Telegram Web
👍1
#እኔ__ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ #እሰግዳለሁ
፤ አቤቱ፥ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅህ ምራኝ፤ መንገዴን በፊትህ አቅና።
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፤ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
፤ አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፤ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና።
፤ በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ #ለዘላለሙ ደስ ይላቸዋል፥ እነርሱንም ትጠብቃለህ፤ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ #ይመካሉ
፤ አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 5፣7-11


#___ሰናይ____ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
13🙏1
🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

     [   በእኛም ባሕርይ ተገለጠ  !    ]

🕊                    💖                       🕊


❝ ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ከአብ ባሕርይ የተገኘ አንድ ወልድ ቃል እንደሆነ ተናገሩ ፤ ከባሕርይ አምላክ [ ከዘለዓለም ] የተገኘ የባሕርይ አምላክ ፤ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ፤ ሁሉ የተፈጠረበት እርሱ ነፍስን ሥጋን ነሥቶ ሰው ሆነ።

ከድንግልም በሥጋ ይወለድ ዘንድ ወደደ። በእኛም ባሕርይ ተገለጠ ፤ ሰው የሆነበት ባሕርይ ይህ ነው። አብ አንድ ነው ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አንድ ነው ፤ ይኸውም ከአብ የተገኘ አንድ ቃል ነው ፤ ሰው ሆነ። ገንዘቡ ከሚሆን ከልዑል ጌትነቱም አልተለየም ሰውም ቢሆን በአምላክነቱ ጸንቶ ይኖራል። ገዢ እርሱ በተገዢ ባሕርይ ተገለጠ ፤ ንዴት በሚስማማው በእኛ ባሕርይ ሳለ ፍጹም መለኮት ገንዘቡ ነው።

በድካመ ሥጋ ተገልጦ ሳለ የኀያላን መላእክት ጌታ ነው ፤ በሰው መጠን በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ሳለ ከፍጥረት ሁሉ በላይ ነው ፤ ከኃጢአት ብቻ በቀር በሰውነቱ የሰውነት ሥራ ሁሉ ገንዘቡ ነው። አንድ የእግዚአብሔር ልጅ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ፤ ሕይወት ፣ ኀይል የሚሆን እርሱ እግዚአብሔር ባሕርዩ ያልነበረ ሥጋን ተዋሐደ ፤ ሰው ስለሆነም በሥጋ ተገለጠ ፤ በማይመረመር ረቂቅ ተዋሕዶ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ ሥጋን ስለተዋሐደ የሰውነትን ሥራ ሁሉ ገንዘብ አደረገ ፤ ሥጋም ገንዘቡ ነው የሌላ አይደለም። ❞

[    🕊   ቅዱስ ቄርሎስ   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                     🕊                      💖
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †


           [   ክፍል  አርባ ሁለት  ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ገዳም ምድራዊ ገነት ነው፡፡ ስለዚህ ልባችንን ጌታን እንደሚያገለግሉ መላእክት ይመስል ዘንድ እናዘጋጀው፡፡ አንዳንዴ በዚህ ገነት ውስጥ የሚኖሩ የድንጋይ ልቦች አሏቸው፡፡ ዳግመኛም አንዳንዴ በጸጸት አማካኝነት መጽናናትን አግኝተው እንዲህ ባለው መንገድ ትዕቢትን አሊያም አጉል ድፍረትን በማስወገድ ፣ ድካማቸውንም በእንባዎቻቸው
ያቀላሉ፡፡

ጥቂት እሳት ብዙውን ስም ያለዝበዋል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ጥቂት ትሕትና [ ተዋርዶ ] ዘወትር ቍጠኝነትን ፣ ቸልተኝነትን ፣ የልባችንንም ድንዳኔ ሁሉ ድንገት አለዝቦ ፣ አጣፍጦ ፣ በማስወገድ ይደመስሰዋል፡፡

አንድ ጊዜ ሁለት ሰዎች በድብቅ ተቀምጠው [ ቁጭ ብለው ] የመናንያንን ጻማዎች ሲመለከቱና ልቅሶአቸውን ሲሰሙ ተመለከትሁ፡፡ ሆኖም ግን አንደኛው ይህን ያደርግ የነበረው እነርሱን ለመምሰል ሲሆን ፣ ሌላኛው ግን ዕድሉን ሲያገኝ በግልጽ ለማፌዝና ስለ እግዚአብሔር ብሎ የሚደክመውን ሰው ከመልካም ሥራው ይገታው ዘንድ ነበር፡፡

ሌሎችን የሚያስቆጡትንና የሚያስመርሩትን ያለ አግባብ ዝም አትበላቸው፡፡ እንድትፋጠንም ስትታዘዝ በሁኔታህና በድርጊትህ አትዘግይ፡፡ አሊያ ግን ከክፉዎችና ከአመፀኞች የባስክ ትሆናለህ፡፡ ብዙውን ጊዜ ኢዮብ እንደ ተናገረው ያሉ ነገሮችን እመለከታለሁ ፣ ያም ነፍስ በሀኬት ጠባይና አንዳንዴም በበዛ ብልሃት መታወኳ ነው፡፡ [ ኢዮ.፲፫፥፩ ] እኔም ከክፋት ዓይነቶች ብዛት የተነሣ ተገረምሁ፡፡

የድምፆቹ ማደናገር ዘማሪውን ውሉ ለማይታወቅ ድምፅ የሚዳርገው ነውና ከሌሎች ጋር እንጂ ለብቻው ያልሆነ ሰው ከጸሎት እንደሚያገኘው ጥቅም ያለ ከሌሊት ዝማሬ [ ከዝማሬ ] አያገኝም፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                      💖                     🕊
2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷  "  ከእንባ የሚገኝ በረከት  " 

💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖  ]

[                       🕊                        ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ አምላክ ሆይ ፥ ሕይወቴን ነገርሁህ ፤ እንባዬን እንደ ትእዛዝህ በፊተህ አኖርህ።

በጠራሁህ ጊዜ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ፤ አንተ አምላኬ እንደ ሆንህ እነሆ ፥ አወቅሁ። በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ ፤ በእግዚአብሔር ቃሉን አከብራለሁ። ❞

[  መዝ . ፶፮ ፥ ፰ - ፲  ]



🕊                       💖                   🕊
🙏2👏1
🥰4
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

†   እንኳን አደረሳችሁ   †

[ †  ሰኔ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት † ]


🕊 † ቅዱስ ሙሴ ጸሊም [ ጥቁሩ ሙሴ ] † 🕊

ግብጻውያን ስማቸውን ጠርተው ከማይጠግቧቸው ቅዱሳን መካከል አንዱ ኢትዮዽያዊው አባ ሙሴ ጸሊም ነው:: በእኛ ኢትዮዽያውያን ግን ይቅርና በወርኀዊ በዓሉ [በ፳፬ [24] ] በዓመታዊ በዓሉ እንኩዋ ሲከበር ብዙም አይታይም::

ቅዱሱ ሰው በትውልዱ ኢትዮዽያዊ ሲሆን ያደገውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ እንደሆነ ይታመናል:: ገና በወጣትነቱ አገር የሚያሸብር ሽፍታ ነበር:: ሙሴ ጸሊም ወደ ግብጽ የሔደበት ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም መምለክያነ ጣዖት [ፀሐይን ከሚያመልኩ ሰዎች] ጋር ይኖር ስለ ነበር ምናልባት እነርሱ ወስደውት ሊሆን ይችላል::

ቅዱስ ሙሴ በምድረ ግብጽም በኃይለኝነቱ ምክንያት የሚደፍረው አልነበረም:: ፀሐይን ያመልካል: እንደ ፈለገ ቀምቶ ይበላል: ያሻውን ሰው ይደበድባል:: ነገር ግን በኅሊናው ስለ እውነተኛው አምላክ ይመራመር ነበርና አንድ ቀን ፀሐይን "አምላክ ከሆንሽ አናግሪኝ?" አላት:: እርሷ ፍጡር ናትና ዝም አለችው::

ቅዱስ ሙሴ ምንም አስቸጋሪ ሰው ቢሆንም ፈጣሪን መፈለጉን ግን ቀጥሏልና አንድ ቀን ተሳካለት:: መልካም ክርስቲያኖችን አግኝቶ . . . ወደ ገዳመ አስቄጥስ ቢሔድ በዛ ያሉ መነኮሳት ወደ እውነት እንደሚመሩት ነገሩት:: እርሱም ሰይፉን እንደታጠቀ ወደ ገዳም ገባ:: መነኮሳቱ ፈርተውት ሲሸሹ ታላቁ አባ ኤስድሮስ ግን ተቀብለው አሳረፉት::

"ምን ፈለግህ ልጄ?" አሉት:: "እውነተኛውን አምላክ ፊት ለፊት ማየት እፈልጋለሁ" የሙሴ ጸሊም መልስ ነበር:: አባ ኤስድሮስም "የማዝህን ሁሉ ካደረግህ ታየዋለህ" ብለው ወደ መነኮሳት አለቃ ቅዱስ መቃርስ ታላቁ ወሰዱት:: መቃሬም ክርስትናን አስተምረው አጠመቁትና ለአባ ኤስድሮስ መለሱላቸው::

ከዚህ ሰዓት በሁዋላ ነበር የአባ ሙሴ ጸሊም ሕይወት ፍጹም የተለወጠው:: በጻድቁ እጅ ምንኩስናን ተቀብሎ ይጋደል ጀመር:: በጠባቧ በር ይገባ ዘንድ ወዷልና ያ በሽፍትነት የሞላ አካሉን በገድል አረገፈው:: ከቁመቱ በቀር ከአካሉ አልተረፈለትም:: ወገቡን በአጭር ታጥቆ መነኮሳትን አገለገለ:: አጋንንት በቀደመ ሕይወቱ በሕልም: አንዳንዴም በአካል እየመጡ ይፈትኑት ነበር::

እንዳልቻሉት ሲረዱ ተሰብስበው መጥተው በእሳት አለንጋ ገርፈው አቆሳስለውት ሔዱ:: እርሱ ግን ታገሰ:: በበርሃ ለሚኖሩ አበው መነኮሳት ሁሉ ብርሃን በሆነ ሕይወቱ ሞገስ ሆነላቸው:: ለኃጥአን ደግሞ መጽናኛ ሆነ::

"በተራራ ላይ ያለች ሃገር ልትሠወር አይቻላትምና ስም አጠራሩ በመላው ዓለም ተሰማ:: ሁሉም "ሙሴ ጸሊም ይል ጀመር ፡፡"

በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያን መኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግን ራሱን "አንተ ጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ: ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር:: ከቆይታ በኋላም በመነኮሳት ላይ እረኛ [አበ ምኔት] ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ:: የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩ አጣፍጦ: ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ::

ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩ ሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ፫፻፸፭ [375] ዓ/ም በርበረሮች [አሕዛብ] ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳት ሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ፯ [7] ደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚሕች ቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል::

ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ ለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪው ያድለን::

🕊

[ †  ሰኔ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም [ ኢትዮዽያዊ ]
፪. "፯ቱ [ 7ቱ ] " ቅዱሳን መነኮሳት [ ደቀ መዛሙርቱ ]
፫. አባ ኤስድሮስ ታላቁ

[ †  ወርኃዊ በዓላት ]

፩ ፡ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
፪ ፡ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፫ ፡ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
፬ ፡ ቅዱስ አጋቢጦስ
፭ ፡ ቅዱስ አብላርዮስ
፮ ፡ አቡነ ዘዮሐንስ ዘክብራን
፯ ፡ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ

" መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ "የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ" ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል::" [ሉቃ.፲፭፥፫-፯] (15:3-7)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3
#አባታችን__ተክለሃይማኖት

እልፍ አእላፍ ቢኖሩ ቃላት
ሥራው ብዙ ነው
#የተክለሃይማኖት
የምድር ስፋት ቢሆንም ሰሌዳ
ሁሌም አዲስ ነህ ሁሌም እንግዳ
ተክልዬ ተክልዬ ስንልህ
#ኢትዮጵያን
አስባት ዛሬም አትተዋት

#_ሰናይ_ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
12
🕯🕯🕯💖🕯🕯🕯

ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ [ ጥቁሩ ሙሴ ]

ከሽፍትነት ህይወት ተጠርቶ በቅድስናና በንጽህና ህይወት ያሸበረቀ ገዳማዊ !

🕊

በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያን መኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግን ራሱን "አንተ ጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ ፥ ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር::

ከቆይታ በኋላም በመነኮሳት ላይ እረኛ [አበ ምኔት] ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ:: የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩ አጣፍጦ: ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ::

ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩ ሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ፫፻፸፭ ዓ.ም [375 ዓ/ም] በርበረሮች [አሕዛብ] ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳት ሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ፯ [7] ደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚሕች ቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል::

ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ ለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪው ያድለን::

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
1
2025/07/10 15:17:18
Back to Top
HTML Embed Code: