Telegram Web
1
#ጾም_ከሆድ ብቻ አይደለም
#ዐይን ከዝሙት ይጾማል፡፡
#ምላስ ከሀሜትና ከስድብ ይጾማል፡፡
#እጅ ከዘፈን ጭብጨባ ይጾማል፡፡
#ስሜት ከሆታ ይጾማል፡፡
#ጆሮ ከመጥፎ ወሬ ይጾማል፡፡

ከመብል ብዛት ጨጓራ ያርፋል፡፡
ጾም ሁለንተናዊ ነው  የጠገበን ያበርዳል፡vየቆሸሸን ያጸዳል፡  ሰውን ከእንስሳት የሚለየው ጾም ነው
ጾም ሲመጣ ሳጥናኤል ይናደዳል፡ ስጋ ይጨነቃል፡፡
ነፍስ ግን ደስታውን አትችለውም፡፡
ጾምን አምላክ በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀን ጹሞ በተግባር ያስተማረን ነው፡፡
መጾም አምላካዊ ባህሪን መላበስ ነው፡፡
ዛሬ መጾም አቅቶት ምግብ ሲውስ የነበረው ስጋ በስብሶ አፈር መሆኑ አይቀሬ ነው፡ ዐይን ቢያምር ፈራጭ ነው፡ ገላ ቢለሰልስ አፈር ነው፡፡
አንጎል በጥበብ ቢጠበብ ነገ ይበላሻል፡፡ ጥፍርም ይነቀላል፡፡ ዛሬ ይምንኮራበት ተክለ ቁመና ነገ አፈር ይሆናል ነፍስ ግን ህያው ናት የአምላክ እስትንፋስ ናትና ፆሙን በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስጨርሰን አሜን 🙏🙏🙏

         
#ሰናይ__ቀን 🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
9🙏5👍3
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †

💖 

    [   ዓ ለ ም ን   ስ ለ መ ተ ው !   ]

           [     ክፍል ስድስት     ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

የቀደመው ሙቀት ሊመለስ የሚችለው ... !

❝ ገና በጅምሩ ከውጊያ ተጋድሎ መዘግየትና በዚህም ምክንያት የመምጣታችንን ምልክት [ማስረጃ]  ለገዳዩ መስጠት በጣም የተጠላና አደገኛ ነገር ነው። ጽኑ የሆነ ጅማሮ በርግጥ ኋላ ላይ ደከም ስንል የሚጠቅመን ነው። መጀመሪያ ላይ ብርቱ ፣ በኋላ ግን ዛል የምትል ነፍስ በቀደመ ቅንዓቷ ትውስታ የምትገፋፋ ናት፡፡ በዚህም መንገድ ሁሌም አዳዲስ ክንፎች የሚገኙ ናቸውና፡፡

ነፍስ ራሷን ስትክድና በረከቷን እንዲሁም ትኵሳትን መናፈቅ ስታጣ ፣ ይህ የማጣቷ መንስኤ ምን እንደ ሆነ በጥንቃቄ ትመርምር፡፡ ለዚህ መንስኤው ምንም ሆነ ምን ራሷንም በናፍቆትና በቅንዓት ሁሉ ታስታጥቅ፡፡ የቀደመው ሙቀት ሊመለስ የሚችለው በወጣበት ተመሳሳዩ በር ብቻ ነው፡፡

ከፍርሃት የተነሣ ዓለምን የሚተው ሰው በመዐዛ እንደሚጀምር ዳሩ ግን በጢስ እንደሚጠናቀቅ የሚቀጣጠል ዕጣን ነው፡፡ የሚያገኘውን ዋጋ አስቦ ዓለምን የሚተው ሰው ሁሌም በተመሳሳይ አቅጣጭ እንደ ሚዞር የወፍጮ ድንጋይ ነው፡፡ ነገር ነገር ግን እግዚአብሔርን ከመውደዱ የተነሣ ከዓለም የሚለይ ሰው ገና ከጅምሩ እሳትን አገኘ ፤ ነዳጅ እንደ ተደረገበት እሳትም ፈጥኖ በዝቶ ይቀጣጠላል፡፡ ❞


[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                       💖                     🕊
2👍2
4
                       †                           

†    🕊  ተግባራዊ ክርስትና  🕊   †

💖 

     [   ጥቅም አልባ እውቀት !   ]

            [     ክፍል አንድ     ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

ዓለማዊ ወሬዎችን እያስወገድኩ ነው ....!


❝ ክርስቲያናዊ ፍጹምነትን ለማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ሕሊናህን ለነፍስህ ከማይጠቅም ወሬ መጠበቅ አለብህ፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ዘመኑ የመረጃና የመረጃ ጥበብ ዘመን ነው፡፡ ዓለም በቲቪ፣ በመጻሕፍት፣ በጋዜጦች ብቻ ሳይሆን በመረጃ መረብ ጭምር የሚያጥለቀልቅ መረጃን ከምንጊዜም በላይ እያቀረበችልን ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ጥቅም የለሽ መረጃ እኔ የአእምሮ ብክለት ብዬ ለምጠራው ችግር ይዳርጋል፡፡ በዚህ ዘመን ለሥራቸው ውጤታማነት ቢጠቅምም ባይጠቅምም መረጃን በመረጃነቱ ብቻ የሚፈልጉ የመረጃ ሱሰኞች አሉ፡፡

በዐቢይ ጾም ወቅት የማደርገውን ልንገራችሁ ፤ በሬድዮ ዜናን ከመስማት ፣ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ከማንበብ እከለከላለሁ፡፡ እመኑኝ ምንም ነገር አያመልጠኝም ፤ አይጎድልብኝም ፤ ይልቁንስ ሕሊናዬ ከመረጃ ብክለት ነፃ ይሆናል ፤ ስለዚህ በትክክል እንደሚሰራ አምናለሁ፡፡

የአንድ መነኩሴ ታሪክ ሰምተን ነበር ፤ ይህ መነኩሴ ከሌሎች መነኮሳት ጋር ሲነጋገር ቆይቶ ወደ በዓቱ ከሔደ በኋላ እጅግ በተደጋጋሚ በአቱን ሲዞር አንድ መነኩሴ ተመለከተውና ምን እያደረገ እንደሆነ ጠየቀው ፤ እርሱም መለሰ "ስናወራቸው የነበርናቸውን ዓለማዊ ወሬዎችን እያስወገድኩ ነው ፤ ወደ በዓቴ ይዤ መግባት አልፈልግም፡፡ ❞

[ አቡነ አትናስዮስ እስክንድር ]


🕊                       💖                     🕊
3👍1
5
🕊

[  † እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሆሴዕ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †  ቅዱስ ሆሴዕ ነቢይ  †  🕊

† ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን [አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር] : መጻዕያትን [ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን] የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: [ሐዋ.፲፩፥፳፯] ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::

ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: [ቅዳሴ ማርያም]

የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: [ዮሐ.፬፥፴፮]

ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: [ማቴ.፲፫፥፲፮ , ፩ዼጥ.፩፥፲] ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት

¤ ፲፭ [15] ቱ አበው ነቢያት :
¤ ፬ [4] ቱ ዐበይት ነቢያት:
¤ ፲፪ [12] ቱ ደቂቀ ነቢያትና
¤ ካልአን ነቢያት ተብለው በ፬ [4] ይከፈላሉ::

"፲፭ [15] ቱ አበው ነቢያት" ማለት :-

- ቅዱስ አዳም አባታችን
- ሴት
- ሔኖስ
- ቃይናን
- መላልኤል
- ያሬድ
- ኄኖክ
- ማቱሳላ
- ላሜሕ
- ኖኅ
- አብርሃም
- ይስሐቅ
- ያዕቆብ
- ሙሴና
- ሳሙኤል ናቸው::

"፬ [4] ቱ ዐበይት ነቢያት"

- ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
- ቅዱስ ኤርምያስ
- ቅዱስ ሕዝቅኤልና
- ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

"፲፪ [12] ቱ ደቂቀ ነቢያት"

- ቅዱስ ሆሴዕ
- አሞጽ
- ሚክያስ
- ዮናስ
- ናሆም
- አብድዩ
- ሶፎንያስ
- ሐጌ
- ኢዩኤል
- ዕንባቆም
- ዘካርያስና
- ሚልክያስ ናቸው::

"ካልአን ነቢያት" ደግሞ :-

- እነ ኢያሱ
- ሶምሶን
- ዮፍታሔ
- ጌዴዎን
- ዳዊት
- ሰሎሞን
- ኤልያስና
- ኤልሳዕ . . . ሌሎችም ናቸው::

ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::

- የይሁዳ [ኢየሩሳሌም]:
- የሰማርያ [እሥራኤል] ና
- የባቢሎን [በምርኮ ጊዜ] ተብለው ይጠራሉ::

በዘመን አከፋፈል ደግሞ :-

- ከአዳም እስከ ዮሴፍ [የዘመነ አበው ነቢያት] :
- ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል [የዘመነ መሳፍንት ነቢያት]
- ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት [የዘመነ ነገሥት ነቢያት]
- ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ [የዘመነ ካህናት ነቢያት] ይባላሉ::

ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::

ቅዱስ ሆሴዕ ቁጥሩ ከ፲፪ [12] ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ/ል/ክርስቶስ በ፰ መቶ [800] ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ ፲፬ [14] ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::

ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ሆሴዕ 'ዖዝያ' በመባልም ይታወቃል:: ቅዱሱ ነቢይ የቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ-ቃል ባልንጀራ የነበረ ሲሆን በ፬ [4] ነገሥታት ዘመን [ዖዝያን : ኢዮአታም : አካዝና ደጉ ሕዝቅያስ] ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናግሯል:: የትንቢት ዘመኑም ከ፸ [70] ዓመት በላይ ነው::

ከ፲፪ [ 12 ]ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሆሴዕ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራም በስፋት ተንብዩዋል:: ፲፬ [14] ምዕራፎች ያሉት የትንቢቱ ጥራዝ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል:: ሆሴዕ ማለት መድኃኒት ማለት ነው:: የመዳን ትምሕርትንና ትንቢትን ሊናገር ተመርጧልና::

† ቸር አምላከ ነቢያት የነቢያቱን መከራ አስቦ ከመከራ: በእንባቸውም ከእንባ ይሰውረን:: ከተረፈ በረከታቸውም አያጉድለን::

🕊

[   † የካቲት ፳፮ [26] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ሆሴዕ ነቢይ [ከ፲፪ [12]ቱ ደቂቀ ነቢያት]
፪. ቅዱስ ሳዶቅ ሰማዕት
፫. ፰፻፰ ["808"] ሰማዕታት [ከቅዱስ ሳዶቅ ጋር የተሰየፉ]

[    † ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፭. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

" ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንመለስ:: እርሱ ሰብሮናልና: እርሱም ይፈውሰናል:: እርሱ መትቶናል: እርሱም ይጠግነናል:: ከሁለት ቀን በሁዋላ ያድነናል:: በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል:: በፊቱም በሕይወት እንኖራለን:: እንወቅ:: እናውቀውም ዘንድ እንከተል . . . "
[ሆሴዕ.፮፥፩-፫]  (6:1-3)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
4👍2
Audio
👍1
4👍1
#አርጋኖን__ዘረቡዕ 

ምዕራፍ ፩ 

፩. ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሜ እግዚአብሔርን አመግናለሁ፡፡ ስላንቺም፡፡ (ሮሜ ፩- ፰)
፪. የውዳሴሽ ወሬ በዓለም ሁሉ ተሰምቷልና በመንፈስ ቅዱስ እንደተናገርሽ እንዲህ ስትይ እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል፡፡ (ሉቃ፣ ፩፣ ፵፰) 
፫. በውነት ምስጋና ይገባሻል፡፡ የእግዚአብሔር እናቱ ሁነሻልና በውነት መደነቅ ይገባሻል፡፡ ዓለምን ሁሉ በመሐል እጁ የያዘ እርሱን ወልደሻልና በዕውነት ብፅዓን ይገባሻል ለዕውነተኛ ፀሐይ መውጫ ሆነሻልና፡፡ 
፬. በዕውነት መመስገን ይገባሻል ለማለዳው ኮከብ ምሥራቅ ሆነሻልና በውነት መደነቅ ይገባሻል፡፡ ለጥምቀት ልጆች መመከያ ሆነሻልና፡፡ በውነት ብፅዕና ይገባሻል፡፡ ለሃይማኖት መሠረት ጽናተ ሆነሻልና፡፡ 
፭. ከኪሩቤል ክብር ገናንነት ላንቺ ይገባል፡፡ ከሱራፌልም ውዳሴ ከመላእክትም እልልታ ከመላእክት አለቆችም ዝማሬ ላንቺ ይገባል፡፡ 
፮. ከነቢያት ትንቢት ከሐዋርያት ስብከት ላንቺ ይገባል፡፡ ከቅዱሳን ሰማዕታት እናታችን መባል ከመሐይምናንም እመቤታችን መባል ከክርስቲያንም ሁሉ አፍ የመድኃኒታችን ቀንድ መባል ላንቺ ይገባል፡፡ 
፯. ከመሲሓውያን ነገስታት አፍ ንግሥታችን መባል ከልዑላንም መላእክት በላይ ከፍ ከፍ ማለት ከታችኞችም ፍጡራን ላንቺ መገዛት ይገባል፡፡ እንግዲህ አንቺ ከሰማይ ትበልጫለሽ ከተራሮችም ከፍ ትያለሽ፡፡ ስለ አንቺም እንዲህ እላለሁ ከፀሐይ ብርሃን ከጨረቃም ድምቀት አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ 
፰. ስለ አንቺ እንዲህ እላለሁ፡፡ ከአርዮብ መልክ ከመብረቅም ብርሃን አንቺ ታበሪያለሽ፡፡ ስላንቺ ደግሞ እንዲህ እላለሁ በሰማይ ካሉ ትጉሃን መላእክት ትከብሪያለሽ፡፡ ከመናብርትም ከሥልጣናትም ትቀደሻለሽ፡፡ 

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
11👍1🙏1
#መድኃኒዓለም_ዛሬም_የወደድከኝ_ተመስገን!

የነፍሴ ንጉስ የህይወቴ ቤዛ ጌታዬኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! አመሰግንሃለሁ ። እኔን መውደድህ
#ይገርመኛል እንደሞተ ውሻ የምቆጠረውን ማፍቀርህ #ይደንቀኛል ። ኣምላኬ ሆይ ! ምኔን አይተህ ነው #የወደድከኝ ? ራሴን በጽሞና ሳየው ራሴን እንኳ መውደድ አቃተኝ ። አንተ ግን ህይወት ንጹህ ሳለህ እንደ ወንጀለኛ #ተከሰስክልኝ ። የኔ አፍቃሪ ንጉስ የማይገባኝን ልትሰጠኝ የማይገባህን መከራ #ተቀበልክልኝ ።የምለው ባጣ እንዲሁ ተመስገን ! እልሃለው ።በማላውቀው ጉዳይ እፈርዳለሁ አንተ ግን ብምታውቀው ጉዳይ #ትምራለህ ። እባክህን እውቀትና ዕድሜ ያልለወጠኝን እባክህ አንተ የልቤ ጌታ #ለውጥልኝ ። እንደወደድከኝ መጠን ልወድህ #አልችልም ነገር እባክህን አቅም ስጠኝና እንደ አባቶቼ ቅዱሳን አብዝቼ #ልውደድህ! ዛሬም ተመስገን!

        
#መልካም__ቀን 🙏

ለመቀላቀል👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
8🙏3
🕊              

[  † እንኳን ለታላቁ ሊቅና ጻድቅ ቅዱስ አንስጣስዮስ እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  ቅዱስ አንስጣስዮስ ሊቅ  †  🕊

† ቅዱስ አንስጣስዮስ በ ፬ [4] ኛው ክ/ዘመን የተነሳ ሶርያዊ የነገረ መለኮት ሊቅ: ገዳማዊ ጻድቅና የመንበረ አንጾኪያ ሊቀ ዻዻሳት ነበር:: ቅዱሱ ርጉም አርዮስን ካወገዙ ፫፻፲፰ [318]ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው:: በወቅቱ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ሱባኤውንና ጉባኤውን የመሩ ሲሆን አንዱ ይህ ቅዱስ ነው::

ከ ፭ [5] ዓመታት በሁዋላም ብዙ ድርሳናትን ጽፎ: ሐዋርያዊ አገልግሎቱን ፈጽሞ በ፫፻፴ [330] ዓ/ም አርፏል:: ያረፈው ግን አርዮሳውያን ባቀረቡት ክስ በሃሰት ተመስክሮበት በግፍ ተሰዶ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ስለ ውለታው የውዳሴ ድርሳን ጽፎለታል::


🕊   †  አቡነ ዓምደ ሥላሴ  †  🕊

† እኒህ ታላቅ ጻድቅ ሐዋርያዊ አባት አቡነ ዓምደ ሥላሴ የትውልድ ሃገራቸው ጎጃም ሲሆን የተወለዱት በዚሁ ዕለት [የካቲት ፳፯ (27) ነው:: ጻድቁ በአጼ ሱስንዮስ [በ፲፯ [17]ኛው መቶ ክ/ዘ)] የነበሩ ድንቅ ሠሪ : ተአምረኛና ገዳማዊ አባት ናቸው::

የካቲት ፲፮ [16] ቀን መንኩሰው ወደ ተጋድሎ ገብተዋል:: በዋልድባ በነበራቸው ቆይታም እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት የካቲት ፲፮ [16] ቀን እንድትከበር ማድረጋቸውም ይነገራል:: ጻድቁ በሌሎች ገዳማትም የነበሩ ሲሆን ዛሬም ድረስ ረድኤታቸው የሚደረግበት : ስማቸው የሚጠራበት ገዳም ግን ማኅበረ ሥላሴ ይባላል::

ገዳሙ የሚገኘው በሃገራችን ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ : በመተማ በርሃ ውስጥ ነው:: ይህንን ቅዱስ ገዳም የመሠረቱትም ራሳቸው አባ ዓምደ ሥላሴ ናቸው:: ገዳሙ ዛሬም ብዙ ምሑራንና መናንያን ያሉበት : በደህና ሁኔታም የሚገኝ ነው:: ግን በርሃውን የኔ ብጤ ደካማ ሰው የሚችለው አይደለም::

ስለ ጻድቁ ዓምደ ሥላሴ ከሚነገሩ ታሪኮች ቅድሚያውን የሚይዘው የተዋሕዶ ጠበቃነታቸው ነው:: በ፲፮፻፫ [1603] ዓ/ም ዼጥሮስ [ፔድሮ] ፓኤዝ የሚባል ካቶሊካዊ እሾህ ወደ ሃገራችን ገብቶ ነበርና ንጉሡን ሱስንዮስን አባብሎ ተዋሕዶን አስካዳቸው:: ነገሩ ውስጥ ለውስጥ ሲበስል ቆይቶ በ፲፮፻፱ [1609] ዓ/ም በመገለጡ እነ ራስ ዮልዮስ ለሃይማኖታቸው ጠዳ ላይ ተዋግተው ግንቦት ፮ [6] ቀን ተሰው::

ይህ ነገር ሲሰማ ወንድ ሴት : ትልቅ ትንሽ ሳይመረጥ በገጠሩም : በከተማውም : በገዳሙም ያሉት ሁሉ የተዋሕዶ ልጆች መንቀሳቀስ ጀመሩ:: ፯ [7] ዓመታት እንዲህ አልፈው በ፲፮፻፲፮ [1616] ዓ/ም ግጭቱ በይፋ ተጀመረ::

"ተዋሕዶን ካልካዳችሁ" በሚል በቀን እስከ ፰ሺህ [8,000] ሰው በሰይፍ ታረደ:: ይህን ያደረጉት ደግሞ አልፎንሱ ሜንዴዝ : ንጉሡ ሱስንዮስና ጀሌዎቻቸው ነበሩ::

በጊዜውም ከቤተ መንግሥት እነ ንግሥት ወልድ ሰዓላ [የሱስንዮስ ሚስት] : ከጻድቃን አበው ዘርዓ ቡሩክ ዘግሺ : ሐራ ድንግል ዘደራ : ምዕመነ ድንግል ዘጩጊ : ዓምደ ሥላሴ ዘማኅበረ ሥላሴ . . . ከቅዱሳት እነ ፍቅርተ ክርስቶስ : ወለተ ዼጥሮስ : ወለተ ዻውሎስ : እኅተ ዼጥሮስ . . . ለሃይማኖታቸው ተዋሕዶ ጥብቅና ቆመው ሕዝቡን አስተማሩ:: መከራም ተቀበሉ::

ብዙ ኢትዮዽያውያን የመከራ ጽዋን ተጐንጭተው ለክብር ከበቁ በሁዋላ የእግዚአብሔር ፍርድ ተገለጠ:: በጻድቃኑ እነ አባ ዓምደ ሥላሴ ሐዘን ንጉሡ ታመመ:: ምላሱ ተጐልጉሎ ወጣ::

በዚህ ጊዜ አቤቶ ፋሲለደስ ለአባ ዓምደ ሥላሴና ለሌሎቹ ቅዱሳን "አባቴን አድኑልኝ! ተዋሕዶም ትመለስ" አላቸው:: ጻድቁም ከባልንጀሮቻቸው ጋር ጸልየው ንጉሡን አዳኑት:: በፈንታውም ይህንን አሳወጁ::

† ፋሲል ይንገሥ!
ሃይማኖት (ተዋሕዶ) ይመለስ!
የሮም ሃይማኖት ይፍለስ! †

ከዚህ በሁዋላ በ፲፮፻፳፬ [1624] ዓ/ም ፋሲል ሲነግሥ አባ ዓምደ ሥላሴ ለገዳማቸው ብዙ ቦታ አስከልለው : በተጋድሎ ኑረው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

† አምላከ ቅዱሳን በቀናችው እምነት ተዋሕዶ ሁላችንም እስከ ፍጻሜ ዘመናችን ያጽናን:: ከበረከተ ቅዱሳንም ይክፈለን::

🕊

[  † የካቲት ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. አባ አንስጣስዮስ ርቱዓ ሃይማኖት [ዘአንጾኪያ]
፪. አቡነ ዓምደ ሥላሴ

[    † ወርኀዊ በዓላት    ]

፪. የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
፪. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፫. ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት ሁሉ አለቃ]
፬. ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
፭. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፮. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፯. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት

" የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::"
[፩ጴጥ.፪፥፳፩-፳፭] [1ዼጥ. 2:21-25]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
1👍1
3
2025/07/14 00:57:37
Back to Top
HTML Embed Code: