Telegram Web
🥰5
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     [  ም ክ ረ   ቅ ዱ ሳ ን    ]   🕊


▷   " በእግዚአብሔር ላይ ታመን "


  [   በሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስ  ]

[                         🕊                         ]
--------------------------------------------------

❝ በእግዚአብሔር ታመን ፥ መልካምንም አድርግ ፥ በምድርም ተቀመጥ ፥ ታምነህም ተሰማራ።❞ 

[ መዝ.፴፯፥፫ ]


🕊                       💖                   🕊
👍4
1👍1
🕊

[  † እንኳን ለኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊 † እመ ምዑዝ [ እም ምዑዝ ] †  🕊

† ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሐዋርያዊት: ጻድቅትና ሰማዕት ናት:: ይህስ እንደምን ነው ቢሉ :-

- ወር በገባ በ፳፱ [29] በቤተክርስቲያናችን ታስበው ከሚውሉት እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ከገባላቸው [ ከሰጣቸው ] እናቶች ኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ [ እመ ምዑዝ ] ትገኛለች:: ፍቅርተ ክርስቶስ [ እመ ምዑዝ ] ማን ናት? ምን ቃል ኪዳን ተሰጣት ? ያደረገችውን ተጋድሎ በጥቂቱ እንመልከት :-

✞ ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ
ይወስዳል፡፡ [ ማቴ.፲፥፵ ] [ 10፡40 ] ✞

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመቂት ወረዳ ጥባ ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ በ፲፮ [16] ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ ኪዳነ-ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳም ትገኛለች፡፡

ይህች ገዳም ከአዲስ አበባ በደሴ ወደ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ፮፻፷፭ [665] ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ ገራገር [ፍላቂት] ከምትባለው ከተማ በመውረድ በእግር 2፡30 እንደተጓዙ ከ፫፻፸ [370] ዓመት ባለይ ያስቆጠረችውን እመ ምዑዝ ኪዳነምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በአንድ ቀን የሠራቻትና ለጌታ በአራቱም አቅጣጫ የሰገደችውን ታላቅና ድንቅ ቤተመቅደስ ያገኛሉ፡፡

የዚህች ታላቅ ገዳም መስራች ኢትጵያዊት ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በደቡብ ጎንደር ደራ ፎገራ አንበሳሜ ወረዳ ልዩ ስሙ አቡነ ሐራ ገዳም አዋሳኝ ከተታ ማርያም ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚያዚያ ፬ [4] ቀን ተፀንሳ ታህሳስ ፳፱ [29] በጌታ ልደት ቀን ተወለደች፡፡

አባቷ ላባ እናትዋ ወንጌላዊት የተባሉ እግዚዘብሔርን የሚወዱ ትዕዛዙን የሚከብሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ መሀን ሆነው ልጅ ባመውለዳቸው እያዘኑ ተግተው ወደ እግዚአብሔር በመፀለያቸው ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን የመሰለች ልጅ: በፀሎትዋ ለሀገር ለወገን የምትበቃ ሰጥቷቸዋል፡፡

ከዚያም ፹ [80] ሲሆናት ለልጅነት ጥምቀት ወደ ቤተ መቅደስ በወሰዷት ጊዜ ከጥምቀት በኋላ ስጋ አምላክ ስትቀበል [ስትቆርብ] "ሕይወት የሆነውን ቅዱስ ስጋህን ክቡር ደምህን የሰጠኸኝ አምላኬ ክብር ምስጋና ይግባህ" ብላ አመስግናለች፡፡ ስመ ክርስትናዋ ማርያም ፀዳለ ሲሆን የአለም ስሟ 'ሙዚት' ነው፡፡ ፍቅርተ ክርስቶስ የምንኩስና [የቆብ] ስሟ ነው፡፡

እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አባ ዳንኤል ከሚባል አባት መፅሐፍን እየተማረች ካደገች በኋላ ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ እናትና አባቷ ሊድሯት በመፈለጋቸው ዘርዓ ክርስቶስ ለሚባል ከደጋግ ሰዎች ወገን ለሆነ ሰው አጋቧት፡፡

ማታ እንደ ሙሽሮች ደምብ ወደ ጫጉላ ቤት ሲገቡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ዘርዓ ክርስቶስን "ወንድሜ ሆይ! እኔ የእናት አባቴን ፍቃድ ለመፈፀም ነው እንጂ ስጋዊ ሙሽራ መሆን አልፈልግም ፡፡ ፍላጎቴ የእግዚአብሔር ሙሽራ መሆን ነው" በማለት ብታማክረው ቅዱስ ዘርዓ ክርስቶስም ፀጋ እግዚአብሔር የበዛለት ሰው ነበርና "እኔም እናት አባቴን ላክበር ፈቃዳቸውን ለመፈፀም ነው እንጂ የስጋ ፈቃድ የለኝም በማለት ተነጋገሩ::

በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ለቤተሰቦቻቸው: ለአገሬው እንደ ባልና ሚስት ግን በንፅህና ለ፵ [40] ዓመት ሁለቱም በድንግልና ኖረዋል፡፡

ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ ቢግራቸውም ሁለቱም "ይህስ አይሆንም" ብለው ለ፵ [40] ቀን በጾም: ፀሎት: በትጋት ጸልየዋል፡፡ መልአኩ ተገልጦ "ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ሁለታችሁም ድንግልናችሁ አይፈርስም ብሎ ነግሮአቸዋል፡፡

ከዚያም ወንድ ልጅ ወልደዋል:: ህፃኑ በተወለደ በ፯ [7] ዓመቱ በቅዱስ ሚካኤል እቅፍ ገነትን ለ፯ [7] ቀናት ከጎበኛት በኋላ ወደ ምድር ሲመልሰው "በእናት አባቴ አምላክ ይዤሃለሁ ወደዚች ወደ ከፋች ዓለም አትመልሰኝ" ብሎ ቢለምነው ቅዱስ ሚካኤልም ከአምላክ ጠይቆ በብሔረ ህያዋን የህፃናት አለቃ ተብሎ እንዲቀመጥ አድርጎታል፡፡ ስሙም ዳግማዊ ቂርቆስ ተብሏል፡፡

ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶና ቅዱስ ዘርዓ ክርስቶስም ልጅ ከወለዱ በኋላ እንደ ቀደሞው በቅድስና: በንፀህና ፀንተው ኑረዋል፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው አፄ ሱስንዮስ ሃይማኖቱን ለውጦ 'ሁለት ባህርይ የሚሉ ካቶሊኮችን በመቀበሉ ክርስቲያኖችን እየገደለ ነው' የሚል ወሬ ሰምተው ወደ ንጉሱ በመሄድ ሳይፈሩ ስለ ተዋህዶ ሃማኖታቸው በንጉሱ ፊት መስክረዋል፡፡

ንጉሱም በጣም የበዛ መከራን አድርሶባቸዋል፡፡ መከራ በበዛ ቁጥር እነርሱም እየፀኑ ተከታዮቻቸውንና የንጉሱን ሠራዎቶች ሳይቀር አሳመኑ:: ፷ ሺህ [60,000] ክርስቲያኖችም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡

ንጉሱም በጣም የበዛ መከራ አድርሶባቸዋል፡፡ መከራ በበዛ ቁጥር እነርሱም እየጸኑ ተከታዮቻቸውንና የንጉሱን ሰራዊቶች እያሳመኑ ቢያስቸግሩ በሰማዕትነት አንገታቸውን አስቆርቷቸዋል፡፡ አንገታቸውም ሲቆረጥ ከሁለቱም ደም ውሃ ወተት ፈሷዋል፡፡

በዚያን ዘመን ከእነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ጋር ሰማዕትነት ከተቀበሉት ውስጥ የማህበረ ስላሴው ጻድቁ አምደ ስላሴ: የጎረጉር ማርያም አባ መርአዊ: የመሲ ኪዳነ ምህረት እመ ወተት እና ከ፷ [60] ሺ በላይ ክርስቲያኖች ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡

ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንገቷ ከተቆረጠና ሰማእትነት ከተቀበለች በኋላ ወደ ምድር መልሶ አንገቷን ከቀሪው የሰውነቷ ክፍል ጋር አዋህዶ ከአንቅልፍ አንደሚነቃ ሰው ቀስቅሶ አስነስቷቷል፡፡ ከዚያም ከአቡነ ማርቆስ ስርዓተ ምንኩስናን በመቀበል ዋልድባ ገዳም ለ፬ [4] ዓመት አገልግላለች፡፡

ከዚህም ከ፭፻ [500] የሚበልጡ ተከታዮችዋን መነኮሳትን አስከትላ በሰሜን ወሎ ቆቦ ወረዳ ወደምትገኘውና በፃድቁ በአባ ጉባ ተመስርታ ጠፍታ ወደ ነበረችው ራማ ኪደና ምህረት አንድነት ገዳም በመሄድ ገዳሟን አቅንታ: የወንድ የሴት ብላ ስርዓት ሰርታ: ገዳሟን አስተካክላ: ፭፻ [500] የሚሆኑ አገልጋች መነኮሳትን አኑራ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ ጀምራለች፡፡

በመንገዷም ላይ ሰውን የሚበሉ ወደ ሚኖሩበት አካባቢ በመድረስ እነርሱም እርሷንና ፷ [60] የሚሆኑ አገልጋዮችዋን ዓይኖቻቸውን በጉጠት በማውጣት ለ፬ [4] ወራት በጨለማ ቤት ውስጥ ዘግተውባቸዋል፡፡ ከአራት ወር በኋላም በዓል አድገው ለመብላት ከቤት ቢያወጧቸው መልካቸው እንደ ፀሐይ የሚያበራ ቢሆንባቸው "አንቺ ሴት ምንድን ናችሁ?" ብለው ጠይቀዋታል፡፡

እርሷም ክርሰቲያን መሆናቸውንና እነሱ የስላሴ ሕንፃ የሆነውን የሰውን ልጅ መብላት እንደሌለባቸው ብትመክራቸው "ምን አንብላ?" ብለዋታል፡፡ እርሷም ከራማ ኪዳነ ምህረት ስትነሳ የእህል ዘርን በአገልጋዮቿ አሲዛ ነበርና ስንዴውን በአንድ ቀን ዘርታ: በቅሎ: ታጭዶ: ደርቆ: ተፈጭቶ ለምግብነት በቅቷል፡፡

እርሷ ቀምሳ ብታቀምሳቸው እንደማር እንደ ወተት የሚጣፍጥ ሆኖላቸው በደስታ ተመግበውታል፡፡ ከዚያም እንደዚህ እያደረጉ እየሰሩ እንዲበሉ አስተምራ: አስጠምቃ ከ፮ [6] የሚበልጡ አብያተ ክርስቲያናትን አስተክላላቸዋለች፡፡
1
ከዚያም የተወሰኑ አገልጋዮችን አስቀምጣላቸው ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ለ፯ [7] ዓመታት በአየሩሳሌም ከኖረች በኋላ የእመቤታችን በዓል ለማክበር ወደ ግብፅ በመሄድ ላይ ሳለች በመንገድ አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብታ ስትፀልይ እመቤታችን በስዕሏ ላይ ተገልጣ: ቦታዋ በኢትዮጵያ መሆኑን ነግራ: እጇን ዘርግታ "ወደ ኢትዮጵያ ሂጂ" ብላ ነገረቻት::

በኋላ በብርሃን አምድና በቅዱስ ሚካኤል እየተመራች አሁን ወደ ምትታወቅበትና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ወደ ተገለፀበት እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህረት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም ደርሳለች፡፡ በቦታው ስትደርስ የቦታው ልምላሜ የሚያስደስት ነበርና "ይህች ቦታ ምን ታምር!" ብላለች፡፡ ቦታውም እስከ አሁን ድረስ ምንታምር በመባል ይጠራል፡፡

ምንታምር ላይ ከአገልጋዮቿ ጋር በመሆን አርፋ ሳለ ከኢየሩሳሌም መርቶ ያመጣት የብርሃን አምድ በዚያ ቦታ ላይ በስፋት ረቦ [ከምድር እስከ ሰማ ተተክሎ] ብታየው: መልአኩም "ቦታሽ ይሄ ነው" ብሎ ቢነግራት በዚያው ተቀምጣለች፡፡

የቦታው ባለ አባት "ይህን ቦታ ልቀቂ" ቢሎ ቢጠይቃት "እግዚአብሔር የሰጠኝ ቦታዬ ነው" ብላዋለች፡፡ እርሱም ለክስ ወደ ጎንደር በመሄድ አፄ ሱስንዮስ አርፈው አፄ ፋሲል ነግሰው ነበርና እሳቸውን ፍርድ ቢጠይቃቸው በዝና ያውቋት ነበርና "ቤተ ክርስቲያን ካልተሰራ ትልቀቅልህ: ከተሠራ ግን ሌላ ቦታ ይሰጥሃል" የሚል ፍርድ አስፈርዶ ነበር::

ሲመለስ ቅዱስ ሚካኤል ቀድሞ "ቶሎ ቤተ ክርስቲያን ስሪ እንዲህ የሚል ፍርድ ተፈርዷል ብሎ ነግሯት " ታህሳስ ፲፬ [14] ቀን ከነግህ ፀሎት በኋላ በሰንሰልና በስሚዛ ግድግዳዋን: በአይጥ ሀረግ ማገር አድርጋ: የግድግዳ ቤተ መቅደስ በዕለተ አርብ: በአንድ ቀን ሰርታ ታህሳስ ፲፮ [16] ቀን እሁድ ታቦተ ኪዳነ ምህረትን አስገብታ ቅዳሴ አስቀድሳለች::"

ቅዳሴውም ከተፈፀመ በኋላ ጌታችን ከቅዱስ መንበሩ ላይ እንዳለ ሆኖ ከእናቱ ከእመቤታችን ጋራ ታያቸው፡፡ ከመንበሩ ወርዶም ይህን ቦታ በባረከው ጊዜ የስሚዛው ቤተ መቅደስ በአራቱም አቅጣጫ ለፈጣሪው ሰገደ፡፡

የመሬት መናወጥም ሆነ:: ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም
"ልታጠፋን መጣህን? ቤተ ክርሰቲያኔንስ ልታፈርሳት ነው?" ብላ ብትጠይቀው "ይህ የሰንሰል ቤተ መቅደስሽ ዳግም እስከምመጣ ድረስ ሳይፈርስ: ሳይታደስ ፀንቶ ይኖራል ፣ በውስጡም እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ የክሀድያንና ፣ መናፍቃን እግር አይገባበትም ፣ በውስጧ ቁርባንን የተቀበሉ ሁለ ኃጢያታቸው ይሰረይላቸዋል ፣ ዘወትር ምህረቴ በረከቴ ከእነርሱ ጋር ይኖራል" በማለት ተናግሮ ተሰወራቸው፡፡

ከዚያም በኋላ መነኮሳትና መነኮሳይያት የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን የትሩፋት ዜናዋን ሰምተው ከየአቅጣጫው ተሰበሰቡ፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም በአምላክ ሀይል ተጋድሎአቸውን ይፈፅሙ ዘንድ ታስተምራቸው ፣ ትመክራቸው ፣ በተግባርም እያሳየቻቸው ለብዙ ዘመናት ከኖሩ በኋላ በገዳሙ ላይ የአጋንንት ፆር እንዳይነሳ ወንዶቹን ለብቻ ሴቶቹን ለብቻ አደረገች፡፡

ዘወትርም እንዳይተያዩ የእግዚአብሔር መልዐክ በቅድስተ ፍቅርተ ክርሰቶስ ፀሎት ይጠብቃቸው ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከዚህ ኃላፊ ዓለም መለየቷ በቀረበ ጊዜ ሁለት መላዕክት ወደ እርሷ መጥተው በብርሃን  ሰረገላ ጭነው ወደ ደብረ ነባት [ወደ ብሔረ- ህያዋን] ወስደው በዚያ ቅዱስ ቁርባንን አቀብለው ወደ ቦታዎ መለሷት፡፡

መልዐኩም "ከጻማ: ከድካም: ከመታረዝ: ከረሐብ ከጥም: ከመትጋት: ከእንባ: ከዚህ ዓለም የምትለይበት ጊዜ እነሆ ደረሰ" አላት፡፡ የካቲት ፳፯ [27] ቀንም ወደ ምስራቅ እጇን ዘርግታ ቆማ ስትጸልይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከደስታ ብርሀን ጋር ያማረ ሽታ መላ::

ጌታችን ከአዕላፋት መላዕክትና ቅዱሳን ጋር ወደ እርሷ መጣ፡፡ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ሰገደች፡ ተንበረከከች: እጅግም አለቀሰች፡፡ ከወደቀችበት ቦታ አንስቶ "ላጠፋሽ አልመጣሁም ወዳጄ ላከብርሽ ነው እንጂ" አላት፡፡

"የዘለአለም መንግስት አዘጋጅቼልሻለሁና ደስ ይበልሽ"፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ቃል ኪዳን እንዲገባላት ተማጸነችው:: ጌታችንም "ሁሉም እንደ ቃልሽ ይሁንልሽ:: በስምሽ ስሜ ተጨምሯልና ለቤተ ክርስቲያንሽ መባ የሰጠ ፣ የተላከ ፣ የተቀበረ ፣ ቤተ መቅደስሽ መጥቶ የተሳለመ ፣ እስከ ፲፪ [12] ትውልድ የምህረት ቃል ኪዳን ሰጠሁሽ::

በረከቴም በቤቱና በልጆቹ በገንዘቡም ላይ ይደር:: የገድልሽ መጽሐፍ ባለበት አጋንንት [ሰይጣናት] አይቀርቡም:: በአዝመራ ስምሽን በጠሩት ጊዜ የለመለመ ይሁን:: በጸሎትሽ የተማጸነ ሁሉ ባለጤና ይሁን::

ስምሽን በእውነት የሚጠራ የከበረ ነው፡፡ ያለመጠራጠር በቀናች ሐይማኖት የገድልሽን መጽሐፍ የጻፈ : ያጻፈ : ያነበበ : የተረጎመ በሐይማኖት የሰማ: እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ የሰጠ ኃጢያቱ ይሰረይለታል:: ስለ ድካምሽ ስለ ትሩፋትሽ ፯ [7] አክሊሎችን እና ይህን ሁሉ ቃል ኪዳን ሰጠሁሽ፡፡ ላልምረው ቦታሽን አላስረግጠውም" ብሏት ወደ ሰማይ አረገ፡፡

በማግስቱ ትንሽ ህመም ታመመች ደናግል መነኮሳትን ጠርታ የእረፍት ቀኗ መድረሱን ነገረቻቸው:: ከመካከላቸው አንዷን ለገዳሙ አስተዳዳሪነት መርጣ በፍቅር ስም ተሰናበተቻቸው፡፡ የዳዊት መዝሙርንም ስትጸልይ የካቲት ፳፱ [29] ቀን እሁድ አጥቢያ ጠዋት በጌታ በዓል አንቀላፋች [ነፍሷ ከስጋዋ ተለየች]፡፡

ጌታችንም ከእናቱ: ከቅዱሳኑ ጋር መጥቶ ነፍሷን ተቀብሎ ወደ ዘለዓለም ገነት ወሰዳት፡፡ ቅዱሳንም
ከመላእክት ጋር እልል እያሉ እያመሰገኑ ወደ ዘለዓለም ቦታ ገነት አስገቧት፡፡ ከቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ መቃብር ላይ ፵ [40] ቀናት ብርሃን ሲበራበት ታይቷል፡፡

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት : በመቂት ወረዳ ጥባ ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ በ፲፮ [16] ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳምም በዓላቶቿ የሚከበሩት ታህሳስ ፲፮ [16] የቅዳሴ ቤቷ እንዲሁም የካቲት ፳፱ [29] ቀን በዓለ እረፍቷ ይከበራል፡፡

† ከቅድስት እናታችን በረከት አምላክ አይለየን::

🕊

[  † የካቲት ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
፪. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ [ጻድቅና ሰማዕት]
፫. ቅዱሱ ሕፃን [የፍቅርተ ክርስቶስ ልጅ]
፭. ቅዱስ ቢላካርዮስ ዘሃገረ አርሞኒ [አረጋዊ: ደራሲ: ጻድቅና ሰማዕት]

[    † ወርኀዊ በዓላት     ]

፩. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪. ቅድስት አርሴማ ድንግል
፫. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ

" መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ:: ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው:: እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥራዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት::" † [ምሳሌ.፴፩፥፳፱]  [31:29]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
3👍1
3🥰2👍1
#እኔ__ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ #እሰግዳለሁ
፤ አቤቱ፥ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅህ ምራኝ፤ መንገዴን በፊትህ አቅና።
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፤ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
፤ አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፤ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና።
፤ በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ #ለዘላለሙ ደስ ይላቸዋል፥ እነርሱንም ትጠብቃለህ፤ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ #ይመካሉ
፤ አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 5፣7-11


#___ሰናይ____ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
10👍1
🕊                       💖                      🕊

[       የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት      ]

💖

[ እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። ]

                      †                           

[        ምኵራብ !           ]

" ሦስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት " ምኵራብ " ይባላል፡፡ ምኵራብ አምልኮተ እግዚአብሔር ሲፈጸምበት ፣ ሕገ ኦሪት ሲነበብበት የነበረ በአይሁድ የሚሠራ መካነ ጸሎት ነው፡፡ ዘወትር ቅዳሜ ብዙ ሕዝብ ይሰበሰብበት ስለ ነበር ጌታችን ለማስተማር ብዙ ጊዜ በምኵራብ ተገኝቶአል፡፡

ስያሜው የተወሰደው በዮሐንስ ፪፥፲፬ "ወረከበ በምኵራብ እለ ይሠይጡ አልህምተ ወአባግዐ ወአርጋበ … ፤ በመቅደስም በሬዎችን ፣ ላሞችን ፣ በጎችን ፣ ርግቦችን ፣ የሚሸጡትን አገኘ …" ተብሎ ከተገለጸው ኃይለ ቃል ላይ ሲኾን ፣ ‹ምኵራብ› የሚለው ቃልም በአማርኛ ‹መቅደስ› ተብሎ ተተርጕሟል፡፡

ምኵራብ የሚባለው ሳምንት ጌታችን ወደ ምኵራብ ገብቶ ማስተማሩ የሚነገርበት ፤ "ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል ፤ እናንተ ግን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት" ብሎ በምኵራብ ይሸጡ ፣ ይለውጡ የነበሩትን የገሠፀበት ፤ ቤተ መቅደስን የከብት መንጃ የወርቅና የብር መነገጃ ያደረጉ ሰዎችን ከነሸቀጣቸው ከቤተ መቅደስ ያስወጣበት ፤ ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ፣ የስሙ መጠሪያ፣ የጸሎት ሥፍራ መኾኗን ያስረዳበትና ያወጀበት ፤ በቤተ መቅደስ የንግድ ሥራ ማከናወን እንደማይገባ ያረጋገጠበት ዕለት ነው፡፡ "

[ በመምህር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ ]

†                       †                       †

[ " ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና።

ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል ፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው
።" [ ማቴ . ፳፩ ፥ ፲፪ ]

🕊                        💖                       🕊
👍1
👍10
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   [  ሦ ስ ተ ኛ ሳ ም ን ት    ]   🕊


▷   " ም ኩ ራ ብ "

  [    በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን   ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

[                         🕊                         ]

❝ ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ ፥ ሊያነብም ተነሣ። ❞ 

[ ሉቃ.፬፥፲፮ ]


🕊                       💖                   🕊
3👏1
4👍2
#ምኩራብ
የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት

ምኩራብ ማለት ቤተ-ጸሎት ሲኾን ኢየሱስ በሰንበት ቀን ከአይሁድ ምኩራብ ገብቶ ቢመለከት ምኩራቡን ገበያ አድርገው ሲገበያዩበት አገኛቸው።

"ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል" ያለውን አላነበባችኹምን?
ትንቢተ ኢሳይያስ ፭፮፥፯
እናንተ ግን ገበያ አደረጋችኹት በማለት በተናቸው! ዕቃውንም ገለባበጠባቸው በሮቹንም፣ በጎቹንም በገመድ እየገረፈ አባረራቸው። የዮሐንስ ወንጌል ም. ፪፥፩፯ (ማቴዮስ ፪፩፣፩፫)

ደቀ መዛሙርቱም የቤትኽ ቅንዓት በላኝ ተብሎ የተጻፈው ለካ አኹን ተፈጸመ ብለው አስተዋሉ።


ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
9
2025/07/14 22:24:11
Back to Top
HTML Embed Code: