Telegram Web
Forwarded from Elias Gebru
ዛሬ አርምሞ የሥልጠና ማዕከል ከStemPower ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 5 ኪሎ ካምፓስና AASTU ካምፓስ ሁለት ሥልጠናዎችን ሠጥተናል፡፡ አሪፍ ጊዜ ነበረን፡፡

https://www.tgoop.com/+WPPwKov-SIczNGNk
Forwarded from Elias Gebru
የአርምሞ 4ኛ ዙር ሥልጠና ነገ፣ ቅዳሜ፣ ሐምሌ 1 ከቀኑ ስምንት ሰዓት ይጀምራል። በዚሁ አጋጣሚ የአርምሞ የTiktok እና YouTube ቻናሎች በይፋ ሥራ ጀምረዋል። የተለያዩ እውቀትና ጥበቦችን ለመቃረም ከታች ባሉ ሊንኮች እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ😊። እናመሰግናለን🙏🙏🙏

YouTube 👇👇👇

https://youtu.be/2DWe8td-wYg

Tik Tok 👇👇👇

https://www.tiktok.com/@aremimo/video/7253143673330830598?_r=1&u_code=e3fjgji509l1b9&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=dkakelkd4jabc8&share_item_id=7253143673330830598&source=h5_m&timestamp=1688754486&user_id=7137362558869488666&sec_user_id=MS4wLjABAAAAeyeOOW_90jUJ8TwplCUZuMb-xq47oZ8sq9I77rP13rT0v1ywcbVeoNfH1YkMlHE3&social_share_type=0&utm_source=copy&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7250639154673403653&share_link_id=886f59de-000a-47f9-a5ef-993a07600151&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main&ug_btm=b8727%2Cb2878

አርምሞ የስልጠና ማዕከል!

ውስጣዊ ሰላም፣ ውጫዊ እድገት!
ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ ወጎች ግጥሞች እና ቁም ነገሮች pinned «የአርምሞ 4ኛ ዙር ሥልጠና ነገ፣ ቅዳሜ፣ ሐምሌ 1 ከቀኑ ስምንት ሰዓት ይጀምራል። በዚሁ አጋጣሚ የአርምሞ የTiktok እና YouTube ቻናሎች በይፋ ሥራ ጀምረዋል። የተለያዩ እውቀትና ጥበቦችን ለመቃረም ከታች ባሉ ሊንኮች እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ😊። እናመሰግናለን🙏🙏🙏። YouTube 👇👇👇 https://youtu.be/2DWe8td-wYg Tik Tok 👇👇👇 https://www.tiktok.com/@are…»
ደስታን ከሚሰጣችሁ ነገር ውስጥ ብቻ አትዘውትሩ። በተለይ መሻሻልና ማደግን ካለማችሁ አዲስ ነገር ለመሞከርና ለመሳሳትም ዝግጁ መሆን አለባችሁ። ኢ-ምክንያታዊ ፍርሃት ብዙ ጊዜ መድረስ ካለብን የማንነት እርከን ያስቀረናል።
ፍርሃታችንን ለመጋፈጥ እንጀግን።

(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ)

@eliasgebru
የዘንድሮ ተመራቂዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ። ተምሮ ለምርቃት መብቃት ለተመልካች የጊዜ ጉዳይ ነው፣ ለተማሪው ግን የከባድ ፈተና ጎዳና፣ የአእምሮ አቅም ማጣሪያ፣ መዓት የጭንቀት ድንበሮች መዳረሻ፣ የመጨረሻው የፅናት ወሰን ማጣሪያ መሰናክሎችን የማለፍ ድምር ውጤት ነው።

ያለፍነውን ዘርፈ ብዙ ፈተና የምናውቀው የትምህርት ዓለሙ ፅኑ ተጓዦቹ የነበርን ተማሪዎች ብቻ ነን። በዚህ የዓመታት ማራቶን ውስጥ ያገዛችሁንን በሙሉ ከልባችን ምስጋናችን ይድረሳችሁ። መልካም መምህራኖቻችን (ሲኒየሮቻችን) በሙሉ ስለአርአያነታችሁ እሱ ያክብርልን።
ከሁሉም በላይ ግን ሙሉ ክብርና ምስጋናውን ቸሩ ፈጣሪያችን ይውሰድ።

(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ፣ ረ/ፕሮፌሰር፣
የሥነ-አእምሮ ስፔሻሊስት፣ ሳይኮቴራፒስት፣
የአርምሞ ደራሲና የሥልጠና ማዕከል መሥራች)

https://www.tgoop.com/+WPPwKov-SIczNGNk

https://vm.tiktok.com/ZM2qjuNCq/
Forwarded from Elias Gebru
ከ2 ወራት በላይ ከገበያ ጠፍቶ የነበረው ተወዳጁ መጽሐፍ "አርምሞ" ለ16ኛ ጊዜ ታትሞ ዛሬ ከህትመት ወጥቷል። ፈልጋችሁ ያጣችሁት አንባብያን በሙሉ ከነገ ጀምሮ በመጽሐፍ መደብሮችና አንባቢያን እጅ ማግኘት ትችላላችሁ።

ዋና አከፋፋይ - ጃዕፈር መጽሐፍት መደብር
ስልክ - 0911125324

https://www.tgoop.com/+WPPwKov-SIczNGNk
Forwarded from Elias Gebru
የፊታችን እሁድ አንድ ላይ ነን!
አርምሞ 😊
https://www.tgoop.com/+WPPwKov-SIczNGNk
Glad to invite you to my workshop on
'Growth Mindset' in collaboration with American Embassy.
Day - Sep. 7 - Tomorrow
🕔 - 4 PM
📍- St. Mary's University Graduate Campus.
Miss it not 😇

Aremimo Training Center
Dr. Elias Gebru Aimero

@eliasgebru
ለአዲስ አመት እየተንደረደርን ነው። የተሻለውን እንዲያድለን ፆም ፀሎትም ይዘናል።
ከወዲሁ መልካም ሆነን አመቱን መልካም ለማድረግ እንዘጋጅ።

(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ፣
አርምሞ ሥልጠና ማዕከል)

@eliasgebru
መልካም አዲስ አመት ውድ ኢትዮጵያውያን🌼🌼🌼
አርምሞ የስልጠና ማዕከል 4ኛ ዙር ተማሪዎቹን እንዲህ በደማቅ ዝግጅት አስመርቋል።
የዛሬ ዓመት ሀ ብለን እንደጀመረን ይሄው በፈጣሪ ቸርነት ለዚህ ደርሰናል። ቀጣዩንም ዓመት 2016 ለሀገራችን በተለይ የሰላም፣ የፍቅር፣ የስክነት፣ የማስተዋልና የጥበብ 💎 እንዲያደርግልን ከልብ እንመኛለን።

መልካም በዓል! 💫💫
(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ)
(ዋና ሥራ አስኪያጅ)
@eliasgebru
📒 ያፍቃሪዋ ማስታወሻ
"አገኘሁትኮ! ታግሼ በተራዬ … ገነቴን የኔ አደረኩት! ውስጡ ዘልቄ
በአትክልት ቦታው ተምነሸነሽኩኝ። ውብ ጽጌሬዳ ቀስሜ እየዘለልኹኝ
ቦረቅኹበት። የደስታን ምንነት፣ የሀሴትን ጽዋ ተጎነጨሁት፤ በፍቅሩ
ሰክሬም ሀ ብዬ ሴት ሆንኩኝ። ውድዬን አቅፌው ተኛሁ፣ ስሜው
ነቃሁ፣ ህብረ-ከዋክብት የሚቀኑበትን ብርሃን በህይወቴ ሳሎን በርቶ
አየሁ - ሞቅም አለኝ።
እነሆ ሰርክ የማልጠግበውን የሰማይ መናም ቀመስኩኝ። ደስም
አለኝ። ማርና ሃለዋ እንዲጣፍጡ ሁሉ ኑሯችን ጣፈጠ። ቢራቢሮ አደይ እንዲያምሩ ሁሉ አማርን። ያልበረታውን ገመናውን ባልበረታው
ገመናዬ ጎበኘሁት። አብረንም የዘላለም የሚመስል ፈንጠዚያ ውስጥ
እርቃናችንን ጠለቅን። አብረንም እፎይ አልን። አንድ ሆንን። ማንም
ላይለየን ተጣመርን - ተጣበቅን።"

(አርምሞ፣ ገጽ 153/
ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ)

@eliasgebru
ስልኮች መጽሐፎችን እየገደሉ ባለበት ዘመን ላይ እንገኛለን።
.
.
.
.
.
ወደፊታችን ያስፈራል!

@eliasgebru
2025/02/06 12:04:25
Back to Top
HTML Embed Code: