Telegram Web
3👍2
                         †                        

 [       🕊    ፍኖተ ቅዱሳን    🕊      ]

[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

             [        መታዘዝ !         ]

🕊

ኑ የመታዘዝን ፍሬ ብሉ ! ...  "

❝  ሌላ አባት ደግሞ ጀማሪ ተማሪያቸውን በገዳሙ ደጃፍ እንዲቆምና ወደገዳሙ የሚገቡትን ሰዎች ሁሉ በፊታቸው እየሰገደ ፦ " የሥጋ ደዌ ተጠቂ ነኝና ጸልዩልኝ ! " እንዲል አዘዙት፡፡

ይህ ምናልባት ለእኔና ለእናንተ መቀለድ ሊመስለን ይችላል፡፡ ነገር ግን እነዚያ አባቶች እንዴት ባለ መንገድ ታዛዥነትን እንደሚለማመዱ የሚያሳይ ነው፡፡ እናም በሚከተሉት ስልት ላይ ውሳኔ ከማሳለፍህ በፊት እባክህን ወደሚያገኙት ውጤትና ወደሚያፈሩት ፍሬም ተመልከት፡፡

ዓመታትን ከፈጀ ደረቅ በትርን ውኃ ማጠጣት በኋላ እንጨቱ ለምልሞ አፈራ፡፡ እኚያም መምህር ፍሬውን ወደ ሌሎች መነኮሳት ወስደው ፦ " ኑ የመታዘዝን ፍሬ ብሉ ! " አሏቸው፡፡ ❞

🕊

የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡


†                         †                         †
💖                      🕊                      💖
3
5
🕊

[  † እንኳን ለቅዱሳን አክሎግ ቀሲስ : መርምሕናም : ወዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊 †  ቅዱስ አክሎግ ሰማዕት † 🕊

† ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ዓበይት ሰማዕታት አንዱ ይህ ቅዱስ ነው:: "አክሎግ" ማለት "በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ [ተወዳጅ]" ማለት ነው:: እውነትም ጥዑም ዜና: ጣፋጭ ሕይወት ያለው አባት ነው:: "መልአክ ስምን ያወጣል" የሚባለው እንዲህ ላለው ነውና::

እርሱ የወላጆቹ ፍሬ ነው:: በ፫ኛው መቶ ክ/ዘ የነበሩ ወላጆቹ ለልጃቸው ያወረሱት ሞልቶ የተረፈ ሃብታቸውን አልነበረም:: ይልቁኑ ፍቅረ ክርስቶስን: ምሥጢረ መጻሕፍትን: ክርስቲያናዊ ስምን ነው እንጂ::

ቅዱስ አክሎግ ገና ከልጅነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ: ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሮ: ሐዲስ ኪዳንን በሙሉ: መኀልየ ነቢያትን: መዝሙረ ዳዊትን አክሎ በቃሉ አጠና:: ቅዱስ ቃሉ ለእርሱ እውቀት አልነበረም: ሕይወት እንጂ:: ሳይሰለች ያነበው: በሕይወቱም ይተረጉመው ነበርና::

በዚህ ንጹሕ ሕይወቱም ፈጣሪውን አስደስቶ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: ከዚያም ተጋድሎውን ቀጥሎ በትሕርምት ኑሯል:: ቀሲስ ሆኖ ሲሾምም ቅዱሳን መላእክት "ይገባዋል!" ሲሉ ፫ ጊዜ ጮሁ:: በጽድቅ ጸንቶም ዘመናት አለፉ::

በዘመነ ሰማዕታትም ነጭ በነጭ ለብሶ ብዙ መከራን ተቀበለ:: በዚህች ቀንም ከብዙ ተከታዮቹ ጋር ደሙ ፈሷል:: ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን "ጻድቅ: ንጹሕ: ድንግል: ባሕታዊ: ቀሲስ ወሰማዕት" ብላ ታከብረዋለች:: ጌታም "ስምህን ያከበረውን: የተሰየመውን እምርልሃለሁ" ብሎታል::


🕊 † ቅዱስ መርምሕናም ሰማዕት † 🕊

† ሰማዕቱ በቤተ ክርስቲያን ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ዐበይት ቅዱሳን አንዱ ነው:: በየአብያተ ክርስቲያናቱ ከሚሳሉ ቅዱሳንም አንዱ ነው:: ሃገሩ አቶር [በፋርስ አካባቢ] ሲሆን አባቱ ሰናክሬም የሚባል ንጉሠ ነገሥት ነው::

እናቱ ምንም ክርስቲያን ብትሆንም ስለ ፈራች ሁለቱን ልጆቿን [መርምሕናምና ሣራን] ክርስትናን አላስተማረቻቸውም:: ሁለቱም ወጣት በሆኑ ጊዜም ከንጉሥ አባታቸው ጋር ይወጡ ይገቡ ነበርና እናታቸው በሐዘን ጸለየች:: ወዲያውም ወጣቷ ሣራ በለምጽ ተመታች::

የሚፈውሳት ጠፋ:: መርምሕናም ግን ጐበዝ ወጣት ነውና ፵ [40] የጦር አለቆችን ይመራ ነበር:: በዚያው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ቅዱስ መርምሕናም ፵ [40] ተከታዮቹን ይዞ ለአደን ወደ ዱር ሲወጣ ከአባ ማቴዎስ ገዳማዊ ጋር ተገናኘ::

ጻድቁ ለብዙ ዓመታት በበርሃ የኖሩ አባት ናቸው:: አካላቸው በጸጉር ስለ ተሸፈነ ደንግጦ ሲሸሽ "ልጄ አትፍራ! እኔም እንዳንተ የክርስቶስ ፍጡር የሆንኩ ሰው ነኝ" አሉት::

እርሱ ግን "ደግሞ ክርስቶስ ማነው?" ሲል ጠየቃቸው:: አባ ማቴዎስም ምሥጢረ ክርስትናን ከመሠረቱ አስተምረው የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት ነገሩት::

ቅዱስ መርምሕናም ግን "ክርስቶስ አምላክ እንደ ሆነ አምን ዘንድ እህቴን አድንልኝ" አላቸው:: "አምጣት" ብለውት አመጣት:: ጻድቁ ጸሎት አድርሰው መሬትን ቢረግጧት ውኃን አፈለቀች:: "በእምነት: በስመ ሥላሴ ተጠመቁ" አሏቸው::

ቅዱሱ: እህቱ ሣራና ፵ [40] የጦር አለቆች ተጠምቀው ሲወጡ ሣራ ከለምጿ ነጻች:: ፈጽሞም ደስ አላቸው:: ወደ ቤተ መንግስት ተመልሰውም ቅዱስ መርምሕናም ከእናቱ: ከእህቱና ከ40 ተከታዮቹ ጋር ክርስቶስን ሊያመልኩ ጀመሩ::

ንጉሡ ሰናክሬም ግን ነገሩን ሲሰማ ተቆጣ:: እነርሱም ወደ ተራራ ሸሹ:: ንጉሡ "ልጆቼ! መንግስቴን ውረሱ" ብሎ ቢልክባቸውም እንቢ አሉ:: ስለ ተበሳጨም ቅዱስ መርምሕናምን: ቅድስት ሣራንና ፵ [40ውን] ቅዱሳን በሰይፍ አስመታቸው::

ሥጋቸውን በእሳት ሊያቃጥሉ ሲሉ ግን መነዋወጥ ሆኖ ብዙ አረማውያን ሞቱ:: ንጉሡም አብዶ አውሬ [እሪያ] ሆነ:: ያን ጊዜ አባ ማቴዎስ ከበርሃ ወጥተው ንጉሡን ሰናክሬምን ፈወሱት::

እርሱም አምኖ የልጆቹና የ40ውን ሥጋ በክብር አኖረ:: በሃገሩ አቶርም የእመ ብርሃን ማርያምን ቤተ መቅደስ አነጸ:: በክርስትና ኑሮም ዐረፈ:: እርሱ ከተቀበረ በኋላ ግን የከለዳውያን ንጉሥ መጥቶ አቶርን ወረራት::

ንግሥቲቱን [የቅዱሳኑን እናት] ከሕፃኑ ልጇ ጋርም ገደለ:: በኋላም "ለጣዖት ስገዱ" ማለቱን የሰሙት የቅዱስ መርምሕናም ወታደሮች ደርሰው በምስክርነት ተሰየፉ:: ቁጥራቸውም መቶ ሰባ ሺህ [170,000] ሆነ::


🕊 †  ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ [ ወንጌሉ ዘወርቅ ]   † 🕊

† ቅዱሱ "ወንጌሉ ዘወርቅ" እየተባለ የሚጠራው ከሌሎች "ዮሐንስ" ከሚባሉ ቅዱሳን ለመለየት ቢሆንም ዋናው ምክንያት ግን እድሜ ልኩን የሚያነበው: ከእጁ የማይለየውና አቅፎት የሚተኛ በወርቅ የተለበጠ ወንጌል ስለ ነበረው ነው::

የቅዱስ ዮሐንስ ታሪኩ በሆነ መንገድ ከመርዓዊ [ሙሽራው] ገብረ ክርስቶስ እና ከቅዱስ ሙሴ ሮማዊ ጋር ተመሳሳይነት አለው::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በሮም ግዛት ሥር የሚኖሩ አጥራብዮስና ብዱራ የሚባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ:: እግዚአብሔር በቀደሰው ትዳር የሚኖሩና ነዳያንን የሚዘከሩ ነበሩና ይህንን ቅዱስ ወለዱ:: ስሙን ዮሐንስ ብለው: እንደሚገባም አሳድገው: ምሥጢረ መንግስተ ሰማያትን እንዲረዳ ለመምህር ሰጡት:: ቅዱስ ዮሐንስ ከመምህሩ ዘንድ ቁጭ ብሎ መጻሕፍተ ቤተ ክርስቲያንን ተማረ::

ለወላጆቹ ቅንና ታዛዥ ነበርና አባቱ "ልጄ ! የምትፈልገውን ጠይቀኝ:: ምን ላደርግልህ ትወዳለህ?" አለው:: ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድሮ እኛን የሚያምረን ሁሉ አላሰኘውም:: አባቱን "ቅዱስ ወንጌልን ግዛልኝ: በወርቅም አስለብጠው" አለው:: አባትም የተባለውን ፈጸመ::

ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ከዚህ ዓለም ተለይቶ እስካረፈባት ቀን ድረስ ቅዱስ ዮሐንስና የወርቅ ወንጌሉ ተለያይተው አያውቁም:: ሁሌም ያለመታከት ያነበዋል:: ሲቀመጥም ሲነሳም: ሲሔድም ሲተኛም አብሮት ነበር::

ቅዱስ ዮሐንስ ወጣት በሆነ ጊዜ ወላጆቹ ይድሩት ዘንድ ተዘጋጁ:: ልብሰ መርዐም [የሙሽራ ልብስ] አዘጋጁ:: በዚያው ሰሞን ግን አንድ እንግዳ መነኮስ ወደ ቤታቸው መጥቶ ያድራል:: በዚያች ሌሊት መነኮሱ በጨዋታ መካከል ስለ ቅዱሳን መነኮሳት ተጋድሎና ክብር ነገረው:: የሰማው ነገር ልቡናውን የማረከው ቅዱስ ዮሐንስ ከዚያች ቀን ጀምሮ ወደ ፈጣሪው ይለምን ነበር::

አንድ ቀን ግን ያ መነኮስ በድጋሚ መጥቶ አደረ:: ቅዱስ ዮሐንስ መነኮሱን ወደ ገዳም እንዲወስደው ቢጠይቀው "አይሆንም: አባትህ ያዝንብኛል" አለው:: ቅዱሱ ግን "በእግዚአብሔር ስም አማጽኜሃለሁ" ስላለው ሁለቱም በሌሊት ወጥተው ወደ ገዳም ሔዱ::

አበ ምኔቱ "ልጄ! የበርሃውን መከራ አትችለውም: ይቅርብህ" ቢለውም "አባቴ! አይድከሙ:: ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር አይለየኝም'' ስላላቸው እንደሚገባ ፈትነው አመንኩሰውታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከመነኮሰ በኋላ በጾም: በጸሎት: በስግደትና በትሕርምት ያሳየው ተጋድሎ በርካቶችን አስደነቀ::

ለሥጋው ቦታ አልሰጣትምና በወጣትነቱ አካሉ ረገፈ:: ቆዳውና አካሉም ተገናኘ:: ሥጋውን አድርቆ ነፍሱን አለመለማት:: በእንዲሕ ያለ ሕይወት ለ7 ዓመታት ከተጋደለ በኋላ በራዕይ "ወደ ወላጆችህ ተመለስ" እያለ ፫ ጊዜ አናገረው::
ቅዱስ ዮሐንስ ወደ አበ ምኔቱ ሔዶ ቢጠይቀው "ራዕዩ ከእግዚአብሔር ነው" ብሎ ወደ ቤተሰቦቹ አሰናበተው::
👍1
ቅዱስ ዮሐንስ በላዩ ላይ የነበረችውን ልብስ በመንገድ ለነዳይ ሰጥቶ: በፈንታው ቆሻሻ ጨርቅ ለብሶ ከወላጆቹ በር ላይ ለመነ:: "እባካችሁ አስጠጉኝ" አላቸው:: ወላጆቹ በጭራሽሊለዩት አልቻሉም:: ነገር ግን አሳዝኗቸዋልና በበራቸው አካባቢ ትንሽ ቤት ሠሩለት::

በዚያች በዓት ውስጥ እንዳስለመደ በትጋት ለ፯ ዓመታት ተጋደለ:: በእነዚህ ዓመታት እንኳን ሌላው ሰው ወላጆቹም ቢሆኑ ፍርፋሪ ከመስጠት በቀር አይቀርቡትም ነበር:: ምክንያቱ ደግሞ "ይሸተናል" የሚል ነበር:: በመጨረሻም መልአከ እግዚአብሔር ከሰማይ ወርዶ "ከ፯ ቀናት በኋላ ታርፋለህ" አለው::

እናቱን ጠርቶ "አንድ ነገር ልለምንሽ" አላት:: "እሺ" አለችው:: "ከሞትኩ በኋላ በለበስኳት ጨርቅ እንድትገንዙኝ: በበዓቴ ውስጥም እንድትቀብሩኝ" አላትና የወርቅ ወንጌሉን አውጥቶ ሰጣት:: ያን ጊዜ አባቱም ደርሶ ነበርና ደነገጡ::

የወርቅ ወንጌሉን ለዩት:: ልጃቸውን ግን መለየት አልቻሉምና እያለቀሱ ስለ ልጃቸው የሚያውቀው ካለ እንዲነግራቸው ለመኑት:: እርሱም "ልጃችሁ ዮሐንስ እኔ ነኝ" አላቸው::

በዚያ ቅጽበት ወላጆቹ የሰሙትን ማመን አልቻሉም:: በፍጹም ዋይታ እየጮሁ አለቀሱ:: ለቅሷቸውን የሰሙ ሁሉ ተሰበሰቡ:: ለ7 ቀናት እኩሉ እያለቀሰ: እኩሉ እየተባረከ በዓቱን ከበው ሰነበቱ:: በ7ኛው ቀን መልአኩ መጥቶ በክብር ነፍሱን ተቀበለ::

እናቱ የልጇን አደራ ረስታ [እሷስ መልካም አደረግሁ ብላ ነው] ለሠርጉ ባዘጋጀችው የወርቅ ልብስ ገነዘችው:: ወዲያው ግን በጽኑ ታመመች:: አባት ግን ፈጠን ብሎ በዚያች ጨርቅ ገንዞ በበዓቱ ውስጥ ቀበረው:: ያን ጊዜ እናት ፈጥና ዳነች:: ከቅዱሱ መቃብርም ብዙ ተአምራትና ፈውስ ተደርጓል::

† ቸሩ እግዚአብሔር ከወዳጆቹ በረከት ያሳትፈን፡፡

🕊

[  † ጥር 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ [ ሰማዕትና ጻድቅ ]
፪. ቅዱስ መርምሕናም ሰማዕት [ ቅዳሴ ቤቱ ]
፫. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ [ ቅዳሴ ቤቱ ]
፬. አባ አብድዩ ጻድቅ
፭. ቅዱስ ብሕኑ ሰማዕት
፮. ቅዱስ አብሮኮሮስ ሐዋርያ [የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር]
፯. አባ ኖሕ

[   † ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፪. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት
፫. ቅዱስ አሞንዮስ
፬. ቅዱስ ካሌብ ንጉሠ ኢትዮጵያ
፭. ቅድስት ሳድዥ የዋሂት

" እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ: የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ: በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ:: በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሱ:: የመዳንንም ራስ ቁር: የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ:: እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው:: በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ:: በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ::" † [ኤፌ. ፮፥፲፬]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🙏4
2
እግዚአብሔር ባደረበት ሰይጣን፤ ሰይጣን ባደረበት እግዚአብሔር አያድርም። ብርሃን ከጨለማ ጋር አንድ የሚያደርገው ምንድን ነው? ማኅደረ መለኮት በሆነች በድንግል ማርያም መርገመ ዲያብሎስ የለም። [2ኛ ቆሮ፤6-14]

"ሰው ከተግባር ኃጢአት ቢነፃ ፤ ከመናገርና ከማሰብ ኃጢአት ሊነፃ አይችልም። ከማሰብ ኃጢአት ከነፃ ግን ከመናገርም ሆነ ከተግባር ኃጢአት የፀዳ ነው። በሀሳብሽም ድንግል ነሽ እያልን የምናመሰግናት እናታችን በእውነት ንፅህት ናት። [ሉቃ 1:29]

እንዴት ከሰው ተለይታ መርገም ሳይወድቅባት ቀረ የሚል ካለ እንዴት ከሴቶች ተለይታ ቡርክት እንደተባለች ይወቅ። [ሉቃ 1:28]

በአዳም ምክንያት ምድር የተረገመች ብትሆንም። ሙሴ የቆመባት ሥፍራ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ ተብሎ ነበር። [ዘፀ 3:5]

ቅዱስ ገብርኤል ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ማለቱ ለሙሴ የተነገረችው ንፅህት ምድር አንቺ ነሽ ማለቱ ነው።

"ከሴቶች ተለይታ አምላክን መውለድ ለእርሷ ብቻ እንደተቻለ ፤ ከሴቶች ተለይታ ቡርክት መሆንም እመቤታችን ብቻ የቻለችው ነው። ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ነውርም የለብሽም።” መኃ. 4፥7

            #_ሰናይ__ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
9👍2
                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]

            [     ክፍል  ሰባ ስድስት     ]

                         🕊  

[  ስለ ሰናፍጭ ቅንጣት ትርጉም ተናገረ ! ]

🕊

❝  ጥቂት አኃው በአባ መቃርዮስ ዙሪያ ተቀምጠው ፦ ስለ ሰናፍጭ ቅንጣት ትርጉም ንገረን ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ ብሎ ነገራቸው ፦ “የሰናፍጭ ቅንጣት ከመንፈሳችን ጋር ልትነጻጸር ትችላለች ፣ አንድ ሰው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እውቀት ገንዘብ ካደረገ መንፈሱ ብሩህና የተመጠነ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡ የሰናፍጭ ቅንጣት የተመጠነና የተቀመመ እንደ ሆነ ሁሉ እንደዚሁም መምህሩም ነገሩ የተቀመመና መረዳቱም ብልህ ነው ይባላል” አለ፡፡

አኃውም ፦ “ማደግ ምንድን ነው ? የእኛ ቅጠሎችስ ምንድን ናቸው?” አሉት፡፡

አባ መቃርዮስም እንዲህ አላቸው ፦ “ዕድገት መንፈሳዊ የመልካም ተጋድሎ ሕይወቶች ናቸው ፤ ቅጠሎች ደግሞ የዋሃንና ንጹሐን የሆኑት ሰዎች ናቸው፡፡ ዛፍ ሲኖር የሰማይ ወፎች መጥተው በቅርንጫፎቹ ጎጇቸውን ሊሠሩበት ይችላሉ፡፡ እኛም ሰማያውያን ሰማያውያን ዛፎች ለመገኘት እንድንችል እንሁን !

ዛፉ የሚያስተምረው መምህር ነው ፤ ለተማሪዎቹ የሚሰጣቸው ትምህርቶችና ማበረታቻዎች ቅርንጫፎች ናቸው፡፡ የሰናፍጭ ቅንጣት ውስጧ [ልቧ] አንድ ነው ፤ ወንድሞቼ ሆይ ፦ በሦስት መሥፈሪያ የሰወርነውን እርሾ ማለትም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ እንቀበል ዘንድ እኛም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ልባችን አንድ ይሁን፡፡

ሦስት መሥፈሪያ የተባሉም ሥጋ ፣ ነፍስና መንፈስ ናቸው፡፡ሦስቱ መሥሪያዎች አንድን ሙሉና ፍጹም ሰው የሚያስገኙ ፣ የክርስቶስ ሙላት ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ ለመድረስ መለኪያዎች ናቸው፡፡

አኃውም እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ በአእምሮው ርቀትና አስተዋይነት ተገረሙ ፣ ልቡናቸውም ታደሰ ፣ “ከማሰቤ የተነሣ እሳት ነደደ” [መዝ.፴፰፥፫] የተባለውም ተፈጸመ፡፡ ❞

🕊

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


💖                      🕊                      💖
4
                         †                       

[   🕊 ሕይወት እናት ሞት !  🕊   ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒

[ † እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

🕊

❝ የአምላክ እናት ሆይ ጌታን በመውለድሽ ምክንያት ድንግልናሽን እንዳልተውሽ በመሞትሽም ይህንን ዓለም አልተውሽውም:: የሕይወት እናት ነሽና ዛሬ ወደ ሕይወት ተሻገርሽ:: በአማላጅነትሽም ነፍሳችንን በኃጢአት ከመሞት ታደጊ"

‹ ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ ❞

[ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ]

❝ ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ ❞

[ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ] (Homily on the Dormition)

❝ በእርሱ ምክንያት ሰማይ ተብላ የተጠራችበት የሚመስለው የሌለ የማሕፀንዋ ፍሬ ለመሞትና ለመቀበር ፈቃደኛ ከሆነ ያለ ዘር የወለደችው እናቱ እንዴት ሞትን ትፈራለች ? ❞

[ ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ] (The life of Virgin Mary)


❝ የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው ❞

[ ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ]  (aka Doctor of Dormition)


[  † እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

💖                      🕊                      💖
3👍1
6❤‍🔥1
🕊

[ አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ]

❝ ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው። በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው። በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው።

በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ። አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [ የተለያየ ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ። ❞

[  ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ]

💖                      🕊                      💖


[ መጽሐፍ እንደተናገረ በፈጣሪ እና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የቃል ኪዳን ማደሪያ [ ምልክት ] የሆንሽ የብርሃን ቀን ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ሆይ በገነት ያሉ ጻድቃን በአንቺ ደስ ይላቸዋል፡፡ ኃጥአንም ከደይን በአንቺ ይወጣሉ፡፡ ]

[   አባ ጽጌ ድንግል   ]


[ † እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]


💖                      🕊                      💖
❤‍🔥2🙏1
3❤‍🔥1👍1
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ እረፍት(ጥር21) ፤አስተርዮ ማርያም በሰላም አደረሳችሁ

#የህይወት_እናት_ድንግል_ማርያም_ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል።


እመቤተ ማርያም ሆይ ያለመጨነቅ ያላፃር ከሥጋዋ ለተለየች ነፍስሽ ሰላምታ ይገባል አነዋወሯም በልጅሽ ቀኝ ጐን በክብር ነው። ድንግል ሆይ ከፈጣሪ ዘንድ የባለማልነትን ግርማ የተጐናፀፍሽ ነሽ። በረድኤትሽ ሰውነቴን ከድካሟ አሳርፊያት። ክብሯም (ኃይሏም) ከድጋግ አባቶቿ ክቡር (ኃይል) ያነሰ አይሁን። መልክአ ቅድስት ድንግል ማርያም።

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
11❤‍🔥1👍1
🕊

[  † እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !  † 

🕊   †   ዕረፍተ ድንግል   †   🕊

† እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::

- ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ "እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ፭ ቀን ተኩል  [5500 ዘመናት] በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ ንጽሕት ዘር ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::

- ከአዳም አንስቶ ለ፭ ሺህ ፭ መቶ [5500] ዓመታት አበው: ነቢያትና ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::

† የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ ፦

- ከአዳም በሴት
- ከያሬድ በሔኖክ
- ከኖኅ በሴም
- ከአብርሃም በይስሐቅ
- ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
- ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::

- ከሌዊ ደግሞ በአሮን: አልዓዛር: ፊንሐስ: ቴክታና በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::

- አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በ፭ ሺህ ፬ መቶ ፹፭ [5,485] ዓመት ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ ኢያቄም ወሐና ትወለዳለች:: [ ኢሳ.፩፥፱ , መኃ.፬፥፯ ] "ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ:: [ ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ ]

ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ፫ [3] ዓመታት ቆይታ ወደ ቤተ መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ፲፪ [12] ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና እያገለገለች: እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመገቧት ኑራለች:: ፲፭ [15] ዓመት በሞላት ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::

- በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው:: ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር: ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ:: [ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ለብሐዊ ]

- ወልደ እግዚአብሔርን ለ፱ [9] ወራት ከ፭ [5] ቀናት ጸንሳ: እንበለ ተፈትሆ [በድንግልና] ወለደችው:: [ኢሳ.፯፥፲፬]  "ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በገሊላ ለ፪ [2] ዓመታት ቆዩ::

- አርዌ ሔሮድስ እገድላለሁ ብሎ በተነሳበት ወቅትም ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም: በዕንባና በኃዘን ለ፫ [3] ዓመታት ከ፮ [6] ወራት ከገሊላ እስከ ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን ፭ [5] ዓመት ከ፮ [6] ወር ሲሆነው: ለድንግል ደግሞ ፳፩ [21] ዓመት ከ፫ [3] ወር ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::

- በናዝሬትም ለ፳፬ [24] ዓመታት ከ፮ [6] ወራት ልጇን ክርስቶስን እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች:: እርሷ ፵፭ [45] ዓመት ልጇ ፴ [30] ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ፫ [3] ዓመታት ከ፫ [3] ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::

- የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: [ሉቃ.፪፥፴፭] ጌታ በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች:: ለ፵ [40] ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::

- ከልጇ ዕርገት በሁዋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ፲፭ [15] ዓመታት ኖረች:: በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ: ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና: ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::

- ዕድሜዋ ፷፬ [64] በደረሰ ጊዜ ጥር ፳፩ [21] ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ: ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ::
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ::" እንዲል::

- ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት :-

"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ::
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ::
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::

- በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል [ጠባቂ መልአክ ነው] እነርሱን ቀጥቶ: እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል:: በዚያም መላእክት እያመሰገኗት ለ፪፻፭ [205] ቀናት ቆይታለች::

- ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ ፩ [1] ሱባኤ ጀመሩ:: ፪ [2] ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል ማርያምን ንጹሕ ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል::

- በ፫ [3]ኛው ቀን [ነሐሴ ፲፮ (16)] እንደ ልጇ ባለ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ ፩ [1] ቀን ሱባኤ ገቡ::

- ለ፪ [2] ሳምንታት ቆይተው: ሁሉንም ወደ ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ ደብረ ዘይት ተመልሰዋል::

† ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን: ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን:: †

🕊 †  ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሊቅ  †  🕊

† ለዚህ ቅዱስ አባት ብጹዕ መባል ተገብቷል:: ክቡር: ምስጉን: ንዑድ ሰው ነውና:: በ፬ [4]ኛው መቶ ክ/ዘመን በቂሣርያ ቀዸዶቅያ የተወለደው ቅዱሱ ሰው ለደሴተ ኑሲስ ብርሃኗ ነው:: አባቱ ኤስድሮስ: እናቱ ኤሚሊያ: ወንድሞቹ ቅዱሳን "ባስልዮስ: ዼጥሮስ: መክርዮስና መካርዮስ" ይባላሉ::

የተቀደሰች እህቱም ማቅሪና ትባላለች:: ከዚህ የተባረከ ቤተሰብ ለቅድስና ያልበቃ አንድም ሰው የለም:: ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከማር በጣፈጠ ዜና ሕይወቱ እንደ ተጻፈው :-

- በልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል::
- ሥጋውያን ጠቢባንን ያሳፍር ዘንድም የግሪክን ፍልሥፍና በልኩ ተምሯል::
👍2
2025/07/09 17:16:46
Back to Top
HTML Embed Code: