Telegram Web
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

❖   ሐምሌ ፭    ❖

[ 🕊 ✞ እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ዼጥሮስ ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ 🕊 ]

ፍጡር ቢከብር ከእመ ብርሃን ቀጥሎ የእነዚህን ቅዱሳን ያህል የሚከብር አይኖርም:: ለቤተ ክርስቲያን ያልሆኑላት ምንም ነገር የለምና እርሷም "ብርሃኖቼ: ዐይኖቼ: ዕንቁዎቼ" ብላ ትጠራቸዋለች::


🕊  † ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት †  🕊

የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ [ኬፋ] የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው:: ይሔውም ዓለት [መሰረት] እንደ ማለት ነው::

¤ በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ አድጐ

¤ ሚስት አግብቶ ዕድሜው ፶፮ [56] ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው:: በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ: በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል:: ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል:: [ማቴ.፲፮፥፲፯] (16:17) , [ዮሐ.፳፩፥፲፭] (21:15)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው ስሕተት ንስሃ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል:: ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በሁዋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል:: ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል::

በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል:: አሕዛብ ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል:: እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል:: የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ::

ቅዱስ ዼጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ፷፮ [66] ዓ/ም የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው:: "እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም" አላቸው:: እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል:: በበጐ እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል:: በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ ፹፰ [88] አካባብ ደርሶ ነበር::

†  የቅዱስ ዼጥሮስ መጠሪያዎች :-

፩. ሊቀ ሐዋርያት
፪. ሊቀ ኖሎት [የእረኞች / ሐዋርያት አለቃ]
፫. መሠረተ ቤተ ክርስቲያን
፬. ኰኩሐ ሃይማኖት [የሃይማኖት ዐለት]
፭. አርሳይሮስ [የዓለም ሁሉ ፓትርያርክ]

🕊 † ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ † 🕊

የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን ባለ አማርኛ እንገልጠዋለን?

¤ ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ ሰው ነው?
¤ የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን እጽፈዋለሁ?
¤ ይልቁኑስ የርሱን ፲፬ [14] ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም::

ቅዱስ ዻውሎስ ከነገደ ብንያም ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር:: ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ፫ [3] ቀናት ልዩነት ምርጥ ዕቃ አደረገው:: ይህ የሆነው በ፵፪ [42] ዓ/ም: ጌታ ባረገ በ፰ [8] ኛው ዓመት ነበር:: ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ:: ጨው ሆኖ አጣፈጠ::

ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም: ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን [የዓለም መጨረሻ] ወንጌልን ሰበከ:: ስለ ወንጌል ተደበደበ: ታሠረ: በእሳት ተቃጠለ:: በድንጋይ ተወገረ: በጦር ተወጋ:: ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ:: በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ:: ለ፳፭ [25] ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ::

እርሱን የመሰሉ: እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ: በ፷፯ [67] ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል:: ከ፲፬ [14] ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል:: ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘው ማለት ነው::

🕊 † የቅዱስ ዻውሎስ መጠሪያዎች ፦

፩. ሳውል [ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ]
፪. ልሳነ ዕፍረት [አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ]
፫. ልሳነ ክርስቶስ [የክርስቶስ አንደበቱ]
፬. ብርሃነ ዓለም
፭. ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን [የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ]
፮. የአሕዛብ መምሕር
፯. መራሒ [ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ]
፰. አእኩዋቲ [በምስጋና የተሞላ]
፱. ንዋይ ኅሩይ [ምርጥ ዕቃ]
፲. መዶሻ [ለአጋንንትና መናፍቃን]
፲፩. መርስ [ወደብ]
፲፪. ዛኅን [ጸጥታ]
፲፫. ነቅዐ ሕይወት [የሕይወት ትምሕርትን ከአንደበቱ
ያፈለቀ]
፲፬. ዐዘቅተ ጥበብ [የጥበብ ምንጭ / ባሕር]
፲፭. ፈዋሴ ዱያን [ድውያንን የፈወሰ] . . .

ጌታችን እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

🕊

[ †  ሐምሌ ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
፫. ቅዱሳን ፸፪ [72] ቱ አርድእት [ዛሬ ሁሉም ይታሠባሉ]
፬. ቅዱስ ሳቁኤል ሊቀ መላእክት
፭. ቅድስት መስቀል ክብራ [የቅዱስ ላሊበላ ሚስት]
፮. ቅዱሳን ዘደብረ ዓሣ
፯. ቅዱሳት አንስት [ዴውርስ: ቃርያ: አቅባማ: አቅረባንያና አክስቲያና-የቅዱስ ዼጥሮስ ተከታዮች]

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፪. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
፫. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
፬. ቅድስት አውጋንያ [ሰማዕትና ጻድቅ]

"ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው:: "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይሕንን አልገለጠልህምና ብጹዕ ነህ:: እኔም እልሃለሁ:: አንተ ዼጥሮስ ነህ:: በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ:: የገሃነም ደጆችም አይችሏትም:: የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ:: በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል::"  [ማቴ.፲፮፥፲፯] (16:17)

" በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና:: የምሔድበትም ጊዜ ደርሷል:: መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ:: ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ:: ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል:: ይሕንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል:: " [፪ጢሞ.፬፥፮] (4:6)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2🙏1
1
#ሐምሌ 5

በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት
#የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው። በረከታቸው ይደርብን አሜን!!

ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
የዮና ልጅ ስምዖን ጴጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው። ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው።

በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ አድጐ፣ ሚስት አግብቶ ዕድሜው ሃምሳ ስድስት ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው። በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ፣ በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል። ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል።

(ማቴ. ፲፮፥፲፯ ፣ ዮሐ. ፳፩፥፲፭)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሠራው ስሕተት ንስሐ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል። ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በኋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል። ምንም የእርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል።
በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል።

#መልካም__ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
🙏83
                        †                           

🕊   💖  ዼጥሮስ ወዻውሎስ  💖   🕊

                         🕊                         

[  እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ዼጥሮስ ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ   ]

ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕትነትን ከመቀበሉ ጥቂት አስቀድሞ ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ከመከረው ምክር እነሆ

❝ በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ ...

ቃሉን ስበክ !
በጊዜውም አለጊዜውም ጽና !
ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም።

ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና ፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።

እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ

አንተ ግን
ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ !
መከራን ተቀበል !
የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ !
አገልግሎትህን ፈጽም
!

በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል።

መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ ሩጫውን ጨርሼአለሁ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም። ❞

[ ፪ኛ ጢሞቴዎስ ፬ ፥ ፩ ]

እንኳን አደረሳችሁ የቅዱስ ጴጥሮስ እና የቅዱስ ጳውሎስ በረከታቸው ይደርብን !

†     🕊   እንኳን  አደረሰን    🕊    †


🕊                        💖                       🕊
🙏1
1
                        †                             

†      🕊   እንኳን  አደረሰን    🕊    †

በደመ ስምዖሙ ተማኅጸነ ፤
ለጴጥሮስ አቡነ ፥ ወጳውሊ ፍቁርነ ፤
ጸሎተነ አጽምዕ ፍጡነ ፤
እስመ ንጸንሐከ እምዘመን ዘመነ !

ቸሩ ሆይ ፥ ስለ ፈሰሰ ደማቸው ብለህ ከምድሩ መቅሠፍት፥ ከሰማዩ እሳት አድነን !


🕊                        💖                       🕊
                         †                         

[  የክብር ኮከብ ፤ የገዳም መብራት  ]

🕊

የማይሰለች ተጋዳይ ፤ የክብር ኮከብ ፤ የገዳም መብራት ስም አጠራሩ እርግናው የተመሰገነ ፤ ብፁዕ ቅዱስ ደግ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወርሐዊ በዓላቸው ነው።

†     🕊   እንኳን  አደረሰን    🕊    †

እግዚአብሔር አምላክ ስለ እውነተኛ ወዳጁ ስለ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ብሎ ይማረን፡፡


🕊                        💖                       🕊
6
2025/07/12 16:12:46
Back to Top
HTML Embed Code: