Telegram Web
4🔥2
                        †                          

እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

🕊  †  መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ  †  🕊

🕊                        💖                     🕊

" በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። "

[ ሉቃ.፩፥፲፬ ]


† የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ :-

- በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ
- በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
- በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
- እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
- የጌታችንን መንገድ የጠረገ
- ጌታውን ያጠመቀና
- ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን :-

ነቢይ :
ሐዋርያ :
ሰማዕት :
ጻድቅ :
ገዳማዊ :
መጥምቀ መለኮት :
ጸያሔ ፍኖት :
ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች::


"ሰባኬ ወንጌል በጥዑም ልሣኑ ፣
ርስነ መለኰት ገሠሠት የማኑ ፣
ጸጉረ ገመል ተከድነ ዘባኑ ፣
ለዮሐንስ ሂሩቶ ንዜኑ ንዜኑ" ድጓ ዘዮሐንስ።

ትርጉም ፦

{ በጣፋጭ አንደበቱ ወንጌልን የሚሰብክ ፣
ቀኙ የሚያቃጥል መለኮትን የዳሰሰች ፣
ጀርባው በግመል ጸጉር የተሸፈነ ፣
የዮሐንስን ደግነት ፈጽመን እንናገራለን }


" እውነት እላችኋለሁ ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፡፡" [ ማቴ.፲፩፥፲፩ ]


እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ስለወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።


🕊                        💖                     🕊
2🙏2
🙏5
🕊                    💖                   🕊

[  ግፉዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ  !  ]

                        🕊                       

❝ ሰላም ለዮሐንስ ግፉዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ  ወስቡሕ ላእከ ወነቢይ ወሰማዕት ድንግል ካህን ጸያሒ ወሰባኪ መጥምቀ እግዚኡ ❞

[ ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ ፤ መንገድ ጠራጊ ፤ ካህን ድንግል ሰማዕት ፣ ነቢይና አገልጋይ ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ]

[ አቤቱ ስላጠመቀኽ ስለ ዮሐንስ ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ ፤ ከታናሽነቴ ዠምሮ እስከ ዛሬ አንተን የበደልኹኽን ኅጢአቴን ስለ ርሱ ብለኽ እኔን አገልጋይኽን አንጻኝ አሜን። ]

[ ተአምኆ ቅዱሳን ]

🕊

❝ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። ❞

[ ሉቃ.፩፥፲፬ ]


[ 🕊 እንኳን አደረሳችሁ 🕊 ]


🕊                        💖                       🕊
🙏31
1
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

[ † እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]

🕊 ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ 🕊   

ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ሉቃ.፩፥፮]

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ [አድናቆት] ይገባል !
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ [90] የዘካርያስ ፻ [100] ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫] (40:3) , [ሚል.፫፥፩] (3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ [26] ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ [6] ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ [6] ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን [ሰኔ ፴] (30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

+ የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
+ በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
+ በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
+ እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
+ የጌታችንን መንገድ የጠረገ
+ ጌታውን ያጠመቀና
+ ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::

ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::

†  🕊  አባ ጌራን ሕንዳዊ  🕊  †

ዳግመኛ በዚህች ቀን ሕንድ ካፈራቻቸው ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ጻድቁ አባ ጌራን ይታሰባሉ:: የእኒህ ቅዱስ ታሪክ አሳዛኝ ነው:: ቅዱሱ በሕንድ ተወልደው: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድገው: ገና በወጣትነታቸው መንነው: ደሴት ውስጥ ወደሚገኝ አንድ በርሃ ገብተዋል:: ከገድላቸው ጽናት: ከቅድስናቸውም ብዛት የተነሳ በሃገረ ሕንድ ሰይጣን እንዳይገባ: ጠብ ክርክር እንዲጠፋ: ሰው ሁሉ በፍቅርና በሰላም እንዲኖር ማድረግ ችለው በጣም ተወዳጅ ነበሩ::

በዚህ የተበሳጨ ሰይጣን ግን ባልጠረጠሩት መንገድ መጣባቸው:: አንዲት ሴት ወደ እርሳቸው መጥታ [የንጉሡ ልጅ ነኝ በሚል] አስጠግተዋት ነበር:: አንድ ሌሊት ላይ ግን አውሬ ያባረራት በመምሰል ሩጣ ወደ ቤታቸው ገብታ አቀፈቻቸው:: በዚያ ቅጽበት ፍጡር ደካማ ነውና ታላቁ አባ ጌራን ተሰነካከሉ:: ከአፍታ በሁዋላ የሆነውን ሲያውቁ ደም አለቀሱ::

ልብሳቸውን ቀደው: እንባቸው እንደ ዥረት እየፈሰሰ አለቀሱ:: ራሳቸውን በትልቅ ድንጋይ እየቀጠቀጡት የጭንቅላታቸውና የደረታቸው አጥንቶች ተሰባበሩ:: እርሱ እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ይቅር ብሎ: የቅድስና ስም ሰጥቶ በዚሕች ቀን ወደ ገነት አሳርጉዋቸዋል:: ለዚህ ነው መጽሐፉ "ጻድቅ ፯ [7] ጊዜ ይወድቃልና: ይነሣማል" ያለው:: [ምሳ.፳፬፥፲፮] (24:16)

አምላካችን ከቅዱሱ ቤተሰብና ከጻድቁ አባ ጌራን በረከት ይክፈለን::

🕊

[ † ሰኔ ፴  [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት [ልደቱ]
፪. ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ [ወላጆቹ]
፫. አባ ጌራን መስተጋድል [ሕንዳዊ]
፬. ቅዱሳት ደናግል ማርያና ማርታ [ከ፴፮ (36) ቱ ቅዱሳት አንስት-የአልዓዛር እህቶች]

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ [ሐዋርያ]
፪. አባ ሣሉሲ ክቡር
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፬. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

" ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ:: መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና:: እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ:: ይሕም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው::" [ሉቃ.፩፥፸፮]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🙏3
"#ስለትሕትና"

ከአባቶች አንዱ እንዲህ በማለት ተጠየቀ :- #ትሕትና ምንድን ነው ?እርሱም ሲመልስ እንዲህ አለ :- ትሕትና #ታላቅ_ስራ ነው ፡፡ የእግዚአብሔር ስራ ነው ፡፡ የትሕትና መንገዱ ስጋዊ ስራን መስራትንና ኃጢአተኛ መሆንን ማመን ነው፡፡ ራስህን ለሌሎች መግለጥ ነው ፡፡ ይህንን ከሰማ በኀላ ከአኃው አንዱ እንዲህ አለ:- #ራስን_ለሁሉ መግለጥ ማለት ምን ማለት ነው ? ሽማግሌው መለሰ ራስን ኃጢአተኛ አድርጎ መመለከት የሌሎችን በደል እንድትመለከት አያደርግህም፡፡ ሁልገዜም ትኩረትህ የምትሰጠው #ለራስህ_ኃጢአት ነው ፡፡ ያለማቋረጥ ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለህ ፡፡

ከአባቶች አንዱ እንዲህ አለ :- በማናቸውም ጊዜ የበላይነት ስሜት የሚሰማህ ከሆነ #ያጠፋሀል ፡፡ ትእዛዙን መጠበቅ አለመጠበቅህን ታውቅ ዘንድ አእምሮህንና ልቡናህን ቢታዘዙህ ፤ ትእዛዙን ሁሉ መጠበቅ ቢቻልህ ፤ ጠላትህን መውደድ ቢቻልህ ራስህን የማይጠቅም አገልጋይ እድርገህ ብትቆጥር ፤ #የኃጢያተኞችም ዋና አድርገህ ራስህን ብትቆጥር ትጠቀማለህ ፡፡ #ትሑትም ትሆናለህ ፡፡ ይህ አሳብህ በውስጥህ ያለውን ክፋት ያሰወግድልሃል ፡፡

#መልካም_ቀን🙏

የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
15
🕊                    💖                     🕊

[       ምን ልታዩ ወጣችሁ ?       ]

                        🕊                       


❝ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ ? ነቢይን ? አዎን እላችኋለሁ ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን።

እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። እውነት እላችኋለሁ ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም ፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።

ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች ፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። ❞

[ ማቴ . ፲፩ ፥ ፱ ]

🕊                        💖                     🕊

❝ የአዋጅ ነጋሪ ቃል። የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ። ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል ፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል ፤ ጠማማውም ይቃናል ፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል ፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል ፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። ❞ [ ኢሳ . ፵ ፥ ፫ ]


[      🕊   እንኳን አደረሳችሁ   🕊      ]


🕊                        💖                       🕊
5
4
2025/07/12 23:30:40
Back to Top
HTML Embed Code: