Telegram Web
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                       †                        

🕊

† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። †
በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል::

    🕊  †  የጠበል በዓል  †   🕊

[   ለእህታችን የተፈጸመ ድንቅ ተአምር  ]

በአንጀት ካንሰር በሽታ በጽኑ ታማ ለስምንት ዓመታት በጽናት እግዚአብሔርን ስትማጸን ቆይታ በሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል የተፈወሰችና ተአምር የተፈጸመላት እህታችን ታሪክ

[ ክፍል - ፪ - ]

† አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን::

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
2
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት  "    ]
             
             [     ክፍል ሰባት    ]

❝ ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። ❞ [ ፪ጴጥ.፩፥፳ ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                         👇
🕊

[ † እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሳሙኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †  ነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል  †  🕊

† እሥራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው ከነዓንን ከወረሱበት ዘመን ጀምረው መሳፍንትና ካህናት ያስተዳድሯቸው ነበር:: በወቅቱ ታዲያ ክህነት ከምስፍና ተስማምቶለት ኤሊ የተባለ ሊቀ ካህናትና ልጆቹ [አፍኒና ፊንሐስ] ያስተዳድሩ ጀመር::

በዘመኑ ደግሞ ማኅጸኗ ተዘግቶባት ዘወትር የምታለቅስ ሐና የሚሏት ደግ ሴት ነበረች:: እግዚአብሔር የእርሷን ጸሎትና የሊቀ ካህናቱን ምርቃት ሰምቷልና ቅዱስ ልጅን ሰጣት:: "ሳሙኤል" አለችው:: "ልመናየን አምላክ ሰማኝ" ማለት ነውና::

ሐና ስዕለቷን ትፈጽም ዘንድ ሳሙኤልን በሦስት ዓመቱ ለቤተ እግዚአብሔር ሰጠችው:: በዚያም ስብሐተ እግዚአብሔርን እየሰማ : ማዕጠንቱን እያሸተተ : ከደብተራ ኦሪቱ ሳይለይ በሞገስ አደገ:: የኤሊ ልጆች [አፍኒና ፊንሐስ] ግን በበደል ላይ በደልን አበዙ::

ወቅቱ የአሁኑን ዘመን ይመስል ነበር:: ሁሉም ሰው ክፋተኛ የሆነበት በመሆኑ : እግዚአብሔር ርቆ ስለ ነበር ትንቢትና ራዕይ ብርቅ ነበር:: አምላክ ተቆጥቷልና ሳሙኤልን በሌሊት ሦስት ጊዜ ጠራው:: ነቢዩም ታጥቆ የፈጣሪውን ቃል ሰማ:: በዚሕም የተነሳ ታቦተ ጽዮን ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ ተማረከች:: ከሰላሳ አራት ሺ በላይ ሕዝብ በኢሎፍላውያን አለቀ:: አፍኒና ፊንሐስም ተገደሉ:: ኤሊም ወድቆ ሞተ::

ከዚህች ቀን በኋላ ቅዱስ ሳሙኤል በእሥራኤል ላይ ነቢይና መስፍን ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ ሁሉ እንደሚገባው እየኖረ : የእግዚአብሔርን ለእሥራኤል : የእሥራኤልን ለእግዚአብሔር ሲያደርስ ኑሯል:: ሕዝቡ ንጉሥ በፈለጉ ጊዜ ሳዖልን ቀብቶ አነገሠላቸው:: እርሱ [ሳዖል] እንደ ሕጉ አልሔደምና ፈጣሪ ናቀው::

ሳሙኤል ግን ደግ አባት ነውና ክፋተኛውን [ሳዖልን] ከጌታው ጋር ያስታርቅ ዘንድ ብዙ ደከመ:: አለቀሰም:: እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን:- "አትዘን! እንደ ልቤ የሆነ : ፈቃዴን የሚፈጽም ዳዊትን አግኝቸዋለሁና እርሱን በእሥራኤል ላይ አንግሠው" አለው:: ቅዱስ ሳሙኤልም ወደ ቤተ ልሔም ሔዶ : ከእሴይ ልጆችም መርጦ ልበ አምላክ ዳዊትን ቀባው : አነገሠውም::

ቅዱስ ሳሙኤል በተረፈው ዘመኑ ለፈጣሪው እየተገዛ ኑሯል:: ነቢዩ ዘወትር ከእጁ የሽቱ ሙዳይና የቅብዐት እቃ [ቀንድ] አይለይም ነበረ:: እነዚህም የድንግል ማርያም ምሳሌዎች ናቸውና አባ ሕርያቆስ :-
"ሙዳየ ዕፍረት ወቀርነ ቅብዕ ዘሳሙኤል" ብሎ አመስግኗታል:: ነቢዩም በወገኖቹ መካከል በዚሕች ቀን አርፏል:: እሥራኤልም አልቅሰውለታል::

🕊  † ቅዱስ ሉክያኖስ  †   🕊

† ዳግመኛ በዚህ ቀን ቅዱስ ሉክያኖስ ይታሠባል:: በቀደመ ሕይወቱ ጣዖት አምላኪና አጣኝ የነበረው ቅዱሱ ማንም ሳያስተምረው ክርስቲያኖቹን በመመልከት ብቻ አምኗል:: የወቅቱ ክርስቲያኖች አኗኗራቸው : ትጋታቸው : ጽናታቸውና ፍቅራቸው እንዲሁ ይስብ ነበር::

ከእነርሱ እምነት መውጣቱን የተመለከቱ ኢ-አማንያን አታልለው ሊመልሱት ሞከሩ:: እንቢ ቢላቸው በድንጋይ ጥርሱን አረገፉት:: ደሙን አፈሰሱ:: አሁንም በሃይማኖተ ክርስቶስ በመጽናቱ በዚሕ ቀን [ሰኔ ፱ (9) ] ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ በመስቀል ላይ ሰቅለው ገድለውታል::

† የቅዱሳኑን በረከት አምላካቸው ያድለን::

🕊

[ † ሰኔ ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ
፪. ቅዱስ ሉክያኖስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ዮሐንስ

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት ]
፪. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ [ ኢትዮጵያዊ ]
፫. ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት [ ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ ]
፬. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
፭. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ [ ኢትዮጵያዊ ]
፮. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ [ ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት ]

" እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ . . . " † [ዕብ. ፲፩፥፴፪]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3
እግዚአብሔር ሆይ ሁለመናዬ ያንተ ነው ፡እንደ አንተ ፈቃድ እንጂ እንደ እኔ አይሁን ለምትፈልገኝ አላማ ሁሉ ይሄው ተጠቀምብኝ ፣ምንም ነገር አልፈልግም የምፈልገው ካንተ ጋር መሆን ብቻ ነው ። ገና ከመጀመርያው ምን ያህል እንደ ምትወደኝ ተረድቻለሁ! እኔም የምትወድደኝን ያህል እወድህ ዘንድ እሻለሁ ! አንተን ማገልገል እንዴት ያለ ክብር ነው !እንዴትስ ያለ ብኩርና ነው! እንዴትስ ያለ ደስታ ነው! እባክህ እርዳኝ! ጌታ ሆይ ለፈቃድህ መገዛት እንድችል አጽናኝ በልቤ ውስጥ አንተ ብቻ ኑር እስከ መጨረሻው ያንተው አድርገኝ፤ ለዘላለም
በቤተ መቅደስክ ልኑር አሜን 🙏


#መልካም_ቀን🙏

ለመቀላቀል👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
12🙏1
🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

 [  ስለእኛ ይህን ሁሉ ገንዘብ አደረገ !  ]

🕊                    💖                       🕊

❝ እግዚአብሔር አብን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው እርሱ ቀምቶ እግዚአብሔር የሆነ አይደለም ራሱን አዋርዶ የተገዢ [ የአዳምን ] ባሕርይን ገንዘብ አደረገ እንጂ ተብሎ እንደ ተጻፈ። [ ፊልጵ.፪፥፮ ና ፯ ]

መለኮትስ እንደ ሰው በድንግል ማሕፀን ያለ የዕለት ፅንስ መሆን በድንግል ማሕፀን ሳለ በሰማይም በምድርም ምሉ ነው ፤ ለፅንሱ ወራት ዘጠኝ ወር እስኪፈጸም ድረስ እንደ ሰው ሁሉ በየጥቂቱ አደገ። [ ሉቃ.፪፥፬፯ ]

ከዚህ በኋላም የእግዚአብሔርን ቃል ከእርስዋ በነሳው ሥጋ ወለደችው ፤ በጨርቅ ጠቅልላ በበረት አስተኛችው ፤ ፍጹም መለኮቱ የሰውን ሥጋ ተዋሐደ ተብሎ እንደ ተጻፈ ፤ ሰው ሆኖ ሠላሳ ዘመን እስኪመላ ድረስ በአካል ፥ በጥበብ ፤ በሕዋሳት መጽናት በየጥቂቱ አደገ። [ ሉቃ.፪፥፶፪ ። ቆላ.፪፥፱ ]

በየጥቂቱ ያደገ መለኮት አይደለም በሰማይም በምድርም ምሉእ ነውና ፤ በሁሉ በሰማይም በምድርም የመላው እንዴት ያድጋል ?! ከተዋሐደው ሥጋ ጋር አንድ አካል ፤ አንድ ባሕርይ ነውና በየጥቂቱ ማደግን ገንዘብ አደረገ እንጂ። [ መዝ.፻፫ [፻፪)፥፳፪ ። ኢሳ.፷፮፥፩ ። ግብ.ሐዋ.፲፯፥፵፱ ]

ከኃጢአት ብቻ በቀር እንደ እኛ በሥራው ሁሉ ተፈተነ ፤ ተራበ :ተጠማ : ደከመ : አንቀላፋ : በላ ጠጣ : አለቀሰ : ተከዘ : አዘነ : ታመመ : ሞተ : ተገነዘ : በመቃብርም ተቀበረ። እግዚአብሔር ቃል በተዋሐደው በሥጋ ስለእኛ ይህን ሁሉ ገንዘብ አደረገ ። ❞

[    🕊   ቅዱስ ቄርሎስ   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                     🕊                      💖
🙏1
1
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †


          [   ክፍል  ሠላሳ ስምንት  ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ልጄ ሆይ ፥ ገና ከጅምሩ በፍጹም ነፍስህ ራስህን ለተዋርዶዎች አሳልፈህ ከሰጠህ ፣ የተባረከውን ውሳጣዊ ሰላም በመፈለግ ብዙ ዓመታት አትደክምም፡፡

ለእግዚአብሔር እንደምትናዘዝ አድርገህ ለረዳትህ እየሰገድህ መናዘዝን ተገቢ እንዳልሆነ አድርገህ አታስብ፡፡ የተፈረደባቸው ወንጀለኞች በአሳዝኝ አቀራረባቸውና በጽኑ ኑዛዜያቸው እንዲሁም ልመናቸው የጨካኙን ዳኛ ልብ ሲያራሩና ቍጣውንም ወደ ምሕረት ሲመልሱ ተመለከትሁ፡፡

ለዚህ ነው መጥምቁ ዮሐንስ እንኳ ወደ እርሱ ይመጡ የነበሩትን ከጥምቀት በፊት እንዲናዘዙ ያደርግ የነበረው ፣ የእነሱን ኃጢአቶች ለራሱ ማወቅ አስፈልጎት አይደለም ፣ ዳሩ ግን ለድኅነት እንዲረባቸው ነው እንጂ፡፡

ከኑዛዜም በኋላ እንኳ ቢሆን የምንጠቃ ብንሆን አንደነቅ ፤ ከትዕቢት ጋር ከመዋጋት ከርኵሰት [ ከዕድፈት ] ጋር መዋጋት የሚሻል ነውና፡፡

የባሕታውያንንና የግሑሳንን ታሪክ ስትሰማ ከመጠን በላይ የምትጓጓና የምትደነቅ አትሁን፡፡ አንተ በሰማዕትነት የመጀመሪያ ሰልፍ ላይ በመራመድ ላይ ያለህ ነህና፡፡ ከዚህ በኋላ በተለይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሐኪም የሚያሻን ነንና ብትወድቅ የተግባር ሜዳህን አትተው፡፡ የሚረዳው ሳለ እግሮቹ በድንጋይ የሚደናቀፍ ሰው ፣ በርግጥ ባለ መረዳቱ የተነሣ የሚሰናከል ብቻ አይደለም ፣ የሚሞትም ጭምር ነው እንጂ፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                      💖                     🕊
1
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷    "  የ እ ር ጋ ታ ዓ ይ ቶ ች   " 

💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖  ]

[                       🕊                        ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው። ❞

[  ያዕ . ፪ ፥ ፳፮  ]



🕊                       💖                   🕊
1
2
🕊

[ † እንኳን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ የተድላና የደስታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† በዚሕች ቀን ለ፵ [ 40 ] ዓመታት በመላው ዓለም የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት የተከፈቱበት ቀን ይታሠባል:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ : በዓለመ መላእክት ከታየች በኋላ :-

- አበው ተስፋ ሲያደርጓት
- ነቢያት ትንቢት ሲናገሩላት
- ሱባኤ ሲቆጥሩላት
- ምሳሌም ሲመስሉላት ኑረዋል::

† ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ :-

- በመጸነሱ ተጸንሳ
- በመወለዱ ተወልዳ
- በጥበብና በሞገስ አብራው አድጋ
- በጥምቀቱ ተጠምቃ
- በትምሕርቱ ጸንታ
- በደሙ ተቀድሳ
- በትንሣኤው ከብራ
- በዕርገቱ ሰማያዊነቷን አጽንታ
- በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላት በይፋ ለልጆቿ ተሰጥታለች::

† አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት በመላው ዓለም ዞረው በብዙ ድካም የሠሯት ቤተ ክርስቲያን ለ፪፻ [200] ዓመታት እጅግ የበዙ መከራዋችን አሳልፋለች:: በ፪፻፷፭ [265] ዓ/ም የመጣባት መከራ ግን በዓለም ታሪክ እስካሁን አልታየም:: የወቅቱ ኃያላን ነገሥታት [ዲዮቅልጢያኖስና መክስምያኖስ] ዓለምን ለ፪ [2] ተካፍለው ክርስቲያኖችን የማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ::

በመጀመሪያም በዓለም ያሉ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት እንዲቃጠሉ ካልሆነም እንዲዘጉ : በፈንታቸው ደግሞ አዽሎን: አርዳሚስ የተባሉ ጣዖቶች እንዲተኩ ትዕዛዝ ተሰጠ:: ለ፵ [40] ዓመታት ክርስቲያን ስለሆኑ ብቻ ሚሊየኖች ተገደሉ: ታሰሩ: ተሰቃዩ: ተሰደዱ:: መጻሕፍት ተቃጠሉ: አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ወደሙ::

በአባቶቻችንና እናቶቻችን ላይ ልንናገረው ከምንችለው በላይ ጭንቅና መከራ ደረሰ:: ነገር ግን ቅዱሳኑ ያን ሁሉ ችለው ጸኑ:: ፵፯ [47] ሚሊየን የሚያሕሉትን ደግሞ ሰይፍና እሳት በላቸው:: በዛ ዘመን አንድ ቤተ ክርስቲያን ለማግኘት ከአሕጉር አሕጉር መሔድን ይጠይቅ ነበር::

ከዚሕ ሁሉ በኋላ ግን እግዚአብሔር "ግፍ ይበቃል" ሲል በ፫፻፭ [305] ዓ/ም ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ነገሠ:: መክስምያኖስን በጦርነት ሲማርከው አውሬው ዲዮቅልጢያኖስ ግን አብዶ ሞተ:: ይህ ከተደረገ ከዓመታት በኋላ [በ፫፻፲፫ [313] ዓ/ም] ታላቁ ቆስጠንጢኖስ የዓለም መሪዎችን በዚሕች ቀን ጠርቶ አዋጁን በአዋጅ ሻረው:: "ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ:: በፈንታው ደግሞ ሁሉም ጣዖት ቤቶች ይዘጉ" አለ::

በሺሕ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን በወርቅ አስለበጠ:: በዚሕ ምክንያት ይህች ቀን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን "ዕለተ ትፍሥሕት [የደስታ ቀን]" ተብላ ትከበራለች::

† ቸሩ አምላክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከመከራ ይሠውርልን:: ከበረከቷም ያድለን:: ትውልዱ ደካሞች ነንና ከማንችለው ፈተናም ይጠብቀን::

🕊

[ † ሰኔ ፲ [ 10 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፪. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
፫. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት [ከታላላቆቹ ሶፍያዎች አንዷ ናት]
፬. ቅዱሳት ሰማዕታት ደባሞንና ብስጣሞን [የቅድስት ሶፍያ ልጆች]
፭. ቅዱስ አውሎጊስ ሰማዕት
፮. ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
፫. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ እልፍዮስ]
፭. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
፮. ቅዱስ ዕፀ መስቀል

" ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ:: ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ:: ኢየሩሳሌምስ እርስ በርሷ እንደ ተገለጠች ከተማ ተሠርታለች . . . ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም በውስጥሽ ሰላም ይሁን አልሁ:: ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ:: " † [መዝ.፻፳፩፥፩-፱] (121:1-9)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🙏1
4
2025/07/12 11:35:45
Back to Top
HTML Embed Code: