#ኪዳነምህረት_እናቴ 16 🙏🙏
#የብርሃን_እናቱ_ሆይ ካንቺ በነሳው ስጋ እኛነታችንን አከበረ፡ መዐዛሽ ስቦት አንችን በወደደ ጊዜ ድህነታችን ተሰራ #ድንግል_ሆይ እውነተኛው የህይወት እንጀራ : ጣፋጩን የነፍስ መጠጥ አማናዊው የፅድቅ ብርሀን የፈነጠቀብሽ ነሽና ከትውልድ መሀል #ብፅዕናሽን እንናገራለን ጥማችንን የቆረጠ ጥዑም ወይን ረሀባችንን ያጠፋ እውነተኛው መብል ካንቺ ወጥቶልናልና #እንወድሻለን ምስራቃዊት በራችን ሆይ ከሴቶች አንችን የሚመስል የለም፡ ባንቺ ላይ ስለተደረገልን ታላቅ ነገር ዛሬም ለዘላለምም ስምሽን እናገናለን፡፡
#ዝምተኛይቱ_ድንግል_ሆይ አንቺ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የአይሁድ ሴቶች አይደለሽም በትሕትና ተልመሽ በንፅሕና አጊጠሽ የባህርያችንን መመኪያ ያስገኘሽልን የፅድቅ በራችን ነሽ።
ኪዳነምሕረት ሆይ #አንችን_ማመስገን የነፍስ ምግብ የህሊና እርካታ ነው #ስናመሰግንሽ እናርፋለን ስናርፍ #እናመሰግንሻለን ክብርሽ ከሰማይ ምስጋናሽም ከአርያም ነውና አንችን ለማመስገን ልቦናችን ይብራ አሜን🙏
#መልካም__ቀን 🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam

❤6🙏4👍2👏2❤🔥1
†
[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]
[ ክፍል ሰባ አራት ]
🕊
[ ለአንድ እኁ ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ሲያስረዳ ! ]
🕊
❝ አንድ እኁ አባ መቃርዮስን ፦ “ መጀመሪያ ከቤተ ክርስቲያን ሁን እያለ ሕሊናዬ ይወቅሰኛልና ምን ባደርግ ይሻለኛል? ” ሲል ጠየቀው፡፡
አባ መቃርዮስም እንዲህ አለው ፦ “ እየተናገርህ ያለኸው ስለ ሰማይ ደጅ እና ስለ ሕያዋን ሁሉ እናት ነው፡፡ እኔ የምልህ ፣ የእኔ ልጅ ፣ የዲያብሎስን ግብር ወደ ኋላህ ትተህ ስትመጣ የተወደደችውን ሰዓት እወቅ ፣ የመዳንን ቀን አስተውለህ ተረዳ፡፡፡ ብዙዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመግባት የሚከለከሉበትና ለምሥጢራት እንግዶች የሚሆኑበት ቀን እየመጣ ነውና፡፡
ምክንያቱም ከፍርሃት የተነሣ ዘመኑ የሚያመጣውን ሕግና መመሪያ በመከተል ታስረው ይያዛሉና፡፡ አንደበታቸውም በውቅያኖስ ውስጥ እንዳለ ዘንዶ የተከፈተ ነው ፣ ጉንዳን በበጋ ዘመን ወደ ጉድጓዷ እንደምትሰበስብ እነርሱም ብዙ ገንዘብ ያከማቻሉ፡፡ ልጄ ! የምልህ ነገር ማንኛውም ክፉ ግብር የሚወለደው ከዝሙትና ገንዘብን ከመውደድ ፣ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገሮች ነው፡፡
ምንም እንኳ ዝሙት የባሰ ክፉ ቢሆንም ጊዜያዊ ነገር ነው ፤ ከግብሩ መጥፎነትና አስጸያፊነት የተነሣ አድራጊው ራሱ የግብሩን ወራዳነት ተረድቶ ፊቱን ያዞርበታል ፣ ይጸየፈዋል፡፡ ገንዘብን መውደድ ግን ሁል ጊዜም ይጣፍጥሃል፣ ብታገኝም በቃኝ የማያስብልና ርካታን የማያውቅ ነው፡፡
ስለዚህ በዚያ ዘመን ከሚሰፍነው ፍርሃት የተነሣ በበረሓው በቤተ ክርስቲያን በሮች ላይና በሙታን አፎች [መቃብሮች] ላይ ማኅተም ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ካረፉትና ካንቀላፉት እንኳ ሳይቀር ውርስን ሊካፈሉ የሚሹና የሚፈልጉ አንዳንዶች ይነሣሉና ፤ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኩራ የተባለውንም የማያስተውሉ ይመጣሉና፡፡
ሐዋርያው ስለ ገንዘብ ያለውም ይኽ ነው ፦ "የኃጢአት ሁሉ ሥር ገንዘብን መውደድ ነው፡፡" ስለዚህ የእኔ ልጅ ! በኃይልህ ሁሉ ተጋደል ፣ አባ እንጦንስ እንዲህ ዓይነት በሆነው ዘመን እያንዳንዱ ሰው የራሱ ቤተ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ይገባል ብሏልና፡፡ ማለትም እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን የሆነች ነፍሱን ለማንጻት ያለ ኃይሉን በሙሉ አሟጥጦ መጠቀም ይገባዋልና ነው ፤ በዚህም ለእግዚኣብሔር አምላካችን ኦርቶዶክሳዊውን እምነት በመግለጥና በመመስከር በጸጥታ ድምፅ ዝማሬያችንን ወደ እርሱ ማቅረብ እንችል ዘንድ፡፡ ❞
🕊
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡
ይቆየን !
💖 🕊 💖

👍2
†
[ 🕊 " አበዊነ ቅዱሳን ! 🕊 ]
" አበዊነ ቅዱሳን መክሲሞስ ወዱማቴዎስ "
💖
እኒህ ቅዱሳን የሥጋ ወንድማማቾች ሲሆኑ በቤተ
ክርስቲያን ታሪክ እጅግ ተወዳጅ አባቶች ናቸው::
ስንጠራቸውም " አበዊነ ቅዱሳን : ወክቡራን : ሮማውያን : መስተጋድላን : ወከዋክብት ብሩሃን " ብለን ነው፡፡
በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢም ጥር ፲፬ ቀን ታላቁ ቅዱስ መክሲሞስ ዐረፈ:: ከ፫ ቀን በኋላ ደግሞ ቅዱስ ዱማቴዎስ ዐረፈ:: ነገ ጥር ፲፯ ዓመታዊ በዓላቸው ይከብራል።
በረከታቸው ይደርብን፡፡
† † †

❤3
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †
† ጥር ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † አበዊነ መክሲሞስ ወዱማቴዎስ † 🕊
- እኒህ ቅዱሳን የሥጋ ወንድማማቾች ሲሆኑ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እጅግ ተወዳጅ አባቶች ናቸው:: ስንጠራቸውም "አበዊነ ቅዱሳን: ወክቡራን: ሮማውያን: መስተጋድላን: ወከዋክብት ብሩሃን" ብለን ነው::
- ይኸውም "እንደ ንጋት ኮከብ የምታበሩ: ተጋዳይ: ቅዱሳንና ክቡራን የሆናችሁ ሮማውያን አባቶቻችን" ማለት ነው:: ሃገረ ሙላዳቸው ሮም ሁና አባታቸው ንጉሥ ለውንድዮስ ይባላል::
- ይህ ንጉሥ ሮምን በምታክል ታላቅ ሃገር በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነግሦ ሳለ መልካም ሰው ሆኖ ተገኝቷል:: ከመልካም ሚስቱ [ንግሥቲቱ] ከወለዳቸው መካከልም ፪ቱ ከዋክብት ይጠቀሳሉ:: ፪ቱ ቅዱሳን በአጭር የጊዜ ልዩነት የተወለዱ በመሆናቸው እንደ መንትያ ይቆጠራሉ::
- ንጉሡ ለውንድዮስም ከእግዚአብሔር ዘንድ ላገኛቸው ልጆቹ ስም ሲያወጣ ታላቁን መክሲሞስ: ታናሹን ደግሞ ዱማቴዎስ ብሎታል:: ቅዱሳኑ በንጉሥ አባታቸው መልካም ፈቃድ ክርስትናን ተምረዋል::
- ምንም እንኳ የንጉሥ ልጆች እና ልዑላን ቢሆኑም ተቀማጥለው አላደጉም:: ምቾት ብዙዎችን አጥፍቷልና:: ይህንን የተረዳ አባታቸው ሞገስን በፈጣሪያቸው ዘንድ እንዲያገኙ እንዲህ በበጐ ጐዳና አሳደጋቸው::
- ቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስ ካደጉና ለአካለ መጠን ከደረሱ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ ይተጉ ነበር:: በተለይ ዜና ቅዱሳንን ከማንበብ አይጠግቡም ነበር:: እግዚአብሔርንም በፍቅር እያመለኩ በጾምና በጸሎት ይገዙለት ነበር::
- ቅዱሳኑንም ለየት የሚያደርጋቸው አንዱ ይሔው ነው:: ወርቅና ብር በፊታቸው ፈሶ: በእግራቸው እየረገጡት: አገሩና ምድሩ እየሰገደላቸው: የላመ የጣመ ምግብ እየቀረበላቸው: የሞቀ የደመቀ መኝታ እየተነጠፈላቸው . . . ሁሉንም ስለ ፍቅረ ክርስቶስ መናቃቸው ይደነቃል::
- እነርሱ በክርስቶስ ፍቅር ሆነው የዚህን ዓለም ጣዕም ንቀዋልና የአባታቸውን ቤተ መንግስት ሊተዉ አሰቡ:: አሳባቸው ደግሞ በመመካከር ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንዲሉ አበው በጌታ መሪነት ነው::
- ወደ በርሃ ሔደው ለፈጣሪ ለመገዛት ሲያስቡ መውጫ መንገዳቸውን ይሹ ነበርና አንድ ጐዳና ተገለጠላቸው:: ከዚያም ለንጉሥ አባታቸው ሔደው "አባ! እኛ ወደ ኒቅያ [ ታናሽ እስያ ] ሔደን መባረክ እንፈልጋለን" ሲሉ ጠየቁት::
- ወቅቱ ቦታዋ ስለ ፫፻፲፰ [ 318ቱ ] ቅዱሳን ሊቃውንት ሞገስን ያገኘችበት ጊዜ ነበር:: አባታቸውም መንፈሳዊ ሰው ነበርና ደስ እያለው ፈቀደላቸው:: ብዙ ወርቅን ሰጥቶ: ሸልሞ ከብዙ ሠራዊት ጋር ሸኛቸው::
- ቅዱሳኑ መክሲሞስና ዱማቴዎስም ለጥቂት ጊዜ በኒቅያ ሲጸልዩና ሲባረኩ ሰነበቱ:: ቀጥለውም የአባታቸውን ሰራዊት ሰብስበው "እኛ ሱባኤ ልንይዝ ስለ ሆነ እንመጣለን" የሚል ደብዳቤን ሰጥተው ወደ ሮም ሸኟቸው::
- ወታደሮችን ከሸኙ በኋላ ቅዱሳኑ በአካባቢው ወደ ሚገኝ አንድ ገዳም ሒደው ለአንድ ደግ መናኝ ምሥጢራቸውን ገለጹለት:: ልክ የንጉሡ ለውንድዮስ ልጆች መሆናቸውን ሲያውቅ 'አመንኩሰን' ያሉትን እንቢ አላቸው::
- "ለምን?" ሲሉት "ደጉን አባታችሁን ማሳዘን አልፈልግም:: ግን ፈቃዳችሁ እንዲፈጸምላችሁ ወደ ሶርያ ዝለቁ:: በዚያ አባ አጋብዮስ የሚባል ጻድቅ ገዳማዊ ሰው ታገኛላችሁ" ብሎ ወደ ሶርያ አሰናበታቸው::
- በምድረ ሮም: በተለይም በቤተ መንግስቱ አካባቢ የ፪ቱ ልዑላን መጥፋት [ መሰወር ] ሲሰማ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: ንጉሡ አባታቸው በወታደሮቹ ዓለምን ቢያካልልም ሊያገኛቸው አልቻለም:: እርሱ ፈጽሞ ሲያዝን እናታቸው ፈጽማ መጽናናትን እንቢ አለች::
- መክሲሞስና ዱማቴዎስ ግን ምድረ ሶርያ ገብትው የጻድቁ አባ አጋብዮስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ:: በእርሱም ዘንድ ለምናኔ የሚያስፈልጉ በጐ ምግባራትንና ትሩፋትን ከተማሩ በኋላ ፪ቱንም አመነኮሳቸው:: በዚያ ቦታም እየታዘዙ: ፈጣሪን እያመለኩ: በጾም: በጸሎትና በትህትና ኖሩ::
- አንድ ቀን ግን አባ አጋብዮስ ጠርቶ " ልጆቼ ! ተባረኩ ! በእናንተ ምክንያት ደስ ብሎኛልና:: በዚህች ሌሊት የመነኮሳት ሁሉ አለቃ ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ በራዕ ተገልጦ: ልጆች እንዲሆኑኝ ስጠኝ ብሎኛልና እኔ ሳርፍ ወደ ግብጽ ገዳመ አስቄጥስ እንድትሔዱ" አላቸው::
- አባ አጋብዮስ ካረፈ በኋላ ግን እንደ ትዕዛዙ አልሔዱም:: ውዳሴ ከንቱን ይፈሩ ነበርና:: በዚያው በምድረ ሶርያ ግን በጥቂት ጊዜ: ገና በወጣትነት ከብቃት መዓርግ ስለ ደረሱ በርካታ ተአምራትን ሠሩ:: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ ሆኑ::
- ስም አጠራራቸውም ሶርያን መላት:: በዘመኑ በአካባቢው አንድ ግዙፍ ዘንዶ ተነስቶ ሰውንም እንስሶችንም ፈጃቸው:: ሕዝቡም ሒደው በቅዱሳኑ ፊት አለቀሱ:: ያን ጊዜ ቅዱስ መክሲሞስ [ ትልቁ ] ክርታስ አውጥቶ "አንተ ዘንዶ ይህ ክርታስ ወደ አንተ ሲደርስ ከማደሪያህ ውጣ: ሙት: ወፎችም ይብሉህ" ሲል ጻፈበት::
- "ሒዳችሁ በበሩ ጣሉት" አላቸው:: አንድ ደፋር ሰው ተነስቶ ሰዎች ሁሉ እያዩት ወስዶ በዘንዶው መውጫ ላይ ጣለው:: በቅጽበትም ዘንዶው ወጥቶ ሞተ:: አሞሮችም ተሰብስበው በሉት:: ከዚህ ድንቅ ተአምር የተነሳ ሕዝቡ የቅዱሳኑን አምላክ አከበረ::
- ከዚህ በተረፈም በቅዱሳኑ ስም ታላላቅ ተአምራት ተደረጉ:: ርኩሳት መናፍስት ሁሉ ስማቸውን እየሰሙ ይሸሹ ነበርና:: ድውያን እነሱ በሌሉበት ስማቸው ሲጠራላቸው ይፈወሱ ነበር:: የአካባቢው ሰው ስማቸውን እየጠራ: በእነርሱም እየተማጸነ ከመከራው ሁሉ ይድን ነበርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ሞገስ ሆኑ::
- መርከበኞች ደግሞ ከማዕበል ለመዳን የቅዱሳኑን ስም በጀልባዎቻቸው ላይ ይጽፉ ነበር:: አንድ ቀን ግን የንጉሡ ለውንድዮስ ባለሟል ይህንን ጽሑፍ ተመልክቶ ስለ ጠረጠረ መርከበኛውን በንጉሡ ፊት አቀረበው::
ንጉሡም መርከበኛውን "የጻፍከው የማንን ስም ነው?" ቢለው "በሶርያ የሚገኙ ፪ ወንድማማች ቅዱሳን ስም ነው" አለው:: ልጆቹ እንደ ሆኑ ገምቶ በመርከበኛው መሪነት ንግሥቲቱንና ሴት ልጁን ላካቸው:: እነርሱ በሐዘን ተሰብረው ነበርና::
- ወደ ሶርያ ወርደው ባገኟቸው ጊዜም ከናፍቆትና ደስታ የተነሳ ታላቅ ጩኸትን እየጮሁ አለቀሱ:: "እንሒድ ወደ ሮም" ሲሏቸው ግን ቅዱሳኑ "የለም! እኛ የክርስቶስ ነን" ብለው እንቢ ስላሏቸው እያዘኑ ተመለሱ:: ንጉሡ ግን ይህንን ሲሰማ ደስ አለው:: "እነርሱ የዚህን ዓለም ኃላፊነት ተረድተዋል" ሲልም አወደሳቸው::
- በኋላ ግን "የሮሜ ሊቀ ዻዻሳት መሆን አለባችሁ" የሚል ነገር ሲሰማ ቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስ ከሶርያ ወጥተው ወደ ግብጽ ወረዱ:: የከታላቁ ቅዱስ መቃርስ ዘንድ ደርሰውም ልጆቹ እንዲሆኑ ለመኑት::
" ልጆቼ ! በርሃ አይከብዳችሁም ? " ቢላቸው " ግዴለም ! " አሉት:: በዚያም ከተራራው ሥር በዓት ሠርቶላቸው ለ ፫ ዓመታት በአርምሞ ቆዩ:: አንድ ቀንም ቅዱሳኑ እየጸለዩ ከአፋቸው የወጣ የብርሃን ምሰሶ ከመንበረ ጸባኦት ሲደርስ አይቶ ታላቁ መቃርስ አደነቀ::
- በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢም ጥር ፲፬ ቀን ታላቁ ቅዱስ መክሲሞስ ዐረፈ:: በዕለቱም የሰማይ ቅዱሳን ሁሉ ወርደው እየዘመሩ ወሰዱት:: ከ፫ ቀን በኋላ ደግሞ ቅዱስ ዱማቴዎስ ዐረፈ::

- በተመሳሳይ ቅዱሳኑ ሲወስዱት 2ቱንም ቅዱሳን ታላቁ መቃርስ በበዓታቸው ቀብሯቸዋል:: ቦታውም ደብረ ብርስም [ በርሞስ ] ተብሏል:: ትርጉሙም የሮማውያኑ ቅዱሳን ደብር እንደ ማለት ነው::
አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን:: ክብራቸውንም አያጉድልብን::
🕊
[ † ጥር ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱሳን እና ክቡራን የሚሆኑ አባቶቻችን "መክሲሞስ እና ዱማቴዎስ"
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ ቀዳሜ ሰማዕት ]
፪. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ ወልደ ዘብዴዎስ ]
፫. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፬. አባ ገሪማ ዘመደራ
፭. አባ ዸላሞን ፈላሢ
፮. አባ ለትጹን የዋህ
፯. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ [ ዘደሴተ ቆዽሮስ ]
" ፍቅር ያስታግሳል:: ፍቅር ያስተዛዝናል:: ፍቅር አያቀናናም::ፍቅር አያስመካም:: ፍቅር አያስታብይም:: ብቻዬን ይድላኝ አያሰኝም:: አያበሳጭም:: ክፉ ነገርን አያሳስብም:: ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም:: ሁሉን ይታገሣል:: ሁሉን ያምናል:: ሁሉን ተስፋ ያደርጋል:: በሁሉ ይጸናል::" [ ፩ቆሮ.፲፫፥፬ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

#ጸሎትና_ትህትና
#ጸሎትና_ትህትና አብረው የሚያያዙ ነገሮች ናቸው። ወደ እግዚአብሔር በጸሎት መቅረብ ያለብን በትህትና ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጸሎት በተናገረበት ክፍል በሉቃ ፲፰፥፩_፲፬ ላይ ያስተማረን፥ትህትናን ከጸሎታችን ጋር #እንድናዋህድ ነው። ፈሪሳዊው ራሱን በመካብ በሌላው ላይ ጣቱን በመቀሰር #እግዚአብሔር_ሆይ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም ፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ #አመሰግንሃለሁ ፤» ይል ነበር። ፈሪሳዊው ከሌላው ለመብለጡ ማስረጃ አድርጎ ያስቀመጠው፥ ጦሙንና አሥራቱን ነበር ። #ቀራጩ ግን ወደ እግዚአብሔር የቀረበው በተለየ መንገድ ነበር ፤ #በትህትና ነበር የቀረበው፤ « ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን፦ አምላክ ሆይ፥ እኔን #ኃጢአተኛውን #ማረኝ_እያለ_ደረቱን_ይደቃ_ነበር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌውን ሲደመድም፥ ከፈሪሳዊው ይልቅ ያ #ቀራጭ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ እንደተመለሰ በመናገር እንዲህ ይለናል። #ራሱን_ከፍ የሚያደርግ ሁሉ #ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።»
#_ሰናይ__ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

🙏5❤2👍2
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
❝ ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል ? ቃልህን በመጠበቅ ነው። ❞ [ መዝ . ፻፲፱ ፥ ፱ ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ሕይወተ ወራዙት [ የወጣቶች ሕይወት ! ]
[ ክፍል - ስምንት - ]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ወጣትነትና ፈተናዎቹ [ የዕውቀት ፈተና ]
❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
🕊 💖 🕊
👇

❤2
በዓለ ንግስ ጥር 18
እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ
እንዲያነቡት ተጋሩት
ጥር 18 ቀን በዕለተ ቅዳሜ የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ንግስ በገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታቦተ ሕጉ ስለሚከብር እርስዎም የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በማክበር እንዲገኙ ስንል በልዑል እግዚአበሔር ስም ጠርተንዎታል ።
አድራሻ :- ከቦሌ ገርጂ ት/ቤት 100 ሜትር ገባ ብሎ ፣ ለሁሉም ሼር አድርጉ 🙏

❤12👍3🥰1
🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡
† ጥር ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ † 🕊
መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው : አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ፯ ዓመታት
ስቃይ በኋላ ተሰይፏል:: ይህስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ :-
- ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ [ አንስጣስዮስ ] እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም [ ልዳ ] ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::
- ቅዱስ ጊዮርጊስ ፳ ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት [ የአሁኗ ቤይሩት-ሊባኖስ ] ሰዎች ዘንዶ/ደራጎን ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::
- ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና ፸ ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ [ ዐውደ ስምዕ ] ደረሰ::
- ከዚያም ለተከታታይ ፯ ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: ፫ ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ የሰማዕታት አለቃቸው: ፀሐይና የንጋት ኮከብ በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ:
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ" እንዲል መጽሐፍ::
- ከ፯ ዓመታት መከራ በኋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: ፯ አክሊላትም ወርደውለታል::
† ዝርወተ ዓጽሙ †
- ይህቺ ዕለት ለሰማዕቱ 'ዝርወተ አጽሙ' ትባላለች:: በቁሙ 'አጥንቱ የተበተነበት' እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው:: ፸ ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ [ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ] አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ::
- በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ:: ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው: በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት:: ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት:: ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት::
- በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ [ ደብረ ይድራስ ] ወጥተውም በነፋስ በተኑት:: "ሐረድዎ ወገመድዎ: ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ዓመድ" እንዲል:: [ ምቅናይ ]
- እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች: ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ "ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" የሚል ጽሑፍ ተገኘ:: ስለዚህም ይህቺ ዕለት ቅዱሱ አለቅነትን የተሾመባት ናት ማለት ነው::
- ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና "በክርስቶስ እመኑ" ብሎ: አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው:: ፹ው ነገሥታት ግን አፈሩ::
🕊 † ቅዱስ ባኮስ ጃንደረባው † 🕊
- 'ጃንደረባ' የሚለው ቃል በግዕዙ 'ሕጽው' ተብሏል:: ይህ ስም በቤተ ክርስቲያን የተለመደ እንጂ እንግዳ አይደለም:: መድኃኒታችን እንዳለው በተፈጥሮ የሆኑ: ሰዎች እንዲያ ያደረጉዋቸውና ራሳቸውን ስለ ጽድቅ ጃንደረባ ያደረጉ ብዙዎች ናቸውና::
- ኢትዮዽያዊው ጃንደረባ ቅዱስ ባኮስም [ አንዳንዴ አቤላክ / አቤሜሌክም ይባላል] :-
- በ፩ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ኢትዮዽያ ተወልዶ ያደገ
- ነገሥታቱንና ሃገሩን በሙያው ያገለገለ
- በተለይ ከ፴፬ እስከ ፵፮ ዓ/ም ለነገሠችው ንግሥት ሕንደኬ ገርስሞት በገንዘብ ሚንስትርነት ያገለገለ
- በገንዘቧ ላይ ሁሉ አዛዥ [ ታማኝ ] የነበረ
- ጃንደረባ በመሆኑ ለንግሥቲቱና ቤተሰቧ ቅርብ የነበረ
- መጻሕፍትን የሚያነብና የሚመረምር
- ዘወትር ወደ ኢየሩሳሌም እየሔደ ከቅዱሳት መካናት የሚሳለም በጐ ሰው ነበር::
- በግብረ ሐዋርያት ምዕ.፰፥፳፮ ላይ እንደ ተጠቀሰው ቅዱሱ ከኢየሩሳሌም ለፋሲካና ለእሸት በዓል ነበር የሔደው:: ሲመለስ መንፈስ ቅዱስ ከፊልዾስ ጋር በጋዛ አገናኝቶታል:: በዚያም ምሥጢረ ክርስትናን ተምሮ: በክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት አምኖ ተጠምቁዋል::
- ክርስትናን ለኢትዮዽያ በ፴፬ ዓ/ም አምጥቷል:: "ጃንደረባው ለወገኖቹ ሐዋርያ ሆነ" ሲል ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንደ ተናገረው ወደ ሃገራችን ተመልሶ: ስለ ክርስቶስ ሰብኮ በርካቶችን አሳምኗል::
- ቀጥሎም ሃብቱን ንቆ [ መንኖ ] : ከኢትዮዽያ እስከ ሕንድ ወንጌልን ሰብኮ በዚህች ዕለት በሰማዕትነት ዐርፏል:: [ ተሰውሯል የሚሉም አሉ ]
" በእውነት ለቅዱስ ባኮስ ክብር ይገባል:: "
🕊 † ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን † 🕊
+ ይህ ቅዱስ ሰው :--
- እጅግ የተመሠከረለት ሊቅ
- በፍጹም ትሕርምት የኖረ ገዳማዊ
- በርካቶችን ወደ ክርስትና ያመጣ ሐዋርያዊ
- ለአእላፍ ምዕመናን እረኛ የሆነ የንጽቢን [ ሶርያ ] ዻዻስ
- ለጀሮ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን የሠራ ገባሬ መንክራት
- ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊን ጨምሮ በርካታ ሊቃውንትን ያፈራ ታላቅ መምሕር
- ለክርስቶስና ለእመቤታችን ታጥቆ የተገዛ የፍቅር ሰው
- እጣቶቹ እንደ ፋና የሚያበሩለት ማኅቶት
- ራሱን ዝቅ አድርጐ በቆሸሸ ልብስ የሚኖር የትህትና ሰው ነው::
- በ፫፻፳፭ [፫፻፲፰] 325 (318) ዓ/ም: በኒቅያ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡና አርዮስን ሲያወግዙ እርሱ አንዱ ነበር:: በሥፍራውም ሙት አስነስቶ ሕዝቡን አስደምሟል:: በዚያም የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ሠርቶ ወደ ሃገሩ ተመልሶ በቅድስና ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::
🕊 † ደናግል ማርያ ወማርታ † 🕊
- በዘመነ ሐዋርያት በተመሳሳይ 'እንተ ዕፍረት-ባለ ሽቱ' ተብለው የሚጠሩ ፪ እናቶች ነበሩ:: 2ቱም ስማቸው ማርያም ስለ ነበር ለመለየት እንዲያመች አንደኛዋን 'ማርያም ኃጥዕት- ከኃጢአት የተመለሰች': ፪ኛዋን ደግሞ 'ማርያም እኅተ አልዓዛር-በቢታንያ የነበረችው ብለው አበው ይጠሯቸዋል::
- በሉቃስ ወንጌል ላይ የምትገኘው ከኃጢአት ሕይወት የተመለሰችው ስትሆን በዮሐንስ ወንጌል ፲፪፥፩ ላይ ያለችው የአልዓዛር እህት [ ድንግሊቱ ] ናት:: ዛሬም የምናስባት ይህቺውን እናታችን ነው::
- ቅድስት ማርያም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሚያስተመርበት ዘመን በቢታንያ አካባቢ ትኖር የነበረች ድንግል ወጣት ናት:: ወላጆች ባልነበረበት ቤት ውስጥ ታላቆቿ አልዓዛርና ማርታ አሳድገዋታል::
- በቤተሰብ ደረጃ እንግዳን ይቀበሉ ነበርና ጌታችን ወደዳቸው:: አልዓዛርን ከ፸፪ቱ አርድእት: ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: ወንድማቸው አልዓዛር በታመመ ጊዜ ወደ ጌታ ልከው ነበር::
- ያለ ጊዜው የማይሠራ ጌታ ባይመጣ አልዓዛር ሞተ:: በ፬ኛው ቀን አምላክ ሲመጣ ቅድስት ማርያም በጌታ ፊት ሰግዳ
"እግዚእየ ሶበሰ ኀሎከ ዝየ እምኢሞተ እሑየ-አንተ በዚህ በኖርክስ ወንድሜ ባልሞተ ነበር" ብላ አለቀሰች:: [ ዮሐ.፲፩ ]

👍5❤1