Telegram Web
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[ 💖 መንፈሳዊው መሰላል 💖 ]


[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ] "መንፈሳዊው መሰላል" ድርሳን ]

🕊

❝ የሕይወት ምንጭ እግዚአብሔር እንደ መሆኑ ፣ ከእርሱ ውጭ በራሱ ሕይወት ያለው ነገር የለም፡፡

ስለሆነም መንፈሳዊ ሕይወት ስንል ሰዎችና መላእክት ከእግዚአብሔር ሕይወትነት ያላቸው ሱታፌ ሲሆን ይህ ሱታፌም አንድ ቦታ ላይ የሚያቆምና የተገደበ ሳይሆን እያደገ የሚሄድ ነው፡፡

እግዚአብሔር ፍጻሜ የሌለውና “እስከዚህ ድረስ” ተብሎ የማይወሰን አምላክ እንደመሆኑ ፣ ከእርሱ ጋር ኅብረትና አንድነት ይኖራቸው ዘንድ በእርሱ ሕይወት የሚሳተፉ ሁሉ ጉዟቸው መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ የለውም፡፡ የመንፈሳዊ ጉዞ አስደሳችነቱም ይህ ነው ፤ ወደማይደረስበት ፣ ግን ደግሞ ከመጀመሪያው ጀምሮ አብሮ ወዳለ አምላክ የሚደረግ የማያቋርጥ ጉዞ !

ይህ ጉዞ ፣ ያዕቆብ ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግቶ ባየው መሰላል አንጻር ሥዕላዊ በሆነ ሁኔታ ተገልጦልናል፡፡ በመሰላሉ ላይ [ ከመሰላሉ ጫፍ ላይ ሳይሆን ከመሰላሉ በላይ ] እግዚአብሔር “ተቀምጦ” ነበር፡፡ መሰላሉ በመሬት ላይ የተዘረጋ መሆኑ እግዚአብሔር ወደ እርሱ የምንወጣበትን የቅድስና መሰላል ልንደርስበት በምንችለው በመሬት ላይ የዘረጋልን መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ፣ እግዚአብሔር ከመሰላሉ በላይ ቆሞ መታየቱ ደግሞ ከላይ ሆኖ “አይዟችሁ ፣ ወደ እኔ ኑ" እያለ በፍቅሩ የሚጠራንና የሚስበን እርሱው ራሱ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ ከታች ከመሬቱ ጀምሮ የሚጠራንና የሚስበን ፣ በመሰላሉ ላይ የትኛውም ደረጃ ላይ ብንደርስም አሁንም ከዚያ በላይ ወዳለው እንድንቀጥል የሚያደርገን ከመሰላሉ በላይ ያለው እርሱ ነው፡፡

እንደዚያ ሆኖም ግን እርሱ ከመሰላሉ በላይ [ ማለትም በባሕርዩ ሊደረስበት የማይችል ] ነው፡፡ እግዚአብሔር ማለት ይህ ነውና ፤ ከራሳችን በላይ ለራሳችን የቀረበ የውስጥና የቅርብ መጋቢና ተንከባካቢ አባት ፣ ሆኖም ግን በባሕርዩ የማይታወቅና የማይደረስበት ረቂቅ አምላክ ! ❞

[   ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ በቅዱስ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]  "መንፈሳዊው መሰላል" ድርሳን ትርጓሜ ላይ የሰጡት አስተያየት  ]


🕊                       💖                     🕊
3👍1
2
                        †                           

†   🕊   ዘ ወ ረ ደ   🕊   †


[ የጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት ! ]

💖

❝ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንደዚህ በልጆቿ ስትደምቅ እናንተም ጉባኤውን ለመታደም ደስ ብሏችሁ ተሰባስባችሁ ስትመጡ ዐይቼ ሐሴት አደረግሁኝ ፤ ደስም አለኝ፡፡ ፊታችሁ እንዴት በደስታ እንደተመላ ስመለከት ጠቢቡ ፦ "ልብ ደስ ሲለው ፊት ይበራል" እንዳለው ልባችሁ ምን ያህል እንደተደሰተ ተገነዘብሁኝ፡፡ [ምሳ.፲፭፥፲፫] በመሆኑም ዛሬ ማለዳ የተነሳሁት ከወትሮ በተለየ ትጋት ነው፡፡ ይኸውም ይህን መንፈሳዊ ደስታ ከእናንተ ጋር እንድካፈልና ቀጣዩ ወራት ቁስለ ነፍሳችሁ ድኅነት የሚያገኝበት ወርሐ ጾም መኾኑን አበስራችሁ ዘንድ ነው፡፡ የሁላችንም ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ልክ እንደ ደግ አባት ባለፉት ወራት ለሠራነው ኃጢአት ሥርየት እናገኝበት ዘንድ ሽቶ መድኃኒት የሚሆን ቅዱስ ጾምን አዘጋጅቶልናል፡፡

ስለዚህ የነፍሳችን ጠባቂ እግዚአብሔር የሕመማችንን ፈውስ የምናገኝበትን መድኃኒት ስላዘጋጀልን እያመሰገንን ወርሐ ጾሙን ደስ ብሎን ልንቀበለው ይገባናል፡፡ ከእኛ መካከል ጾም በመግባቱ አንድስ እንኳን የሚከፋው ወይም የሚበሳጭ ሊኖር አይገባም፡፡ ወርሐ ጾሙን እንዲህ ደስ ተሰኝተን መቀበላችንን ዐይተውም አሕዛብ ይፈሩ ፤ አይሁድም ይራዱ፡፡ በእኛና በእነርሱ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ ዐይተው የማሩ፡፡

የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በዓል የምትሠራው ምእመናን ራሳቸውን መግዛት እንዲችሉ ፣ በበጎ ምግባር ያጌጡ ያሸበረቁ እንዲሆኑ እንደሆነ እነርሱ ግን በዓላትን የሚያደርጉት በዘፈንና በስካር ይህንም በመሰለ በሌላ ጸያፍ ግብር ለመንከባለል እንደኾነ ለይተው ይወቁ፡፡ በእርግጥም በዓል ተከበረ የሚባለው ፦ ሰዎች ነፍሳቸውን ካዳኑበት ፣ ውስጣዊ ሰላምንና ፍቅረ ቢጽን [ወንድምን መውደድ] ገንዘብ ካደረጉበት ፣ ዕለት ዕለት ከሚያጋጥማቸው የነፍስ መታወክ ካረፉበት ፣ ያለ ሁካታና ጋጋታ እንዲሁም እንስሳትን በማረድ ከልክ በላይ ከኾነ መብልና መጠጥ ርቀው ያከበሩት እንደሆነ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በዓል ተከበረ የሚባለው ፦ አርምሞንና ጸጥታን ፣ ፍቅርንና ደስታን ፣ ሰላምንና ራስን መግዛትን ፣ እንዲሁም ሌሎች እዚህ መዘርዘር የማንችላቸውን ብዙ ምግባር ትሩፋቶችን ገንዘብ ያደረግንበት እንደ ኾነ ነው፡፡ ❞

[  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ]


         †               †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
2
Audio
🥰6
8🥰3
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊    ም ክ ረ ቅ ዱ ሳ ን   🕊

▷   "  የመንፈሳዊ ሰው ልብ   "


[    " አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! "    ] 

[                        🕊                        ]
-----------------------------------------------

❝ ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።

አቤቱ ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። ❞ [ መዝ.፶፩፥፱ ]


🕊                       💖                   🕊
3
👍6
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

[  የካቲት ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

🕊 †  ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ †  🕊

ቅዱስ ያዕቆብ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያደገ : የአረጋዊው ቅ/ዮሴፍ የመጨረሻ ልጅ : በንጽሕናውና ድንግልናው የተመሠከረለት : ከጸሎትና ገድል ብዛት እግሩ ያበጠ : የመጀመሪያው የኢየሩሳሌም ኤዺስ ቆዾስ ሲሆን ቁጥሩም ከ፸፪ [72] ቱ አርድዕት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

ይህ ቅዱስ ሐዋርያ በአባቶቻችን ሐዋርያት መካከል ትልቅ ሞገስ የነበረውና የጌታችን ወንድም ተብሎ የተጠራ ነው:: ቅዱስ ያዕቆብ ወላጅ አባቱ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ [የእመቤታችን ጠባቂ] ሲሆን በልጅነቱ ጥላው የሞተችው እናቱ ደግሞ ማርያም ትባላለች:: በቤት ውስጥም ስምዖን: ዮሳና ይሁዳ የተባሉ ወንድሞችና ሰሎሜ የምትባል እህትም ነበረችው::

እናቱ ማርያም ከሞተች በሁዋላ ዕጉዋለ ማውታ [ደሃ አደግ] ሆኖ ነበር:: ነገር ግን በፈቃደ እግዚአብሔር አረጋዊ ዮሴፍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከቤተ መቅደስ ሊጠብቃት [ሊያገለግላት)] ተቀብሎ ሲመጣ ያ ቤተሰብ ተቀየረ:: የበረከት: የምሕረትና የሰላም እመቤት የአምላክ እናቱ ገብታለችና ያ የሐዘን ቤት ደስታ ሞላው::

እመ ብርሃን ግን ገና ወደ ዮሴፍ ልጆች ስትደርስ አለቀሰች:: የአክስቷ ልጆች የሚንከባከባቸው አጥተው ቆሽሸው ነበር:: በተለይ ደግሞ ትንሹ ቅዱስ ያዕቆብ ያሳዝን ነበር:: እመ ብርሃን ማረፍ አልፈለገችም:: ወዲያው ማድጋ አንስታ ወደ ምንጭ ወርዳ ውሃ አምጥታ የሕጻኑን ገላ አጠበችው:: [በአምላክ እናት የታጠበ ሰውነት ምስጋና በጸጋ ይገባዋል!]

እመቤታችን ጌታ ከመወለዱ በፊት ለ፱ [9] ወራት: ከተወለደ በሁዋላ ደግሞ ለ፪ [2] ዓመታት ሕጻኑን ያዕቆብን ተንከባከበችው::

ለ፫ [3] ዓመታት ከ፮ [6] ወራት ግን ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን ይዛ ተሰዳለችና ተለያዩ:: ከስደት መልስ ግን ለ፳፭ [25] ዓመታት ቅዱስ ያዕቆብ ከጌታችን ጋር ሲያድግ ወላጅ እናቱ ትዝ ብላው አታውቅም:: አማናዊቷ እናት ከጐኑ ነበረችና::

ሊቃውንት እንደ ነገሩን እመቤታችን ለቅዱስ ያዕቆብ ያልሰጠችው ነገር ቢኖር ሐሊበ ድንግልናዌ [የድንግልና ወተትን] ብቻ ነው::

ስለዚህም :-

"እመ ያዕቆብ በጸጋ ማርያም ንግሥተ ኩሉ" ይላል መጽሐፍ:: [መልክዐ ስዕል]

ቅዱስ ያዕቆብ "የጌታ ወንድም" ተብሎ በተደጋጋሚ በሐዲስ ኪዳን ተጠርቷል:: ለዚህ ምክንያቱ :-

፩. ለ፴ [30] ዓመታት ሳይነጣጠሉ አብረው በማደጋቸው፡፡
፪. የጌታችን የሥጋ አያቱ [የቅድስት ሐና] የእህት ልጅ በመሆኑ፡፡
፫. በዮሴፍ በኩልም የአንድ ቅድመ አያት ልጆች
በመሆናቸው፡፡
፬. ጌታችን ከትህትናው የተነሳ ደቀ መዛሙርቱን "ወንድሞች" ይላቸው ስለ ነበር ነው:: [ሥጋቸውን ተዋሕዶ ተገኝቷልና]

ራሱ ቅዱስ ያዕቆብ ግን "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ነኝ" ብሎ በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለውን ልዩነት ገልጧል:: [ያዕ.፩፥፩] (1:1) ቅዱስ ያዕቆብ ጌታችን ሲያስተምር ተከተለው::

¤ ከ፸፪ [72] ቱ አርድእት ተቆጠረ
¤ ፫ [3] ዓመት ከ፫ [3] ወር ወንጌልን ተማረ
¤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከድንግል ማርያምና ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ሆኖ "የጌታን ትንሳኤ ሳላይ እሕል አልቀምስም" ብሎ ማክፈልን አስተማረ
¤ መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ወንጌልን አስተማረ
¤ የኢየሩሳሌም የመጀመሪያው ሊቀ ዻዻስ ሆኖ አገለገለ
¤ በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ዘመናት የሐዋርያት
ሲኖዶሶችን በሊቀ መንበርነት መራ
¤ ሙታንን አስንስቶ: ድውያንን ፈውሶ: የመካኖችን ማሕጸን ከፍቶ: አጋንንትንም አስወጥቶ ብዙ ተእምራትን ሠራ:: እጅግ ብዙ አይሁዳውያንን ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሶ መልካሙን ገድል ተጋደለ::

በመጨረሻ ዘመኑ ያላመኑ የአይሁድ አለቆች ወደ ቤቱ ተሰብስበው "የናዝሬቱ ኢየሱስ ማነው የማንስ ልጅ ነው?" ሲሉ ጠየቁት:: እነርሱ ሰይጣን በሰለጠነበት ልቡናቸው "የዮሴፍ ልጅ ነው: የእኔም ወንድሜ ነው" እንዲላቸው ጠብቀው ነበር:: [ሎቱ ስብሐት ወአኮቴት!]

በልቡናቸው ያሰቡትን ተንኮል የተረዳው ሐዋርያ ወደ ቤቱ ጣራ ወጥቶ መናገር ጀመረ:: "ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ወልደ አብ ወልደ ማርያም: ሥግው ቃል: እግዚአብሔር ነው:: እኔም ፍጡሩና ባሪያው እንጂ እንደምታስቡት ወንድሙ አይደለሁም" አላቸው::

ንዴታቸውን መቆጣጠር ያልቻሉት አይሁድ ከላይ ወጥተው ወደ መሬት ወረወሩት:: በገድል የተቀጠቀጠ አካሉንም እየተፈራረቁ ደበደቡት:: አንዱ ግን ከእንጨት የተሠራ ትልቅ ገንዳ አምጥቶ የቅዱሱን ራስ ደጋግሞ መታው:: ጭንቅላቱም እንዳልነበር ሆነ:: ሰማዕቱ ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብ ወደ ወደደው ክርስቶስ በዚህች ቀን ሔደ::

ቅዱሱ ሐዋርያ ያዕቆብ ቤቱን እንደ ቤተ መቅደስ አበው ሐዋርያት ይጠቀሙባት ነበር:: በመላ ዘመኑ የሚያገድፍ ነገር [ጥሉላት] ቀምሶ: ጸጉሩን ተላጭቶ: ገላውን ታጥቦና ልብሱን ቀይሮ አያውቅም::

"ወዝንቱ ጻድቅ እኅወ እግዚእነ::
ኢያብአ ውስተ አፉሁ ሥጋ ወወይነ::
ወኢገብረ ሎቱ ክልኤተ ክዳነ::" እንዲል::

ከጾም: ከጸሎትና ከመቆሙ ብዛትም እግሩ አብጦ አላራምድህ ብሎት ነበር:: ስለዚህም አበው "ጻድቁ [ገዳማዊው] ሐዋርያ" ይሉታል:: ቅዱሱ ሐዋርያ "የያዕቆብ መልዕክት" የሚለውን ባለ፭ [5] ምዕራፍ መልዕክት ጽፏል::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሙ ይባል ዘንድ ካደለው ሐዋርያ በረከትን ያድለን:: በምልጃውም ምሕረትን ይላክልን::

🕊

[  † የካቲት ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [የቅዱስ ዮሴፍ ልጅ : ከ፸፪ [72] ቱ አርድእት አንዱ]
፪. ቅዱስ አባ መላልዮስ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት [በአንጾኪያ ሊቀ ዽዽስና ተሹሞ በአርዮሳውያን ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው]

[   † ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት
፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
፬. ማር ያዕቆብ ግብፃዊ

" የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ: ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች:: ሰላም ለእናንተ ይሁን:: ወንድሞቼ ሆይ! የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት:: ትዕግስትም ምንም የሚጐድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም::" [ያዕ.፩፥፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
1🙏1
4
#እናንተስ_ስትፆሙ እንደግብዝ አትሁኑ
ፆም ማለት በኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትልቅ ቦታ የምንሰጠው ከ3ቱ ቀኖና ውስጥ አንዱነው ሰዎች የሚኖሩት መዝሙረኛው ዳዊት ከፈቃዴ እሰዋልሀለሁ እንዳለ እኛምፈቃዳችንን ሁሉ ለአምላካችን የምናስገዛበት እግዚአብሔር የምንጠላውን ጠልተን የምንወደው አምላክ አይደለም የምንወደውንና የሚያስፈልገንን ትተንና ጠልተን የምናመልከው የምንከተለው አምላክ ነው ምግባችንን ባሎች ሚስቶቻቹን ሚስቶች እንቅልፋችሁን ትታችሁ #ኪዳን እያደረሳቹ የሚያስፈልገንንና የምንወደውን ፍላጎታችንን ሁሉ ለእግዚአብሔር እየሰወዋን የምንፆመው ፆም ነው በእግዚአብሔር ፊትሞገስ የሚያገኘው፡፡ ሊቁ ማር ይህሳቅ "ከመብል ከመጠጥ የሚፆም አንድ በሐሜት የሰውን ስጋ የሚበላ ከሆነ ይህ ፆም #የግብዞች_ፆም ነው እንዳለ ከሐሜትም ተጠበቁ፡፡

#ፆም_የስራ_መጀመሪያ_ናት
#የዝምታን_የምታስተምር_ናት
#ለጸሎት_ምክንያት_ናት
#የወንጌል_ስራ_መጀመሪያ_ናት
#ዝሙትን_መውጊያ_ጦር_ናት

#_ሰናይ__ቀን 🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
6👍2
                       †                           

†   🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †

💖 

[ ዓ ለ ም ን ስ ለ መ ተ ው ! ]

[ ክፍል አንድ ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ምላካችንና ንጉሣችን እግዚአብሔር መልካም ፣ እጅግ መልካምና ከሁሉ ይልቅ መልካም ነው፡፡ [ ለአምላክ አገልጋዮች ስለ እግዚአብሔር በመጻፍ መጀመር ማለፊያ [ደግ] ነው]፡፡

በእርሱ ከተፈጠሩ አዋቂ ከሆኑና በነጻ ፈቃድ ከከበሩ ፍጥረታት አንዳንዶቹ ወዳጆቹ ናቸው ፣ ሌሎቹ እውነተኛ አገልጋዮቹ ናቸው ፣ አንዳንዶቹ የማይጠቅሙ ናቸው ፣ [ ሉቃ.፲፯፥፲ ] [ 17 ፥ 10 ] አንዳንዶቹ ፈጽሞ ከእግዚአብሔር የተለዩ ናቸው ፣ ሌሎቹም ደካማ ፍጥረት ሆነው ሳሉ ጠላቶቹ ናቸው፡፡

በትክክል ለመናገር የእግዚአብሔር ወዳጆች የምንላቸው በእግዚአብሔር ዙሪያ ያሉ አዋቂና ረቂቃን የሆኑ ፍጥረታትን ነው፡፡

የእግዚአብሔር እውነተኛ አገልጋዮች የምንላቸው ያለ ድካምና ያለ ማቋረጥ ሆነው ፈቃዱን የሚያደርጉና የሚፈጽሙትን ነው፡፡

ረብ የለሽ አገልጋዮች ማለታችን ፣ ራሳቸውን እንደ ተጠመቁ የሚቆጥሩ ፣ ሆኖም ግን ለእግዚአብሔር የገቡትን ቃል ኪዳን ለመጠበቅ ያልታመኑ ናቸው፡፡ ከእርሱ የራቁና የተለዩ የምንላቸው ኢአማንያን እና መናፍቃን ናቸው፡፡ በመጨረሻም የእግዚአብሔር ጠላቶች የሚባሉት የጌታን ትእዛዝ ለራሳቸው ያልተቀበሉና ከእርሱ የሸሹ ብቻ ሳይሆኑ ነገር ግን ይህን የሚፈጽሙትን አጥብቀው የሚዋጉም ጭምር ናቸው፡፡ ❞


[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                       💖                     🕊
7👍2
7👍3😢2
                        †                           

†    🕊         ዘ ወ ረ ደ         🕊   †


[  የጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት !   ]

💖

[   ክፍል ሁለት   ]


❝ እንኪያስ እጅግ የምወዳችሁ ምእመናን ሆይ ! ከኹሉም በፊት እነዚህን ነገሮች በስፋት እንነጋገርባቸው ዘንድ ፤ ዳግመኛም አንዳች የሚረባንን ነገር ይዘን ወደ ቤታችን እንመለስ ዘንድ ቃላችንን በታላቅ ትጋትና ጉጉት ሆናችሁ ትቀበሉት ዘንድ አሳስባችኋለሁ፡፡

ኹላችንም ወደዚህ ጉባኤ ስንመጣ እንዲሁና ያለ ዓላማ አይደለም፡፡ ወሬ ለማውራት ፣ ምን እንደተባለ እንኳን ሳንሰማ ለማጨብጨብ ፣ ከዚያም ምንም የሚረባ ነገርን ሳንይዝ ወደ ቤታችን ለመመለስ ወደዚህ ጉባኤ አልመጣንም፡፡ እኔ የመጣሁት ለነፍሳችሁ ድኅነት የሚጠቅም አንዳች ነገርን ለመናገር ነው ፤ እናንተም ስትመጡ በእኔ በባሪያው አድሮ እግዚአብሔር የሚናገረውን ነገር አድምጣችሁ ለመጠቀምና አንዳች የሚረባ ነገርን ይዛችሁ ወደ ቤታችሁ ለመመለስ ነው፡፡

ተመልከቱ ! ቤተክርስቲያን ማለት ቤተ ድኅነት ናት፡፡ ወደ እርሷ የሚመጡትም ለችግራቸው ተገቢውን መድኃኒት አግኝተው መሔድ አለባቸው፡፡ ተግባራዊ የኾነ ለውጥ ሳያመጡ ቃለ እግዚአብሔርን መማር ብቻ ምንም ጥቅም እንደሌለው ሲናገርም ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ እንዲህ ብሏል ፦

"በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቁት ሕግን የሚያደርጉት እንጂ ሕግን የሚሰሙ አይደሉም፡፡" [ሮሜ.፪፥፲፫]

በቃል መነገሩ ፣ በልብ መታሰቡ ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ ይበልና አምላካችን ክርስቶስም ሲያስተምር ፦

"በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡" ብሏል [ማቴ.፯፥፳፩] ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ ! ቃሉን በመስማታችን ብቻ አንዳች የምንጠቀመው ነገር ስለሌለ የሰማነውን የምናደርግ እንጂ የምንሰማ ብቻ አንሁን፡፡ እንዲህ ከሆነም እምነታችን ሕይወት ያለው እምነት ይሆናል፡፡

በመኾኑም ስለ ጾም የሚሰጠውን ስብከት ለማዳመጥ እዝነ ልቦናችሁን ክፈቱ፡፡ ከትሕትና እና ዓይናፋር ሙሽሪት ጋር ለማነጻጸር ያህል ፦ ሙሽሪቱን በሰርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች አስቀድመው ቤቱን ያስጌጡታል ፡ ይጠርጉታል፡፡ የቆሸሸ ልብስን የለበሰ ሰው ወደ ሰርጉ አዳራሽ እንዳይገባ ያደርጉታል፡፡ ወደ አዳራሹ መግባት የሚችለው የሰርግ ልብስ የለበሰ ሰው ብቻ ነው፡፡

እናንተም እንዲሁ ልታደርጉ ይገባችኋል ፦ ልቡናችሁን በማንጻት ፣ አብዝቶ ከመብላትና ራስን ካለመግዛት በመራቅ - የምግባር እናት ፣ የማስተዋልና የሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትሆን ጾምን ደጀ ልቡናችሁን በመክፈት ልትቀበሏት ይገባችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ታላቅ ሐሴት ታደርጋላችሁ ፤ እርሷም ቁስለ ነፍሳችሁን ትፈውስላችኋለች፡፡

ሌላ ምሳሌ መስዬ ብነግራችሁ ፦ ሐኪሞች በህሙማን ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻና መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ ሕሙማኑ ምግበ ሥጋን ከመውሰድ እንዲቆጠቡ ያደርጓቸዋል፡፡ ሕሙማኑ ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከሉ ግን ሐኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት የተፈለገውን ያህል ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም የነፍስንና የሥጋን ቁስል የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚህ በላይ ልንሆን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡ ድህነትን የምንሻ ከሆነ ልቡናችንን ንጹህና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል ፤ እንዲህ ካልሆነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡ ❞

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]


      †                 †                †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
2
🥰4
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ዐ ቢ ይ ጾ ም     🕊

▷   ❝  ዘ ወ ረ ደ   ❞


[ [ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ ] ] 

[                        🕊                        ]
-----------------------------------------------

❝ በመለኮት ሞት ሳይኖርበት በሥጋ ሞትን ገንዘብ አደረገ ፤ በመለኮት መወሰን ሳይኖርበት በሥጋ ተወሰነ ፥ የማይመረመር ሰማያዊ እርሱ ሥጋን ተዋሕዶ በምድር ተገለጠ ፤ የማይታየው ታየ ፥ በኃጢአት ወድቆ የነበረ የቀደመ ሰው አዳምን ዳግመኛ ያከብረው ዘንድ እግዚአብሔር ፍጹም ሥጋን ነፍስንም ተዋሕዶአልና። ❞

[  ቅዱስ ጎርጎርዮስ  ዘእንዚናዙ ]


🕊                       💖                   🕊
1👍1
2025/07/12 22:56:11
Back to Top
HTML Embed Code: