል። በራሱ ሀሳብ የማይመራ እና የራሱ ጠንካራ እምነት
የሌለው ሰው እንዲህ ነው። በሰው ሀሳብ ይመራል፣ ወደነፈሰበት ይነፍሳል።
ዝም ብሎ ማንኛውንም ሰው በጭፍን መከተል ስኬታማ አያደርግም፣ በራስ
መተማመንንም ይገድላል።
በራሱ የሚተማመን ሰው በሰዎች አስተያየትም ሆነ አመለካከት በቀላሉ
አይሸወድም፣ የራሱ የሆነ ጠንቃራ አመለካከት አለው። የሰዎችን ጭብጨባና ማዳመቂያ አይፈልግም። እያንዳንዱን ርምጃ በራሱ ተነሳሽነት ነው የሚወስደው። የሚያደርገው ነገር በሙሉ ትክክል ለመሆኑ ደግሞ የሰዎችን ማረጋገጫና ይሁንታ አይፈልግም፤ ምክንያቱም የሚያደርገውን ያውቃል።
ያመነበትን ነገር ያለ ምንም መሸማቀቅና እፍረት ይሰራል፣ መናገር ያለበትን ይናገራል። ሰዎች ያዘዙትን ነገር ሁሉ እሽ ብሎ አይቀበልም፣ “አይሆንም፣ የራሴ የምሰራው ስራ አለኝ፣ እንደዚህ አላደርግም።” ብሎ የሰዎችን ሃሳብ
ውድቅ ማድረግ ይችላል። “ኖ” ማለቱን ይችልበታል።
በራሱ የሚተማመን ሰው ራሱን ያውቃል። ስለራሱ ጥሩ ግንዛቤ አለው። ጥንካሬውንና ደካማ ጎኑን ለይቶ ያውቃል። ስለራሱም በጎ ምልከታ አለው። ራሱን ይወዳል፣ ራሱን ያከብራል። ለመሻሻል ይጥራል። ተጨባጭ ግቦችን ያስቀምጣል፣ ተጨባጭ ውጤቶችን ይጠብቃል። እንዲሁም የሰዎችን ትችት
በቀላሉ ተቋቁሞ ያልፋል። በራሱ የሚተማመን ሰው እንግዲህ እንዲህ ነው። የሚያወራውንም ሆነ የሚሰራውን ነገር ያውቃል።
በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች፣ ለራሳቸው የሚሰጡት ዋጋ ከፍ ያለ ነው።
እንደዚህ አይነት ሰዎች ህይወትን በደስታ ይኖራሉ። ሁሌም ለህይወት ጥሩ የተነሳስሽነት ስሜትም አላቸው። በራስ መተማመን የሌለው ሰው ደግሞ በተቃራኒው ነው። ለራሱ ክብር የሌለው ወይም በራሱ የማይተማመን ሰው
በሌሎችም ዘንድ ዋጋ እንደሌለው ያስባል።