"አንድ ወንድና አንዲት ሴት የተጋቡት (የሚጋቡት) መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ አብረው እየተጋገዙ ለመሔድ ከኾነ፥ ትዳራቸው ታላቅ የኾነ ደስታን ያመጣላቸዋል፡፡"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#መልካም_ቀን 🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#መልካም_ቀን 🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
❤8🙏3👍2
†
🕊 ቅዱሳን ቂርቆስ ወኢየሉጣ 🕊
🕊
❝ ጥቡዕ ልቡ ለሕጻን እንዘ ሀሎ ውሥተ ምኩናን ይቤላ ሕጻን ለእሙ ጥብኢኬ እም ንፈጽም ገድለነ ወስምአነ ንፈጽም ገድለነ ወስምአነ ከመ ንርአይ ገጾ ለአምላክነ ❞
[ ትርጉም ፦
[ በፍርድ ቦታ የህጻኑ ልብ ቆራጥ ነው። እምዬ [ እናቴ ] ሆይ ምሥክርነታችንን ገድላችንን እንፈጽም ዘንድ ቁረጭ የአምላካችንን ፊቱን እናይ ዘንድ ! ]
[ ዚቅ ዘማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ]
🕊
† እንኳን ለቅዱሳኑ ቂርቆስ ወኢየሉጣ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †
🕊 💖 🕊

❤3
†
[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]
[ ክፍል ሰባ ሦስት ]
🕊
[ ለአባ ጴሜን ስለ መንግሥተ ሰማያት ጣፋጭነት እንደ ነገረው ! ]
🕊
❝ አባ ጴሜን እንዲህ አለ ፦ “ በአንድ ወቅት ከተወሰኑ አኃው ጋር ሆኜ ከአባ መቃርዮስ ጐን ተቀምጬ ሳለ እንዲህ አልኩት ፦ " አባቴ ሆይ ! አንድ ሰው ለራሱ ሕይወትን ገንዘብ ያደርግ ዘንድ ምን ማድረግ አለበት ? ” ብዬ ጠየቅሁት፡፡
አረጋዊው አባትም እንዲህ አለ ፦ “ በአባቴ ቤት ሕፃን ሳለሁ በአፋቸው ውስጥ ያለውን ምራቃቸውንና የእስትንፋሳቸውን መዓዛ መልካም እንዲያደርግላቸው ትልልቅ ሴቶችና ወጣቶች በአፋቸው የሆነ ነገር ሲያላምጡ እመለከት እንደ ነበር አስታውሳለሁ፡፡ እንዲህ ቁሳዊ የሆነ ነገር የሚያላምጡትንና የሚያኝኩትን ሰዎች መዓዛቸውን መልካም የሚያደርግና የሚያጣፍጥ ከሆነ የሕይወት ምግብ ፣ የድኅነት ምንጭ ፣ የሕይወት ውኃ መገኛ የጣፋጮች ሁሉ ጣፋጭ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ያህል ያጣፍጥ ይሆን !
አጋንንት የከበረ ስሙ በአንደበታችን ሲጠራና ሲመሰገን ሲሰሙ አንደ ጢስ ተነው ይጠፋሉ፡፡ ይህን የተቀደሰ ስም በአንደበታችን አጽንተን ብንይዘውና ብናጣጥመው ክፉ ሃሳቦችን በሙሉ ከውስጣችን ያስወጣልናል፡፡ መንፈስ ቅዱስንም ያቀርብልናል ፤ ለነፍሳችንም ሰማያዊ ነገርን ፣
በተለይም ደግሞ በሰማያት ያለውንና በፍጹም ልባቸው ለሚለምኑት ሰማያዊ ዋጋን የሚሰጣቸውን የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይገልጥላታል፡፡ "
አባ ጴሜን ከአባ መቃርዮስ እነዚህን ነገሮች በሰማ ጊዜ በዕንባ ሆነው ከአባ መቃርዮስ ከእግሩ ሥር ወደቁ፡፡ ከጸለየላቸውም በኋላ አሰናበታቸዉ፡፡ እነርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገኑት፡፡ ❞
🕊
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡
ይቆየን !
💖 🕊 💖

👍1
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ መታዘዝ ! ]
🕊
" ውኃው ከጉድጓዱ ሥር ወደ ላይ መጣ ... "
❝ ከአባቶች አንዱ ረድኡን ውኃ እንዲቀዳ ላከው::
የውኃው ጉድጓድ ከበኣታቸው በጣም ሩቅ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደ ጉድጓዱ ከደረሰ በኋላ ውኃውን የሚስብበትን ገመድ እንደረሳው ተረዳ፡፡
በዚህ ጊዜ ጸሎት አደረገና ፦ "የውኃ ጉድጓድ ሆይ ፣ መቅጃውን በውኋ መልተህ ና ያለኝ አባቴ ነው" ብሎ ጮኽ ብሎ ተናገረ፡፡
ወዲያውኑም ውኃው ከጉድጓዱ ሥር ወደ ላይ መጣ ፣ ያ ረድእም ማሰሮውን መላ ፣ ከዚያም በኋላ ውኋው ወደ ቦታው ተመልሶ ወረደ፡፡፡ ❞
🕊
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †

❤6
Forwarded from @Bini photographer 📷 (ቢኒ ፲፪)
🥰🥰🥰
@Bini photographer 📷
Join👇👇👇 share
👇👇👇
https://www.tgoop.com/bini_image
https://www.tgoop.com/bini_image
@Bini photographer 📷
Join👇👇👇 share
👇👇👇
https://www.tgoop.com/bini_image
https://www.tgoop.com/bini_image
🕊
[ † እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ ዳንኤል" : "አባ ዸላድዮስ" : ወቅዱስ "ፊላታዎስ ሰማዕት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ማር ዳንኤል † 🕊
" ዘዓምድ " በሚል ስም ከሚታወቁ የቤተ ክርስቲያን አበው መካከል ፬ቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ:: እነዚህም :-
፩. ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ:
፪. ቅዱስ አጋቶን ዘዓምድ:
፫. ቅዱስ ዳንኤል ዘዓምድ እና
፬. ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ ናቸው::
- " ዘዓምድ " የሚለውን ቃል ምሥራቃውያን በልሳናቸው 'THE STYLITE' ይሉታል:: የእኛው ቃል ደግሞ ከግዕዝ የተወረሰ ነውና በቁሙ ቢተረጐም "የምሰሶው" የሚል ትርጉምን ይይዛል:: ይህም በ፪ ምክንያቶች ነው::
- አንደኛው ቅዱሳኑ ተጋድሏቸውን የፈጸሙት ከረዥም ምሰሶ ላይ ወጥተው በመጸለይ ስለሆነ ነው:: ሌላኛው ምክንያት ደግሞ እነዚህ አባቶች በዘመኑ ለነበሩ ምዕመናንና መነኮሳት አጽናኝ: አስተማሪ: መሪና ፈዋሽ በመሆናቸውና እንደ ምሰሶ ተተክለው ሳይነቃነቁ በመጸለያቸው ነው::
- ልክ ከዓለም ሃገራት ብዙ ስውራንን እና ቅዱሳን ነገሥታትን በመያዝ ሃገራችን ቀዳሚ እንደ ሆነችው ሁሉ ምሰሶ ላይ ወጥተው የሚጋደሉ ቅዱሳንም ሶርያውያንና ምሥራቃውያን ናቸው:: በዚህ ዕለትም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የታላቁን ቅዱስ ማር ዳንኤልን በዓል ታከብራለችና ከዜና ሕይወቱ ለበረከት ጥቂት እንካፈል::
- ይህ ቅዱስ ሰው [ በስዕሉ የሚታየው ] ሶርያዊ ሲሆን ተወልዶ ያደገባት አካባቢ በቀድሞው አጠራር "ሃገረ ዓምድ" ይሏታል:: "ማር" የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን ቅድስናንና አለቅነትን የሚገልጽ ስም ነው:: በዚህ ስም ጥቂቶች ብቻ ሲጠሩበት ለሊቃውንትም: ለሰማዕታትም: ለጻድቃንም አገልግሏል::
- ቅዱሱ "ማር" ብቻ ሳይሆን "ዘዓምድ" ተብሎም ተጠርቷል:: ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እርሱም በፊት እንደ ጠቀስናቸው አበው ምሰሶ ላይ ተጠግቶ [ ቆሞ ] : ትኩል ከመ ዓምድ ሆኖ በመጸለዩ ነው::
- ማር ዳንኤል በምድረ ሶርያ ስመ ጥር ጻድቅ ነው:: በዘመነ ጻድቃን መጨረሻ አካባቢ ከክርስቲያን ወገኖቹ ተወልዶ: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድጐ: ገና በልጅነቱ ለቤተ እግዚአብሔር ተሰጥቷል::
- የወቅቱ የሃገረ ዓምድ ዻዻስ [ አባ ዼጥሮስ ] ለማር ዳንኤል ፍኖተ ጽድቅን [ የሕይወት - የእውነትን ጐዳና] በማሳየት ከፍ ያለውን አስተዋጽኦ አበርክቷል:: አስተምሮም ለመዓርገ ክህነት አብቅቶታል::
- ቅዱሱ በእድሜው እየበሰለ ሲሔድ ግን ምርጫው ምናኔ ሆኖ በመገኘቱ በፈቃዱ ወደ በርሃ ሔደ:: በዚያም መዓርገ ምንኩስናን ተቀብሎ በጾም: በጸሎትና በትሕርምት ይጋደል ገባ::
- ማር ዳንኤል በበዓቱ ተወስኖ ሲጾም: ሲጸልይና እግዚአብሔርን ሲያመልክ ከጸጋ [ከብቅዓት] ደረሰ:: ብዙ ተአምራትንም በመሥራቱ ስም አጠራሩ በአካባቢው ተሰማ:: እርሱ ግን ከሰው: ይልቁንም ከሴቶች ይርቅ: ላለማየትም ራሱን ይከለክል ነበር::
- ለአንድ መናኝ በሰዎች መካከል: ይልቁንም በተቃራኒ ጾታ ጐን መኖር ያልተፈቀደ: ፈታኝም ድርጊት ነውና ከፈጣሪው ጋር እንዲህ የሚል ቃልን ገባ:: "ከዚህ በሁዋላ ሴት ልጅን አላይምም" አለ:: በእንዲህ ያለ የቅድስና ሕይወት ሳለ ወላጅ እናቱ ልታየው ተመኘች::
- ወደ ገዳሙ መጥታም "ልጄ ! ላይህ ሽቻለውና ልግባ : ወይ ብቅ በል" ስትል ላከከችበት:: ቅዱሱ ግን "እናቴ ! ሴትን አላይም ብየ ቃል ስለ ገባሁ አልችልም" ሲል መለሰላት:: በጣም አዝና "እኔ ወልጄ: አዝዬ: አጥብቼ: አሳድጌ እንደ ሌሎች ሴቶች አስመሰልከኝ? በል ፈጣሪ ፪ ሴቶች በአንድ ልብስ ሆነው ይዩህ!" ብላ ረግማው ወደ ቤቷ ተመለሰች::
- የሚገርመው ማር ዳንኤል በበርሃ የበቃውን ያህል እናቱ በዓለም ሳለች በጐ ሰርታለችና እርሷም ጸጋውን አብዝቶላታል:: በምን ይታወቃል ቢሉ :- ያቺ የተናገረቻት ነገር ሁሉ ደርሶበታልና::
- አንድ ቀን ለገንዘብ ሲል አንድ ሰው የገደለውን አምጥቶ በቅዱሱ በር ላይ ጣለው:: ቅዱሱም ያለ አበሳው ታሥሮ ወደ ከተማ ሲወሰድ መታጠቢያ [ shower ] ቤት ውስጥ የነበሩ ሴቶች ሊያዩት ቸኩለው: አንድ ልብስ ለብሰው ወጥተዋል:: ማር ዳንኤል ይህንን ሲያይ የእናቱ ነገር ትዝ ብሎት ሳቅ ብሏል::
- በታሠረበት ቦታ ግን የሞተውን ሰው በጸሎቱ በማስነሳቱ በክብር ወደ በዓቱ ተመልሷል:: የከተማዋ ንጉሥም ገዳምን አንጾለታል:: በተረፈ ዘመኑም ለብዙ ቅዱሳን አባት ሆኖ እስከ እርጅናው አገልግሏል:: በዚህች ቀንም በክብር ዐርፏል::
🕊 † አባ ዸላድዮስ † 🕊
- አባ ዸላድዮስም በተመሳሳይ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ ነው:: በርሃ ከገባባት ቀን ጀምሮ ጾምን: ጸሎትን አዘውትሮ ክርስትናውን አጽንቷል:: ሙሉ እድሜውን በጐ በመሥራት በማሳለፉ ፈጣሪውን ሲያስደስት ለብዙዎች አንባ: መጠጊያ መሆን ችሏል::
- በጸሎቱ አካባቢውን በደህንነት ይጠብቅ ነበር:: ምዕመናን እንኩዋን ወደ እርሱ መጥተው ተባርከው ባሉበት ቦታ ሁነው ተማጽነው እንኩዋ መሻታቸውን አያጡም ነበር:: ምንም ያህል ኃጢአተኞች ይሁኑ እግዚአብሔር ስለ አባ ዸላድዮስ ሲል ይለመናቸው ነበር::
- አንድ ቀን አንድ ነጋዴ ሰው በባሕር ላይ ሲሔድ ድንገት ማዕበል ይነሳበታል:: ብቻውን ነበርና ጨነቀው:: እሱ ያለባት ጀልባም ትንሽ በመሆኗ ልትሠበር ደረሰች:: መዳን እንደ ማይችል ሲያውቅ ተስፋ ቆረጠ::
- ድንገት ግን አባ ዸላድዮስ ትዝ ብሎት ቀና ብሎ "ጌታየ! ስለ ቅዱሱ አባት ብለህ ብትምረኝ ለወዳጅህ መቶ ዲናር ወርቅ እሰጣለሁ" ሲል ተሳለ:: ቃሉን ተናግሮ ሳይጨርስ አባ ዸላድዮስ በጀልባው ላይ ቁጭ ብሎ ታየው:: ማዕበሉም ጸጥ እንዲል አድርጐ ከወደብ አድርሶ ተለየው::
- ነጋዴውም ፈጣሪውን ስለ ድኅነቱ እያመሰገነ ፻ ዲናር ወርቁን ይዞ አባ ዸላድዮስን ፍለጋ ወጣ:: የሚያውቀው በዝና ብቻ ነበርና:: መንገድ ላይም ሞሪት የሚባል መሪ አግኝቶ ከአባ ዸላድዮስ በዓት ደረሰ::
- ከቅዱሱ ተባርኮ ወርቁን ቢያቀርብለት "ልጄ! እኔ ይህን አልፈልገውም:: ለነዳያን በትነው" አለው:: ነጋዴው ሲወጣ ግን ሞሪት [መሪው] ገንዘቡን ፈልጐ ገደለውና ከጻድቁ በር ላይ ጣለው:: ሃገረ ገዢውም ሲሰማ አባ ዸላድዮስን አሠረው::
- ጻድቁ ግን የሞተውን ባርኮ አስነሳውና "ማን ገደለህ" ቢለው "ሞሪት" ሲል መልሷል:: መኮንኑ ሞሪትን ሊገድለው ቢልም "የለም" ብሎ ነጋዴውን በደስታ: ሞሪትን ደግሞ በንስሃ ሸኝቷቸዋል:: አባ ዸላድዮስ ግን ተረፈ ዘመኑን በቅድስና ሲጋደል ኑሮ በክብር ዐርፏል::
🕊 † ቅዱስ ፊላታዎስ ሰማዕት † 🕊
- "ፊላታዎስ" ማለት "መፍቀሬ እግዚአብሔር - እግዚአብሔርን የሚወድ: እርሱም የሚወደው" ማለት ነው:: ቅዱሱ የዘመነ ሰማዕታት [፫ኛው መቶ ክ/ዘመን] ፍሬ ሲሆን ለየት ያለ ታሪክ ያለው ቡሩክ ወጣት ነው::
- እርሱ የባለ ጸጐች ልጅ: ስለ ክርስትና ምንም ሰምቶ የማያውቅ ሕጻን ነበር:: ወላጆቹ የሚያመልኩት ላምን ሲሆን የአካባቢው ሰው ደግሞ ለጸሐይ ይንበረከክ ነበር:: ቤተሰቦቹ ስለ አምልኮ ሲጠይቁት "እናንተ የምታመልኯቸው ፍጡራን ስለ ሆኑ አልፈልግም" አላቸው::
- ሕጻን ቢሆንም ስለ ፈጣሪው ተመራመረ:: በመጨረሻውም ፀሐይን "አንተ ምንድነህ?" ቢለው "እኔ ፍጡር ነኝ" ሲል መልሶለታል:: በዚያች ዕለት ግን ቅዱስ መልአክ ወርዶ: ሁሉን ነገር አስተምሮ የክርስቶስ ወታደር አድርጐታል::

👍2
- ወደ ቤቱ ተመልሶም የወላጆቹን ላም "እውነትን ተናገር" ብሎ ገስጾታል:: ላሙም ሰይጣን እንዳደረበት በሰው ልሳን ተናግሮ: የቅዱሱን ወላጆች ወግቶ ገድሏቸዋል:: ቅዱስ ፊላታዎስ ግን ላሙን አስገድሎ: ወላጆቹን ከሞት አስነስቶ ከአካባ
ቢው ሰው ጋር በስመ ሥላሴ አስጠምቁዋቸዋል::
- በድንግልና ኑሮም ዘመነ ሰማዕታት ሲጀምር በርጉም ዲዮቅልጥያኖስ እጅ ብዙ ተሰቃይቷል:: በጸሎቱም ጣዖታቱን [እነ አዽሎንን] ከነ አገልጋዮቻቸው ወደ ጥልቁ አስጥሟቸዋል:: እርሱም በዚህች ቀን በሰይፍ ተከልሎ ለክብር በቅቷል:: ለእኛ ለኃጥአን የሚሆን ቃል ኪዳንንም ከጌታው ተቀብሏል::
የቅዱሳን አባቶቻችን አማናዊት ርስት ድንግል ማርያም አትለየን::
🕊
[ † ጥር ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ፊላታዎስ ሰማዕት
፪. አባ ዸላድዮስ ገዳማዊ
፫. ማር ዳንኤል ሶርያዊ
፬. አባ ዮሐንስ መሐሪ [ሊቀ ዻዻሳት]
፭. 11,004 ሰማዕታት [ የቅ/ቂርቆስ ማሕበር ]
፮. 11,503 [ የቅ/ፊላታዎስ ማሕበር ]
፯. አባ ጽሕማ [ ከተስዓቱ ቅዱሳን አንዱ ]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. በዓለ ኪዳና ለድንግል
፪. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፬. ቅድስት ኤልሳቤጥ
፭. አባ ዳንኤል
፮. አባ አቡናፍር ገዳማዊ
፯. አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
" ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል:: እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል:: በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል:: በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ:: ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ:: ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ::" [ መዝ.፺፩፥፲፪ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬