Telegram Web
🎂

ከመቼው እንደዚህ እንዳረጀው አላውቅም።

ብዙ ተምሬ ብዙ አንብቤ የማስታውሰው ነገር ግን ማንበብ መማሬን ብቻ ነው።

በቀደም መስታዎት ፊት ቆሜ ፀጉሬ መሐል ጥጥ ነገር መስሎኝ ላነሳ ስል የኔ ጥጥ ነው።

ሽበት ጀምሮኛል😀

ብዙ ነገር አይቻለሁ ባይ ነኝ። ብዙ ነገር አይቶኛልም።

መኖር ቀሎኝ አያውቅም።
የከበደኝ ገላዬ ውሰጥ መኖር ይሆን ሰው መሐል መኖር እንጃ ።

ለጉድ ስቄያለሁ
ለጉድ አዝኛለሁ።


አላውቀውም ነገዬን።
ያኖረኛል ከፈለገ ይገድለኛል ከፈለገ።

ሀገር እና ሰዎች የሉኝም ካልኩ ረጅም ዘመን ሆኖኛል።
እንጃ ለሌሎች አለሁ መሰለኝ እልፍ ሰዎች መወደድና ክብር መሐል ያቆመኛል 🙏  መባረክ ነው።

ወይ እኔ ቆሜያለሁ ወይ ጊዜው ይሮጣል።

ብቻ ልደትህ ነው አሉ።
ማመን ነው መቼም።

እንጃ ምሽቴን እንጃ ያን ወጋገን
ሁሉ አይነገረም እግዚአብሔር ይመስገን!
2024/11/20 01:21:46
Back to Top
HTML Embed Code: