Telegram Web
ጥር 25 እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤አደረሰን።

#መርቆርዮስ" ማለት የአብ ወዳጅ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።
ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ መድኃኔዓለም ቃልኪዳን ሲገባለት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀጥሎ
ሁለተኛው ሊቀ ሰማዕት አንተ ንህ ብሎታል። በጣም የሚገርመው ቃልኪዳን ደግሞ የቅዱስ
#መርቆሬዎስ_ስዕል አድኀኖ የያዘው ሰው የተወረወረ ጦርም ሆነ ቀስት፤ የተተኮስ ጥይትም ቢሆን
አይነካውም ብሎ መድኃኔዓለም ቃል ገብቶለታል። ገዳሙ ላይ ያለው ስዕል አድኀኖም ካህናት
ማህሌት እና ሰዓታቱን ሲያደርሱ ፈረሱ ይንቀሳቀሳል።
በእውነት የሰማዕቱ ቅዱስ መርቆርዮስ ረድኤት በረከት ይደርብን ከክፉ መከራ ይሰውን፣ ይታደገን፣
ይጠብቀን፣ አለው ይበለን አሜን !
#ሰማዕቱ_ቅዱስ_መርቆርዮስ ሆይ እኔ ደካማ ነኝ እና ከመከራ ነፍስ ከመከራ ስጋ ጠብቀኝ!። ✞ አሜን !!! አሜን !!! አሜን !!!

#መልካም_ዕለተ_ሰንበት🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
6🙏5👍1
                          †                          

[     🕊    ቅዱስ መርቆሬዎስ !  🕊     ]
           

[ የአብ ወዳጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ  ]

💖                      🕊                      💖

❝ ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: [ ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ ]" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው::

ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ❞

🕊

ሰማዕቱ በዚህች ዕለት : በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖችን ያሰቃይና ይገድል የነበረውን ዑልያኖስን ያጠፋበት መታሠቢያ ይከበራል::

† አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን:: ቸሩ እግዚአብሔር እድሜ ለንስሃ ዘመን ለፍሥሃ አይንሳን::

†    🕊   ክብርት ሰንበት   🕊    †


💖                      🕊                      💖
👍3🙏1
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ]

🕊             
             
❝ ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል ? ቃልህን በመጠበቅ ነው። ❞  [ መዝ . ፻፲፱ ፥ ፱  ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ሕይወተ ወራዙት [ የወጣቶች ሕይወት ! ]

          [   ክፍል -  አሥራ አንድ  -    ]

            💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

      [    ድንግልናን መጠበቅ    ]


የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]


🕊                        💖                      🕊
                             👇
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                          †                          



[    🕊   ታቦት በሐዲስ ኪዳን   🕊    ]




▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬
1
🕊

[  † እንኳን ለቅዱሳን አርባ ዘጠኝ አረጋውያን ሰማዕታት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  አረጋውያን ሰማዕታት  †  🕊

† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: [ ማቴ.፭፥፵፬ ] ነገር ግን
ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

የእነዚህ ሰማዕታት ቁጥራቸው ፵፱ [49] ሲሆን አባ ቢስዱራ የሚባል ጻድቅ ሰው ፶ [50] ኛ ሁኖ ይመራቸው ነበር:: መኖሪያቸው ገዳመ አስቄጥስ [ግብጽ] ሆኖ ዘመኑ ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘ ነበር::

ሃምሳውም ሙሉ ዘመናቸውን በምናኔና በቅድስና ፈጽመው በስተእርጅና ደግሞ ሰማዕትነት መጣላቸው:: በ፬፻፴ [430] ዎቹ አካባቢ
የዚያን ጊዜ በርበር ይባሉ የነበሩት አረማውያኑ [የዛሬዎቹ አሕዛብ አባቶች] "ሃይማኖት ካዱ" እያሉ ሰይፍን መዘዙባቸው::

በጊዜው አባ ቢስዱራ በማረፉ ሃላፊነቱን የወሰዱት አባ ዮሐንስ ከአርባ ስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ተስማምተው በበርበር እጅ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል:: ከንጉስ ቴዎዶስዮስ [ትንሹ] ተልኮ የነበረ አንድ ክርስቲያንም በፍቅረ ክርስቶስ ተስቦ ከወጣት ልጁ ጋር ተሰይፏል:: የብርሃን አክሊልም ለሃምሳ አንዱም ወርዷል::

† አምላከ ቅዱሳን ከተከፈተ ገነት : ከተነጠፈ ዕረፍት በቸርነቱ ያድርሰን::

[  † ጥር ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. አርባ ዘጠኝ አረጋውያን ሰማዕታት [ግብጽ ገዳመ አስቄጥስ ውስጥ]
፪. ቅድስት አንስጣስያ [በ፭ኛው መቶ ክ/ዘ ከቁስጥንጥንያ ወደ ግብጽ ወርዳ ፡ ንግሥናን ንቃ በበርሃ ስትጋደል የኖረች ቅድስት
እናት ናት::]
፫. ቅዱስ ዮሴፍ [ መፍቀሬ ነዳያን ]
፬. አባ ጽሕማ [ ከተስዓቱ ቅዱሳን ]

[    † ወርኀዊ በዓላት     ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ኢትዮጵያዊ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

" ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን' ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: " † [ ሮሜ. ፰፥፴፭-፴፰ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2👍2
2
#ወዳጄ

አንተ በመከራ ውስጥ ካለህ
#የዩናስን ዓሣ ነባሪ አስታውስ ከፍራቻ ትገላገላለህ ። መከራው #እግዚአብሔር ጸጋውን ሊያበዛልህ ስለፈለገ ያዘጋጀው ዓሣ ነባሪ እንደሆነ የምታውቅበት ጊዜ ይመጣል። የዚህ ዓለም የባሕር ዓሣዎች ብዙ ስለሆኑ ስትዋጥ እንዳይከፋህ መጠንቀቅ ይኖርብሃል። የመጀመሪያው ባህታዊ ጻድቁ #አባ_ጳውሊ የተናገረውን መዘንጋት የለብህም #ከመከራ መራቅ የሚወድ #ከእግዚአብሔር ይርቃል" ብሏል። በእውነት መከራ የጸሎት ትምህርት ቤት ነው። "በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ጮኽሁ እርሱም ሰማኝ። በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ። ቃሌንም አደመጠ" ዮናስ 2፥3

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

     
#መልካም_ቀን 🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
8👍2😢1
🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

       [    ስለዚህ ይቅር አለን !    ]

🕊                        💖                       🕊

❝ እርሱ ተመልክቶን እነሆ ለእግዚአብሔር ጠላቶቹ ሆነን ተገኘን። ሀብቱን ለማግኘት ኪዳንም ቢሆን ፤ መሥዋዕትም ቢሆን ወደ እርሱ ያቀርበን ዘንድ የሚችል ፈጽሞ አልነበረንም ፤ ስለዚህ ይቅር አለን ዙፋኑን ከበው ከሚቆሙ ከመላእክት ፤ ከኃይላትም ወገን ሊቀ ካህናት አልሾመልንም። [ ኢሳ.፷፫.፱ ። ፷፬፥፮  ፤ ዕብ.፭፥፩፩ ]

እርሱ አንዱ ወደዚህ ዓለም ወርዶ ባሕርያችንን ባሕርይ አድርጎ ሊቀ ካህናት [ አስታራቂ ] ሆነን እንጂስለእኛም ሥጋውን መሥዋዕት አድርጎ ወደ አባቱ አቀረበ እንጂ ፤ በታመመበት በሥጋው ለርሱ ገንዘብ ለመሆን አበቃን። [ ዕብ.፱፥፳፰ ]

እርሱ መከራ የሚቀበሉትን እርሱ ማዳን ሲቻለው መከራ እንደተቀበለ ተናገረ ፤ በባሕርዩ ሕማም ሞት የሌለበት ሲሆን ስለ እኛ ሰው ሆኖ ታሞ ሞቶ አዳነን እንጂ እንደ ማለት ነገራቸው። [ ዕብ.፪፥፲፰ ]

በመከራ የሚፈተኑትን ማዳን ሲቻለው ማለቱ ምንድር ነው ? በሕማሙ የሕማምን መጥፊያ መጥፊያውን ዐውቋልና ፤ በመከራቸው ጊዜ ታሞ ሞቶ እንደ አዳናቸው መናገሩ ነው እንጂ

የሕዝን ኃጢአት ያስተሰርይ ዘንድ ለምን አለ? የአሕዛብን ኃጢአት ለማስተስረይ አላለም ፤ ፈቃዱ በፊት እሥራኤልን በኋላ አሕዛብን ለማዳን ስለሆነ ነው ስሙ ኢየሱስ ይባላል ፤ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ነው ብሎ መልአክ ለዮሴፍ እንደ ነገረው። [ ማቴ.፩፥፳-፳፪ ። ሉቃ.፩፥፴፪ ] ❞

[    ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ    ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                      🕊                      💖
🥰6👍1
🥰10
                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]

           [       ክፍል  ሰማንያ      ]

                         🕊  

[    አንድን አረጋዊ እንደ ጠየቀው !   ]

🕊

❝ አባ መቃርዮስ እንዲህ አለ ፦ “ ታሞ አልጋ ላይ የነበረን አንድ አረጋዊ ልጠይቅ ሄድኩ፡፡ እርሱ ግን ሕይወትና ቅዱስ የሆነውን የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ይጠራ ነበር፡፡

ስለ ጤናው ሁኔታ በጠየቅኩት ጊዜ በደስታ ሆኖ እንዲህ አለኝ ፦ “ በጽናት ሆኜ ጣፋጭ የሕይወት ምግብ የሆነውን ቅዱስ ስሙን በመመገብ ላይ ሳለሁ ደስ የሚል የሰላም ዕንቅልፍ ያዘኝ፡፡ በራእይም ንጉሥ ክርስቶስን እንደ ናዝራዊ ሆኖ አየሁት ፣ ሦስት ጊዜም እንዲህ አለኝ ፦ “ ተመልከት ፣ እኔ እንደ ሆንኩና ከእኔ ሌላ ማንም እንደ ሌለ ተመልከት፡፡ "

ከዚያ በኋላ ታላቅና ሰማያዊ ለሆነው ነገር በታላቅ ደስታ ውስጤ ተቃጠለ ፣ ብቸኝነቴንና ሕመሜንም ረሳሁት፡፡ ❞

🕊

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


💖                      🕊                      💖
8
10
                         †                        

 [       🕊    ፍኖተ ቅዱሳን    🕊      ]

[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

             [        መታዘዝ !         ]

🕊

❝ ከአበው አንዱ አራት ሠራዊት በእግዚአብሔር ዘንድ አየሁ አለ።

የመጀመሪያው በደዌው ሆኖ እግዚአብሔርን የሚያመሰግን በሽተኛ [ ድውይ ዘበአኰቴት ]  ነው:: ሁለተኛው ሰዎችን [ እንግዶችን ] ደስ እያለው በፍቅር የሚቀበልና የሚያሳርፋቸው ነው። ሦስተኛው በገዳም የሚኖር ከሰው ጋር የማይነጋገር [ ዝጉሐዊ ] ነው። አራተኛው ደግሞ ስለ እግዚአብሔር ብሎ ለመምህሩ የሚታዘዝና የሚላላክ ረድእ ነው

በዚህ ረድእ በአንገቱ ላይ የወርቅ ባዝግና ተሸልሞ መንበሩም ከሁሉም በላይ ሆኖ አየሁት። ይህን ለሚያሳየኝ ይህ ታናሽ እንዴት ከሁሉ በለጠ ? ብዬ ጠየቅሁት።

እርሱም ፦ " እነዚህ መልካም የሠሩ በራሳቸው ፈቃድ ነው ፤ ይህ ግን የራሱን ፈቃድ ለእግዚአብሔርና ለመምህሩ የተወ ነው ፣ ስለዚህም ከፍ ያለ ክብርና መንበር ተሰጠው" አለኝ። ❞

🕊

የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡


†                         †                         †
💖                      🕊                      💖
7
10
🕊

[  † እንኳን ለቅዱሳን ቅዱስ ኄኖክ : ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ : ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊   †  ቅዱስ ኄኖክ   †   🕊

† ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን ቅዱስ ኄኖክ ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ ነው:: አዳም: ሴት: ሔኖስ: ቃይናን: መላልኤል: ያሬድ ብለን ሰባተኛው ኄኖክ ነውና::

ቅዱሱ የማቱሳላ አባትም ነው:: አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረጉም ሞትን ያላየ: ብሔረ ሕያዋን የገባ የመጀመሪያው ሰው ሁኗል:: ለአዳም ልጆችም ተስፋ ድኅነት እንዳለ ማሳያ ሁኗል:: "በአቤል አፍርሆሙ: ወበኄኖክ አንቅሆሙ" እንዳለ ሊቁ::

ቅዱስ ኄኖክ በ፲፬፻፹፮ [1486] ዓ/ዓ የመጀመሪያውን የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል [መጽሐፈ ኄኖክን] ከመጻፉ ባሻገር በብዙ ሥፍራ በክብር ተጠቅሶ ይገኛል::


🕊 † ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ †  🕊

† ይህ ቅዱስ ሐዋርያ አንድ የቤተ ክርስቲያናችን መብራት ነው:: ወደ ክርስትና የመጣው በ40ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ሲሆን አሳምኖ ለቅድስና ያበቃው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ነው::

በጊዜውም በነበረው ትጋትና ተጋድሎ ፍሬ አፍርቷል:: ሆዱንም እጅግ ያመው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ሲጠራው "የምወድህ ልጄ" እያለ ነበር:: በኤፌሶንም ጵጵስናን ሹሞ ፪ መልዕክታትን ልኮለታል:: ቅዱስ ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያንን ለብዙ ዘመናት አገልግሎ በሰማዕትነት ዐርፏል::
ዛሬ ሥጋው ከኤፌሶን ወደ ቁስጥንጥንያ የፈለሰበት ነው፡፡ ጊዜውም ፫፻፴ [330] ዎቹ መጀመሪያ ላይ እንደሆነ ይታመናል፡፡

"መድኃኒታችን እግዚአብሔር: ተስፋችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዘዘው ትእዛዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ: በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ:: ከእግዚአብሔር ከአባታችን: ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን: ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን . . ." [፩ጢሞ. ፩፥፩]


🕊 † ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት † 🕊

† ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም:: የመላእክት መዓርግ ሲነገር ሚካኤል: ገብርኤል: ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው::

በሦስቱ ሰማያት ካሉት ዘጠኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ [የሥልጣናት] መሪ [አለቃ] ነው:: መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው:: ለኖኅ መርከብን ያሳራው: ከጥፋት ውኃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው::

በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: ቅዱስ ሱርያል በሌላ ስሙ "እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት:: ዛሬ ደግሞ የሊቀ መልአኩ ቅዳሴ ቤቱ ነው::

† የይቅርታ ጌታ መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ አይተወን . . . አይጣለን !

[  † ጥር ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ [ወደ ብሔረ ሕያዋን ያረገበት]
፪. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ [ፍልሠቱ]
፫. ቅዱስ አባ ቢፋሞን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ሰራብዮን ሰማዕት
፭. ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት [ከሰባቱ ሊቃናት አንዱ]

[    † ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ
፪. አቡነ መባዐ ጽዮን
፫. አባ መቃርስ ርዕሰ መነኮሳት
፬. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት [ንጉሠ ኢትዮጵያ]
፭. ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
፮. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ

" የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ:: " † [፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3
2025/07/12 18:29:25
Back to Top
HTML Embed Code: