#ቹሩ_መድኃኔዓለም
#አቤቱ__ጌታዬ_ሆይ ወደ አንተ ስጣራ ስማኝ የልመናዬንም ቃል አድምጥ እንደ በደለው ልጅ #በመጸጸት አቤቱ በሰማይም በፊትህም በደልሁህ እላለሁ ሉቃ 15:18 በእውነት ሰውን የምትወድ አንተ በፊትህ ተቀበለኝ #ጸሎቴንም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ተቀበለኝ እንደ ቀራጩ ሰው በንስሀ ይቅር በለኝ ጌታዬ ብዬ ለመንኩህ እኔ #ኃጢአተኛ ነኝ ባንተ ዘንድ ግን ብዙ ይቅርታና ምህረት #አለ::
#መልካም_ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

❤11🙏6👍3❤🔥2🥰1👏1
†
[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]
[ ክፍል ሰማንያ አንድ ]
🕊
[ አባ ወቅሪስን ስለ ትዕግሥትና ራስን ስለ መካድ አስተማረው ! ]
🕊
❝ ዳግመኛም አባ ወቅሪስ እንዲህ አለ ፦ “ በቀኑ ሙቀቱ በጣም ከፍተኛ በሆነበት ሰዓት [ቀትር] ላይ አባ መቃርዮስን ላየው ሄድሁ፡፡ በጥም እየተቃጠልሁ ነበርና ፦ 'አባቴ ሆይ ፣ በጣም ተጠምቻለሁ' አልሁት፡፡ እርሱም እንዲህ አለኝ፡- “በጥላው ዐረፍ ማለት ይብቃህ ፣ በዚህ ሰዓት ላይ በመንገድ እየተቃጠሉ ጥላ እንኳ ማግኘት የማይችሉ ብዙ ሰዎች አሉና፡፡”
ከእነዚህ ቃላት በኋላ ከእርሱ ጋር ስለ መልካም ምግባር ሕይወት ተነጋገርኩ፡፡ እርሱም እንዲህ አለኝ ፦ “ልጄ ሆይ ፣ በእውነት ሰውነቴን በዳቦና በውኃ ሳልሞላ ፣ ትንሽ ሽለብ እስኪያደርገኝ ድረስ ከግድግዳ ጠጋ ከምል በስተቀር ዕንቅልፍ ሳላጠግብ ሃያ ዓመት አሳልፌያለሁ፡፡ ❞
🕊
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡
ይቆየን !
💖 🕊 💖

❤2
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ትሕትና ! ]
------------------------------------------
❝ በአፉ ዐረፋ እስኪያስደፍቀው ድረስ ርኩስ መንፈስ ያደረበት አንድ ሰው አንድን መነኵሴ ፊቱን በጥፊ መታው፡፡ መነኵሴውም ሌላኛውን ፊቱን አዙሮ ሰጠው:: በዚህ ጊዜ ጋኔኑ የመነኲሴው ትሕትናው ስላቃጠለው ወዲያውኑ ከሰውዬው ወጥቶ ጠፋ፡፡ ❞
-------------------------------------------
❝ አጋንንት ለምን ይህን ያህል አጽንተው ይዋጉናል?" ብለው አንድን አረጋዊ ጠየቁት፡፡ እርሱም ፦ "መሣሪያዎቻችንን አሽቀንጥረን ስለ ጣልናቸው ነው ፤ መሣሪያዎቻችን ማለቴም ክብርን መናቅን ፣ ትሕትናን ፣ ድህነትንና ጽናትን ማለቴ ነው" አላቸው፡፡ ❞
--------------------------------------------
🕊
የደጋግ አባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †

👍1
🕊
[ † እንኳን ለጌታችን አማኑኤል ክርስቶስ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
[ 🕊 † ተአምረ እግዚእ † 🕊 ]
† " ተአምር " የሚለውን ቃል በቁሙ "ምልክት" ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ [በላይ] : ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ [ሲፈጸም] ተአምር ይባላል::
ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው "ኤልሻዳይ - ከሐሌ ኩሉ - ሁሉን ቻይ" እያልን የምንጠራው::
እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ [ኦሪትን ተመልከት] እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ [፩ ነገሥት] እንደ ነበር ይታወቃል::
እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: [ ማቴ.፲፥፰ , ፲፯፥፳ , ማር.፲፮፥፲፯, ሉቃ. ፲፥፲፯, ዮሐ.፲፬፥፲፪ ]
እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: [ሐዋ. ፫፥፮ , ፭፥፩ , ፭፥፲፪ , ፰፥፮ , ፱፥፴፫-፵፫ , ፲፬፥፰ , ፲፱፥፲፩]
[ 🕊 † ተአምራተ እግዚእ † 🕊 ]
† ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: እያንዳንዱ ግን ቢጻፍ ዓለም ለራሷ ባልበቃች ነበር:: ከእነዚህ መካከልም አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው በዚህ ዕለት በ፯ እንጀራ እና በጥቂት ዓሣ ሴቶችና ሕፃናትን ሳይጨምር ፬ ሺህ ሰዎችን በቸርነቱ አበርክቶ አጥግቡዋል:: ደቀ መዛሙርቱም ፯ ቅርጫት ማዕድ አንስተዋል::
ጌታችን በከሃሊነቱ የተራቡትን ሲያጠግብ እንዲሁ አይደለም:: በጊዜው የነበሩ አይሁድ ጠማሞች ነበሩና እነሱን ምላሽ በሚያሳጣ መንገድ ነበር እንጂ:: አይሁድ ላለማመን ብዙ ጥረት ነበራቸውና::
በዚህ ዕለትም እንጀራውን አበርክቶ ሲያበላቸው :-
፩. ጊዜው አመሻሽ ላይ ነበር:: ምክንያት :- ጧት ላይ ቢሆን ከቤታችን የበላነው ሳይጐድል ብለው ከማመን ይርቁ ነበርና::
፪. ከውሃ ዳር አድርጐታል:: መታጠቢያ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን እንዳይሉ::
፫. ሳር የበዛበት ቦታ ላይ አድርጐታል:: ምክንያቱም መቀመጫ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን እንዳይሉ::
፬. ከከተማ አርቆ ምድረ በዳ ላይ አድርጐታል:: ያማ ባይሆን "ፈጣን: ፈጣን ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው እየገዙ አቀረቡለት" ባሉ ነበርና::
† ለመድኃኒታችን ክርስቶስ አምልኮና ምስጋና ይሁን !
አማኑኤል አምላካችን ጣዕመ ፍቅሩን ያሳድርብን::
🕊
[ † ጥር ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሰማዕት [ስለ ሃይማኖት ፯ ጊዜ ሙቶ የተነሳ , ፯ አክሊል የወረደለት ]
፪. ቅዱስ አካውህ መነኮስ
፫. ፰ መቶ "800" ሰማዕታት
፬. ቅዱስ ዮሴፍ አይሁዳዊ [የእመቤታችን ወዳጅ]
፮. ቅድስት ሳቤላ
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. አባቶቻችን አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ
፪. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
† " ጌታ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ :- ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስከ አሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለ ሌላቸው አዝንላቸዋለሁ:: በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም' አላቸው::
ደቀ መዛሙርቱም :- 'ይህን ያህል ሕዝብ የሚያጠግብ ይህን ያህል እንጀራ በምድረ በዳ ከወዴት እናገኛለን?' አሉት:: ጌታ ኢየሱስም:- 'ስንት እንጀራ አላችሁ?' አላቸው:: እነርሱም:- 'ሰባት: ጥቂትም ትንሽ ዓሣ' አሉት::
ሕዝቡም በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ:: ሰባቱንም እንጀራ: ዓሣውንም ይዞ አመሰገነ:: ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ:: ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ:: ሁሉም በሉና ጠገቡ:: የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሱ:: የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ::" † [ ማቴ.፲፭፥፴፪ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

❤3👍1
#አማኑኤል__ሆይ
#አቤቱ_ተወዳጅ_አማኑኤል_ሆይ ፦
የምንኮራበት ክብራችን የምንደምቅበት አክሊላችን አንተ ነህ፤ ቀና ያልንብህ ትምክህታችን ያረፍንብህ ክንዳችን አንተ ነህ፤ እግራችን እንዳይሰናከል የምትጠብቀን እንዳንባዝን የምታረጋጋን አንተ ነህ፤
#አማኑኤል_ሆይ ፦ ፍቅርህን የሚመስለው የለም፡፡ እንዳንወድቅ የምትጠብቀን ብንወድቅ የምታነሳን አንተ ነህ፤ እንዳንደክም የምትራራልን ብንደክም የምታበረታን አንተ ነህ፤ እንዳንታመም ባንተ እንታመናለን ብንታመምም ስላንተ ተስፋ አለን፤
#አማኑኤል_ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? እንዳንሰናከል መላእክቱን ስለእኛ አዘጋጀልህን ጠላቶች እንደበዙብን አይተህ ወዳጆችን አበዛኅልን፤ ፈተናወቻችንን አይተህ መውጫውን ደግሞ አመላከትከን የቀደመውን ፍቅራችንን ብንቀንስ ያንተን ፍቅር አበዛህልን፤
#አማኑኤል_ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ራቅንህ አንተ ወደኛ ቀረብክ፤ በግብራችን ናቅንህ አንተ ግን እኛን አከበርክ፤ ያለአንተ መኖር እንደማንችል ታውቃለህና ክፋታችንን ሳታይ ራራህልን ስንፍናችንን ሳታይ ቀረብከን ፤
#አማኑኤል_ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ተወዳጅ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ማንም የለንምና ክብራችንን አውቀን እንኖር ዘንድ አንተን ሳናስብ የምንውልበት ጊዜ አይኑረን፡፡
#ክብርና_ምስጋና_ላንተ_ይሁን🙏
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇

❤7🙏2❤🔥1
†
[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]
[ የመጨረሻ ክፍል ]
🕊
[ ስለ እግዚአብሔር ቃል መስማት ! ]
🕊
❝ አባ መቃርዮስ ታላቁ እንዲህ አለ ፦ “በጌታ ቃል ደስ የሚልህ መሆኑ መልካም ነው ፣ ቃሉን ስትሰማ ግን ለመስማት ብቻ ሳይሆን ለመታዘዝና ለማድረግ እንድትችል ሆነህ እንድትማር ሁን ፤ የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ኃይሉ የሚሰማ ሰው ለማድረግም ይማራልና፡፡
ብዙዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተዋል ፣ ሆኖም ግን በእግዚአብሔር ኃይልና በደስታ ሆነው አልሰሙትም ፤ ስለዚህም የሕይወት መሻሻልና ዕድገት አላመጡም፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደዚህ ስላሉት ሰዎች እንዲህ ሲል አሰምቶ ተናግሯል ፦ "የሚሰማ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ፡፡" ሁሉም መስማትን ባያቆሙ ኖሮ እንደዚህ ብሎ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ ብሎ ደጋግሞ ባልተናገረ ነበር፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዲያብሎስ ሥራ ነፍሳት የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይሰሙና ሰምተው እንዳይድኑ መዋጋት መሆኑን ያውቃልና፡፡ ስለዚህም ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ” አለ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰሙ ለውጥና ዕድገት ያሳያሉና ፣ በነፍስና በሥጋ ፈቃዳትና በፍትወታት ሁሉ ላይም ድል አድራጊዎች ናቸውና፡፡
“ ነገር ግን ዲያብሎስ ነፍስን የእግዚአብሔርን ቃል በኃይል ከመስማት ቢያስቆማት [ቢያግዳት] መሻሻልና ማደግ አትችልም ፣ የሰውነት ፈቃዳትንና ፍትወታትን ለመዋጋትም መንገድ አታገኝም ፤ የእግዚአብሔር ቃል በውስጧ አይኖርባትምና፡፡ ጠላት በእርሷ ላይ ኃይል ቢጠቀም ከክፉ ፍትወታትና ከእኩያት ሕሊናት አንዳቸውንም ከእርሷ ለማባረር የምትችልበት መንገዱ ይጠፋባታል፡፡
ቃሉን ገንዘብ ያደረገች ነፍስ ግን ፍትወታት እኩያትንና ክፉ ሕሊናትን ከእርሷ በማባረር ብርቱ ናት ፣ ጠላት ዲያብሎስንም ከእርሷ ታስወጣዋለች ፣ እርሱም ኃፍረትን ተከናንቦ ፈጥኖ ተለይቷት ይሸሻል ፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና ፦ 'የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና ፣ የሚሠራም ሁለትም አፍ ካለው ሠይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው ፣ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል ፣ የልብንም ስሜትና ሃሳብ ይመረምራል፡፡'
“ሰው የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ከቻለ እንዴት ክፉ ሃሳቦችን መቋቋምና ማባረር እንደሚችል ማየት እንችላለን ፣ የማይሰማ ከሆነ ግን ነፍስ ምንም ዓይነት ክፉ ሃሳቦችን ሳታባርር እንደ እርሳስ ትሆናለች፡፡ ስለዚህም ዲያብሎስ እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ይሳለቅባቸዋል ፤ እንደዚህ ያሉ ሰዎች ሕይወታቸውን በሙሉ በገዳምና በድንግልና ያሳለፉ ቢሆኑም እንኳ በምንም ነገር መለወጥና ማደግ አይችሉም፡፡ ከማርና ከማር ወለላ ይልቅ እጅግ በጣም ጣፋጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ጣፋጭነት ጣዕምም አላወቁትም ፣ በተጨማሪም ከምንም ነገር በላይ የሆነውንና የጻድቅ ሰው ልቡ ከአንበሳ ይልቅ ጀግና ነው' እንደ ተባለ ነፍስን ዕለት በዕለት የሚያበረታታትን ፣ ኃይል የሚሰጣትንና የሚያጸናትን የእግዚአብሔርን ኃይል አያውቁም፡፡
“ልጆቼ ሆይ ! እውነተኛና ጻድቅ የሆነ ሰው ልብ እንዴት ጽኑና ጀግና እንደ ሆነ ታያላችሁን ? ምክንያቱም መንፈሳዊ ምግብን ለመቀበል ስለሚፈቅድለት ነው ፣ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ስለዚህም ምክንያት ለሰውነቱ ቀን በቀን ጥንካሬን ስለሚሰጠው ሥጋዊ ምግብን እንደሚወስድ ሰው ነፍሱ ጽኑዕና ደፋር ናት፡፡ ስለሆነም ለመብላትና ኃይል ጽንዕ የሚሆነውን ምግብ ለመውሰድ የማይፈልግ ከሆነ ሰውነቱ እየዛለ ይሄዳል፡፡
ጠላቶቹ ቢዋጉት በቀላሉ ያሽንፉታል፡፡ እናም ልጆቼ ሆይ ፣ በጠላቶቻችሁ ላይ ድል አድራጊዎች ትሆኑ ዘንድ እንዲህ ዓይነት ምግብ ለመመገብ ራሳችሁን አለማምዱ ፣ ይኸውም ቃለ እግዚአብሔር ነው ፤ ጠላቶቻቸውን ድል ለማድረግ የሚያስችላቸውን ኃይልና ድፍረት ያገኙበት የነበረውን ይህን መንፈሳዊ ምግብ መላ የሕይወት ዘመናቸውን አጋንንት ሳይመገቡ እንዲቀሩ ያደረጓቸው ቁጥራቸው በጣም ብዙ የሆነ መነኰሳትና ደናግል አሉና፡
ይህን ምግብ መመገብ ያልቻሉት ለምንድን ነው ? ምክንያቱ ልባቸው የቀና ስላልሆነና የልባቸውን ምኞት መቋቋም ስለማይችሉ ነው ፣ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ልባቸው የረከሰ ስለ ሆነና ስለ እግዚአብሔር ትንሽ እንኳ እውቀት ስለሌላቸው ነው:: ከዚህም የተነሣ ነፍሳቸውን ያበረቱ ዘንድ አጋንንት የተቀደሰ የሆነውን መንፈሳዊ ምግብ ይመገቡ ዘንድ አያሰናብቷቸውም፡፡
ስለዚህም ምክንያት መላ ሕይወታቸውን በፈሪነት ፣ ግራ በመጋባት ፣ በሥቃይ እና እርስ በእርስ በመወነጃጀልና በማመካኘት አጠፉት፡፡ ስለዚህ ተወዳጆች የሆናችሁ ልጆቼ ሆይ ፣ በሕይወት ትኖሩ ዘንድና በመድኃኒታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ሱቱፋን [ተሳታፊዎች] ሆናችሁ ትቆጠሩ ዘንድ ራሳችሁን ከዚህ መጥፎ ፍሬ ጠብቁ፡፡ ❞
🕊
አነሳስቶ ላስጀመረን ፥ አስጀምሮም ላስፈጸመን ለቅዱሳን ሁሉ አምላክ ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን፡፡ የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

👍4❤1