Telegram Web
👏4😢2
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  እንኩዋን ለቅዱስ "አናሲሞስ ሐዋርያ" እና ለእመቤታችን "ቅድስት ድንግል ማርያም" በዓል በሰላም አደረሳችሁ  †   🕊   ]


🕊  †  ድንግል ማርያም  †   🕊

የአምላክ እናቱ እመ-ብርሃን ድንግል ማርያም :-
- በ፫ [3] ወገን [በሥጋ: በነፍስ: በልቡና] ድንግል
- በ፫ [3] ወገን [ከኀልዮ: ከነቢብ: ከገቢር] ንጽሕት
- ሳትጸንስ: በጸነሰች ጊዜና ከጸነሰች በሗላ ድንግል
- ጌታን ሳትወልድ : በወለደችው ጊዜና ከወለደችው በሗላ ድንግል ስትሆን እናትም ድንግልም መሆኗን አምነን እመሰክራለን::

- እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ በላይ ክብርትና ንዕድ ናት:: ሊቃውንት አበው እንዳስተማሩን በዚህ ዕለት እንዲህ ብለን እንጸልያለን::
"ረስዪ ፍና ትሕትና አእጋርየ ይሑሩ:
ትዕቢትሰ ለአምላክ ጸሩ"
[እመቤቴ ሆይ ትዕቢትን አምላክ ይጠላልና እግሮቻችን በትሕትና እንዲሔዱ አድርጊ]


🕊  †  ቅዱስ አናሲሞስ ሐዋርያ  †  🕊

በዘመነ ሐዋርያት ምስጉን ከነበሩ አበው አንዱ ቅዱስ አናሲሞስ ነው:: ስለ ቀና አገልግሎቱና መልካም እረኛነቱ አባቶቻችን ሐዋርያት አብዝተው በቀኖናቸው መስክረውለታል:: እርሱ ከኃጢአት ኑሮ ወደ ዘለዓለማዊ የቅድስና ሕይወት መጥቷልና::

¤ ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

በሮም ከተማ የሚኖር ፊልሞና የሚባል አንድ ባለጸጋ ነበር:: ይህ ሰው በስብከተ ቅዱስ ዻውሎስ አምኖ ከርስቲያን ሆነና በመንፈሳዊ አገልግሎት ተጠመደ:: ነገር ግን ከአገልጋዮቹ መካከል ያላመነ አንድ ሰው ነበር:: "ተጽዕኖ አላደርግበትም" ብሎ ዝም ይለዋል:: ግን ክርስትና እንዲገባው ለተልዕኮ መንፈሳዊ በሚሔድበት ሥፍራ ያስከትለው ነበር::

አገልጋዩ ግን በመለወጥ ፈንታ ሌብነትን ለመደ:: ይባስ ብሎም የአሳዳሪውን [የፊልሞናን] ገንዘብ ሠርቆ ወደ ሮም ጠፍቶ ተመለሰ:: ቅዱስ ፊልሞናም ለገንዘቡ ሳይሆን ለሕይወቱ አዘነ::

ያ ሠርቆ የጠፋው አገልጋይ ግን በሮም ከተማ ሲመላለስ ስብከተ ወንጌልን ይሰማል:: ሰባኪው ደግሞ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ነበር:: ቁጭ ብሎ ሲማርም ልቡናው በርቶለት ተጸጸተ:: ከሐዋርያውም ዘንድ ቀርቦ ኃጢአቱን ተናዞ ተጠመቀ::
ከዚያች ዕለት ጀምሮም ብርቱ ክርስቲያን ሆነ:: በጥቂት ጊዜም የተጋ ሰባኪ : ርሕሩሕ እረኛ ሆነ:: ፈጣሪውንም ደስ አሰኘ:: ነገር ግን ስለ አንድ ነገር ፈጽሞ ያዝን : ይተክዝም ነበር::

+ የድሮ አሳዳሪው ቅዱስ ፊልሞና እንዳዘነበት እያወቀ ዝም ማለት ባያስችለው ለመምህሩ ቅዱስ ዻውሎስ ነገረው:: ያን ጊዜም ሐዋርያው በእሥራትና በግርፋት ይሰቃይ ነበር:: በሮም ሳለም አጭር ክታብ [ደብዳቤን] ጽፎ ለዚህ ደቀ መዝሙሩ ሰጠውና ወደ ቀድሞ አሳዳሪው ወደ ፊልሞና ላከው::

+ ይህች ጦማር [ክታብ] ዛሬም ድረስ ከ፹፩ [81] ዱ አሥራው መጻሕፍት : ከቅዱስ ዻውሎስ ፲፬ [14] መልዕክታት አንዷ ሆና ተቆጥራ እንጠቀምባታለን:: ክታቧ እጅግ አጭር ብትሆንም ምሥጢሯ ግን ሰፊ ነው::

+ ያ የተላከ ክርስቲያንም ያችን ክታብ ወስዶ ለቅዱስ ፊልሞና [ለቀድሞ አሳዳሪው] አስረከበ:: ቅዱስ ፊልሞናም በደስታ አቅፎ ሳመው:: ቀድሞውንም ያዘነ በወጣቱ አገልጋይ የነፍስ እዳ እንጂ በገንዘቡ አልነበረምና:: ያ ተላኪ ሰውም በአካባቢው ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ቅዱስ ዻውሎስ ተመልሷል:: ደቀ መዝሙሩ ሆኖም ብዙ አገልግሏል::

+ ቅዱስ አናሲሞስ ማለት . . . የቀድሞ የሰው አገልጋይ . . . ዛሬ የክርስቶስ ባሪያ . . . ቀድሞ ሠራቂ . . . ዛሬ ግን ለመንጋው የሚራራ ሰው የሆነው ይህ ክርስቲያን ነው::

+ በ፷፯ [67] ዓ/ም ቅዱስ ዻውሎስ መሰየፉን ተከትሎ እርሱንም አሳድደው : አሰቃይተው : ጭኑንም ሰብረው አሕዛብ ገድለውታል:: በሰማይም የሐዋርያነትና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጅቷል:: [ጢሞ.፬፥፮-፰ [4:6-8] , ፊልሞና.፩፥፩-፳፭] 1:1-25]

አምላከ ቅዱሳን የአናሲሞስን መመለስ : ንስሃና በረከት ያድለን::

🕊

[   † የካቲት ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ አናሲሞስ ሐዋርያ [የቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ ደቀ መዝሙር ሲሆን ከ፲፬ [14] ቱ መልዕክታት አንዱ የሆነው 'ወደ ፊልሞና' የተጻፈው በዚህ ቅዱስ ምክንያት ነው:: [ፊል.፩፥፲፩ 1:11]
፪. አባ ዘካርያስ ዘሃገረ ስሃ
፫. አባ አካክዮስ ጻድቅ
፬. አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት
፭. አባ ገብርኤል [የኢትዮዽያ ዻዻስ]

[    + ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም
፪. አበው ጎርጎርዮሳት
፫. አቡነ ምዕመነ ድንግል
፬. አቡነ አምደ ሥላሴ
፭. አባ አሮን ሶርያዊ
፮. አባ መርትያኖስ ጻድቅ

" ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . . አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ:: የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ:: በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: " [ኢሳ.፷፪፥፩-፫] [62:1-3)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2
11
#የወላዲተ_አምላክ_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የድንግልና ሕይወት ፤ እንደ ማንኛውም ሰው ድንግልና አይደለም። ይህን የመሰለ ድንግልና፣ ንፅሕናና ቅድስና ከእርስዋ በስተቀር በሌላ በማንም አልታየም። ሌሎች ከነቢብ ከገቢር ድንግል ቢባሉ(ቢሆኑ) ፥ ከሐልዮ ወይም ከማሰብ ድንግል አይደሉምና። በወንጌል "ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል" ተብሎ እንደ ተፃፈ። እርሷ ለነበረውም ለመጪውም ትውልድ የክብር አክሊል ናት። የዘወትር ድንግል(ወትረ ድንግል) የሆነች እናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም፥ ምድራዊ ዘመኗን ሁሉ ፥ ቅድስናዋን ምንም ሳይልውጠው እንዴት መኖር ቻለች? አካላዊ ቃል በማህፀኗ ባደረ ጊዜ፣ ፈጣሪዋን ስትወልድ፣ በክንዷ ስታቅፈውና በዓይኖቿ ስታየውስ፥ ምን ተሰማት? ይህ ጥያቄ በሰው ልጅ ጥበብ የሚመልስ ወይም ሊገለጥ የሚችል አይደልም።

          #_ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
14🥰4❤‍🔥2🔥1
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †

💖 

    [   ዓ ለ ም ን   ስ ለ መ ተ ው !   ]

           [     ክፍል አራት     ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

ባለ መድኃኒት የሆነ መሪ ያስፈልገናል !

❝ ከግብፅ ወጥተን ለመሄድ ፣ ከፈርዖንም አገዛዝ ለማምለጥ የምንመኝ ሁሉ ፣ በርግጥም ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያማልድ [ መካከለኛ የሚሆን ] ና የእግዚአብሔር ወገን የሆነ በተግባርና በመንፈሳዊ ተከስቶ መካከል ቆሞ ፣ ስለ እኛ ብሎ እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ለጸሎት በማንሣት ፣ በፈቃዳተ ሥጋ አማሌቅ ድል ከመነሣት መርቶ ባሕረ ኃጢአትን የሚያሻግረን እንደ ሙሴ ያለ ሰው ያሻናል [ዘጸ.፲፯ ]፡፡

ለዚህ ነው ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አሳልፈው የሰጡ መሪ እንደ ማያሻቸው ሲያስቡ ራሳቸውን ያታለሉ የሚሆኑት፡፡ ከግብፅ የወጡ ሁሉ እንደ መሪ ሆኖ ሙሴ ነበራቸው ፣ ከሰዶም ያመለጡም መልአክ ነበራቸው [ዘፍ.፲፱ ]፡፡ የመጀመሪያዎቹ በሐኪሞች ክብካቤ ከነፍስ ምኞቶች የተፈወሱትን የሚመስሉ ናቸው ፤ እነዚህም ከግብፅ የወጡ ናቸው፡፡ የኋለኞቹ ንጹሕ ያልሆነውን የተዋረደ ሰውነት አውልቆ ለመጣል እንደ ሚናፍቁ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው እንደ መልአክ የሚናገር ወይም ይልቅ ከመልአክ ጋር የሚተካከል እንደ መልአክ ያለ ረዳት የሚያስፈልጋቸው፡፡ እንደየ ቍስሎቻችን መበስበስ መጠን በእውነት ብልህ አዋቂና ባለ መድኃኒት የሆነ መሪ ያስፈልገናል፡፡

ሰውነታቸውን ወደ ሰማይ ከፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ፣ በተለይም ገና ዓለምን በተዉበት ጊዜ ፣ ተድላ ወዳድ የሆኑ ጠባዮቻችንና የማይጸጸቱ ልቦቻችን ፍቅረ እግዚአብሔርንና ንጽሕናን ገንዘብ እስኪያደርጉ እንዲሁም ኀዘንን እስኪያሳዩ ድረስ ፣ በእውነት ኃይለኛና የማያቋርጥ መከራን መቀበል ያስገልጋቸዋል [ማቴ.፲፩፥፲፪]፡፡ ❞


[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                       💖                     🕊
6👍1
9
                        †                           

†    🕊         ዘ ወ ረ ደ         🕊   †


[  የጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት !   ]

[   ክፍል አምስት   ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ተወዳጆች ሆይ ! ድኅነተ ሥጋን ድኅነተ ነፍስን እናገኝ ዘንድ ራስን አለመግዛትን ከእኛ ዘንድ እናርቀው ፤ ጾምንና ከእርስዋ ጋር ያሉትን ሌሎች በጎ ምግባራትን እንውደዳቸው ፤ ከዛሬ አንሥተን አዲስ ኑሮን እንጀምር ፤ ዕለት ዕለት በጎ ምግባራትን መሥራትም የሚያስደስተን እንኹን፡፡

እንዲህ መንፈሳዊ ተግባራትን የምንፈጽምና የበጎ ምግባር ሀብትን አከማችተን ጾሙን የምናሳልፍ ከኾንንም ወደ ጌታ ቀን  ለመድረስ የተገባን እንኾናለን ፤ ወደዚያ ወደ አስደናቂው ማዕድ [ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ] መቅረብ ይቻለናል።

በጌታችን ቸርነትና ሰው ወዳጁ አምላካችን ክርስቶስን ደስ ባሰኙ ቅዱሳን ጸሎትና ምልጃም ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን፡፡

ከእርሱም ጋር ለባሕርይ አባቱ ለአብ ፣ ለባሕርይ ሕይወቱ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ፣ ኃይልና ጌትነት ይኹን ፤ ዛሬም ዘወትርም እስከ ትውልደ ትውልድ ድረስ አሜን፡፡ ❞

  [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
🕊                    💖                    🕊
4🥰1
4
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   ዐቢይ ጾም [  ጾመ እግዚእ  ]  🕊


▷   "  ት  ሕ  ት  ና   "


[  " በቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ... ! "  ] 

[                         🕊                         ]
----------------------------------------------------

❝ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም ፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ ❞ [ ኤፌ.፬፥፪ ]


🕊                       💖                   🕊
3👍2🥰1
Audio
👍1
5👍4
#ሳታቋርጡ__ጸልዩ

"ሥራ የሚሠራ ሰው ቀኑን ሙሉ በጸሎት ተጠምዶ መዋል አይችልም" አትበለኝ፤ ይችላል። በጸሎት የሚያስፈልገው ድምፅ ሳይሆን ሀሳብ ነው ፤ እጅ ሳይሆን እደ ልቦናን ማንሣት ነው፤ አፍአዊ ሳይሆን ውስጣዊ አኳኋን ነው ።ይህን ለማድረግ ደግሞ ቦታም ጊዜም አይገድብህም። በጉልበትህ ባትንበረከክ፤ ደረትህንም ባትደቃ እንኳን መንፈስህ ትጉ ከሆነ
#ጸሎትህ ሥልጡን ነው ።

#ቅዱስዮሐንስአፈወርቅ

          
#መልካም_ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
8🙏4
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

†  የካቲት ፳፪ [ 22] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

🕊  †  አቡነ አቢብ [ አባ ቡላ ]  †   🕊

ይህን ታላቅ ቅዱስ በምን እንመስለዋለን !
- እኛ ኃጥአን ጣዕመ ዜናውን: ነገረ ሕይወቱን ሰምተን ደስ ተሰኝተናል !
- ቅዱሱ አባታችን :- "ቡላ-የእግዚአብሔር አገልጋይ" ብለን እንጠራሃለን::
- ዳግመኛም "አቢብ-የብዙኃን አባት" ብለን እንጠራሃለን::

- እርሱ ቅሉ አባትነትህ አንተን ለመሰሉ ቅዱሳን ቢሆንም እኛን ኃጥአንን ቸል እንደማትለንም እናውቃለን::
- አባ! ማነው እንዳንተ የክርስቶስን ሕማማት የተሳተፈ !
- ማን ነው እንዳንተ በፈጣሪው ፍቅር ብዙ መከራዎችን የተቀበለ !
- ማንስ ነው እንዳንተ በአንዲት ጉርሻ አማልዶ ርስትን የሚያወርስ !
- የፍጡራንን እንተወውና በፈጣሪ አንደበት ተመስግነሃልና ቅዱሱ አባታችን ላንተ ክብር: ምስጋናና ስግደት በጸጋ ይገባሃል እንላለን::

†    ልደት    †

አባታችን አቡነ አቢብ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ ሮሜ ናት:: ወላጆቹ ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሐሪክ እጅግ ጽኑ ክርስቲያኖች ነበሩ:: ልጅ ግን አልነበራቸውም:: ዘመነ ሰማዕታት ደርሶ ስደት በሆነ ጊዜ እነርሱም በርሃ ገቡ::

- በዚያም ሳሉ በቅዱስ መልአክ ብሥራት ሐሪክ ጸንሳ ብሩሕ የሆነ ልጅ ወለደች:: ቅዱሱ ሕጻን ሲጸነስ ማንም ሳይተክለው የበቀለው ዛፍ ላይ መልአኩ እንዲህ የሚል የብርሃን ጽሑፍ ጽፎበት ወላጆቹ ዐይተዋል::
"ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር: ወቅዱሱ ለአምላከ ያዕቆብ: ዘየኀድር ውስተ ጽዮን"

†   ጥምቀት   †

ቅዱሱ ሕጻን ከተወለደ በኋላ ሳይጠመቅ ለ ፩ ዓመት ቆየ:: ምክንያቱም ዘመኑ የጭንቅ ነውና ካህናትን እንኳን በዱር በከተማም ማግኘት አይቻልም ነበር:: እመቤታችን ግን ወደ ሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ሒዳ 'አጥምቀው' አለችው::

ወደ በርሐ ወርዶ ሊያጠምቀው ሲል ሕጻኑ ተነስቶ: እጆቹንም ዘርግቶ :- "አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የሕጻኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው:: እነርሱም ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ::

†   ሰማዕትነት   †

የቅዱሱ ቡላ ወላጆች ለ፲ [10] ዓመታት አሳድገውት ድንገት ሕዳር ፯ [7] ቀን ተከታትለው ዐረፉ:: ሕጻኑን የማሳደግ ኃላፊነትን የአካባቢው ሰዎች ሆነ:: ሕጻኑ ቡላ ምንም የ፲ [10] ዓመት ሕጻን ቢሆንም ያለ ማቁዋረጥ ሲጾም: ሲጸልይ ክፉ መኮንን "ለጣዖት ስገዱ" እያለ መጣ::

በዚህ ጊዜ በሕጻን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ የተበሳጨ መኮንኑ ስቃያትን አዘዘበት:: በጅራፍ ገረፉት: በዘንግ ደበደቡት: ቆዳውን ገፈፉት: በመጋዝ ቆራርጠውም ጣሉት:: ነገር ግን ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ፪ [2] ጊዜ ከሞት ተነሳ:: በመጨረሻ ግን ሚያዝያ ፲፰ [18] ቀን ተከልሎ ሰማዕት ሆኗል::

†   ገዳማዊ ሕይወት   †

ቅዱስ ቡላ ሰማዕትነቱን ከፈጸመ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል በአክሊላት አክብሮ ወስዶ በገነት አኖረው:: ከሰማዕታትም ጋር ደመረው:: በዚያም ቡላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተመልክቶ ተደነቀ:: መንፈሳዊ ቅንዐትን ቀንቷልና "እባክህን ወደ ዓለም መልሰኝና ስለ ፍቅርህ እንደ ገና ልጋደል" ሲል ጌታን ለመነ::

ጌታችን ግን "ወዳጄ ቡላ! እንግዲህስ ሰማዕትነቱ ይበቃሃል:: ሱታፌ ጻድቃንን ታገኝ ዘንድ ግን ፈቃዴ ነውና ሒድ" አለው:: ቅዱስ ሚካኤልም የቅዱስ ቡላን ነፍስ ከሥጋው ጋር አዋሕዶ: ልብሰ መነኮሳትንም አልብሶ ግብጽ በርሃ ውስጥ አኖረው::

†   ተጋድሎ   †

አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዐርብ ዐርብ የጌታን ሕማማት እያሰበ ራሱን ያሰቃይ ገባ:: ራሱን ይገርፋል: ፊቱን በጥፊ ይመታል: ሥጋውን እየቆረጠ ለአራዊት ይሰጣል: ከትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ወደ ታች ይወረወራል::

በጭንቅላቱ ተተክሎ ለብዙ ጊዜ ጸልዮ ጭንቅላቱ ይፈሳል:: ሌላም ብዙ መከራዎችን የጌታን ሕማማት እያሰበ ይቀበላል:: ስለ ጌታ ፍቅርም ምንም ነገር ሳይቀምስ ለ፵፪ [42] ዓመታት ጹሟል:: ጌታችንም ስለ ክብሩ ዘወትር ይገለጥለት ነበር::

የሚታየውም እንደ ተወለደ: እንደ ተጠመቀ: እንደ ተሰቀለ: እንደ ተነሳ: እንዳረገ እየሆነ ነበር:: አንድ ቀንም ጌታችን መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! እንዳንተ ስለ እኔ ስም መከራ የተቀበለ ሰው የለም:: አንተም የብዙዎች አባት ነሕና ስምህ አቢብ [ሃቢብ] ይሁን" አለው::

"እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኮቴት ማሕዘኔ: ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኩነኔ:
ዘመጠነዝ ታጻሙ ነፍስከ በቅኔ" እንዲል::

†   ዕረፍት   †

አቡነ አቢብ ታላቁ ዕብሎን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት እየተጨዋወተ ዘለቀ:: በተጋድሎ ሕይወቱም ከ፲ [10] ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: በዚህች ቀን ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ::
- ጌታም ከድንግል እናቱ ጋር መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! ስምህን የጠራውን: መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ:: አቅም ቢያጣ 'አምላከ አቢብ ማረኝ' ብሎ ፫ [3] ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን: በስምሕ እንኳ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ" ብሎት ነፍሱን በክብር አሳረገ: በሰማይም ዕልልታ ተደረገ::


🕊  †  ሰማዕታተ ፋርስ  †   🕊

† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬] ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

ፋርስ [ persia ] በአሁን መጠሪያዋ "ኢራን" የምትባል: በቀደመው ዘመን የበርካታ እውነተኛ ክርስቲያኖች ቤት ነበረች:: ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድን የመሰሉ አእላፍ ሰማዕታት በዚሕች ሃገር ውስጥ በ2ኛውና ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን የሰማዕትነት ጽዋዕን ጠጥተዋል:: በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመንም አባ ማሩና በተባለ ጻድቅ ሰው በዚህች ቀን ዐፅማቸው ተሰብስቦ ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል::
† አምላከ ቅዱሳን ይራዳን: ይባርከን: ይቀድሰን:: ከወዳጆቹ በረከትም ያሳትፈን:: የቅዱሳኑን ግፍና መከራ አስቦም ከምንፈራው ጭንቅ ሁሉ ይሰውረን:: ለመንግስቱም ያብቃን::

🕊

[  † የካቲት ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱሳን ሰማዕታተ ፋርስ [ፍልሠታቸውና ቅዳሴ ቤታቸው]
፪. ቅዱስ አባ ማሩና ጻድቅ ኤዺስ ቆዾስ [የፋርስ ሰማዕታትን አጽም የሠበሠበ]
፫. ቅዱስ አባ ቡላ

[    † ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
፫. ቅዱስ ደቅስዮስ [የእመቤታችን ወዳጅ]
፬. አባ እንጦንዮስ [አበ መነኮሳት]
፭. አባ ዻውሊ የዋህ

" ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ መራቆት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቆጠርን::' ተብሎ እንደተጻፈው ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::
"
† [ሮሜ.፰፥፴፭-፴፯]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
3👍1
2025/07/13 20:19:57
Back to Top
HTML Embed Code: