👉አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወለዱ በተወለዱበት ቀን ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ሦስት ጊዜ አመሰግነው 9 ጊዜም ለሥሉስ ቅዱስ ለድንግል ማርያምና ለመስቀለ ክርስቶስ ሰግደዋል፡፡
👉አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በቅዱስ ሚካኤል ጠባቂነት በመልካም አስተዳደግ አድገው 5 ዓመት ሲሆናቸው ኪራኮስ ወደሚባል ታላቅና ቅዱስ መምህር ዘንድ ሄደው የቤተ ክርስቲያንን ትምህትና የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጓሜ ተምረዋል፡፡
👉ትምህርቱን ሲጨርሱ ድቁናን ተቀብለው በ14 ዓመታቸው ወደ ገዳም ገቡ በ17 ዓመታቸው ምንኩስናን ተቀበሉ፡፡
👉አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በሚጸልዩበት ሰዓት አስሩ የእግራቸውና የእጃቸው ጣቶች እንደ ፀሐይ ያበራሉ በሚጸልዩበት ጊዜ ጌታችንን ያዩት ነበር፡፡
👉አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሃይማኖትና በመልካም ምግባር ፀንተው ሲኖሩ የቅዱሳን መላእክት ጠባቂነት የልዑል እግዚአብሔር ፍቅር ሳይለያቸው ኖረው ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ፡፡
👉የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሚያዚያ 9 ቀን ነው
👉ልዑል እግዚአብሔር ከአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ረድኤት በረከት ያሳትፈን እኛም በሃይማኖት ጸንተን እንድንኖር ይርዳን "አሜን"
#መልካም_ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

❤7
🕊 💖 🕊
[ ❝ አንዲት ጥምቀት ❞ ] [ ኤፌ.፬፥፭ ]
🕊 💖 🕊
ምስጢረ ጥምቀት ከአምስቱ አዕማደ ምስጢራት መካከል አንዱ ነው፡፡
ምስጢረ ጥምቀትን የመሠረተልን ለሥም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ አምላካችን በጥምቀቱ ፦
፩. በተግባር በመጠመቅ ጥምቀት ለፍጥረታዊው ሰው አስፈላጊ መሆኑን
፪. በውኃ በመጠመቅ ማያት [ ውሆች ] ዳግመኛ የምንወለድባቸው ማኅፀኖች ይሆኑ ዘንድ ኃይልን ሰጣቸው
፫. ጌታችን መጠመቅ ሳይኖርበት ስለ እኛ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ተገልጦ የባህርይ አባቱ አብ ልጅነቱን እንደመሰከረለት እኛም ስንጠመቅ ከእርሱ ዳግመኛ መወለዳችንና የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ይመሠክርልናል፡፡
፬. እርሱ ሲጠመቅ " ሰማያት ተከፈቱ " እንደተባለ በጥምቀቱ አገራችን በሰማይ መሆኑን የአገራችንን በር ከፍቶ አሳየን ፤ የምንጠመቀው ያንን ሰማያዊ ሀገር ለመውረስ የሚያበቃ ልጅነት ለማግኘት መሆኑን በተግባር አሳየን፡፡
🕊 💖 🕊
በመሆኑም በአማናዊቷ ጥምቀት የሚገኘው ፦
፩. [ ሥርየተ ኃጢአት [ መዳን ] ]
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ከፅንሠቱ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ ድረስ ያደረገው ነገርና የሰጠው ጸጋ ፣ እንዲሁም በዕለ ዓርብ በመስቀል ላይ የቆረሰው ሥጋውና ያፈሰሰው ደሙ ፣ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱ ሁሉ ለእያንዳንዳችን የሚደርሰን በጥምቀት አማካኝነት ነው፡፡
በመስቀል ላይ ሳለም ሐራዊ ጎኑን በጦር በወጋው ጊዜ ከቅዱስ ገቦው [ ጎኑ ] ውኃና ደም እንዲወጣ የፈቀደው ለዚህ ነበር ፣ ከጎኑ በተገኘው በውኃና በደሙ ልጅነትንና ሥርየተ ኃጢአትን እንድናገኝ ነው፡፡ በማየ ገቦዎ እንጠመቃለን ፣ ደሙን ደግሞ በምሥጢረ ቁርባን እንቀበለዋለን፡፡ ጥምቀት የኃጢአት ሥርየት እንደሚያሰጥ ቅዱስ መጽሐፍ ፦
❝ ንስሐ ግቡ ፣ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፡፡ ❞ [ ሐዋ.፪፥፴፰ ]
፪. [ የእግዚአብሔርን ልጅነት ማግኘት ዳግም ልደት ]
❝ ኢየሱስም መልሶ። እውነት እውነት እልሃለሁ ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።
...
ኢየሱስም መለሰ ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እልሃለሁ ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው ፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።❞ [ ዮሐ.፫፥፫ ] በማለት በጥምቀት ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት የማይችል መሆኑን በአምላካዊ ቃሉ አስተምሮናል፡፡
፫. [ መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ]
በጥምቀት በምናገኘው የእግዚአብሔር የልጅነት ጸጋ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የምንችል ባለ ተስፋዎች እንድንሆን ያደርገናል፡፡ እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ ለመቀበል በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን ካልተወለድን በስተቀር ከእናት ከአባት በተወለድነው ተፈጥሯዊና ሥጋዊ ልደት መንፈሳዊና ሰማያዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ አንችልም፡፡ [ ዮሐ.፫፥፫ ]
፬. [ ከክርስቶስጋር አንድ መሆን ፣ በሞቱና በትንሣኤው መተባበር ]
ጥምቀት የጌታችንን ሞቱንና ትንሣኤውን ማመናችንን በተግባር የምንመሰክርበትና ከሞቱና ከትንሣኤው የምንሣተፍበት ምስጢር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ገልጾታል ፦
❝ ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን ?
እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።
ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን።❞ [ ሮሜ.፮፥፫ ]
በመሆኑም በጥምቀት ምሥጢር ያልተሳተፈ ሰው ከክርስቶስ ጋር አንድ ለመሆን ሥጋውንና ደሙን ለመቀበልና ወደ መንግሥተ ሰማያት ጉዞ ለመጀመር አይችልም፡፡
፭. [ ክርስቶስን ለመልበስ ]
አሮጌውን አዳማዊ ሰውነታችንንና ማንነታችንን አስወግደን " አዲስ ሰው " የተባለ ዳግማዊ አዳም ኢየሱስ ክርስቶስን የምንለብሰው በጥምቀት ነው፡፡ ስለሆነም ጥምቀት ለሕይወት የሆነ አዲስ ሰውነትን ገንዘብ የምናደርግበት ምስጢር ነው፡፡
❝ የተጠመቃችሁ ክርስቶስን ለብሳችኋልና ❞
[ ገላ.፫፥፳፯ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
† † †

👍2
🕊 💖 🕊
[ ቅ ድ ስ ት ሀ ገ ር ኢ ት ዮ ጵ ያ ! ]
🕊 💖 🕊
💖
ኢትዮጵያ በሠረገላ ሆና የነቢያትን መጻሕፍት ስታነብ ምዕራባውያን ሀገራት ባዶ ምድረ በዳዎች ነበሩ። ሌሎችም በጣዖት አምልኮ የሚኖሩ ነበሩ። የእግዚአብሔር የምስጢር ሀገር ቅድስት ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና ፥ በሕገ ኦሪት ፥ በሕገ ወንጌል በአምልኮተ እግዚአብሔር ጸንታ የተገኘች የቅዱሳን አምባ የከበረች ምድር ናት።
በመንፈስ ቅዱስ ተመርጦ ፥ የተነገረው ትንቢት የተቆጠረው ሱባኤ መፈጸሙን ተረድቶ ገና በ፴፬ ዓ.ም [ በ34 ዓ.ም] የክርስቶስን የባህርይ አምላክነት አምኖ የመሠከረና የልጅነት ክብርን በአማናዊው ጥምቀት የተጎናጸፈ አንድም ሀገር የለም ከኢትዮጵያ በቀር !
🕊 💖 🕊
❝ የጌታም መልአክ ፊልጶስን። ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ አለው። ተነሥቶም ሄደ። እነሆም ፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር ፤
. . .
በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውኃ ደረሱ ፤ ጃንደረባውም። እነሆ ውኃ ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድር ነው ? አለው።
ፊልጶስም። በፍጹም ልብህ ብታምን ፥ ተፈቅዶአል አለው። መልሶም። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ አለ።
ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ ፥ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ ፥ አጠመቀውም። ❞ [ሐዋ.ሥራ.፰፥፳፮-፴፰]
ኢትዮጵያ ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል የተሸጋገረችው በዘመነ ሐዋርያት ነው። ኢትዮጵያን ያጠመቀውም ቅዱስ አባታችን ፊልጶስ ነው።
❝ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። ❞ [ መዝ.፷፰፥፴፩ ]

👍4
🕊
[ የምወደው ልጄ ! ]
💖
" የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው ፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።" [ መዝ.፶፩፥፲፯ ]
" እግዚአብሔር ፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው ፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።" [ ዕብ.፮፥፲ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
ጥር ፲ [ 10 ] ቀን።
† እንኳን ለገሀድ [ ጋድ ] ጾመ ፣ ለከተራ በዓልና ለአባ ታውብንጦ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ ፦ ከሰማዕት ከጠምያኒ ፣ ከኪናርያና ከንግሥት በጥሪቃ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። †
†
- የዕለቱ ሰላም ፦ "ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ ፤ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት ፤ በፍሥሐ ወበሰላም"። [ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ]
+ + +
- በዚች ዕለት ምንም ምን መብልን ሰይቀምሱ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።
- እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።
- በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።
- በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።
- የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህ ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።
- መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረብዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና። እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
- አባ ታውብንጦስ ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ አባ ታኡና በሚባል በሮሜው ሊቀ ጳጳሳት ቤት አደገ እርሱም የምንኵስናን ልብስ አለበሰው። መንፈሳዊ ዕውቀትና ኃይል እንደተሰጠው አይቶ ከእስክንድርያ አገር ውጭ ስሙ ጤናዲራን በሚባል ቦታ ኤጲስቆጶስነት ሹሞ የገዳም አበ ምኔት አደረገው ከእርሱ ሥር ያሉ መነኰሳትም ሰባት መቶ ናቸው።
- ከዚህም በኋላ ከእርሱ ጋር ላሉ መነኰሳት አለቃ የሆነ ኤጲስቆጶስ ታውብንጦስ ከከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ስለሆነው ሁከት በሰማ ጊዜ ሸሽቶ ወደ ደብረ ሲሐት ገዳም ሒዶ እግዚአብሔርን ከምትፈራ ከአንዲት ድንግል ዘንድ ተቀመጠ። በእርሷ ቤትም ብዙ ዘመናት ኖረ በመጀመሪያ ወደርሷ በገባ ጊዜ ግን ንጉሡን ስለ መፍራት ጣዖትን ስታመልክ አገኛትና የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳት።
- ከዚያም ተርኑጥና መርኑስ ወደ ሚባሉ ገዳማት ሔደ የአብያተ ክርስቲያናትን ወሬ ይሰማ ዘንድ ፈልጎ በጾም በጸሎት ሌሊትም በመትጋት እያገለገለ በአንዲት ገዳም ውስጥ ሁለት ሦስት ቀን ተሠውሮ ያድር ነበር። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላዩ እንዳደረ እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራቶችን እንዳደረገ ከወንበዴዎችና ከዓመፀኞች ብዙዎችን መነኰሳትን አድርጎ ለክርስቶስ ወደ መገዛት እስከ መላሳቸው ድረስ መነኰሳቱ ሁሉ መሰከሩለት።
- ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ የሚሞትበትን ቀን ዐወቀ ልጆቹንም የክርስቶስ በሆነች በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ አስተማራቸው ወዲያውኑ ጥር ፲ [10] ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ታውብጦስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
[ ምንጭ ፦ የጥር ፲ ስንክሳር ]
+ + +
"ሰላም እብል ለጾመ ዕለት ዋሕድ። ዘስሙ ገሀድ። መምህራነ ሥርዓት አቀሙ ለዘይመጽእ ትውልድ። እመባልዕት ጥሉላት ወእምነ ቅሡም ማዕድ። አንስት ይትሀረማ ወይጹሙ ዕድ። ሊቁ አርከ ሥሉስ [ አርኬ ] የጥር ፲ [10]
+ + +
- የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ ፦ "ለበስኩ ሠቀ ወኮንክዎሙ ነገረ። ላዕሌየ ይዛውዑ እለ ይነብሩ ውስተ አናቅጽ። ወኪያየ የኀልዩ እለ ይሰትዩ ወይነ"። [ መዝ.፷፰፥፲፩ ] የሚነበበው ወንጌል [ ማር.፩፥፩-፱ ]
+ + +
- የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ ፦ "ሣህል ወርትዕ ተራከባ። ጽድቅ ወሰላም ተሰዐማ። ርትዕሰ እምድር ሠረፀት"። [ መዝ.፹፬፥፲ ]የሚነበቡት መልዕክታት [ ገላ.፫፥፳-ፍጻሜ ] ፣ [፩ኛ ዮሐ.፬፥፲፬-፲፰] እና [የሐዋ ሥራ.፲፫፥፳፬-፴ ] የሚነበበው ወንጌል [ማቴ.፫፥፩-፲፫] ። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የጾም ቀንና የከተራ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
🕊
[ † ጥር ፲ [ 10 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ጾመ ገሃድ
፪. አባ ታውብንስጦስ ዘሲሐት
፫. ቅዱስ ኪናርያ
፬. ቅድስት ጠምያኒ
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
፫. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ እልፍዮስ]
፭. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
፮. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
፯. ቅዱስ እፀ መስቀል
" እነርሱ እሥራኤላውያን ናቸውና:: ልጅነትና ክብር: ኪዳንም: የሕግም መሰጠት: የመቅደስም ሥርዓት: የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና:: አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና:: ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ:: እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው:: አሜን::" [ሮሜ.፱፥፬]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

#ጥር 10 #የከተራ_በአል
👉አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አመታዊ የከተራ በአል እንኳን አደረሰን
👉ከተራ ምንድን ነው? ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ ሲሆን ፍችው ውኃ መከተር መገደብ ማለት ነው፡፡
👉በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ
👉ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ ይገድባሉ ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ ለጥር 11ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡
👉በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
👉በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመሄዱ ምሳሌ ነው
👉ታቦቱ የጌታችን ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
👉አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከጥምቀት ከተራ በአል ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን"
#_መልካም__በዓል🙏
ለመቀላቀል👇👇👇👇

❤9
🕊 💖 🕊
🕊 ተ ዋ ሕ ዶ ሰ ማ ያ ዊ ት 🕊
💖
[ የታቦታቱ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ መውረድ ከክርስቶስ ወደ ባሕር መሄድ ጋር እንዴት ተገናኘ ? ]
“ ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በዮሓንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። [ ማቴ ፫÷፲፫ ] እንደተባለው ፦
◽️ ጌታችን ከተጸነሰባት ካደገባት ከናዝሬት ገሊላ ለመጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ እንደሄ ታቦታትም ከማደሪያቸው ከመንበራቸው ተነስተው ወደባሕረ ጥምቀቱ ይሄዳሉ።
“ ሕዝቡም ዅሉ ከተጠመቁ በዃላ ጌታ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። [ ሉቃ ፫÷፳፩ ] እንደተባለው ፦
◽️ጌታችን ከባሕረ ጥምቀቱ እንደደረሰ ኣልተጠመቀም ሕዝቡ ሁሉ ተጠምቀው ከጨረሱ በኋላ ነው የተጠመቀው ታቦታትም ወደ ባሕረ ጥምቀቱ እንደደረሱ ሳይሆን በተዘጋጀላቸው ቦታ ካረፉና ከቆይታ በኋላ ነው ሥርዓተ ጥመቀቱ ይፈጸማል።
“ ባሕር ዓየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ዃላው ተመለሰ። ” [ መዝ ፻፲፫፥፫ ] እንደተባለው ፦
◽️ ጌታችን ወደ ዮርዳኖስ ለመጠመቅ ሲገባ ባሕረ ዮርዳኖስ እንደሸሸች እና ለሁለትም ተከፍላ እንደ ግድግዳ እንደቆመች [ እንደተከተረች ] ዛሬም ምዕመናን ከመጠመቃቸው በፊት ውኃ በተዘጋጀው ገንዳ ውስጥ ይከተራል በመቀጠልም ጌታችንም እንደተጠመቀ ምዕመናንም የመታሰቢያ ጥምቀትን ይጠመቃሉ።
[ O R T H O D O X Y ! ]
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
✥ ተ ዋ ሕ ዶ ሰ ማ ያ ዊ ት ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

ከምናነበው የምንጠቀም ያድርገን, አሜን
[ O R T H O D O X Y ! ]
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
✥ ተ ዋ ሕ ዶ ሰ ማ ያ ዊ ት ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
† † †
🕊 💖 🕊
❤4