Telegram Web
Audio
🥰21
🥰6
🕊

[  † እንኳን ለቅዱሳት አንስት ሶፍያ ወአዋልዲሃ: ኦርኒ ወማኅበራኒሃ እና ለሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  † ቅድስት ሶፍያና ልጆቿ  †  🕊

† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ታዋቂ ከሆኑ የእናቶቻችን ስሞች "ሶፍያ" ቀዳሚው ነው:: ቃሉ በጥሬው ሲተረጐም "ጥበብ [ጥበበ ክርስቶስ] Wisdom of God" ማለት ነው:: ከጻድቃንና ከሰማዕታት ወገን በዚህ ስም የተጠሩ እናቶች አሉ::

ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆነችው በዕለቱ የምናስባት እናት ቁጥሯ ከሰማዕታት ነው:: ዋናው ዘመነ ሰማዕታት ከመጀመሩ በፊት የነበረችው ቅድስት ሶፍያ ከሕግ ትዳር ፫ ሴቶች ልጆችን አፍርታለች::

ስማቸውንም:- ጲስጢስ [ሃይማኖት] : አላጲስ [ተስፋ] : አጋጲስ [ፍቅር] ስትል ሰይማቸዋለች:: እንደሚገባም በሥርዓቱ አሳድጋ እድሜአቸው 9 : ፲ እና ፲፪ ሲደርስ ለሰማያዊ ሙሽርነት አጭታቸዋለች::

በዘመኑ "ክርስቶስን ካዱ" የሚል መሪ ተነስቶ ነበርና ቅዱሳቱ በመድኃኒታችን አምነው : ጣዖትን ዘልፈው አንገታቸውን ሰጥተዋል:: ክብረ ሰማዕትን : ሃገረ ክርስቶስንም ወርሰዋል::


🕊  †  ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት  †  🕊

† "ኦርኒ" ማለት በምሥራቃውያን ልሳን "ሰላም" ማለት ነው:: ቅድስቲቱ አርበኛ የዘመነ ሐዋርያት የቤተ ክርስቲያን ፍሬ ስትሆን ተወልዳ ያደገችውም በቀድሞው የሮም ግዛት ውስጥ ነው::

ምንም ዛሬ ያለ ትውልድ ቢዘነጋት ቅድስት ኦርኒ ተወዳዳሪ የሌላት ሰማዕት : ሐዋርያዊት : ድንግል ናት:: እርሷ ውበቷን : ንግሥናዋን : ክብሯን : ሃብቷን : ወጣትነቷንና ያላትን ሁሉ ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ሰውታለችና ክብርት ናት::

በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ቤተ መንግስት የተወለደችው ቅድስት ኦርኒ እስከ ወጣትነቷ ድረስ ክርስቶስን ልታውቀው አልተቻላትም ነበር:: ምክንያቱ ደግሞ ንጉሡ አባቷ ጣዖትን ማምለኩ ነበር::

ንግሥት እናቷ ምንም ክርስቲያን ብትሆንም ስለ ክርስትና ልትነግራት አልደፈረችም:: ይህን ብታደርግ የሚደርስባትን መከራ ታውቃለችና:: ግን ደግሞ ውስጥ ውስጡን ትጸልይላት ነበርና ፈጣሪ መንገዱን ሊከፍት ጀመረ::

መምለኬ ጣዖት አባቷ ሰው እንዳያያት ቤተ መንግስት ሠርቶ : ፲፪ ሞግዚቶችን መድቦ ጣዖት ከፊቷ አቁሞ ለዘመናት ዘጋት:: የሚገርመው ግን መልኳን እንዳያይ በበር ሆኖ የሚያስተምራት ፈላስፋ ተቀጥሮ ነበርና የዚህ ሰው ማንነቱ ነው::

መምለኬ ክርስቶስ ደግ ሰው ነበርና ፈሊጥን ይሻላት ገባ:: በዚህ መካከል ቅድስት ኦርኒ ራዕይን ታያለች:: የቤቷ መስኮቶች ተከፍተው ሳሉ በስተምሥራቅ ነጭ ርግብ : የዘይት [የወይራ] ዝንጣፊ ይዛ ገብታ : ከማዕዷ ላይ ጥላው ወጣች::

እርሷን ተከትሎ ቁራ በምዕራብ ገባ:: እባቡን ማዕዷ ላይ ጣለው:: በ3ኛው ደግሞ ንስር ገብቶ አክሊል ትቶላት ወጣ:: ቅድስቲቱም እየገረማት አረጋዊ መምህሯን "ተርጉምልኝ" አለችው::

† እርሱም :-

• ርግብ = ጥበብ [ መንፈስ ቅዱስ ]
• ዘይት = ጥምቀት
• ቁራ = ክፉ ንጉሥ
• እባብ = መከራ
• ንስር = ድል ነሺነት [ ልዑላዊነት ]
• አክሊልም = ክብረ ሰማዕታት ነው" ብሎ ተርጉሞ : ክርስቲያን ሆና ይህ ሁሉ እንደሚደረግ ነግሮ ተሰናበታት::

እርሷም ስትጸልይ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ አጽናናት:: ያጠምቃትና ያስተምራት ዘንድም ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስን ልኮላታል:: ሐዋርያውም የቤተ መንግስቱን ግድግዳ ሰንጥቆ ገብቶ : ለሰማያዊ ሙሽርነት የሚያበቃ ትምህርትና ጥምቀትን ሰጥቷት ሔዷል::

ቅድስት ኦርኒም የአባቷን ጣዖታት ቀጥቅጣ ሰብራ ከአባቷ ጋር ተጣላች:: እርሱም "እገድላታለሁ" ብሎ በእንስሳት ጅራት ላይ ጸጉሯን ሲያስር እንስሶቹ ደንብረው : እጁን ገንጥለው መሬት ላይ ጥለው ገደሉት:: ቅድስት ኦርኒ ግን ጸሎት አድርሳ አባቷን ከሞት አስነሳችው:: እጁንም ቀጠለችለት::

በዚህ ምክንያት በዚያች ዕለት ብቻ አባቷና ፴ ሺህ [ 30,000 ] የከተማው አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል:: ቅድስት ኦርኒ ግን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ ታጥቃ ክርስትናን ሰበከች:: ብዙም ተሰቃየች:: ንጉሡ ዳኬዎስ : ልጁና ሌሎች ፪ ያህል ነገሥታት በእሳት : በአራዊት : በግርፋትና በጦር ፈትነዋታል::

እርሷ ግን ሁሉን በኃይለ ክርስቶስ ድል ነስታለች:: ሙታም የተነሳችበት ጊዜ አለ:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ወደ ሰማያዊ ርስት [ ገነት ] ተመስጣለች:: በዘመነ ስብከቷ ካሳመነቻቸው ባሻገር ፻፴ ሺህ [ 130,000 ] የሚያህሉ ሰዎች ለሰማዕትነት እንዲበቁም ምክንያት ሆናለች::


🕊  † ቅዱስ ጐርጐርዮስ ታኦሎጐስ  †  🕊

† ቅዱሱ :-

• የዘመነ ሊቃውንት ፍሬ:
• የእንዚናዙ ኤጲስ ቆጶስ:
• የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ:
• የጉባዔ ቁስጥንጥንያ [ በ381 ዓ/ም] ፫ኛ ሊቀ መንበር:
• ባለ ብዙ ድርሳን:
• የቂሣርያ [ ቀጰዶቅያ ] ኮከብ:
• ብሩህ ገዳማዊ:
• መልካም እረኛ የነበረ አባት ነው::
መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በጻፋቸው ብዙ መጻሕፍትና በስብከቱ ከሊቃውንት ወገን "ታኦ(ዎ)ሎጐስ" ተብሎ የተጠራ እርሱ ብቻ ነው:: ትርጉሙም በግዕዙ "ነባቤ መለኮት" ማለት ነው:: በአማርኛም "አንድነትን : ሦስትነትን የተናገረ [ያመሠጠረ] እንደ ማለት ነው:: ቅዱሱ ዛሬ ዕረፍቱ ነው::

† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው ይክፈለን፡፡
በመጽናታቸውም ያጽናን፡፡

† እንዲህ ኃጢአታችን ጽዋዑን ሞልቶ በተረፈበት በዚህ ዘመን አንዲት ሰዓትም ውድ የሆነች የንስሃ ዕድሜ ናት:: እግዚአብሔር ግን ደግ ነውና ይሔው ጥርን አስፈጸመን:: ባይገባን ነው እንጂ በዚሕች ወር ውስጥ ሚሊየኖች በደዌ የአልጋ ቁራኛ ሁነዋል::

ሚሊየኖችም ለንስሃ ሳይበቁ እንዲሁ አንቀላፍተዋል [ሙተዋል]:: እስኪ እርሱ አምላካችን ቀሪውን ዘመን ደግሞ ለንስሃና ለመልካም ሥራ ባርኮ ይስጠን::

† ወርኀ ጥርን በቸር ያስፈፀመ አምላከ ቅዱሳን ወርኀ የካቲትን እንዲባርክልን እንለምነው::

🕊

[  † ጥር ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅድስት ሶፍያና ሦስቱ ሰማዕታት ልጆቿ [ጲስጢስ አላጲስና አጋጲስ]
፪. ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት [በ፭ ነገሥታት እጅ የተሰቃየች : የሐዋርያው ጢሞቴዎስ ተከታይና ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነጠቀች እናት]
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፬. አባ አክርስጥሮስ
፭. አምስቱ ደናግል ሰማዕታት [ጤቅላ: ማርያ: ማርታ: አበያ: ዓመታ]
፮. ጻድቃነ ዴጌ [የተሠወሩበት]
፯. አባ ሚናስ ሊቀ ጳጳሳት
፰. ፻፴ ሺህ "130,000" ሰማዕታት [የቅድስት ኦርኒ ማኅበር]

[   † ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ
፪. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፫. አባ ሣሉሲ ክቡር

" ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: " † [ ፩ጴጥ. ፫፥፫ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3👍1
6
#ጌታችን ስምኦን ቤት ተቀምጦ ሳለ፣ መላ #ህይወቷን_ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቶዋ ማርያም)፤‹‹ከእንግዲህ ወዲህ #በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን #ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል #አምላክ_መጣ›› ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦሰት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ(በራሱ)ላይ በማርከፍከፍ ጌታችንን ቀብታዋለች በረከቷ ይደርብን

     
#መልካም__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
11🙏5
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[ 💖 መንፈሳዊው መሰላል 💖 ]


[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ] "መንፈሳዊው መሰላል" ድርሳን ]

🕊

❝ የሕይወት ምንጭ እግዚአብሔር እንደ መሆኑ ፣ ከእርሱ ውጭ በራሱ ሕይወት ያለው ነገር የለም፡፡

ስለሆነም መንፈሳዊ ሕይወት ስንል ሰዎችና መላእክት ከእግዚአብሔር ሕይወትነት ያላቸው ሱታፌ ሲሆን ይህ ሱታፌም አንድ ቦታ ላይ የሚያቆምና የተገደበ ሳይሆን እያደገ የሚሄድ ነው፡፡

እግዚአብሔር ፍጻሜ የሌለውና “እስከዚህ ድረስ” ተብሎ የማይወሰን አምላክ እንደመሆኑ ፣ ከእርሱ ጋር ኅብረትና አንድነት ይኖራቸው ዘንድ በእርሱ ሕይወት የሚሳተፉ ሁሉ ጉዟቸው መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ የለውም፡፡ የመንፈሳዊ ጉዞ አስደሳችነቱም ይህ ነው ፤ ወደማይደረስበት ፣ ግን ደግሞ ከመጀመሪያው ጀምሮ አብሮ ወዳለ አምላክ የሚደረግ የማያቋርጥ ጉዞ !

ይህ ጉዞ ፣ ያዕቆብ ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግቶ ባየው መሰላል አንጻር ሥዕላዊ በሆነ ሁኔታ ተገልጦልናል፡፡ በመሰላሉ ላይ [ ከመሰላሉ ጫፍ ላይ ሳይሆን ከመሰላሉ በላይ ] እግዚአብሔር “ተቀምጦ” ነበር፡፡ መሰላሉ በመሬት ላይ የተዘረጋ መሆኑ እግዚአብሔር ወደ እርሱ የምንወጣበትን የቅድስና መሰላል ልንደርስበት በምንችለው በመሬት ላይ የዘረጋልን መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ፣ እግዚአብሔር ከመሰላሉ በላይ ቆሞ መታየቱ ደግሞ ከላይ ሆኖ “አይዟችሁ ፣ ወደ እኔ ኑ" እያለ በፍቅሩ የሚጠራንና የሚስበን እርሱው ራሱ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ ከታች ከመሬቱ ጀምሮ የሚጠራንና የሚስበን ፣ በመሰላሉ ላይ የትኛውም ደረጃ ላይ ብንደርስም አሁንም ከዚያ በላይ ወዳለው እንድንቀጥል የሚያደርገን ከመሰላሉ በላይ ያለው እርሱ ነው፡፡

እንደዚያ ሆኖም ግን እርሱ ከመሰላሉ በላይ [ ማለትም በባሕርዩ ሊደረስበት የማይችል ] ነው፡፡ እግዚአብሔር ማለት ይህ ነውና ፤ ከራሳችን በላይ ለራሳችን የቀረበ የውስጥና የቅርብ መጋቢና ተንከባካቢ አባት ፣ ሆኖም ግን በባሕርዩ የማይታወቅና የማይደረስበት ረቂቅ አምላክ ! ❞

[   ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]  "መንፈሳዊው መሰላል" ድርሳን ትርጓሜ ላይ የሰጡት አስተያየት  ]


🕊                       💖                     🕊
🥰3
👍54
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊

▷     "  አ  ስ  ተ  ካ  ክ  ለ  ኝ  "

[   💖  አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ  💖  ]

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

❝ ትእዛዝህን እንደ ወደድሁ ተመልከት ፤ አቤቱ ፥ በምሕረትህ ሕያው አድርገኝ። የቃልህ መጀመሪያ እውነት ነው ፥ የጽድቅህንም ፍርድ ሁሉ ለዘላለም ነው። ❞

[   [ መዝ. ፻፲፱፥፻፶፱ ]  ]


🕊                       💖                     🕊
2
Audio
😢2
😢3
🕊

[  † እንኳን ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ዼጥሮስ እና ለ፻፶ [150] ው ቅዱሳን ሊቃውንት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  ቅዱስ ዼጥሮስ ሰማዕት †  🕊

† የቅዱሳን ሰማዕታት መነሻቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ፍጻሜአቸው ደግሞ ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት ነው::

ይህ ቅዱስ የሚታወቀው "ተፍጻሜተ ሰማዕት [የሰማዕታት መጨረሻ]" በሚለው ስሙ ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት:: ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ ፭ ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ዼጥሮስ ወዻውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ዼጥሮስ" አለችው::

ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ዻዻሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ:: ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ዼጥሮስን የግብጽ ፲፯ [17] ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::

ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር:: ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ፲፬ [14] ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ::

አርዮስን [ተማሪው ነበር] አውግዞ ለየው:: ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ዽዽስናው ላይ አልተቀመጠም:: በሁዋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ::

ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ዼጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ:: በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ:: ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ:: ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::

† የቅዱሳንን ዝክር ከማንበብ ባለፈ በስማቸው መጸለይ [ዘፀ. ፴፪፥፲፫ ] : በምጽዋትም ማሰብ [ ማቴ.፲፥፵፩ ] ይገባል::

† ወርኀ የካቲትን ይባርክልን !

🕊

[  † የካቲት ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ፻፶ [ 150 ] ቅዱሳን ሊቃውንት ዻዻሳት [በቁስጥንጥንያ ተሠብሥበው መናፍቃንን ያወገዙበት: ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ያፀኑበት /ጉባዔ ቁስጥንጥንያ/ በ፫፻፲፰ [381] ዓ/ም::
ከወቅቱ ቅዱሳን ሊቃውንት እነዚህ ይጠቀሳሉ:-
- ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
- ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ
- ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት
- ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
፪. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት [ቅዳሴ ቤቱ]
፫. ታላቁ ቴዎዶስዮስ ጻድቅ [ንጉሠ ቁስጥንጥንያ]

[   † ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ልደታ ለቅድስት ድንግል ማርያም እግዝእትነ
፪. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
፬. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
፭. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

" ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በሁዋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ 3 ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቁዋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ:: " † [ ሐዋ. ፳፥፳፰ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
👍1
2👍2
#ቅዳሴ__ማርያም

✥ ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ።

✥ ድንግል ሆይ በቤተ ልሔም ካንቺ የተወለደውን መወለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስን ያሟሟቁትንም አሳስቢ።

✥ ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ከርሱ ጋር ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ።

✥ ድንግል ሆይ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የፈሰሰውን መሪር ዕንባ አሳስቢ።

✥ ድንግል ሆይ ረኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኃዘኑን ከርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ።

✥ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ መዓትን አይደለ ምሕረትን አሳስቢ።

✥ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ ለንጹሓን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ።


#መልካም_ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
8🥰3❤‍🔥2
2025/07/09 22:12:33
Back to Top
HTML Embed Code: